Monday, March 27, 2023

ብጹዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ፡ አጭር የሕይወት ታሪክ





አቡነ
አረጋዊ ታመው አልጋ ላይ ከመዋላቸው አስቀድሞ ምንም አይነት የሕመም ምልክት እንዳልነበረባቸው ታውቋል። ጤንነታቸውንም በየጊዜው "ቸክ" የሚዪደርጉ ጥንቁቅ አባት ነበሩ። በሥርዐተ ቀብራቸው ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ "የብፁዕ አቡነ አረጋዊ አሟሟት ግራ ያጋባል፤ ታመው አልጋ ላይ ከመዋላቸው በፊት ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት አልነበረባቸውም። ብቻ ምክንያቱ ይለያይ እንጂ ተጠርተው ሂደዋል" ማለታቸው በብፁዕነታቸው ሞት ላይ አንዳች የተቀነባበረ ጉዳይ እንዳለ ማሳያ ነው።

1, ብፁዕነታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ታመው ኮሪያ ሆስፒታል እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ በኮሪያ ሆስፒታል ሕክምና ሳያገኙ ተሰቃይተዋል። ይኸውም ከቤተ ክህነት በጀት እንዳይለቀቅ ሴራ በመጠንሰሱ ነው። አባታችን ከቤተ ክህነት የሕክምና በጀት ባለመለቀቁ ሕይወታቸው አስጊ ሲሆን የኮሪያ ሆስፒታል ሠራተኞች እና ወዳጆቻቸው ገንዘብ አዋጥተው የኮሪያ ሆስፒታል ሕክምናው ተጀመረ። (ይህንን እውነት ከኮሪያ ሆስፒታል ሐኪሞች ማረጋገጥ ይቻላል። በአቡነ አረጋዊ ልክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ያሉ አባት ለምን የሕክምና ወጭ ተከለከሉ?

2, ከብዙ ቢሮክራሲ በኋላ ውለው አድረው በጀቱ ሲለቀቅ የኮሪያ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ውጭ ሂደው እንዲታከሙ አዘዙ። በዚህም መሠረት ብፁዕ አባታችን ደክመው በአውሮፕላን አንቡላንስ ውስጥ ሰው ሠራሽ መተንፈሻ ተገጥሞላቸው አንቡላንሱ ወደ ውጭ መብረር ጀመረ። በርካታ ሰአታትን ሲጓዝ የቆየው አንቡላንስ ግን ለሕክምና ወደሚሄድበት ሀገር በሚደርስበት ሰአት

ተመልሶ አዲስ አበባ ዐረፈ። ይህ ለምን ሆነ ተብሎ ሲጠየቅ ብልሽት ገጥሞት ነው የሚል ምክንያት ተሰጠው። አባታችን ይበልጥ እየተዳከሙ መጡ። ከቀናት በኋላም ተበላሸ የተባለው አቡላንስ ሳይጠገን ብፁዕነታቸውን ይዞ ወደ ውጭ ሄደ። ይህ ለምን ሆነ? ይቀጥላል....

የብጹዕ አቡነ አረጋዊ  አጭር የሕይወት ታሪክ  ( ፲፱፻፷፩ - ፳፻፻፭ )

ብጹዕ አቡነ አረጋዊ (/ )  ከአባታቸው ከሊቀ መዘምር መለስ አየነው ደስታ እና ከእናታቸው ከወ/ ፀሐይ ገብረ አብ፣ በሰሜን ጎንደር ደብረ ሰላም ሎዛ ማርያም አካባቢ በ፲፱፻፷፩  .. ተወለዱ

ትምህርት፡- ፊደል፣  ንባብ፣ ዳዊትና ቅዳሴ ከመርጌታ ሙሴ ተምረዋል። ቅኔ ከግጨው መንክር ምንዝሮ ተክለ ሃይማኖት ሐዲሳት ከመጋቤ ሐዲስ ወልደ ሰንበት ግምጃ ቤት ማርያም ተምረዋል።

፩ኛ እና  ፪ኛ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዐፄ ፋሲል መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዳግማዊ ደብረ ሊባኖስ አዘዞ ተክለ ሃይማኖት /ቤቶች ተምረዋል። ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ በቴዎሎጂ ዲፕሎማ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቴዎሎጂ ዲግሪ፣

ከኖርዌይ ስታሻንገር ስፔሻላይዝድ ዪኒቨርስቲ የማስተርስ ዲግሪ ፣ከፕሪቶርያ ዩኒቨርስቲ በፍልስፍና የፒ.ኤች. ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

ቋንቋ፡- ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ የኖርዌይ፥ የስዊድንና የዴንማርክ ቋንቋዎችን ይችላሉ።

መዐርገ ክህነት

ዲቁና ፲፱፻፷፰ - .. ከብፁዕ አቡነ እንድርያስ (ቀዳማዊ) በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል

ምንኵስና1984 .. በታዋቂውና ጥንታዊው ገዳም ጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለዋል።

ቅስናከብፁዕ አቡነ ያዕቆብ (ኤርትራዊ) በወቅቱ የሰሜን ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ተቀበለዋል፤

ቁምስናከብፁዕ አቡነ ገብርኤል በወቅቱ የምዕራብ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል።

አገልግሎት፡-

በሆለታ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፥ በሆለታ ገነት ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል፥ በሆለታ ገነት ደብረ ሣህል መድኃኔ ዓለም፥ በወሊሶ ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናት በአስተዳዳሪነት ሠርተዋል።

የወልመራ ወረዳ ቤተ ክህነት ምክትል ሊቀ ካህናት ሆነው በቅንንነት አገልግለዋል። በኖርዌይ ስታሻንገር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የሕፃናትና ቤተሰብ መምሪያ የቦርድ

ምክትል ሰብሳቢ በመሆን መርተዋል።የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የቦርድ አባል፥ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል

በቤተ ክህነት ጠቅላይ /ቤት ቀደም ሲል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሓላፊ፤ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመጀመሪያ የሪሰርችና ምርምር ሓላፊና አካዳሚክ ዲን፥ /ዋና ዲን በመሆን አገልግሎት ሰጥተዋል፤ የቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቦርድ አባል በመሆንም ሠርተዋል።

በዓለም አቀፍ ተሳትፎ ደግሞ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል፥ የመላው ኦርየንታል ኦርቶዶስ አብያተ ክርስቲያናትን በመወከል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል በተጨማሪ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅነትና   በትርፍ ጊዜአቸውም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ  የድኅረ ምረቃ ደቀ መዛሙርትን በማስተማርም አገልግለዋል

ብጹዕ አቡነ አረጋዊ ፳፻፱ . ላይ ከሌሎች  ፲፬ አባቶች ጋር ተመርጠው ጵጵስና በብፁዕ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ሊቀ ርዕስ ሊቃነ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ መንበረ ተክለ ሃያማኖት በአንብሮተ ዕድ  ተሾመዋል

ብጹዕ አቡነ አረጋዊ የቅዱስ ፓትርያርክ  ልዩ /ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የድሬደዋና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል  ብጹዕ አባታችን አቡነ አረጋዊ ያላፈውን ዓመት በህመም ምክንያት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት መጋቢት ፲፪ /፳፻፲፭ . በተወለዱ በ፶፬ ዓመታቸው ከእዚህ ዓለም ድካም አረፈዋል

የብጹዕ አባታችን በረከታቸው ይደርብን