© መልካሙ በየነ
ሰኔ 29/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
መነሻ እና መድረሻውን የሮም ካቶሊክ ትምህርት ያደረገው በአንዳንድ የምሥራቅ ጎጃም ወረዳዎች የሚገኘው የቅብአት እምነት ሁለተኛውን ልብ ወለድ የፈጠራ ድርሰቱን ከወራት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ በመጀመሪያ ይህን የክህደት መጽሐፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥም ሲታተም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ዝምታ ጉዳዩን እንደሚደግፉት ያሳብቅባቸዋል፡፡ ከወልደ አብ በተለየ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገርሙ ምን ታመጣላችሁ ዓይነት መልእክቶች በጉልህ ይታያሉ፡፡ የመጀመሪያው መጽሐፋቸው “ወልደ አብ” የት እንደታተመ አይታወቅም ነበረ በዚህ መጽሐፍ ላይ ግን በግልጽ ሀፍረታቸውን ገልጠው “አሐዱ ማተሚያ ታተም ስልክ ቁጥር 0923249433” በማለት በድፍረት ለማውጣት ችለዋል፡፡ አሳታሚዋ የእኛው ቤተክርስቲያን “ምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም” በወልደ አብ ውስጥም የተገለጠች ብትሆንም እንዲህ በአደባባይ ሳይሆን በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ ላይ ብቻ ነበረ የተጻፈችው አሁን ግን ይኼው ሽፋኑ ላይም ብቅ ብላለች፡፡ ከዚህ እንደምንረዳው “በቤተክርስቲያናችሁ ስም የፈለግነውን ነገር ማድረግ እንችላለን ምንም አታመጡም” የሚል መልእክት መያዙን ነው፡፡ ደግሞ እኮ ሁለት ስልኮችን ለቆጋ ገዳም አድራሻ አድርገው አስቀምጠዋል፡፡ 0927620794 እና 0911581038 የሚሉ የቆጋ ገዳም አድራሻዎች ሆነው ተገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ስልኮች መካከል አንደኛው ማለትም 0911581038 አባ ገብረ ኢየሱስ ሙጨ የሚባሉ እንደሆኑ የመረጃ ምንጨ ጠቁሞኛል፡፡ ይህ መጽሐፍ በማን እንደታተመ አይታወቅም ወልደ አብ በ “መምህር” ገብረ መድኅን እንዳለው የሚል እንደነበረበት እናስታውሳለን እዚህ ላይ ግን ማን እንዳሳተመው የሚጠቁም የግለሰብ ሥም አላየሁም፡፡

ስለመጽሐፉ አጠቃላይ ነገር ስንመለከት ታሪክን እንደመሰለው ከየትኛውም የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት
ጋራ የማይመሳሰል የክህደት ትምህርት ታሪክን የሚያጥፋፋ ከንቱ እና መና የሆነ ምናምንቴ ድርሰት ነው፡፡
ይህንን ምንፍቅና ለምን ለሕዝብ ትገልጣለህ ብላችሁ ደግሞ ዛሬም የአባቶቻችን ጠላት ሊቃውንቱን
የምታሳድድ አባቶችን የምትከስ ወዘተ ትሉኝ ይሆናል፡፡ እኔ ግን በእውነት ስለእውነት በሐሰት ማንንም አልከስም ማንንም አልወነጅልም
ማንንም አላሳድድም ማን አሳዳጅ አደረገኝና ነው፡፡ እና ሚዛናዊ ሆነን እንነጋገር መፍትሔ ወደመሻት እንምጣ ይህ ውይይት የሚደረግበት
እንጅ የምንሰዳደብበት መሆን የለበትም፡፡ ግን በመሳደቡ ክህደቱን ለመደበቅ የሚሞክር የቅባት እምነት ተከታይ ካለ ያው በብሎክ እንሰነባበታለን፡፡
በእውነት ምንም ርኅራኄ የለኝም ማንም እየመጣ ሊደሰኩርብን መብት የለውም፡፡
ለዛሬ አበቃሁ በቀጣይ ተከታታይ ቀናት ደግሞ ስለመጽሐፉ የውስጥ ይዘት አንድ በአንድ እንመለስበታለን፡፡

No comments:
Post a Comment