Friday, September 29, 2017

✍✝ “ራስን ማሰረቅ የሞት ሞት ነው” ብጹእ አቡነ ቀውስጦስ✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ብጹእነታቸው አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ምዕራብ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነገረ ተሐድሶን በገለጹበት በእንባ የታጀበው ንግግራቸው እጅጉን ልባችንን ነክቶናል፡፡ ቤተክርስቲያናችንን እንድንጠብቅ እምነታ

Thursday, September 28, 2017

✍✝ ወልደ አብ የተሰኘው የቅባት መጽሐፍ ተወገዘ✝✍





፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የተወገዘው የቅባቶች መጽሐፍ፡፡
አቡነ ዘካርያስ ወልደ አብን ያወገዙበት መጽሐፍ፡፡
በመጀመሪያ ለዚህ መጽሐፍ መወገዝ ፊርማ የሰጣችሁ የሰበሰባችሁ እህቶች ወንድሞች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ምንም እንኳ ለዛሬው የዚህ መጽሐፍ መወገዝ እንኳ የእኛ ፊርማ ምንም ድርሻ ባይኖረውም ለጥቅምት ሲኖዶስ ግን ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ የሚያደርግ ሥራ ተሠርቷል፡፡
ብጹእ አቡነ ዘካርያስ ወልደ አብን አወገዙ፡፡







ብጹእነታችው አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ለብዙ ዓመታት ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡ ባሳለፍነው ፳፻፱ ዓ.ም ብጹእነታቸው ምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከትን ያገለግሉ በነበረበት ጊዜ ጠፍቶብኛል ያሉትን አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር አሁን እያገለገሉ ካሉበት ከሰሜን አሜሪካ ከምእመናን አሰባስበው መመለሳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የት እንደደደረሰ ምን እንደተሠራበት በማን አካውንት እንደገባ ወዘተ የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ባያውቁትም ማለቴ ነው፡፡
አቡነ ዘካርያስ

Sunday, September 24, 2017

✍✝ “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ብሒለ መናፍቃን✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በዛሬው ልጥፍ ላይ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን በብዛት እሰበስብበታለሁ ብየ እጠብቃለሁ፡፡ ፕሮቴስታንታዊ መፈክር ከሆኑ ዐረፍተ ነገሮች መካከል አንዱ ይህ በርእሱ ላይ የጻፍኩት ብሒል ነው፡፡
#በነገራችን_ላይ_ለፕሮቴስታንት_እምነት_ጥላቻ_ስላለኝ_አይደለም_ይህን_የምጽፈው፡፡ #የማይመለከታቸውን_የተዋሕዶ_እምነታችንን_ሲሳደቡ_ስሰማ_ጊዜ_ነው_እንጅ፡፡
፠ ማንም ሰው የፈለገውን ዓይነት እምነት በነጻነት ያለፍርሐት ያለችግር ማምለክ ፈጣሪያችን የቸረን መብት ነው፡፡ ነገር ግን አንዱ ያንዱን እያንቋሸሸ ሊናገር አይገባውም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መከራከር መረጃ መለዋወጥ ግን ጤነኛ ነው ብየ አምናለሁ፡፡ እኔም በዚያ በኩል ጤነኛ በሆነው መንገድ ነው የምቀጥለው፡፡ ለመጻፍ ያነሣሣኝ ጉዳይ “ኦርቶዶክሶች ኢየሱስ ሲጠራ አይወዱም” እያሉ በየአዳራሹ ወሬ የሚያራግቡ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ስላሉ ነው፡፡ ይህንንም በተለያዩ ቪዲዮዎች ለመከታተል ሞክሬያለሁ፡፡

Saturday, September 23, 2017

✍✝ ሁለተኛ ጥምቀት አለን ? የቅባቶች ሰፈር ሲመረመር✝✍



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠


ቪዲዮውን ላመየት ይህንን ሊንክ  ተጫኑ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=5fRZKnwkGrc&feature=youtu.be
 

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
#በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ የደረሰኝ ቪዲዮ ይኼ ነው፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት ስለሆነ የድምጹ ጥራት ላይ የተወሰነ ችግር ሊኖርበት ይችላል ለዚያ ችግር ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
#በመጀመሪያ #ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡
#በዋናነት በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚነገረው ነገር #ፊርማ ለማሰባሰብ ብቻ ሲባል #ሙሉ #በሙሉ ውሸት እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡
#በሰላምታ የሚጀምረው ይህ የውሸት አባት በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር መሥራቱ ያሳዝናል፡፡ #የማስተምረው ነገር የለኝም ይላል የመርኃ ግብሩ አስፈጻሚ፡፡ የኦሪት መስዋእት ይሰዋባቸው የነበሩ አምስት አብያተ ክርስቲያናትን ዘርዝሮ ተናገረ፡፡ 

Thursday, September 21, 2017

✍✝ ስም የሌለው ሃይማኖት አለን? ✝✍





፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
#በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ አንድ ቪዲዮ በውስጥ መስመር ተልኮልኛል፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት ስለሆነ የድምጹ ጥራት መስተካከል ስላለበት እርሱን በሚገባ አስተካክየ ጨርሻለሁ፡፡ ድምጹ በሚገባ ስለሚሰማ ጠብቁኝ ይለቀቅላችኋል፡፡
#በመጀመሪያ #ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡
ኤፌ ፬፥፭ “…አንድ ሃይማኖት…” ይላል ብርሃነዓለም ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ይች ሃይማኖት ግን የትኛዋ ናት? እንግዲህ ይህንን ለመመለስ የግድ ??የሃይማኖቶችን?? የትመጣነት ማጥናት እና መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ባለበት ዘመን የነበረው ሃይማኖት የትኛው ሃይማኖት ነበር ቅዱስ ጳውሎስስ የኖረበት ዘመን ከመቸ እስከመቼ ነው? እያንዳንዳችን እየተከተልነው ያለው ሃይማኖትስ መቼ የተጀመረ በማን የተጀመረ እንደሆነ መርምረን እናውቃለን? አሁን ግን የግድ መመርመር ይኖርብናል፡፡

Wednesday, September 20, 2017

✍✝ ተሐድሶ መናፍቃን እና ስልታቸው ---ክፍል ፭ መጨረሻ✝✍


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
#በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ አንድ ቪዲዮ በውስጥ መስመር ተልኮልኛል፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት ስለሆነ የድምጹ ጥራት መስተካከል ስላለበት እርሱን በሚገባ አስተካክየ ጨርሻለሁ፡፡ ድምጹ በሚገባ ስለሚሰማ ጠብቁኝ ይለቀቅላችኋል፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠


በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s

✍✝ ተሐድሶ መናፍቃን እና ስልታቸው ---ክፍል ፬✝✍


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
#በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ አንድ ቪዲዮ በውስጥ መስመር ተልኮልኛል፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት ስለሆነ የድምጹ ጥራት መስተካከል ስላለበት እርሱን እያስተካከልኩ ነው የምገኘው፡፡ ድምጹ በትክክል መሰማት የሚችልበት ደረጃ ላይ ሲሆን ይለቀቃል፡፡
፠ የተሐድሶዎቹን ቀሪ ጉዶች ከዚህ ጋራ የተያያዘውን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡ በጣም የሚገርመኝ ዛሬም ድረስ ሽንጡን ገትሮ የሚከራከርላቸው ሰው መኖሩ ነው፡፡ #ቃለዓዋዲን #የቴሌቪዥን መርኃግብርም የእኛ ነው ብሎ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጥጦ የሚመለከት ሰው መኖሩ ደግሞ በጣም ያሳዝናል፡፡ የእኛን መለየትማ እወቁበት እንጅ ምነው፡፡ 

በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s

አገልግሎት ስብከት ብቻ
አንድ የተሐድሶ መናፍቅ ሰባኪ አርብና ረቡዕን በሌሊት ሲመገብ ቅር አይለውም፡፡ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? ሲሉትም እኔ አገልጋይ ስለሆንኩ እንዳይደክመኝ ነው ይላል፡፡ በእውነት አገልግሎት ስብከት ብቻ ነው? ጹሙ ለ ማለት ስ መጾም አያስፈልግምን? ያለ ምግብ ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማርስ አይቻልምን? እንዲህ አይነቱ የሰባኪነትን ክብር ማቃለል የሚፈልግ የዲያብሎስ የግብር ልጅ ነው፡፡ ሐዋርያት ሳንበላ ሳንጠጣ ወንጌልን አንናገርም ብለው ነበር እንዴ? ቅዱስ ጳውሎስ ዕለት ዕለት የሚያሳስበኝ የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ነገር ነው ያለው ከሆዱ መሙላት በኋላ መሰላችሁ እንዴ? አይደለም ብዙ መከራ እንደደረሰበት ዘርዝሮ ያንን ሁሉ ከምንም ሳልቆጥር የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ያሳስበኛል ነው እኮ ያለው፡፡
የሚደግፈው እንዳያጣ ነው
ብዙዎች “እገሌ በስብከቱ ውስጥ ድንግል ማርያምን የማይሰብከው ለምንድን ነው?” ይላሉ፡፡ ድንግል ማርያምን የማይሰብከውማ ድንግልንአምባ መጠጊያ እያደረገ በእናትነት ጥላዋ ሥር እየተጠለለ የሚኖር ትውልድ እንዳይፈጠር ነው፡፡ ትውልዱ ድንግል ማርያምን ከተጠጋ እርሱን የሚደግፈው ደጋፊ እንዳያጣ ስለሚሰጋ እርሱን ብቻ እንዲከተሉት ለማድረግ ሌሊት ከቀን የራሱን የማይጠቅም ታሪክ ሲዘረዝር ይኖራል፡፡ በተጨማሪም እመብርሃንን የካዱ ለሆዳቸውያደሩ ስለሆኑ የእመቤታችንን ሥም ማንሣት አይፈልጉም፡፡
እውነትን ለማስጠላት
መናፍቃን ሻሽ ጠምጥመው መስቀል ጨብጠው ሰክረው ለመውደቅ ይንገዳገዳሉ፡፡ የምንኩስና ቆብ ገዝተው ይለብሱና ከሴት ጋር ተቃቅፈው መንገድ ለመንገድ ይዞራሉ፡፡ የሰውን ሕሊና ለመስረቅም ጀርባቸውን በብረት እየገረፉ እግዚአብሔር የላከን ነን እያሉ በየቦታው ይልከሰከሳሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት በርካታ ሕዝብ በሚገኙባቸው ቦታዎች መሆኑ አውነተኛ ካህናትን፣ መነኮሳትን ባሕታውያንን ለማስጠላት ነው፡፡ ወይ የዘመኑ ቄስ! ወይ የዘመኑ መነኩሴ! ወይ የዘመኑ ባሕታዊ! እያለ ያያቸውና የተመለከታቸው ሁሉ አውነተኞቹን ይሰድባል፡፡ ቤተክርስቲያንም እንድትጠላ ጃንጥላ ዘቅዝቀው ሰሌን ዘርግተው ቅዱሳት ሥዕላትን አንግበው መስቀል ይዘው የቅዱሳንን ሥም እየጠሩ የዚህ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ እጃችሁን ዘርጉ እያሉ የየዋሃንን ገንዘብ መስከሪያ የሚያደርጉ እየተበራከቱ ነውና ወገኔ መንቂያ ሰዓትህ አሁን ነው እንቅልፍ ይብቃህ፡፡
ድፍረት
የተሐድሶ መናፍቃን ዋና መርኅ ድፍረት ነው፡፡ በትምህርታቸውና በመዝሙራቸው ውስጥ ይህን ድፍረታቸውን ለትውልዱ ሁሉ በማለማመድ ላይ ይገኛሉ፡፡“ዓለምን ተኝቶ የሚገዛ ፈጣሪ ነው የምናመልከው”ይላሉ፡፡ ይህን የድፍረት ቃል ማነው ያስተማራቸው?ከየትስ ነው ያነበቡት?በእውነት ዓለም የምትተዳደረውበሚያንቀላፋ አምላክ ነውን? እስራኤልን የሚጠብቅ አያንቀላፋም ሲባል ነው ከመምህራን የሰማነው ከመጻሕፍት ያነበብነው የዛሬ ደፋሮች ግን እግዚአብሔርን የሚያንቀላፋ እንቅልፍ የሚያሸንፈው አድርገው ያስተምራሉ፡፡“የሳሎኑ ጽጌረዳ” በ ማለት  ክርስቶስን ከሰው ሰራሹ የፕላስቲክ አበባ ጋር የሚደምሩም ድፍረትን በጥሩ ሁኔታ የለመዱ ደፋሮች አሉ፡፡ “ዕድሜ ብቻ! ማቱሳላ ያን ያህል ዘመን ቢኖር ምን ሠራ” እያሉ ማቱሳላን የሚንቁ ሽማግሌዎችንም የሚሳደቡ ድፍረት ገንዘባቸው የሆኑ አፈ ጮሌዎችም አሉ፡፡ እነርሱ በተጠቀሙት ቃል እኛም ብንገልጸው ለጆሮ የሚያሳክክ ከባድ ኑፋቄ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ከድፍረት ኃጢአት ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባናል፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም ፲ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

✍✝ ተሐድሶ መናፍቃን እና ስልታቸው ---ክፍል ፫✝✍


====================================
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
====================================

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በምን ዓይነት መንገድ እንደተጀመረ እና ወደፊት በቤተክርስቲያናችን ላይ ማድረስ የሚፈልጉት ጥቃት ምን እንደሆነ ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡ ዛሬም በጋሻው ዘርፌ አሰግድ ምናምን ተሐድሶ ናቸው ምናምን የሚል ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ካለ እርሱ ችግር አለበት፡፡

በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s
ቤተ ክርስቲያንስ ሄዋን ናት
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ“ያረጀችው ቤተ ክርስቲያን አሮጊቷ ሣራ ወለደች፡፡ እኔን ወለደች፣ እገሌን ወለደች፣ እገሊትን ወለደች” እያለ ተሐድሶ የወለደቻቸውን ይዘረዝራል፡፡ቤተክርስቲያን አሮጌ መባሏ ያበሳጨው የተዋሕዶ ልጅ ወደ “ሰባኪው”ተጠግቶ “መጽሐፍ ማንበብ ይቀርሃል ሣራ በእርጅናዋ ወራት የወለደችው አንድ ልጅ ይስሐቅን ብቻ እንደነበር አላወቅህም እንዴ? አሮጊቷ ሣራ እኔን፣ እገሌን፣ እገሊትን ወለደች እያልህ የምትቀባጥር፡፡ ቤተ ክርስቲያንስ አሮጊት ሣራ ሳትሆን ቀድሞ የነበረች መንታ መንታ የምትወልድ የብዙዎች እናት ሄዋን ናት፡፡፡ የግል ክብርህን ፈልገህ ደግ ይስሐቅን ነኝ ለ ማለት  ክብርት ቤተክርስቲያንን ዝቅ ዝቅ ያደረግህበት ይህ ደፋር አንደበት በደሙ በመሠረታት በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት ስትቆም ምን ይናገር ይሆን?” በ ማለት  ብዙ ትምህርት አስተማረው፡፡

ስብከት ጋዜጠኛነት አይደለም
“እገሌ ሲናገር ሲሰብክ ልዩ ተሰጥዎና ግርማ ሞገስ አለው፡፡ ስለዚህም ተሐድሶ መናፍቅ ሊባል አይገባውም” የሚሉ ደጋፊዎች በዝተዋል፡፡እነዚህ ደጋፊዎች ያልገባቸው ነገር የድምፅ ማማር ወይም የንግግር ግርማ ሞገስ መኖር የሰባኪ መመልመያ መስፈርት ማድረጋቸው ነው፡፡ ስብከት የድምፅ ግርማ ሞገስን ብቻ መሠረት ያደረገ የጋዜጠኛነት ሙያ አይደለም፡፡ ስለዚህ የንግግር ግርማ ሞገስ ያላቸው የተሐድሶ መናፍቃን ጋዜጠኛነት መወዳደር ይችላሉ እንጅ በድምጻቸው ማማር ብቻ ተዋሕዶን ሊሰብኩ አይችሉም፡፡ ስብከት በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጅ እንደጋዜጠኛ መናገር ብቻ አይደለምና፡፡
በጣም ይመቸኛል
“እገሌ እና እገሊት ሲዘምሩ ድምጻቸው በጣም ይመቸኛል” የሚሉ በርካታ ደጋፊዎች በዝተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በመዝሙሩ ውስጥ ምን መልእክት እንደተላለፈ አልተረዱም፡፡ እነርሱ የተማረኩት በዘማሪዎች የድምጽ ማማር ብቻ ነው፡፡ የድምጽ ማማርን የሚደግፉ ሰዎች ደግሞ ዘፋኞችንም የሚደግፉ በመሆናቸው መዝሙርና ዘፈን የተቀላቀለባቸው በመሆናቸው“ድምጻቸው ይመቸኛል” ከ ማለት  የዘለለ ሌላ የሚደግፉበት ቃል የላቸውም፡፡ ስለዚህ መዝሙርን በዘማሪዎች ድምጽ ማማር ብቻ ሳይሆን በውስጡ ባለው መልእክትና በዜማው የቤተክርስቲያናችን መሆን አለመሆኑን ልንገነዘበው ያስፈልጋል፡፡
ሌባ ለአመሉ…
“እገሌ ባዘጋጀው ልዩ የስብከት መርኀ ግብር ይህን ያህል ሺህ ብር ለቤተክርስቲያን ገቢ አደረገ፡፡ ስለዚህ እገሌ ተሐድሶ ሊባል እንዴት ይችላል በእኔ በኩል ግን ተሐድሶ መናፍቅ መባሉን አልደግፍም” የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች “ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል” የሚለውን ሥነ ቃል የዘነጉ ናቸው፡፡ እነርሱ እንደሚሉት ለቤተክርስቲያን የሰጠው ገንዘብ እንጅ ጥሩ ምእመን አይደለም እኮ ፡፡ ቤተክርስቲያን የምትፈልገው ደግሞ በሺህ የሚቆጠር ጥሩ ምእመንን ነው፡፡ ስለዚህ ገንዘብ መስጠት ብቻውን የተዋሕዶ ልጅ የሚያሰኝ ባለመሆኑ ትምህርቱን፣ ሥርዓት አጠባበቁን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ 
የሚያስለቅስህ ፈልግ
ተሐድሶ መናፍቃን ስብከቶቻቸው በቀልድ በሳቅ የታጀቡ በመሆናቸው ለመሳቅ የሚከተላቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ አንድ ወጣት“እገሌ ሲሰብክ እየቀለደና እያሳቀ በጣም እያዝናና ስለሆነ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ብውል ባድር እንዴት ደስ ይለኝ ነበር” እያለ ለአባቱ ይነግራቸዋል፡፡ አባቱም “ልጄ ከዛሬ ጀምረህ ኃጢአትህን እየነገረ ስለኃጢአትህ በንስሓ የሚያስለቅስህ ሰባኪ ፈልግ” አሉት፡፡ ስለዚህ የሚያስፈልገው ኃጢአታችንን እያሰብን ወደ ንስሓ የሚመራን ስብከት እንጅ የሚያስቅ የሚያዝናና አይደለም፡፡ ሳቅ ጨዋታማ በዓለምስ ሞልቶ ተርፎ የለም እንዴ? ቤተክርስቲያን መሄድ ያስፈለገው ለንስሓ ነው እንጅ፡፡
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም ፱ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

Monday, September 18, 2017

✍✝ ተሐድሶ መናፍቃን እና ስልታቸው ---ክፍል ፪✝✍




====================================
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
====================================

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s
ተሐድሶ ሁሌም ለቅሶ
ተሐድሶ በዚህ ዘመን ለተነሡ መናፍቃን መጠሪያ ስም ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችንን ሥርዓት በማፍረስ እና መሠረቷን ለማናጋት የሚንቀሳቀስ ኃይል ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን  የገሐነም ደጆች እንኳ የሚርዱላት በክርስቶስ ደም የተመሠረተች በመሆኗ ከውጭ የሚወረወረው ቀስትና ከውስጥ ለማፍረስ የሚገፏት ምንም ሊያደርጓት አይችሉም፡፡ እነዚህ መናፍቃን በሚያነሧቸው ርዕሰ ጉዳዮች ቤተክርስቲያናችን ስለምትረታቸው “ተሐድሶ ሁሌም ለቅሶ” ሆኖባቸዋል፡፡
ስላልሰማህ ይሆናል
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ ከመድረክ ላይ ወጥቶ በመጀመሪያ ስሙን ቀጥሎም የሚማርበትን ኮሌጅ ከገለጠ በኋላ ስብከት አይሉት ስድብ መናገር ጀመረ፡፡ “ይህች ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከ 10 ዓመታት በፊት ወንጌል አልተሰበከባትም ነበር ክብር ምስጋና ይግባው የኔ ጌታ ዛሬ ግን እኔን በፊታችሁ አቁሞ ወንጌልን እንድሰብክ በክብር ሾመኝ፡፡ ይኼውላችሁ እኔን አስነሥቶ የተመረጠውን ሕዝብ በእግዚአብሔር ቃል ያረሰርሳል፡፡ ለዚህ እልልታ አይገባም? እልል በሉ እባካችሁ! አጨብጭቡ!” እያለ ከስብከቱ ይልቅ የእልልታው ጊዜ በዝቶ እልል የሚሉት ጉሮሯቸው ደረቀ፡፡ ይህን ኑፋቄውን እንደጨረሰ ለመርኀ ግብር መሪው ቦታውን ለቅቆ ከመድረኩ ወርዶ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ መርሐ ግብር መሪው በጣም አስተዋይና የተማረ ነበርና “ወንድማችን ተሐድሶዎች የሚያስተምሩትን ትምህርት በግልጥና በሚገባ ስለነገረን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀድሞ በነቢያት ኋላም በሐዋርያት ትምህርት የጸናች ናት፡፡ ወንድማችን  ምናልባት ከ 10 ዓመታት በፊት ያለውን ስላልሰማህ ይሆናል እንጅ እነ አትናቴዎስ፣ እነ ዮሐንስ አፈወርቅ በሐገራችንም እነ አቡነ ተክለ ሐይማት፣ እን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ኧረ ስንቱ! ወንጌልን ዞረው አስተምረዋል፡፡ አያችሁ ወገኖቼ የዘመኑ መናፍቃን ወንጌል የተሰበከ እነርሱ ከተወለዱ በኋላ ስለሚመስላቸው ከ 10 ዓመታት በፊት ወንጌል የተሰበከ አይመስላቸውም፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ አይነቱን ትምህርት የሚያስተምሩት” በ ማለት  የተሐድሶውን ትምህርት ውድቅ አደረገበት፡፡
ቤተ ክርስቲያንስ ሄዋን ናት
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ“ያረጀችው ቤተ ክርስቲያን አሮጊቷ ሣራ ወለደች፡፡ እኔን ወለደች፣ እገሌን ወለደች፣ እገሊትን ወለደች” እያለ ተሐድሶ የወለደቻቸውን ይዘረዝራል፡፡ቤተክርስቲያን አሮጌ መባሏ ያበሳጨው የተዋሕዶ ልጅ ወደ “ሰባኪው”ተጠግቶ “መጽሐፍ ማንበብ ይቀርሃል ሣራ በእርጅናዋ ወራት የወለደችው አንድ ልጅ ይስሐቅን ብቻ እንደነበር አላወቅህም እንዴ? አሮጊቷ ሣራ እኔን፣ እገሌን፣ እገሊትን ወለደች እያልህ የምትቀባጥር፡፡ ቤተ ክርስቲያንስ አሮጊት ሣራ ሳትሆን ቀድሞ የነበረች መንታ መንታ የምትወልድ የብዙዎች እናት ሄዋን ናት፡፡፡ የግል ክብርህን ፈልገህ ደግ ይስሐቅን ነኝ ለ ማለት  ክብርት ቤተክርስቲያንን ዝቅ ዝቅ ያደረግህበት ይህ ደፋር አንደበት በደሙ በመሠረታት በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት ስትቆም ምን ይናገር ይሆን?” በ ማለት  ብዙ ትምህርት አስተማረው፡፡
ሥርዓቷ ሳይሆን ሕንጻዋ
አንድ መናፍቅ“ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያረጀች ያፈጀች ናትና በአዲስ ነገር መታደስ ይገባታል፡፡” እያለ በይፋ ይናገራል፡፡ ይህን የሰሙ አንድ የቤተክርስቲያን ሊቅ መናፍቁን አስጠርተው“የምትለው ሁሉ ልክ ነው፡፡ መታደስ ያለበት ግን ሥርዓቷ ሳይሆን ሕንጻዋ ስለሆነ የማሳደሻ ገንዘብ አሰባስብ” ሲሉት ያ መናፍቅ“መታደስ የሚገባው ትምህርቷ ሥርዓቷ ነው እንጅ ሕንጻዋ አይደለም”ይላቸዋል፡፡ሊቁም “በል እንግዲያውስ የራስህን አእምሮ በመልካም ትምህርትና ሥርዓት አድስና ከዚያ በኋላ ብንገናኝ ይሻላል” ብለው አባረሩት፡፡
እንዘምራለን ስትናፍቀን
ተሐድሶ መናፍቃን እግዚአብሔርን የሚናፍቁበትና የማይናፍቁበት ቀንና ጊዜ አላቸው፡፡ ምክንያቱም ሲፈልጉ ዘማሪ ክርስቲያን ሲፈልጉም ታዋቂ ዘፋኝ በመሆን በተደበላለቀና በተመሰቃቀለ ሕይወት ውስጥ ስለሚኖሩ ነው፡፡ በዝማሬዎቻው ውስጥ የምንሰማው
“ዛሬም የአንተ ነው አዲሱ ቀን
እንዘምራለን ስትናፍቀን”
የሚል ነው፡፡ በእውነት እግዚአብሔር የማይናፈቅበት ወቅት አለን? በዚያስ ወቅት መዘመር አስፈላጊ አይደለምን? ዝማሬን የናፍቆት መግለጫ ያደረጉት፡፡ ወገኖቼ ሳናውቅ በተኩላ እየተበላን ስለሆነ መንቃት ያስፈልጋል፡፡
መዶሻ ያልያዘ ሠራዊት
ተሐድሶ መናፍቃን በስብከታቸው እና በመዝሙራቸው ውስጥ “መዶሻ ያልያዘ ሠራዊት” የሚለው መሪ ቃላቸው ሆኗል፡፡ በእውነትም መዶሻ ያልያዘ ከንቱ ሰራዊት ነው፡፡መዶሻው ቃለ እግዚአብሔር የሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሆነበየቦታው ሲዞሩ ይህን ማግኘት ባለመቻላቸው ቃለ እግዚአብሔርን ያልያዘ ሠራዊት ነን ሲሉ “መዶሻ ያልያዘ ሠራዊት” ነን ይላሉ፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ያልያዘ ሠራዊት ደግሞ የአጋንንት ስለሆነ ከተዋሕዶ ልጆች ጋር ምንም ሕብረት የለውም፡፡

በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡


✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም ፰ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝