Wednesday, January 31, 2018

ገዳም እና ሰንበት ትምህርት ቤት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በዚህ ርእስ ላይ የምንመለከተው ሰንበት ትምህርት ቤት እና ገዳማትን በተመለከተ ስላላቸው ዝምድና ይሆናል፡፡ ለጽሑፌም ማስረጃ የማደርገው የቤተክርስቲያናችንን መተዳደሪያ ደንብ ቃለ ዓዋዲ ይሆናል፡፡ የምጠቀመው ቃለ ዓዋዲም አዲሱን ባለፈው ዓመት በ፳፻፱ ዓ.ም ለዐራተኛ ጊዜ የተሻሻለውን ይሆናል፡፡

ቃለዓዋዲው ሰንበት ትምህርት ቤት እንዴት ለምን የት በማን ለማን ሊቋቋም እንደሚገባው የሚናገረውን ያህል ስለገዳማትም እንደዚሁ በማብራራት ይናገራል፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ስለገዳማት ቃለ ዓዋዲው የሚለውን እንመልከትና በመቀጠልም ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት እንመለከታለን፡፡

Sunday, January 28, 2018

ጾመ ነነዌ እና የድንግል ማርያም በዓለ እረፍት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ጾመ ነነዌ እና የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም በዓለ እረፍት አንድ ላይ ተገጣጥመዋል፡፡ ነነዌ ከጥፋት የዳኑበት ዕለት የአዳም ተስፋ ከሆነችው ከድንግል ማርያም እረፍት ጋር አንድ ላይ ተገናኝተዋል፡፡ ጾመ ነነዌ ከዐቢይ ጾም ፪ ሳምንታት ቀደም ብሎ ለሦስት ቀናት /ከሰኞ እስከ ረቡዕ/ ድረስ የሚጾም ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ከመጣባቸው የእግዚአብሔር ቁጣ የዳኑበት በመሆኑ እኛም ከሚመጣብን ፈተና ሁሉ እንድን ዘንድ፣ ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ እንድንና እናመልጥ ዘንድ አምነን እንጾመዋለን፡፡ ሙሉ ታሪኩን /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ተመልከት/ ይህ ጾም የዐዋጅ ጾም መሆኑን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭ ቁጥር ፭፻፷፯ ላይ “…የነነዌ ሰዎች ጾም ፫ ቀን…” ብሎ ይናገራል፡፡ ይህ ጾምም እንደ ዐቢይ ጾም በመጠንቀቅ እንዲጾም ያዝዘናል፡፡


Monday, January 22, 2018

ወልዲያን ሳስብ ደብረ ማርቆስ መጣብኝ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በዓለ ጥምቀት በዓለ ቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩን የለወጠ ክስተት ነው የተፈጸመው፡፡ ወልዲያ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት ራሳቸውን ስተው ወድቀዋል ምእመናን ከታቦቱ ፊት ነፍሳቸውን ሰጥተዋል፡፡ የዚህን ክስተት ሙሉ ኃላፊነት ቤተክርስቲያናችን መውሰድ ይገባታል፡፡ ምክንያቱም የበዓላት ሥነሥርዓት አስከባሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሰበካ ጉባዔ እያለ ከሰበካ ጉባዔው ቁጥጥር በላይ የሆነ አንዳች ችግር ሳይፈጠር የመንግሥትን ጸጥታ አስከባሪዎች ወደቦታው መጥራት አስፈላጊ ስላልነበር ነው፡፡ ሕገመንግሥቱ ሃይማኖት እና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው ሃይማኖት በፖለቲካ ፖለቲካም በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ብሎ በደነገገበት ሁኔታ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ከታቦቱ ፊት እንዲገኙ ማድረጋቸው የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች ያስተቻል፡፡

Tuesday, January 16, 2018

ውግዘት በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ሰስብከት በበርካታ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል የተሞላ ሀገረ ስብከት ነው፡፡ ታዲያ ይህን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል ተመልክቶ ዝም ማለት ለተዋሕዶ ልጆች አላስቻላቸውም ነበርና የሚጠበቅባቸውን የልጅነት ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ በርካታዎች ታስረዋል ተደብድበዋል ተንገላተዋል ተጉላልተዋል ተርበዋል ተጠምተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን አያሳስባቸውም ምክንያቱም ትግላቸው ዘላለማዊ ርስትን ስለሚወርሱባት ሃይማኖታቸው ሲሉ ነውና፡፡ ህጋዊውን መንገድ ተከትለው ተስፋ ባለመቁረጥ በልበ ሰፊነት ከሰባት ጊዜ በላይ በግል ወጫቸው አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤት ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን አጥጋቢ መልስ ማግኘት አልተቻለም፡፡

አጣሪ ኮሚቴ ተብሎ በብጹእ ሥራ አስኪያጁ ተልከው የነበሩት ሦስቱ ልዑካንም የእግዚአብሔርን ነገር ትተው ራሳቸውን በይሁዳ መስመር አገኙት፡፡ ይሁዳ እግዚአብሔርን ለአይሁዳውያን ጠቁሞ ስሞ አሳልፎ ይሰጠው እንደሆነ እንጅ ሐዋርያትን መስሎ ከጎኑ አይቆምም፡፡ የእነዚህ የልዑካኑ ጉዳይም እንዲሁ ሆኖ ነው የተገኘው፡፡

Wednesday, January 3, 2018

ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብጹእ አቡነ ዘካርያስን እረፍት ነስቷቸዋል



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ብጹእ አቡነ ዘካርያስን የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ወቅታዊ ሁኔታ ከማንም በላይ አሳስቧቸወል፡፡ ብጹእነታቸው አንድ ሊቀ ጳጳስ በሌላው ሀገረ ስብከት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህግ ሳያውቁ እንዳልሆነ ለቅዱስ ፓትርያርኩ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ገልጠዋል፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ጉዳይ እጅጉን ያሳሰባቸው በጎጃም ተወልደው ያደጉ በዚያው የተማሩ ያስተማሩ በሊቀ ጳጳስነትም ደረጃ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው ብዙ ዲያቆናትን እና ካህናትን ክህነት የሰጡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ሃይማኖትን ደግሞ አድማስ እንደማይገድበው በመግለጽ ጭምር ነው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ የጻፉ፡፡