Friday, June 30, 2017

ዐይናማው ርእሰ ሊቃውንት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ዘደብረ ድማኅ


© መልካሙ በየነ
ሰኔ 23/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
  • በተከታታይ ሦስት ክፍሎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን ፓትርያርኮችን ታሪክ ሳስነብባችሁ መቆየቴ ይታወቃል፡፡ ዐራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ አምስተኛው አቡነ ጳውሎስ ስድስተኛው አቡነ ማትያስ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዐራተኛው እና በአምስተኛው መካከል መከፋፈል ስለመጣ አቡነ መርቆሬዎስ ሳይሞቱ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ፡፡ ይህም ስደተኛው እና የሐገር ውስጥ ሲኖዶስ መባባልንና መከፋፈልን አምጥቷል፡፡ በዚህም የተነሣ ታሪኩ ያን ያህል አስተማሪ እና ገንቢ ባለመሆኑ ወደ ሌሎች ሊቃውንት መሻገርን መርጫለሁ፡፡

  • የዛሬው ጽሑፍ ረዘም ያለ ስለሆነ በትእግስት እንድታነቡት እጋብዛለሁ፡፡
  • ከዚያ በኋላ ውይይት የሚያስፈልገውም ጉዳይ ስለሆነ አስተያየት መስጫው ላይ ሃሳባችሁን አካፍሉን፡፡ 
  •  የቅዱሱ ሊቅ ዐጽም አደጋ ላይ ነው፡፡


Wednesday, June 28, 2017

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ



© መልካሙ በየነ

ሰኔ 22/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጵጵስናቸው በፊት መጠሪያ ስማቸው አባ መልአኩ ሲሆን የተወለዱት መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም የንጉስ  ወልደ  ጊዮርጊስ  ታማኝ ወታደር ከነበሩት አባታቸው ከወታደር ወልደ ሚካኤል አዳሙ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘውዲቱ ካሳ  በጎንደር  ጠቅላይ  ግዛት  ማኅደረ  ማርያም  ተብላ  በምትታወቀው  ገዳም  አካባቢ  ጋዥን  በምትባል  ቦታ  ነው ።  




ገና በህጻንነት ጊዜያቸው አራስ በነበሩበት ጊዜ ነበር ወታደር አባታቸው በህመም ምክንያት በሞት የተለዩት፡፡በዚህም የተነሳ እናታቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ ልጃቸው አባ መላኩ ትንሽ ጠንከር ሲሉ 
ይዘዋቸው  ወደ  ጎጃም ተመለሱ እና አባ መልአኩ እዚያው ጎጃም ውስጥ የረዝ ሚካኤል በሚባል አካባቢ ማደግ ጀመሩ። ነገር ግን ብዙም የመጀመሪያ ትምህርታቸውን እንደጀመሩ እናታቸውምበሞት ከዚህ አለም ስለተለዩባቸው የአባታቸው ዘመዶች ወደሚገኙበት ቦታ ወደ ጎንደር ተመለሱ።ዘመዶቻቸውም እዚያው አካባቢ ተዋቂ መምህር ለነበሩት መሪ ጌታ ወርቅነህ ሠጧቸው። በዚያም ፊደል ከቆጠሩ በኋላ ወደ ደብረ ታቦር ተሻግረው እናቲቱ ማርያም በተባለችው ደብር ያስተምሩ ከነበሩት አለቃ ቀለመወርቅ ዘንድ ሔደው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። ከዚህም በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በወቅቱ የኢትዮጵያ ጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መዓረገ ዲቁናን ተቀበሉ። ከዚያም ወደ ማኅደረ ማርያም ተመልሰው በዲቁና ሲያገለግሉ ቆዩ።

አባ መልአኩ ህይወታቸውን በቤተ ክርስቲያን ትምህርት አጎልምሰው በትኅርምትና እግዚአብሔርንበህይወታቸው ሙሉ በማገልገል ሊኖሩ በመወሰን ከጓደኞቻቸው ጋር ቅኔ ለመማር ወደ ጎጃም ይሄዳሉ። በዚያም በእናታቸው ሃገር አጠገብ ወደሚገኘውና የረዝ ሚካኤል ወደ ተባለው ቦታ መምህርልሳነ ወርቅ ከተባሉ መምህር ዘንድ ቅኔንና ዜማን ለስምንት ዓመታት ያህል ተማሩ። 

ባሕታዊ አባ መላኩ በወላይታ እየተዘዋወሩ በሚያስተምሩመት ወቅት

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ



 © መልካሙ በየነ
ሰኔ 21/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ
አቡነ ቴዌፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ጎጃም በሚገኝው በዝነኛው ደብረ ኤልያስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ማርያም ውቤ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘርትሁን አደላሁ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፪ ዓ/ም ተወለዱ። ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም መልእክቱ ወልደ ማርያም ነበር።
በልጅነታቸው ንባብ እና ዜማን በመምህር መሪ ጌታ ረዳኸኝ እና ግራ ጌታ ሣህሉ እዚያው የተወለዱበት አካባቢ ተምረዋል። ኋላ የቅኔ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዝንባሌ ስላደረባቸው እዚያው ደብረ ኤሊያስ ደብር መምህር ገብረ ሥላሴ በሚባሉ ሊቅ ሥር መማር ጀመሩ።
፲፱፻፻፳ ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ፍትሐ ነገሥትአዲስ ኪዳንን በመምህር ተክሌ (ንቡረ ዕድ በኋላ ቢትወደድ አቡነ ዮሐንስ) በመባል የሚታወቁት መሪነት ሲከታተሉ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የሃይማኖት ችግሮችን ለማወቅ ይፈልጉ እንደነበርና ሰፋ ያለ ዕውቀት እንደነበራቸው ይነገራል።

Monday, June 26, 2017

ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ


© መልካሙ በየነ
ሰኔ 20/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


አባ ገብረ ጊዮርጊስ (አቡነ ባስልዮስ) የኢየሩሳሌም ገዳማት አስተዳዳሪ (፲፱፻፳፭ ዓ/ም)
ቀዳማዊ አቡነ ባስልዮስ (፲፰፻፹፬ዓ/ም (ሚዳ ሚካኤል) - ፲፱፻፷፫ ዓ/ም (አዲስ አበባ)) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበሩ።
አቡነ ባስልዮስ ሲወለዱ የተሰጣቸው ስም ገብረ ጊዮርጊስ ሲሆን መጋቢት ፲፬ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ/ም ከደብተራ ወልደጻድቅ ሰሎሞንና ከወይዘሮ (በኋላ እማሆይ) ወለተማርያም ባዩ በሸዋ አውራጃ ሚዳ ሚካኤል ተወለዱ። ደብተራ ወልደጻድቅ የይፋት ቀውትጌስ ማርያም ተወላጅ ሲሆኑ፣ እማሆይ ወለተማርያም ደግሞ በመንዝ ላሎ ምድር የተወለዱ ነበር።
በሕጻንነታቸው ዘመን መንፈሳዊ ትምህርትን እየተማሩና የኮሶ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን እያገለገሉ አድገዋል። አቡነ ባስልዮስ የዐሥራ ዐራት ዓመት ታዳጊ ወጣት እያሉ በ፲፰፻፺፱ ዓ/ም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ትምህርታቸውን ከመምህር ገብረ ኢየሱስ ሲከታተሉ ቆይተው በዚያው ገዳም መዓርገ-ምንኩስናቸውን እስከተቀበሉበት ድረስ ለሦስት ዓመታት በእርድና አገልግለዋል።

Thursday, June 22, 2017

አለቃ አያሌው ታምሩ



© መልካሙ በየነ

ሰኔ 15/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


ስለጃርቶች ብቻ እያወራን ስለ በቆሎው ማውራትን ዘነጋን፡፡ እስኪ ተስፋን የሚያለመልሙ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እንዘክራቸው፡፡ ባለቤት አልባ ለሆነችው ቤተክርስቲያናችን ባለቤትነታቸውን ያሳዩትን ቆራጥ የተዋሕዶ ልጆችን እናወድሳቸው ስማቸውንም እንጥራው፡፡ ማን ያውቃል እነርሱን የሚተካ በአባቶች ፈንታ የተወለደ ልጅ ቢኖርስ አምላከ ቅዱሳን  ለቤተክርስቲያናችን ብሎ ያስነሣው አርበኛ ቢኖርስ፡፡ ስለጃርቶች ስለአስመሳዮች ስናወራ ሆነው ያሉትን አርበኞችም መዘንጋት የለብንምና ከዛሬ ጀምሮ ከድረገጽ ካገኘሁት መረጃ በጥቂቱ አካፍላችኋለሁ፡፡ ይህን ጽሑፍ በጥቂት በጥቂቱ እያደረግሁ አለቃ አያሌው ለተጠየቁት አጠቃላይ የቤተክርስቲያናችን ሁኔታ የሰጡትን መልስ በቪዲዮ እያያያዝኩ እለጥፋለሁ፡፡
አለቃ አያሌው ታምሩ ዘዲማ!!!
መልካም ንባብ!
ለተጠየቁት በርካታ ጥያቄ የመለሱትን መልስ ከዚህ ሊንክ ላይ ተጭነው መከታተል ይችላሉ፡፡
===============================================================

Monday, June 19, 2017

“የመቅደሱ ቦክሰኛ----ማብራሪያ ለምትሹ”


© መልካሙ በየነ
ሰኔ 12/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
መረጃዎች ለማግኘት (facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ፡፡
===================================================
**************************************************************************************
የሰማ ላልሰማው ያሰማ ይህ የመጨረሻየ ነው የመጨረሻ ብያለሁ!
“ትግላችን ስለቤተክርስቲያናችን ስለ ሃይማኖታችን ነው”
“በሃይማኖታችን በቤተክርስቲያናችን ለመጣ ጠላት ደግሞ ነፍሳችንንም አንሰስትም”
***************************************************************************************
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በአቡነ ማርቆስ ምክንያት በተፈጠሩ ችግሮች ዙሪያ መረጃዎችን ሳደርስ በውስጥ መስመርም፣ በስልክም፣ አስተያየት ላይ በመጻፍም እየተሯሯጡ የሚገኙ በርካታ “ፍቅረ ማርቆስ” የነደፋቸው ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለምን ስልክ ደወሉ፣ ለምን በውስጥ መስመር ለማስፈራራት ሞከሩ፣ ለምን አስተያየት ሰጡ የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ ነገርግን ሁሉ ነገራቸው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ከዚያም የተረፈው ስድብ እና ሃሜት የተጠናወተው ዓይነት ጽሑፍ ስለሆነ ከዓላማችን ጋር አብረው የማይጓዙ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ በውስጥ መስመር በጣም ጎበዝ የተዋሕዶ ልጆች ይህ እኮ እገሌ ነው ይሉኛል፡፡ በዚህም መሠረት ፕሮፋይላቸውን በማጣራት ደረጃ ብቁ እና ተገቢ የሆነ መረጃ አግኝቻለሁ፡፡
==============================================================

Friday, June 16, 2017

እንደ ሳሙኤል እውነትን ግለጥ!



 © መልካሙ በየነ
ሰኔ 09/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


ቤተክርስቲያናችን  በፈተናዎች መካከል ያለፈች እንደሆነች ያልተረዱ ሰዎች አሁንም ድረስ በቪዲዮም በኦዲዮም በምስልም ማስረጃዎችን እየተመለከቱ ማመን ተስኗቸዋል፡፡ ምናልባትም እነዚህ ሰዎች፡-
   1ኛ. በቀደሙት አባቶቻችን እይታ ስለሚመለከቱ ነው፡፡ የቀደሙት አባቶቻችን ንጽሕ ጠብቀው በጾም በጸሎት ተወስነው በትህትና የኖሩ የእግዚአብሔርን እንጅ የሰውን ፍላጎት ለመጠበቅ ያላጎበደዱ ናቸው፡፡ አሁን የምንመለከተው ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ልብ በሉ አሁንም ቢሆን ግነ በቀደሙት አባቶቻችን መንገድ የሚጓዙ አባቶች አሉን፡፡ እነዚህን አባቶቻችንን አይጨምርም አሁን የምላችሁ ጉዳይ፡፡ ቀሚሳቸው፣ ቆባቸው ሲታይ ከድሮ አባቶቻችን ጋራ ተመሳሳይ ነው የለበሱት ሰዎች ግን ለየቅል ናቸው፡፡ ስለዚህ ዲያቆን ስለሆነ፣ ቄስ ስለሆነ፣ ጳጳስ ስለሆነ ወዘተ እንዲህ አይደረግም በውሸት ነው ስም ለማጥፋት ነው ወዘተ ወዘተ የሚለው አነጋገር ምናልባትም እያዩ እንዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

Thursday, June 15, 2017

“ካራ ተዋሕዶ ቅባት ጸጋ ብለው መርዝ ረጭተው ሄዱ”---ብጹእነታቸው



© መልካሙ በየነ

ሰኔ 08/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

አባታችን አቡነ ማርቆስ በሀገረ ስብከቱ እየተሠራ ላለው አዲሱ ህንጻ በየወረዳው እየዞሩ ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ በነበሩበት ወቅት እግር መንገዳቸውን አንዳንድ ጉዳዮችን እንደ ቋሚ አጀንዳ ይዘው የራሳቸውን መልእክት ሲያስተላልፉ ነበር የከረሙት፡፡ በአምበር ከተማም ተገኝተው እንደተለመደው የግል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ከአንድ የመርኃ ግብር ተከታታይ በወረቀት ጥያቄ ተላከላቸው ለዚያም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ በጣም በሚያሳፍር መልኩ እንደነበር ይህን ቪዲዮ ስሙት፡፡
“በ28 በ29 ማለት ሃይማኖት ቀን መቁጠር ይሆናል ወይ፡፡ ሃይማኖት ወልደ አብ ወልደ ማርያም ተወለደ ማለት ነው” ብለው ይጀምራሉ፡፡ የልጁ ጥያቄ ስለ ቅብአት እና ስለተዋሕዶ ልዩነት የጠየቃቸው ይመስላል፡፡ በእውነት ከአንድ ሊቀጳጳስ የገና በዓል በ28 በ29 እያሉ ቀን መቁጠር ሃይማኖት ይሆናልን ሲል መስማት ያሳዝናል፡፡ ቀን መቁጠርን የምታስተምር በባሕረ ሃሳብ ጥበብ የመጠቀች ቤተክርስቲያናችን ይህን ተብላ ስትሰደብ መስማት እጅግ ያስለቅሳል፡፡ በእውነት ቀን መቁጠር የሃይማታችን መገለጫ ካልሆነ “ዓርብ እና ረቡዕ” መጾማችንን ትተን ለምን “ሰኞ እና ማክሰኞ” አንቀይረውም ነበር፡፡ የዐቢይ ጾም መግቢያ መውጫ በባሕረ ሐሳብ በወጣለት የቀን አቆጣጠር ካልተከበረ ሥርዓት አላፈረስንም ወይ፡፡ የገና በዓልስ ቢሆን በ28 በሚከበርበት በ28 በ29 በሚከበርባቸው ዓመታትም በ29 ማክበር እንዳለብን የተቀመጠ ሥርዓት አይደለም ወይ፡፡ ያውስ ቢሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ ነው ብሎ ሳይወስን አንድ ሊቀ ጳጳስ ብቻውን ሥርዓት ሊሠራ ይቻለዋል ወይ፡፡


“በካዱት እግዚአብሔር ለንስሐ የተረፉ ነፍሳት”


© መልካሙ በየነ
ሰኔ 07/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

ሰኔ 04/2009 ዓ.ም የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የከተሞችን መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ የከተሞች መድረክ ላይ ስለመብራት መቆራረጥ ስለ ውኃ እጥረት ስለ ቆሻሻ አወጋገድ ስለ ስልክ ጥራት ስለመኖሪያ ቤት ችግር ወዘተ ወዘተ ሁሉም እየተነሣ የራሱን ጥያቄ አቀረበ፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር አንዲት ጥብእት ቆራጥ የተዋሕዶ አርበኛ እህታችን በሀገረ ስብከቱ ስለተፈጠረው ችግር ያነሣችው፡፡ ወ/ሮ ውባለም “አባታችን ከዚህ

Monday, June 12, 2017

“ጩኸታችንን በአደባባይ የጮኹልን የተዋሕዶ ልጆች”


© መልካሙ በየነ
ሰኔ 05/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

ትናንትና ሰኔ 04/2009 ዓ.ም የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት የከተሞች መድረክን በምሥራቅ ጎጃም መዲና በደብረ ማርቆስ ከተማ አድርጓል፡፡ የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ በከተማ አስተዳድሩ ውስጥ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከህብረተሰቡ በመሰብሰብ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት እዛው መልስ እንዲሰጡበት ማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ጉዳዮች የተነሡ ሲሆን በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የተፈጠረው ከፍተኛ ችግርም አንገብጋቢ መሆኑ ከህብረተሰቡ ተነሥቷል፡፡ 
https://youtu.be/GcbXQQa9sqs

“ቀድሞ መምህር ነበርሁ” አሉ ወ/ሮ ፈንታ “አሁን ግን በጥሮታ ከሥራየ ተሰናብቻለሁ፡፡ እኔ የማነሣው ጉዳይ እስካሁን ከተነሣው ችግር ሁሉ የተለየ ነው” አሉ፡፡ “ስለመብራት ችግር አነሣን መልካም፤ ስለ ውኃ ችግር አነሣን መልካም፤ ስለመኖሪያ ቤት ችግር አነሣን መልካም፤ ስለቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓታችን ችግር አነሣን መልካም ይህ ሁሉ መነሣቱ ጥሩ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ችግር ተፈታ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ሃይማኖታችንን እንዴት እናድርጋት፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ተማሪዎች መንፈሳዊ ትምህርትን የሚማሩበት ግቢ ጉባዔ ተዘግቶባቸዋል፡፡ ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ወረዳ አጥቢያዎች ድረስ በሙሉ የተሰገሰጉ የሊቀ ጳጳሱ የእህት ልጅ የወንድም ልጅ የአጎት ልጅ የአክስት ልጅ የአገር ልጅ ናቸው፡፡ ታዲያ ለማን አቤት እንበል፡፡ በሃይማኖታችን ዙሪያ ችግር አለብን ብለን እንዳናማክር ሁሉም የስጋ ዘመዶቻቸው ናቸው፡፡ የንስሐ አባት እንኳ እስካሁን የለንም ማንን እንያዝ? መድረክ ላይ ወጥተውም ጎጃም ሌባ የማርቆስ ህዝብ ሌባ ነው እያሉ ከመሳደብ ውጭ ይህን አታድርጉ ከዚህ ተቆጠቡ ብለው አላስተማሩንም፡፡ ቤተክርስቲያን የህዝብ ናት የምትመራበት ቃለዓዋዲም አላት በዚህም መሠረት ሕዝበ ክርስቲየኑ የሰበካ ጉባዔ ይመርጣል ነገር ግን በምን ምክንያት እንደሆነ ሳይታወቅ አባታችን ሰበካ ጉባኤውን አፍርሰው በዘመዶቻቸው ይተካሉ፡፡ ታዲያ የት ሄደን እንጸልይ፡፡ ለምን ብለን ስንጠይቅ ከነፍስ ልጅነት አባርርሻለሁ እንባላለን፡፡ አሁን እንዲያውም አባታችን አይነሡብን እያላችሁ አስፈርሙ ብለው እያስፈራሩ እንዲፈረም እያደረጉ ነው፡፡ ልጆቻችን ወደ አልባሌ ቦታ እንዲሄዱ እያደረጉብን ነው፡፡ ዛሬ ይህን የምናገረው ህዝቡ አገሩ ይወቀው ብየ ነው እንጅ ጉዳዩን ከወረዳ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ አሳውቀናል፡፡ በከተማችን ሽብር እየፈጠሩ ነው፡፡ ተነሡ እያሉ ህዝቡን እያነሣሡ ነው፡፡ ስለዚህ አንፈልጋቸውም ይነሡልን አንፈልጋቸውም” አሉ፡፡ በዚህ ንግግራቸው ሁሉም የአዳራሹ ህዝብ በጭብጨባ ነው ደስታውን የገለጸው፡፡ የአባታችን የአቡነ ማርቆስ ጉዳይ በዚህ መልኩ በቀጥታ ስርጭት ሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ሁሉ ተከታትለውታል፡፡ ይህ ችግር የቤተክርስቲያናችን ችግር ብቻ ሳይሆን የከተማውም ችግር ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን በዚህ መልኩ ከተረበሸች ይህ ያጨበጨበው ህዝበ ክርስቲያን ሁሉ ብጹእነታቸውን ከተቃወመ ከፍተኛ ብጥብጥ መፈጠሩ ለማንም የተገለጠ ነው፡፡ ለዚህም ነው የዞኑ ጸጥታ ዘርፍ አስተዳድር ህዝቡ የሚያነሣውን ቅሬታ በአስቸኳይ ፍቱ ብሎ ለብጹእነታቸው በደብዳቤ የገለጠው፡፡

መጋቤ አእላፍ ጥበቡ ዕድሉን አገኙ የድምጽ ማጉያው ተሰጣቸው፡፡ “ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ላይ የተነሣው ጉዳይ ትክክል ነው ተዘግቶባቸዋል፡፡ እንደሃይማኖት አባትነት ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሠጠ ቃል ትወደኛለህ በጎቼን ጠብቅ ግልገሎቼን ጠብቅ ጠቦቶቼን ጠብቅ የሚል ነው፡፡ አይጦች ነው የምንባለው አብሮ አደግ ጋኔን ይዞታል ነው የምንባለው፡፡ ይህን የሚሉን ግን ለዘመዶቻቸው ቦታ ለማመቻቸት ሲፈልጉ ነው፡፡ ከሃገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ የሁለት ወረዳዎች አጠቃላይ የቤተሰብ እና አብሮ አደግነት ነው የተከማቸው፡፡ በእውቀታቸው አይደለም የተመደቡት የእህት የወንድም የአጎት የአክስት ልጅ ነው፡፡” አሉ፡፡ መድረክ መሪው ከወ/ሮ ፈንታ ጋር ተመሣሣይ ስለሆነ ለሌላ እድል እንስጥበት አላቸው፡፡ እርሳቸው ግን ውስጣቸውን መግለጥ ስለፈለጉ “በማይመሳሰል መልኩ አቀርበዋለሁ” አሉ፡፡ ከዚያም ቀጠሉ “ሚሥጢረ ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ የሚል መጽሐፍ በዚህ ዓመት ታትሟል፡፡ የታተመው ምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ገዳም ነው፡፡ ወልደ አብ የሚባል መጽሐፍም አለ በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል ትምህርት የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህንን ችግር የመገናኛ ብዙሃኑ ይፈተዋል ብየ አይደለም ግን ወዴት እያመራን ነው፡፡ ወደፊት የአገራችን ራእይ ምንድን ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ችግር በቅዱስ ሲኖዶስ የተያዘ ነው፡፡ ሚያዝያ 30/2009 ዓ.ም ያስተማሩት ትምህርት ቅስቀሳ ነበር ጎጃም ተጠመቅ ተብለሃል ተነሣ እያሉ ሲቀሰቀሱ ነበር፡፡ …ጳጳስ ስለሆንኩ እንደፈለግሁ አደርጋለሁ የሚሉ ናቸው፡፡ አባታችን እንዳይነሡብን እያሉ እንዲፈርሙ ተደርጓል፡፡ አብማ ማርያም ላይ በግድ ፈርሙ ተብሏል አንፈርምም ያሉ ካህናት እና ዲያቆናት በስጋት ላይ ናቸው፡፡” በማለት ተናገሩ፡፡ ይህንን በመናገራቸው አሁንም የህዝበ ክርስቲያኑ ደስታ በጭብጨባ ተገልጧል፡፡ በዚህ መልኩ ብጹእ አባታችን ላይ የሚታዩትን ችግሮች ለህዝብ አደረሱ፡፡ እኛ በተለያዩ መንገዶች የጮኽናቸው ጩኸቶች ፍሬ አፍርተው  ወ/ሮ ፈንታ እና መጋቤ አእላፍ ጥበቡ በአደባባይ ለዓለም እንዲገለጥ አድርገዋል፡፡ ይህን በማድረጋቸውም ታሪክ የሚዘክራቸው ምርጥ የሃይማኖታችን አርበኞች ብለናቸዋል፡፡

ይህ ከላይ የተነሣው የሀገረ ስብከቱ ችግር እንዲፈታ መንግሥት ምን ሠርቷል የሚለውን ጥያቄ አቶ አብርሃም እንደ ዞን ጸጥታ ዘርፍ ሆነው መልስ ሰጥተዋል፡፡ “ለሰላም እና ጸጥታ ጠንቅ የሆነ አሠራር ስላለ ይህን አሠራር ከማረም አኳያ ለመመመካከር ጥረት አድርገናል፡፡ ባደረግነው ጥረት ውስጥ ግን ሊሳካልን አልቻለም፡፡ ያልቻለበትም ምክንያት በጣም ሳብ ጎትት የበዛበት ነው፡፡ ወይንም የእኛ አሠራር ባህል ችግሩ አለ የሚባለው *ኤሪያ* ላይ ስለሌለ ነው፡፡ መደማመጥ የለም፤ መግባባት የለም፤ ለመነጋገር ፈቃደኛነት የለም፡፡ ይኼ ባለበት ነባራዊ ሁኔታ እኛ *ኢንተርቬን* አድርገን ልንፈታው የምንችለው ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ስለሆነም የመጨረሻ እንግዲህ የዞናችን ጸጥታ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ  ምክንያት ከዚህ በኋላ ለሚደርሰው ችግር ተጠያቂ አይደለሁም ብሎ *ዲክላር* አድርጎበታል በደብዳቤ፡፡ በርግጥ ይኼ መፍትሔ ነው ወይ ሌላ ነገር ነው፡፡ ስለሆነም እኔ መፍትሔ ብየ የምወስደው የቤተክርስቲያኑ አካላት ጉዳዩን አይተው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ ያስፈልጋል ብየ ነው የማስበው፡፡ እንግዲህ አሁን በዚህ መልእክቱን በማድረስ በኩል ትልቅ ሚና ይኖረዋል የሚል አስተያየት ነው ያለኝ፡፡ ችግሩ ግን ትክክል ነው ከመንግሥት ድርሻ አኳያ ጣልቃ ገብተን እርምጃ የምንወስድበት እድል ስለሌለን ህገ መንግሥቱን አክብረን ግን ደግሞ ቤተክርስቲያኗ በራሷ ምላሽ ትሰጣለች ብለን እየጠበቅን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡” በማለት አቡነ ማርቆስ እየፈጠሩት ያለው ችግር ከዞኑ አቅም በላይ እንደሆነ ገልጧል፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያናችንን ችግር አባቶቻችን እንዲፈቱልን አሁንም ወደፊትም እንጠይቃለን፡፡ ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የሁሉ ትኩረት ሊሆን ያሻዋል!

ከታች ያለውን ቪዲዮ ግን ሁላችሁ ተመልከቱልኝ ዞኑ ከተናገረው ውጭ ያለውን የሁለቱን የተዋሕዶ ልጆች ቃል በቃል ስላልገለበጥኩት በዛ ያለ መልእክት ስላስተላለፉ አዳምጡት፡፡
=====================================
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት #comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡

Wednesday, June 7, 2017

“ትኩረት የሚያሻው ሀገረ ስብከት” ምሥራቅ ጎጃም

© መልካሙ በየነ

ግንቦት 30/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


ምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት የጥንታውያን እና የታሪካውያን አድባራት እና ገዳማት መገኛ  የቅኔ እና የዜማ እንዲሁም የትርጓሜ መጻሕፍት መፍለቂያ ቦታም ጭምር ነው፡፡ ለዓለም ሳይተዋወቁ ዓለም በመላ የሚጎበኛቸው ከዋክብት የሆኑ ገዳማት እና አድባራትም በብዛት  ይገኙበታል፡፡ ሐዲስ ዓለማየሁ ዓለምን ባስደመመበት “ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሐፉ ላይ  የጠቀሳቸው ገዳማት እና አድባራት የሀገረ ስብከታችን ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ተወልደው ያደጉበት  ደብረ ኤልያስ እንዲሁም የቅኔ ሊቃውንት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ እና  አለቃ አያሌው ታምሩ ተወልደው ያደጉበት ዲማ፤ መስዋእተ ኦሪት ከተከናወነባቸው አምስቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ የሆነቸው አብርሃ ወአጽብሐ በወርቅ እና በዕንቍ አስውበው የገነቧት መርጡለ ማርያም (የማርያም አዳራሽ) ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በርካታ ገጸ በረከቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሀገረ ስብከት ይህን ያህል የሊቃውንት መፍለቂያ ቢሆንም የጀግንነት ታሪክ በበላይ ዘለቀ በኩል የተላበሰ አርበኝነት የግሉ የሆነ ህዝብ ያለበት ቢሆንም ይህን ታሪኩን ጥላሸት የሚቀባ፡
 “ዘንድሮ ጎጃም ላይ ቅብአት ረከሰ፤
 ከራሳችን አልፎ መቅደስ ውስጥ ፈሰሰ” የተባለለት የቅብአት እምነት መኖሩ ያሳፍራል፡፡ ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ በጥቂት ቦታዎች በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ  “ተዋሕዶ እና ቅብአት” የሆኑ ካህናት በአንድነት የሚያገለግሉበት ሀገረ ስብከት ነው፡፡ “ብርሃን እና ጨለማ” “እምነት እና ክህደት” “ነጭ እና ጥቁር” “መንፈስ ቅዱስ እና መንፈስ ርኩስ” “እግዚአብሔር እና አጋንንት” “ፍቅር እና ጥል” አዎ እነዚህ ሁሉ በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያገለግላሉ ይገለገላሉ፡፡

እስከ አሁን በነበረው የእነዚህ እምነቶች በአንድ መቆየት የጎላ ልዩነት አይታይም ነበር፡፡ “ተቀባት” እና “ተዋሐዳት” ከሚል የጨዋ ክርክር የዘለለ “ቅብአት” ማለት እንዲህ ነው የሚል ሊቅም አልነበራቸውም፡፡ በእኛ በኩል የነበሩት እነመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ግን “መድሎተ አሚን” በተሰኘው መጽሐፋቸው ለካቶሊካውያን መልስ በሰጡበት ላይ ቅባትን ከዚያ ጋር አያይዘው መልስ ሰጥተውበታል፡፡ በ1990ዎቹ አካባቢ ለፍትህ ሚኒስቴር “ሃይማኖታችን ይታወቅልን” ብለው ጥቂት የቅብአት መናፍቃን በደብዳቤ መጠየቃቸው የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን በወቅቱ  “መሥራቹ ማነው? ምን ያህል ተከታይ አለው?” ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ አልቻሉም ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም “እምነታችሁ ይፈቀድላችኋል በነጻነት ማምለክ ትችላላችሁ ይህ ሕገ መንግሥታዊ መብታችሁ ነው፡፡ ነገር ግን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምንም ነገር ይዛችሁ መሄድ አትችሉም” አሏቸው፡፡ በዚህም የተነሣ ድምጻቸውን አጥፍተው ጥቂት የሚባሉ ገዳማትን እና አድባራትን ውስጥ ለውስጥ ለመቆጣጠር ቻሉ፡፡ በተለይ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ደብረ ማርቆስ ወረዳ ቤተክህነት የሚያስተዳድረው አባ ዐሥራት ገዳም አንዱ ሲሆን በጎንቻ ሲሶ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ያለው ቆጋ ኪዳነ ምህረት በሌላ ጎን ተጠቃሽ ነው፡፡

ቆጋ ኪዳነ ምህረት በዋናነት የቅባት መናፍቃን የመሸጉባት ገዳማችን ናት፡፡ ይህንን ተልእኳቸውን በመፈጸም ላይ ያሉት ገዳማውያን ነን ባዮችም ከሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያው “ወልደ አብ” እና “ሚሥጢረ ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ” የሚሉ መጻሕፍት የታተሙት በዚሁ ገዳም ስም መሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ ኆህተ ሰማይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወ እስጢፋኖስ የተባለ አዲስ ህንጻ ቤተክርስቲያን ጉንደ ወይን ከተማ ውስጥ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም በባረኩበት ወቅት ስለ ጎንቻ ሲናገሩ “በዚህም ቢሄድ ቆጋ ነው በዚያም ቢሄድ ጎንቻ ነው” በማለት ጎንቻ የቅዱሳን መፍለቂያ ነው ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ “እዚህ ቆጋ ጓሮ እንዲህ ያለ ጉድ” በማለትም የቅብአት እምነት አማኞችን ተጠመቁ የሚሉትን ገስጸዋል፡፡ ቆጋን ያህል ቦታ እያለ እንዴት የቅብአት እምነት ተከታዮችን ተጠመቁ ይላሉ እንዲህ የሚሏችሁን ስም ዝርዝራቸውን ስጡን በማለት በግልጽ መናገራቸው ለቅብአት እምነት ያላቸውን ድጋፍ የገለጹበት መሆኑን መረዳት አይከብድም፡፡ ስለዚህ ለቅብአት እምነት እንዲህ በይፋ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ተቀምጠው የክህደት መጽሐፍ እንዲጽፉ ኃይል እና ብርታታቸው የሀገረ ስብከታችን ሊቀጳጳስ ለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ሌላው ምሥራቅ ጎጃም ልዩ ትኩረት የሚያሻው ሐገረ ስብከት ነው የምንለው ቤተክርሰቲያኒቱን በዘመድ አዝማድ ቁጥጥር ስር እንድትወድቅ ማድረጋቸው ነው፡፡ በዚህ ሀገረ ስብከት ለመቀጠር የሚያስፈልጉ መስፈርቶች በዋናነት፡
1.  ለሊቀ ጳጳሱ የሥጋ ዘመድ ሆኖ መገኘት…. ተማረም አልተማረም ተማረችም አልተማረችም፡፡
2.  በጥቅማጥቅም መቆራኘት…..ለምሳሌ ዲማን ታሪክ አልባ ለማድረግ የተጠቀሙት መምህር ላእከ ማርያም በአቡነ ጴጥሮስ ዘመነ ጵጵስና የተወገዘ ሰው መሆኑ፡፡ ይህ ሰው የመምህሩን የመምህር ዘሚካኤል ይሁኔን ሚስት የደፈረ ሰው ሲሆን በዚህም ተጸጽቶ ንስሐ ያልገባ ነው፡፡ ይህን ሰው ዲማ ላይ እንዲመደብ በማድረግ የዲማን ሰላም ነስተውት መክረማቸው የታወቀ ነው፡፡
3.  የሰፈር ልጅ ሆኖ መገኘት……ከቤት አልፎ በጣም ቢበዛ የተማሩበትን ቦታ ልጆች ይሰበስባሉ፡፡ መርጡለ ማርያም የተማሩበት ቦታ ስለሆነ ጎንቻም የተወለዱበት ቦታ ስለሆነ እነዚህ በጣም በቅርበት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ 
4.  ገንዘብ መክፈል…..ዘመድ ካልሆንህ በጥቅማ ጥቅም ካልተቆራኘህ የሰፈር ልጅ ካልሆንህ ያለህ የመጨረሻው አማራጭ ሙስና ነው፡፡
በእነዚህ ዐራት ምክንያቶች በየአጥቢያው አለቃ እና የሰበካ ጉባኤ አባላት እያደረጉ መመደባቸው ቤተክርስቲያናችን በቅኝ ግዛት እንድትወድቅ አድርጓታል፡፡ በዚህ አሠራራቸውም አብዛኛው ምእመን ከዳር ቆሞ የሚመጣውን በጎ ዘመን በመናፈቅ ላይ ያለ ነው፡፡ ህዝቡ እና የንስሀ አባቶች ላይ ያለመግባባቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ልዩ ትኩረት የሚያሻው ሀገረ ስብከት ነው፡፡ አባታችን በ19/09/09 ዓ.ም “ጎንቻን ተነሥ ተደፍረሃል” እያሉ ለጦርነት ሲቀሰቅሱት መዋላቸው ሌላው አስፈሪውን የመከፋፈል ስትራቴጅ መከተላቸውን ያመለክታል፡፡ ይህንንም በቪዲዮ አድርጌ ከዚህ በፊት ይፋ ማድረጌ ይታወቃል፡፡


የምእመናንን ይሁንታ ለማግኘት አባታችን በዋናነት ትኩረታቸው “ጎጃም ተጠመቅ ተባለ” የሚለው ብሂላቸው ነው፡፡ “ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች ጎጃም ስለሆናችሁ ዳግም ተጠመቁ ተባሉ” በማለት ያልተደረገውን ተደረገ ያልሆነውን ሆነ ሲሉ መክረማቸው ትዝብት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ እኔም አንዱ ጎጃሜ ነኝ ዩኒቨርሲቲንም አልፌበታለሁ ጎጃሜ በመሆኔ ግን ተጠመቅ ያለኝ ማንም የለም፡፡ ልብ በሉ በተለይ ኤፌ 4÷4ን ይዛችሁ “አንዲት ጥምቀት” እያለ ለምን ተጠመቁ ትላላችሁ የምትሉን  ክርስቲያኖች ነገሩን ከላይ ብቻ አትመልከቱት ገባ ብላችሁ ምሥጢሩን መመርምሩ፡፡ ኤፌ 4÷4 ላይ ያለው “አንዲት ጥምቀት” የሚለው ቃል የማይታበል ማንም የማይሽረው በማንም የማይለወጥ መለኮታዊ ቃል ነው፡፡ ተጠመቁ የተባሉት ጎጃሞች ሳይሆኑ ቅብአቶች ናቸው፡፡ ጎጃም እና ቅብአትን ለያይታችሁ ተረዱት፡፡ “ተጠመቁ ተባልን” የሚሉት ቅብአቶች አቡነ ማርቆስ በመሠረቱት “ማኅበረ ሐዋርያት” በተባለው “የደብረ ወርቅ፣ የጉንደ ወይን፣ የሞጣ እና የመርጡለ ማርያም” የቅብአት እምነት ተከታይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላይነት በቀረበው ሪፖርት መሠረት ነው፡፡ “ማኅበረ ሐዋርያት” ማለት እንደ ግቢ ጉባኤ ሁሉ በየዩኒቨርሲቲዎች የተዋቀረ የራሱ ዓላማ እና ርእይ ያለው ከላይ ከጠቀስኩላችሁ ዐራት ቦታዎች የተውጣጣ ነገር ግን ሁሉን የማይወክል “ማኅበረ ቅብአት” ነው፡፡ የዚህ ማኅበር መንቀሳቀሻ ገንዘብ ከብጹእነታቸው እንደሚገኝ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ በአጠቃላይ ጎጃም እና ቅብአት የሚለውን ለያይተን መመልከት አለብን፡፡ የዋሐንን ለመሳብ “ጎጃም ተጠመቅ” ተባለ እያሉ የሚነዙት ክፉ ወሬ ተቀባይነት የለውም፡፡

የዘመድ አዝማድ መሠብሰቢያ የሆነው ሀገረ ስብከታችን ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ያሻዋል፡፡ እነማን ናቸው ዘመዶች የሚለውን ዝርዝር ከፎቶው ተመልከቱት (የተወሰነ የቆየ መረጃ ስለሆነ ምናልባትም የቦታ መቀያየር እና የሥልጣን እና የማዕርግ መለያየት ሊኖረው ይችላል) በሐገር ልጅነት እንደሚቀጥሩ እና ቅባትን እንደሚደግፉ ደግሞ በቪዲዮው ላይ ተመልከቱት፡፡ የሁሉ ዓይን ወደ ምሥራቅ ጎጃም ይሁን!!!
=====================================
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት #comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡