Tuesday, February 28, 2017

ዝክሪ እና ጳውሊ እነማን ናቸው?---ክፍል ፪



© መልካሙ በየነ
የካቲት 21/ 2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
በመጀመሪያ ( facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ ከዚያ ጽሑፉን ያንብቡ ቀጥለውም ጽሑፉን SHARE, COMMENT, LIKE ያድርጉ፡-
==============================================
በመጀመሪያ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ በዓል በሰላም በፍቅር በአንድነት አደረሳችሁ፡፡ መዋእለ ጾሙን በሰላም በፍቅር አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሣኤው ያደርሰን ዘንድ የአብ ልጅ የድንግል ልጅ ፈቃዱ ይኹንልን፡፡ አሜን፡፡

በክፍል ፩ ሮማውያን በተዋሕዶ እምነታችን ላይ ቀስታቸውን ሊወረውሩ ሲዘጋጁ ንጉሡ ዐፄ ገላውዴዎስ የኢትዮጵያን ሊቃውንት ሰብስቦ ምን እናድርግ ብሏቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንትም ፍርድ በቃ ይስጡን እንከራከርና ሮማውያን ቢረቱን እንልቀቅላቸው ብንረታቸው ይልቀቁልን አሏቸው፡፡ ንጉሡም ፈቅደው ጉባዔ ተደረገ ለኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጉባኤ ዝክሪና ጳውሊ ኾኑ፡፡ ዝክሪና ጳውሊም በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጠገብ የሚገኝ የደብረ ጽሙና ገዳም ሊቃውንት እንደሆኑ ዓይተናል፡፡

እየጻፍኩላችሁ ያለሁት ከራሴ ከመነጨ የመታጀር እውቀት አይደለም በክፍል ፩ እንደገለጽኩላችሁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ካሳተሙት መድሎተ አሚን ከተሰኘው ድንቅ መጽሐፋቸው ከመቅድም ክፍላቸው ላይ በቀጥታ ገልብጨ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የቅብአት እምነት ገብቶናል የሚሉ ጥቃቅን ቀበሮዎች መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ከጥንት የታሪክ መጽሐፍ ወስደው የጻፉትን ታሪክ እኔ ስጽፈው ሲያዩ ታሪክ አበላሽተሃል ብለው ይዘላሉ፡፡ የሚገርመው ይህ መጽሐፍ የታተመው ዛሬ አለመሆኑ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ጥንት የተጻፈ ነው (በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት) ታዲያ ያን ጊዜ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ተሳስተዋል ባሏቸው ነበር፡፡ ግን የት አሉ ስም አጠራር የላቸውም ነበርና ተደብቀው ውስጥ ውስጡን እንደ ፍልፈል የምንፍቅና ጉድጓድ ይምሱ ነበር፡፡ ይህ መጽሐፍ በዕድሜ ቢያንስ የእነዚህን የጥቃቅን ቀበሮዎችን ዕድሜ ሳይበልጥ አይቀርም፡፡ እኔም እየጻፍኩላችሁ ያለሁት ከዚህ የቤተክርስቲያናችን ድንቅ መጽሐፍ እንጅ በድብቅ፣ በስርቆት ማተሚያ ቤቱ እንኳ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ እንደታተመው እንደ “ወልደ አብ” ካለ የክህደት መጽሐፍ ላይ አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህ የመቅድም ገጻቸውን አሁንም እጽፍላችኋለሁ መልካም ንባብ!!!

ኹለተኛ ጥያቄ፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሮማዊ ተነሥቶ መለኮት ሥጋ አልሆነም ሥጋም መለኮት አልሆነም ሥጋ ለመለኮት እንደ ብረት ልብስ እንደ ጥሩር ኾነው መለኮትና ሥጋ እንደ ኀዳሪና ማኅደር ኾነው መለኮት የመለኮትን ሥራ ትስብእትም የትስብእትን ሥራ ሲሰሩ ኖረው በዕርገቱ ጊዜ የለበሰውን ሥጋ አውልቆ በሦስተኛው ሰማይ አኑሮት በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ተቀመጠ፡፡ የዚህም ምሳሌው አንድ ንጉሥ ለጦርነት ወደ ሰልፍ ሲገባ የጦርነት ልብስ ይለብሳል፡፡ ሲዋጋ ውሎ ድል ካደረገ በኋላ የለበሰውን የጦር ልብስ አውልቆ ከግምጃ ቤት ሰቅሎ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ እንደሚቀመጠው ያለ ነው እንጅ ትስብእቱን ከመለኮቱ ጋራ በአባቱ ቀኝ አያስቀምጠውም አለ፡፡

አባ ዝክሪ ሲመልስ ነፍስ ርቀቷን ሳትለቅ ሥጋ ግዙፍ ውሱን መኾኑን ሳይለቅ ተዋሕደው አንድ ሰው እንዲኾኑ መለኮት ምልዐቱን ስፍሐቱን ርቀቱን ሳይለቅ ትስብእትም ግዙፍነቱን ውሱንነቱን ሳይለቅ በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ኾኗል እንጅ እንደ ልብስና እንደ ገላ አይደለም አለ፡፡

ሮማዊ መለኮት ከደረሰበት ኹሉ ይህ መዋቲ ትስብእት ደረሰ ትላለህን አለ፡፡

አባ ዝክሪ ሲመልስ እኔስ መለኮት እና ትስብእት በተዋህዶ አንድ ስለሆኑ መለኮት በሥጋ ውሱን ግዙፍ ኾነ፤ ትስብእትም በመለኮት ምሉዕ ስፉሕ ረቂቅ ኾነ እላለሁ፡፡ ትስብእት ከመለኮት ተለይቶ በሦስተኛው ሰማይ እንዳልቀረ  በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ እንደተቀመጠም ሲያስረዳ አሜሃ ትሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው እንዘ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ብሏል፡፡ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም እንዲመጣ ሲያስረዳም ወአመ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው በስብሐተ አቡሁ ወኲሎሙ መላእክቲሁ ምስሌሁ ብሏል፡፡ ይህ ንባብ በቅዱስ ወንጌል መጻፉን ታምናለህ ትክዳለህ? አለው፡፡ ሮማዊ መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡

ሦስተኛ ጥያቄ፡፡
ሮማዊ እኔ ክርስቶስን ፍጡር እለዋለሁ አለ፡፡
አባ ጳውሊ ሲመልስ ክርስቶስን ፍጡር የሚል ንባብ ከምን ታገኛለህ አለው፡፡

ሮማዊ አምላክ ከኾነ ከሣምራዊት ውኃ እስኪለምን ድረስ ለምን ተጠማ ከላይ ያለው ሐኖስ ከታች ያለው ውቅያኖስ በመኃል እጁ ሲሆን አምላክ ይጠማልን አለ፡፡

አባ ጳውሊ ሲመልስ ፍጡር ከኾነ የእግዚአብሔርንስ ስጦታ አውቀሽ ቢኾን ይህ ውኃ አጠጭኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደሆነ ተገንዝበሽ አንች የሕይወት ውኃን አጠጣኝ ብለሽ በለመንሺው ነበረ እርሱም በሰጠሸ ነበረ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ኹሉ ዳግመኛ ይጠማል እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ዳግመኛ ይህ እኔ የምሰጠው ውኃ ለዘላለም ሕይወት ሊኾነው ከውስጡ ሲመነጭ ይኖራል እንጅ ዳግመኛ አይጠማም ለምን አላት አለው፡፡

======================================================
ከላይ የተመለከትናቸው ጥያቄዎችና መልሶች ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የተዋሕዶ እምነትን ለማስጠበቅ ያደረጉትን ክርክር ነው፡፡ በእያንዳንዱ ጥያቄ ላይ ሰፊ፣ ግልጽ፣የማያሻማ እና አሳማኝ ማስረጃ በማቅረብ እየረቱ ያሉት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ናቸው፡፡ የዛሬ የቅብአት ምንፍቅና አራማጆች እነዚህን ሊቃውንት ስማቸውን ብቻ ወስደው ለግል ፍላጎታቸው እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡ በቅርቡም በእነዚህ ሊቃውንት ስም እንደ “ወልደ አብ” የት እንደታተመ የት እንደሚከፋፈል በማይታወቅበት መልኩ በስውር መጽሐፍ አሳትመው ምንፍቅናቸውን እንደሚዘሩ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እነዚህ መናፍቃን የሚጠቀሙት ስማቸውን (ዝክሪ እና ጳውሊ የሚለውን) ብቻ እንደሆነ ግን ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም ዝክሪ እና ጳውሊ የኢትዮጵያን ሊቃውንት በአፈ ጉባዔነት እየመሩ የሮማውያንን የካቶሊክ ክህደት ያሳደዱ ናቸውና ከካቶሊክ እምነት ቅርንጫፍ ከሆነው ቅብአት ጋር ኅብረት የላቸውም፡፡
ይቆየን
ይቀጥላል፡፡

Monday, February 27, 2017

ዝክሪ እና ጳውሊ እነማን ናቸው?---ክፍል ፩



© መልካሙ በየነ
የካቲት 20/ 2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
በመጀመሪያ ( facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ ከዚያ ጽሑፉን ያንብቡ ቀጥለውም ጽሑፉን SHARE, COMMENT, LIKE ያድርጉ፡-
==============================================
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውስጥ እንደ ትኋን ተጣብቀው ከሀሊበ ጸጋዋ እየተጎነጩ በክህደት በዘረዘረ ጥፍራቸው የሚባጭሩ፤ በምንፍቅና በበለዘው ጥርሳቸው የሀሊብ ምንጮቿን የሚነክሱ የጨለማ ልጆች (ውሉደ ጽልመት) ከላይ ስማቸውን የጠራናቸውን ሊቃውንት በመጥቀስ እየተጓዙበት ያለውን የጥፋት ጎዳና እንዳቀኑላቸው ይናገራሉ፡፡ “ዝክሪ እና ጳውሊ በብራና መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለውልሃል” እያሉ በእነዚህ ሊቃውንት ስም የሚቀልዱ “ወልድ በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ” የሚሉ የካቶሊክ ቅርንጫፎች እያቆጠቆጡ ናቸው፡፡ ለዚህ ማቆጥቆጣቸው ምክንያት ደግሞ ሰይጣን ለራሱ ስራ እና ዓላማ ማስፈጸሚያነት በአንዳንድ ገዳማት እና አድባራት ላይ ያስቀመጣቸው ምሥጢር ያልተገለጠላቸው በፈለገ አርዮስ የሚፈስሱ  “መምህራን” ናቸው፡፡ በቅርቡ ልባቸውን ሞልተው፣ ደረታቸውን ነፍተው፣ ሽንጣቸውን ገትረው፣ ዓይናቸውን አፍጥጠው፣ ጥርሳቸውን አግጥጠው “ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ቅብአትነት ከበረ፤ አብ በቀደመ መውለዱ በማኅጸነ ማርያም ዳግመኛ ወልድን ወልዶታል” እያሉ አርዮስ “ወልድ ፍጡር” ማለቱ ስህተት እንዳልሆነ አብዝተው ይጮኸሉ፡፡ ይህንን ክህደታቸውንም “ወልደ አብ” የሚል ስም በመስጠት መጽሐፍ እስከማሳተም እንደደረሱ ከዚህ በፊት መረጃውን አቅርበናል፡፡ ይህ መጽሐፍ እርስ በርሱ የሚጋጭ አስተምህሮ የያዘ ከንቱ መጽሐፍ እንደሆነ ከዚህ በፊት ከ10 በላይ ትምህርቶችን አስተላልፈናል፡፡ አሁን የምንመለከተው አንዳንድ የዚህ እምነት አስተምሮ በትክክል ሳይገባቸው ገብቶናል ስለሚሉ ወጣቶች ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች የጎንቻው መምህራቸው “ሄኖክ” በሚበርርበት የክህደት ክንፍ የሚበርሩ ናቸው፡፡ ማስረጃ አይጠቅሱም መምህር አይጠይቁም እነርሱ በጭፍኑ ብቻ  ይከራከራሉ፡፡ በተለይ ከላይ ስማቸውን የጠቀስናቸውን ሊቃውንት ለራሳቸው የክህደት አካሄድ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በእውነት ዝክሪ እና ጳውሊ ግን “በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ” ብለዋልን?

ስለእነዚህ ሊቃውንት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ በጻፉት “መድሎተ አሚን” ላይ በመቅድም ገጻቸው ይናገራሉ፡፡ ሊቁ በመቅድማቸው ኹለተኛ ክፍል ላይ “ይህ የካቶሊክ ባህል ወደ ኢትዮጵያ በምን ጊዜ እንደመጣና የኢትዮጵያ ሊቃውንት በምን ዓይነት እንደተቃወሙት የሚገልጽ ታሪክ” በማለት ጽፈዋል ይህንን ክፍል እነሆ መልካም ንባብ!

ኢትዮጵያን ግራኝ መሀመድ በወረራት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ከፖርቹጊዝ መንግሥት እርዳታ ጠይቀው እርሳቸው ከሞቱ በኋላ በፖርቹጊዞች እርዳታ ግራኝ ድል ሆኖ ኢትዮጵያ ሙሉ ነጻነቷን አግኝታ መንግሥቷን በትክክል ማቋቋሟ የታወቀ ነው፡፡

በዚህ ጊዜ ከኢትዮጵያ ተልኮ ፖርቹጊዞችን ለእርዳታ ያመጣው ቤርሙዲዝ ከኢትዮጵያ ግዛት ገሚሱ ለፖርቹጊዝ መንግሥት ይሰጥ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ከእንግዲህ ወዲያ አቡን ከእስክንድርያ መምጣቱ ቀርቶ ከሮም ይምጣ እኔም ለኢትዮጵያ አንደኛ መጀመሪያ ሮማዊ ጳጳስ ልሁን ብሎ ዐፄ ገላውዴዎስን ጠየቀ፡፡ ዐፄ ገላውዴዎስም ሊቃውንቱን ሰብስበው ምን እናድርግ ብለው ጠየቁ፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንትም ፍርድ በቃ ይስጡን እንከራከርና ሮማውያን ቢረቱን እንልቀቅላቸው ብንረታቸው ይልቀቁልን አሏቸው፡፡ ንጉሡም ፈቅደው ጉባዔ ተደረገ ለኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጉባኤ ዝክሪና ጳውሊ ኾኑ፡፡

ዝክሪና ጳውሊም በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጠገብ የሚገኝ የደብረ ጽሙና ገዳም ሊቃውንት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሮማውያንን ሀገራችሁ ወዴት ነው ሃይማኖታችሁ ምንድን ነው ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ ሮማውያን ሲመልሱ ሀገራችን ሮም ነው፤ ሃይማኖታችንም ኹለት ባሕርይ ኹለት ጠባይዕ አንዱ የመለኮቱ አንዱ የትስብእቱ እንላለን፡፡ ኹለተኛም ወልድ ከአብ ያንሳል መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል እንላለን አሏቸው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሲመልሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ የሚል ምን አለ እስኪ አስረዱን አሏቸው፡፡

ሮማውያን ሲመልሱ እርሱው ራሱ ወልድ ደቀመዛሙርቱ ሕልፈተ ዓለም የሚሆነው መቼ ነው ብለው ቢጠይቁት መላእክትም ቢሆኑ ወልድም ቢሆን ከአብ በቀር ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የሚያውቃት የለም ብሏል፡፡ ስለዚህ አብ መለኮት ስለሆነ ያውቃል ወልድ መንፈስ ቅዱስ ግን መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም እንላለን እናንተ ይህን ነገር ምን ትሉታላችሁ አሉ፡፡

አባ ዝክሪ ሲመልስ ሦስቱን አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን አንድ አምላክ የምንላቸው አብን ልብ ወልድን ቃል መንፈስ ቅዱስን እስትንፋስ ብለን በአብ ልብነት ያስባሉ ያውቃሉ፤ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንስነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ ለየራሳቸው ልብ ቃል እስትንፋስ የላቸውም በማለት ነው፡፡ ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ ያለው አንድ ሰው በልቡ አስቦት አውቆት ለመናገር ጊዜው ባለመድረሱ ሰዓት እየጠበቀለት ሰውሮ የያዘውን ነገር ጊዜው ባለመድረሱ ምክንያት በቃሉ ሳይናገረው ቢቆይ ቢጠየቅም ዛሬ አልናገረውም ቢል አያውቅም እንደማይባል ወልድም ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የምትገለጽበት ጊዜው እስኪደርስ በልቤ በአብ ሰውሬ አቆያታለሁ እንጅ ዛሬ በቃልነቴ አውጥቼ አልናገራትም ማለቱ ነው እንጅ የማያውቃት ሆኖ አይደለም፡፡ እንዲህስ ባይሆን የከዊን ስማቸውና ግብራቸው ተፋልሶ አብ ቃል፤ ወልድ ልብ በተባሉ ነበረ አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ሮማውያን መልስ አጥተው ዝም አሉ፡፡
ኹለተኛ ጥያቄ
ይቀጥላል…. ይቆየን!!!

Friday, February 10, 2017

ጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ ሊቃውንት እንደተረጎሙት

© መልካሙ በየነ
የካቲት 03/ 2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
በመጀመሪያ ( facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ ከዚያ ጽሑፉን ያንብቡ ቀጥለውም ጽሑፉን SHARE, COMMENT, LIKE ያድርጉ፡-
==============================================
ነአምን በ፩ዱ አምላክ፡፡
በባሕርይ በሕልውና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ አምላክ በሚሆን፡፡
እግዚአብሔር አብ፡፡
በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፡፡
አኃዜ ኲሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር፡፡
ሁሉን የሚገዛ፡፡ አንድም ሁሉን የፈጠረ እግዚኦ አኃዜ ኲሉ ዓለም እንዲል፡፡ አንድም ሁሉን እንደ ጥና እንደ እንቁላል በመሐል እጁ የያዘ፡፡ ሰማይን ምድርን የፈጠረ ሰማየ ሰማያት ለእግዚአብሔር ብሎ ምድረሰ በሀበ ለእጓለ እመሕያው ካለው ሲለይ፡፡ አንድም ኢትፍርህዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ ካለው ሲለይ አንድም መላእክትን ደቂቀ አዳምን የፈጠረ 

ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ፡፡
የሚታየውን ግዙፋኑን የማይታየውን ረቂቁን የፈጠረ፡፡ ዘያስተርኢ ሐተታ፡፡ የሚታየው ግዙፋኑ ወዘኢያስተርኢ የማይታዩት ረቂቃኑ በርኅቀት በርቀት፡፡ በርኅቀት አድማስ ናጌብ ብሄሞት ሌዋታን በርቀት ነፍሳት ነፋሳት መላእክት ናቸው አንድም ዘያስተርኢ በዘፈቀደ የሚገለጥ ወዘኢያስተርኢ፡፡ በባሕርዩ የማይገለጥ አንድም ለበቁት የሚገለጥ ላልበቁት የማይገለጥ፡፡ አንድም ዘይርኢ ወዘኢያስተርኢ ይላል ፡፡ የሚጠብቅ ሲጠብቅ የማይታይ፡፡
ወነአምን በ፩ዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ
በተለየ አካሉ አንድ በሚሆን አንድም በባሕርይ በሕልውና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ በሚሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡
ወልደ አብ ዋሕድ፡፡
ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው የአብ የባሕርይ ልጁ በሚሆን፡፡
ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም፡፡
ዓለም ሳይፈጠር በሱ ሕልውና፡፡ አንድም ከሱ ጋራ እንደሱ በነበረ፡፡
ብርሃን ዘእምብርሃን፡፡
ከብርሃን ከአብ በተገኘ በብርሃን በወልድ፡፡
አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን፡፡
ከባሕርይ አምላክ ከአብ በተገኘ በባሕርይ አምላክ በወልድ፡፡
ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ፡፡
በተወለደ ወአኮ ዘተገብረ ባልተፈጠረ፡፡ ሐተታ አርዮስ ሸክላ ሠሪ መሥሪያውን ሠርታ እንድትሠራ ደበናንሳ መዶሻውን ሠርቶ ዘመደ ሐፃውንትን እንዲሠራ ፈጥሮ ፈጠረበት ይላልና ወአኮ ዘተገብረ አለ፡፡
ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፡፡
በሥልጣን በጌትነት በባሕርይ ከአባቱ ጋራ አንድ በሚሆን፡፡
ዘቦቱ ኲሉ ኮነ፡፡
ሁሉ በእርሱ ቃልነት በእሱ ህልውና የተፈጠረ
ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ፡፡
ያለሱ ቃልነት ያለሱ ህልውና የተፈጠረ የሌለ፡፡
ወኢምንትኒ፡፡
ምንም የተፈጠረ የሌለ፡፡ ሐተታ አርዮስ ፈጥሮ ፈጠረበት ይላልና ወኢምንትኒ አለበት፡፡
ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ፡፡
በሰማይ ያሉ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት መላእክት በምድር ያሉ ዕፀው አዕባን እንስሳት አራዊት ሰውም ቢሆን ያለሱ የተፈጠረ ምንም የሌለ፡፡
ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ
ዘበእንቲአነና ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት ፩ድ ወገን ስለእኛ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፡፡
ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ፡፡
ወተሰብአ እመንፈስ ቅዱስ ይላል አብነት እም፡ በ፡ ነው በግብረ መንፈስ ቅዱስ፡፡ ሐተታ የከፈለ ያነፃ ያዋሐደ መንፈስ ቅዱስ ነውና ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፡፡ እም እና እም አንድ ወገን ነው እመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው የሆነ፡፡ አንድም መንፈስ ቅዱስ ከመክፈሉ የተነሣ እመቤታችን ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ ከማለቷ የተነሣ ሰው የሆነ፡፡
ኮነ ብእሴ፡፡
የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆነ፡፡ ወአመ ኮንኩ ብእሴ አውሰብኩ ብእሲተ ከመ ኲሉ ሰብእ እንዲል፡፡
ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ፡፡
የጳንጦስ ሰው ጲላጦስ ነግሦበት በነበረ ወራት ስለእኛ የተሰቀለ፡፡ ሐተታ፡፡ እንደ ሰማዕታት ዕሤት ሽቶ እንደ ሌባ እንደ ወምበዴ ስቶ አይደለምና በእንቲአነ አለ፡፡
ሐመ ወሞተ፡፡
ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ሞተ፡፡
ወተቀብረ
ተቀበረ፡፡
ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት፡፡
ንጹሐት ክቡራት በሚሆኑ መጻሕፍት እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ተነሣ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ እሁብ እኩያነ ህየንተ ሞቱ ወአብዕልተ ህየንተ መቅበርቱ ወልድየ ዕርግ እምህዝዓትከ ተብሎ እንደተጻፈ አንድም በከመ ጽሑፍ ዓርገ ይላል፡፡
ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት፡፡
በብርሃን በቅዳሴ በክብር በሥልጣን ዐረገ፡፡
ወነበረ በየማነ አቡሁ፡፡
ባባቱ ዕሪና ኖረ፡፡ ሐተታ፡፡ ንጉሥ የተጣላውን ሰናፊል አትታጠቅ በትር አታንሣ እንዲህ ካለ ቦታ አትውጣ ብሎ ቦታ እንዲወስንበት ቦታ ወሰነበት ማለት አይደለም፡፡ በምልዓት ሲል ነው እስመ ብሂለ የማን ይመርኅ ኀበ ተዋሕዶቶሙ በክብር እንዲል ነበረ የእንግድነት የማን የባለቤትነት ነው፡፡ አንድም ነበረ የባለቤትነት ነው፡፡ እንግዳን ንበር ይሉታል እንጅ ነበረ ይሉታልን፡፡
ዳግመ ይመጽእ በስብሐት፡፡
ዳግመኛ በብርሃን በሥልጣን በቅዳሴ ይመጣል፡፡
ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ፡፡
በሕያዋን በሙታን ይፈርድ ዘንድ አንድም ሕያዋንን ሙታንን ይገዛ ዘንድ ፡፡ ሐተታ ሕያዋን ያላቸው ጻድቃን ናቸው በነፍስ ሕያዋን ናቸውና አንድም በነፍስ ሕያዋን የሚሆኑበትን ሥራ ይሠራሉና አንድም የሕያው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናቸውና ሙታን ያላቸው ኃጥአን ናቸው በነፍስ ሙታን ናቸውና አንድም በነፍስ ሙታን የሚሆኑበትን ሥራ ይሠራሉና አንድም የምውት የዲያብሎስ ማደሪያ ናቸውና አንድም ኃጥአንን ሕያዋን አላቸው ጸላእትየሰ ሕያዋን ወይኄይሉኒ እንዲል በዚህ ዓለም ሕያዋን ናቸውና ጻድቃንን ሙታን አላቸው ምውት አነ በኀበ ዓለም ወዓለምኒ ምውት በኀቤየ እንዲል የሹትን አያገኙትምና አንድም ኃጥአንን ሕያዋን ሙታን አላቸው ሕያዋን እስከዕለተ ምጽአት ሙታን ከዕለተ ምጽአት በኋላ አንድም ሕያዋን አላቸው በዚህ ዓለም ሙታን አላቸው በወዲያው ዓለም አንድም ሕያዋን አላቸው በሥጋ ሙታን አላቸው በነፍስ አንድም ጻድቃንን ሕያዋን ሙታን አላቸው ሙታን አላቸው እስከዕለተ ምጽአት ሕያዋን አላቸው ከዕለተ ምጽአት በኋላ አንድም ሙታን አላቸው በሥጋ ሕያዋን አላቸው በነፍስ አንድም ሙታን አላቸው በዚህ ዓለም ሕያዋን አላቸው በወዲያው ዓለም፡፡
ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ፡፡
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም ሐተታ፡፡ ዳዊት ሰሎሞን ቢገዙ ዐርባ ፤ ዐርባ ዘመን ነው ያውም እስከ ዳን እስከ ቤርሳቤህ ነው የሱ ግን ፍጻሜ የለውምና፡፡
ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ፡፡
የባሕርይ ገዢ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፡፡
ዘሠረፀ እምአብ፡፡
ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የሠረፀ፡፡
ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ፡፡
ከአብ ከወልድ ጋራ እንስገድለት እንደ አብ እንደ ወልድ እናመስግነው፡፡
ዘነበበ በነቢያት፡፡
ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት ብለህ ግጠም ከአብ ከወልድ ጋራ በነቢያት አድሮ የተናገረ ንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ከአብ ከወልድ ጋራ እናመስግነው፡፡
ታሪክ ከጉባዔ ኒቅያ እስከ ጉባዔ ቍስጥንጥንያ ሃምሳ አምስት ዓመት ነው በዚህ ጊዜ መቅዶንዮስ ለአብ መንበር እንዳለው እግዚአብሔርሰ ይነብር ዲበ መንበሩ ቅዱስ ተብሎ ተነግሯል ለወልድ መንበር እንዳለው መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም ተብሎ ተነግሯል ለመንፈስ ቅዱስ ግን መንበር እንዳለው የተነገረበት ቦታ የለምና ሕፁፅ ነው ብሎ ተነሣ ንጉሡ ዘየዓቢ ቴዎዶስዮስ ነው በቍስጥንጥንያ ጉባዔ ይሁን ብሎ አዋጅ ነገረ በዚህ ምክንያት መቶ ሃምሳ ሊቃውንት ተሰብስበዋል አፈ ጉባዔው ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት ነው ኢይቤ ሠናየ ይቤ አብ ኢይቤ ሠናየ ይቤ ወልድ አላ ይቤ፤ ይቤ ሰናየ መንፈስ ቅዱስ በአፈ ሲሳይያስ ነቢይ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ነዋኅ ወብሩህ ያለውን ይህን ባለመንበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ተርጉሞብሃል ብሎ ረትቶበታል በዚህ ጊዜ እሱን ተከራክረው ረትተው አውግዘው ለይተው ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ብለው ጨምረውበታል፡፡
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኲሉ ጉባዔ ዘሐዋርያት፡፡
ሐዋርያት ባነጽዋት ከምኲራበ አረሚ ከምኲራበ አይሁድ በላይ በምትሆን ክብርት ንጽሕት ጽንዕት ልዩ በምትሆን ባንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን ሐተታ አሐቲ አለ በወርቅ በብር በጭቃ በጨፈቃ ቢሠራ በግብጽ በእስክንድርያ በጻድቃን በሰማዕታት በእመቤታችን ስም ቢሠራ አንድ ነውና በወርቅ በብር የተሠራ ቤተክርስቲያን ሥጋውን ደሙን ይለውጣል በጭቃ በጨፈቃ የተሠራ ቤተክርስቲያን ሥጋውን ደሙን አይለውጥም አያከብርም ብለዋልና አሐቲ አለ አንድም ሐዋርያት ያስተማሯት ያሳመኗት ያጠመቋት ከምዕመናነ አሕዛብ በላይ የምትሆን ክብርት ንጽሕት በምትሆን ባንዲት ምዕመን እናምናለን፡፡ ሐተታ አሐቲ አላቸው ምዕመናንን አንድ እምነት ያምናሉ አንድ ጥምቀትይጠመቃሉ አንድ ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉና አንድም ምዕመንን በሚያስተምሩ ባንድ መምህራን እናምናለን፡፡ ሐተታ መምህራንን አሐቲ አላቸው አንድ እምነት ያሳምናሉ አንድ ትምህርት ያስተምራሉ፡፡ አንድ ሥጋውን ደሙን ያቀብላሉና፡፡ አንድም በቤተክርስቲያን ምዕመናንን በሚያስተምሩ ባንድ በመምህራን እናምናለን፡፡ ሐተታ ሲያስተምሩ ሲያሳምኑ ሲያጠምቁ በቤተክርስቲያን ነውና ቅድስትን እንደ ሃይማኖተ አበው አትት፡፡
ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት፡፡
ኃጢአት በሚሠረይባት ባንዲት ጥምቀት እናምናል፡፡ ሐተታ በአብ ስም በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ ስም ቢጠመቁ አንድ ነውና በዐርባ ቀን በሰማንያ ቀን በዐርባ ዘመን በሰማንያ ዘመን ቢጠመቁ አንድ ነውና፡፡ እንድም በሊቀ ጳጳስ በጳጳስ በኤጲስ ቆጶስ በቄስ እጅ ቢጠመቁ አንድ ነውና አንድም በዐቢይ ባሕር በማዕከላዊ ባሕር በንዑስ ባሕር ቢጠመቁ አንድ ነውና ፡፡
ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን፡፡
ከፈረሱ ከበሰበሱ በኋላ አካል አግኝተው ታድሰው ሙታን እንዲነሡም እናምናለን አንድም አንዘ ንሴፎ ይላል ሙታን እንዲነሡ አምነን ባንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡ ሐተታ ማጥመቅ ትንሣኤ ሙታን ካሳመኑ በኋላ ነውና ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም፡፡
ሐይው ከመ መላእክት እንዳለ እናምናለን፡፡