Tuesday, November 28, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፩



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፭ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡


ለእመቤታችን ዓመታዊ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!




ካሳሁን ምናሉ በዚህ በክህደት መጽሐፉ ገጽ ፳፭ እና ፳፮ ላይ የጻፈውን ነገር ሁላችሁ ተመልከቱት፡፡ አንብቡት እኔ ከዚህ በፊት “ወልደ አብ” ላይ ይህንኑ ራሱን መልስ ስለሰጠሁበት ባለፈው የሰጠሁትን መልስ ለዚህ በሚመጥን መልኩ አቀርብላችኋለሁ፡፡ 

“በቅባት ካህን የተጠመቀ ልጅነት የለውም” ብጹእ አቡነ ዘካርያስ




                       ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ይህን ሸር ያላደረገ ሰው #የማርያም_ጠላት ታዲያ ምን ሸር ልታደርጉ ነው!
የምሥራች ነው ደግሞ እኮ!
****************
ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ምሥራቅ፣ ደቡብ ምሥራቅና መካከለኛው አሜሪካ ኒዮርክ ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ስላለው ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እየሠሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ብጹእ አቡነ ዘካርያስ ከአቡነ ማርቆስ በፊት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ በፊት የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ ምሥራቅ ጎጃምን እያስተዳደሩ በነበሩበት ጊዜ ቅባቶች ላይ ቆራጥ አቋም የነበራቸው እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በዚያን ወቅት ቅባቶች በጾም ጊዜያት ላይ ብቻ ክርክር ያነሡ ስለነበር ልዩነታቸው እንደ አሁኑ ጎልቶ አለመታየቱ ብጹእነታቸው በሰፊው አልሄዱበትም ነበር፡፡ እንዲያውም በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ቅባት እና ተዋሕዶ በአንድነት ሲቀድሱ ሁሉ ዝም ይሉ እንደነበር እና በዚህም የተነሣ ከዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ጋር እና ከምእመናን ጋር ቅሬታ ውስጥ ገብተው እንደነበር ለሁሉም የታወቀ ነው፡፡ ምክንያቱ ባልተገለጠ መንገድ ከሀገረ ስብከቱ ገንዘብ ሲጠፋባቸው ሀገረ ስብከቱን ለቀው እንደሄዱም ይታወቃል፡፡ ብጹእነታቸው ግን የገንዘቡን መጥፋት አምነው ጠፍቶብኛል ያሉትን ገንዘብም ከልጆቻቸው አሰባስበው ለሀገረ ስብከቱ እንደሚመልሱ በወቅቱ ለአሜሪካን ድምጽ አሳውቀው ነበር፡፡ በቃላቸውም መሠረት አምና ፳፻፱ ዓ.ም አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለብጹእ አቡነ ማርቆስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተገኙበት አስረክበዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ገንዘብ ለሀገረ ስብከቱ መግባት አለመግባቱን የሚያውቅ ምእመን የለም፡፡ ገንዘቡ ምን ሥራ ላይ እንደዋለም ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተባለ ነገር የለም፡፡



Monday, November 27, 2017

”በሃይማኖታችን አንደራደርም” ደጀን ደብረ አሚን



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ደጀን ከተማ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኝ አነስተኛ ከተማ ናት፡፡ ደጀን የከተማዋም የወረዳዋም መጠሪያ ስም ነው፡፡ ጎጃምን ማየት የሚፈልግ ሁሉ የዓባይን ድልድይ ተሻግሮ በመጀመሪያ የሚያገኛት ደጀንን ነው፡፡ ዋና ዓላማየ ደጀንን ማስተዋወቅ አይደለም፡፡ ደጀን ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ ትናንትና እሁድ ኅዳር ፲፯/ ፳፻፲ ዓ.ም ፀረ ተሐድሶ ጉባዔ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው ጉባዔ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ የደብሩ አገልጋይ ካህናት ዲያቆናት እና በርካታ ህዝበ ክርስቲያን ተገኝቶ ነበር፡፡ በምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት እንዲህ ያለ ጉባዔ ሲዘጋጅ ደጀን የመጀመሪያዋ መሆኗ ነው፡፡ ይህ ጉባዔ ያስፈለገበት ምክንያት፡-

Sunday, November 26, 2017

ጾመ ነቢያት መቸ ይገባል?



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
“መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? የሚለው ተከታታይ ጽሑፍ ይቀጥላል፡፡ ለዛሬ ስለጾመ ነቢያት ትንሽ እንነጋር እስኪ፡፡ እዚህ ላይም በቅባች እና በተዋሕዶ ልጆች መካከል ልዩነት አለ፡፡ ቅባቶች እንብላ ተዋሕዶዎች እንጹም የሚል ክርክር አለ እርሱን በጥቂቱ እንመልከት፡፡

Thursday, November 23, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፩ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ካሳሁን ምናሉ “መሠረተ ሐይማኖት” በተሰኘው የክህደት መጽሐፉ  ገጽ ፳፩ ላይ “ቃልን በስጋ ርስት ትሑት ነዳይ ካላልነው፡፡ ማወራረስ አይቀርብንም ተዋሕዶ አይጎላብንም ቢሉ፡፡ አይጎላብንም በቅርብዓት እንመላዋለን፡፡ በቅብአት እንዴት እንመላዋለን ቢሉ፡፡ ይህ ስጋ ሲፈጠር ንዴት ትሕትና ያድርበት ነበር፡፡ ይህ አንዴት ትህትና ያድርበት የነበረ ስጋ ከቃል ሲዋሐድ ጊዜ ሳይሻ መንፈስ ቅዱስ ቢያድርበት ንዴት ትሕትና ቀረለት” ይላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ስለተነጋገርን መድገሙ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም፡፡ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ እንዳንልማ የተወገዘ ሃይማኖት ነው  “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእርሱ አጋዥነት ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው፤ ርኩሳን አጋንንትን በማውጣት ጊዜም ኃይልን ተአምራትን ከመንፈስ ቅዱስ ይቀበላል፤ በሰውም የአምላክነትን ሥራ ይሠራል የሚለው፤ መንፈስ ቅዱስ የባሕርዩ ነው፤ የአምላክነትንም ሥራ እርሱ ራሱ ይሠራል የማይል ቢኖር ውጉዝ ይሁን” ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ ፸፫÷፵፱ ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለት ክህደት ነው፡፡


Wednesday, November 22, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፱



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ካሳሁን ምናሉ “መሠረተ ሐይማኖት” በተሰኘ የክህደት መጽሐፉ ገጽ ፳ ላይ እንዲህ ይላል “ስጋ በርስቱ ከበረ ብዕለ እንዳይባል በተዋሕዶ ከበረ ማለት ነው፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለትም በህድረት ከበረ  ማለት ነውና እንደ ንስጥሮስ ሁለት አካል ማድረግ ነው ስለዚህ ስጋ ከቃል ከተዋሐደ በኋላ ክቡር ባዕል መባል ይገባዋል ዕንጅ፡፡ ክብረ ብዕለ መባል አይገባውም፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለት እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሁለት አካል ማድረግ ነውና ከንስጥሮስ ባህል ይገባል ማለት እንዴትና፡፡ ተዋሕዶ አንድነትን ይፀናል እንጅ፡፡ ሁለትነትን ያመጣልን እንጅ ቢሉ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ስም ሰጥቶ ግብር መንሳት ነው” ይላል፡፡

Tuesday, November 21, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፰



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፲፱ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
****************
·         የኃያሉ መልአክ የመጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል በዓል ዛሬ በደብረ ማርቆስ ከተማ በገዳመ ሕያዋን ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ፡፡
·         እንኳን ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም በፍቅር በአንድነት አደረሳችሁ፡፡ የመልአኩ ረድኤት በረከት አይለየን አሜን፡፡
***************



Monday, November 20, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፯



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፲፭ ምእራፍ ሦስት ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡


****************
·         እንድማጣ ኢየሱስ የሚገኘው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባዔ ተማሪዎች የመማሪያ አዳራሽ በድንጋይ ተደብድቦ የመስኮት እና የበሮቹን መስታወት  መርገፋቸው ተነገረ፡፡
·         ይህንን ድርጊት የፈጸመው ቄስ በህግ ሊጠየቅ ይገባል ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡
***************
 


ምእራፍ ሦስት ድንግልን ስለ ማንፃትና ስለመክፈል ብሎ የሚጀምረው የካሳሁን ምናሉ የክህደት ትምህርት እንዲህ በማለት ይቀጥላል “የመንፈስ ቅዱስ ግብር ምንድን ነው ቢሉ መንፃት መክፈል መዋሐድ መፍጠር ቅብዕ መሆን ነው” ይላል፡፡ ይህን በተመለከተ ባለፉት ተከታታይ ትምህርቶች በሰፊው ስለተመለከትን በድጋሜ አናየውም፡፡ በዚህ የምንጨምረው ነገር ቢኖር ከመንፈስ ቅዱስ ግብሮች መካከል አንዱ “መዋሐድ” ተብሎ የተጠቀሰውን ክህደት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለለቢሰ ሥጋ በድንግል ማርያም ማኅጸን አላደረም፡፡ በየትኛው ትምህርት በየትኛው መጽሐፍ ነው “መንፈስ ቅዱስ የማርያምን ሥጋ ተዋሐደ” የሚል ገጸ ንባብ የሚገኘው? ይህ ፍጹም ክህደት ነው፡፡ 


Sunday, November 19, 2017

ደጀን በፀረ ተሐድሶ ትግል ውስጥ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የደጀን አበ ብዙኃን አብርሃም ቤተክርስቲያን
እልህ አስጨራሹን የዓባይን በረሃ አቋርጠው የጎጃምን ንጹሕ ዓየር “ሀ” ብለው የሚተነፍሱባት ደጀን ከተማ ዛሬ ኅዳር ፲/፳፻፲ ዓ.ም ፀረ ተሐድሶ ዘመቻዋን በጥንታዊው ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ በይፋ ጀምራለች፡፡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በተጀመረው በዚህ የመጀመሪያው የፀረ ተሐድሶ ዘመቻ ጉባዔ ላይ ከ አምስት መቶ ያላነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተሳተፉበት ተነግሯል፡፡ አዳራሹ ከመሙላቱ የተነሣ በመስኮቶች እና በበሮች አካባቢ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ምእመናን በቁጥር አያሌ እንደነበሩም ተጠቁሟል፡፡ ደጀን ኮራንብሽ ደብረ አሚን እውነትም የእምነት ተራራ ስምን መልአክ ያወጣዋል አሉ፡፡ አባ ሙሴን የመሰሉ ብርቅየ አባት ያስተማሩበት ዐረፍተ ዘመን ሲገታቸውም በዚያው ሥጋቸው ያረፈባት ደጀን በመናፍቃን አትወረርም አትወረስም፡፡



የደጀን ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስ

Friday, November 17, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፮



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፲፫- ፲፭ ድረስ ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ገጽ ፲፫ መጨረሻ መስመር ላይ ጀምሮ ገጽ ፲፬ መጀመሪያው መስመር ላይ የሚቋጨውን የካሳሁን ምናሉን የክህደት ትምህርቶች እንመልከት፡፡ “ጌታ ሰው ሆኖስጋ ለብሶ በስጋ ርስት የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ፡፡ ከአብ የባሕርይ ልደት ተወልዶ ሳለ ለአበው ለነቢያት ለሚመጡ ለሐዋርያት ለምዕመናን በኩር ሆኖ ልጅነት የሚያድል መሆኑ በጊዜው ፅንስ ነው” ይላል፡፡ ይህ አስተምህሮ አርዮሳዊነት መሆኑ ለሁሉም የታወቀ ነው፡፡ ከተዋሕዶ በኋላ በሥጋ ርስት በመለኮት ርስት እያልን አንዱን ለሁለት ልንከፍለው እንዴት እንችላለን? ክርስቶስ የሚለው ስም እኮ በፍጹም ተዋሕዶ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢሆን የወጣለት ስም ነው፡፡ “መንፈስ ቅዱስን በመላ ተቀብሎ” ማለት ምን ማለት ነው? እስኪ እናስተውል ወገኖቼ! በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሆነው አምላክ መንፈስ ቅዱስን በመላ የሚቀበለው ቃል ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተለይቶት ነበርን? ይህን ድንቅ የሆነ የሥጋዌውን ነገር ለመናገር የሥላሴን ምሥጢር ማወቅ መረዳት በቀደመ ነበር፡፡ የሥላሴ አንድነታቸው እና ሦስትነታቸው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

Wednesday, November 15, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፭



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ገጽ ፱ እና ፲ ላይ ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡

ካሳሁን ምናሉ ገጽ ፱ ላይ እንዲህ ይላል “ቃልም ለቃልነቱ ቃል ነው፡፡ ሥጋ ለስጋነቱ ስጋ ነው ነገር ግን ቃልም ስጋም በእንድ ሆኑ ማለት ነው” ይላል፡፡ ገጽ ፰ እና ፱ ላይ መለኮት እና ሥጋ በተዋሕዶ አንድ እንደሆኑ ከሃይማኖተ አበው ጥቅሶችን እየጠቃቀሰ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ ሆኖም ግን በተዋሕዶ ምንታዌነት ብቻ ተወገደ እንጅ ሰው አምላክ፤ አምላክም ሰው አልሆነም ብሎ የሚያምን ስለሆነ “በተዋሕዶ ከበረ” አይልም፡፡ እንዲያውም “በተዋሕዶ ከበረ” ማለት ዐራት ኑፋቄ አለበት ብለው “በወልደ አብ” መጽሐፋቸው ላይ በሰፊው ክደውበት ታይተዋል፡፡ ተዋሕዶ ማለት ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነበትና የሥጋ ገንዘብ ለቃል የቃልም ገንዘብ ለሥጋ የሆነበት ሰው አምላክ አምላክም ሰው የሆነበት  የማይመረመር ከአእምሮ በላይ የሆነ የማይደረስበት ምጡቅ የማይጨበጥ ረቂቅ የሆነ ድንቅ ምሥጢር ነው፡፡ ሰው አምላክ ከመሆን በላይ መክበር አለን? ከወዴትስ ይገኛል? ስለዚህም በተዋሕዶ ከበረ ብለን እናምን ዘንድ እንገደዳለን ማለት ነው፡፡ “በተዋሕዶ ከበረ” የሚል ጥቅስ ከወዴት ይገኛል ካላችሁ በቦታውና በርእሱ ስንገናኝ እዘረዝርላችኋለሁ፡፡ በርካታ ጥቅሶችን አሳያችኋለሁ፡፡ ከዚህ በፊትም የገለጥሁላችሁ መሆኑን ልብ በሉ፡፡

ጣት የሚጠቡ ሕጻናትን ያደረገን ልዑክ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? የሚለውን ተከታታይ ትምህርት ወደፊት የምንመለስበት ይሆናል፡፡ ዛሬ ማወቅ ስላለባችሁ ጉዳይ መረጃ ልሰጣችሁ መጥቻለሁ፡፡
***ብጹእ አቡነ ዲዮስቆሮስን ስለሁኔታው እናናግራቸው መልእክት እንጻፍላቸው፡፡ 00251933074614 የእጅ ስልካቸው ነው***
ነገሬን ፳፻፱ ዓ.ም  በጻፍኋት ትንሽየ ግጥም ለጀምር፡፡
በጉ እረኛ ሆነ
=========
በግ መሆናችንን አምነው ተቀብለው፣
እረኛ ሊሆኑን በእኛ ላይ ተሹመው፣
ዘመነ ግልንቢጥ ጉድ ዘመን ዘመነ፣
እረኛው ተኛና በጉ እረኛ ሆነ፡፡
ትላለች ሲገርመኝ ሲደንቀኝ እረኝነታቸውን ዘንግተው በበጎቻቸው ሲጠበቁ ባይ ጊዜ የጻፍኋት አነስተኛዋ ግጥም!!!

Monday, November 13, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፬




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
·        የምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከትን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮች እንዲያጣራ ከጠቅላይ ቤተክህነት የተመደበው ልዑክ ደብረ ማርቆስ ገብቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በርካታ ምእመናን ወደ ቦታው በመምጣት ላይ ናቸው፡፡

ዛሬ ገጽ ፯ ላይ  ያሉትን ስህተቶች በማስረጃ አስደግፈን እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር አብሬ ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን በቤተክርስቲያናችን ትምህርት ልዩነት ያለውን ብቻ በማስረጃ እያስደገፍሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡


Friday, November 10, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፫


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፭ እስከ ፮ ያሉትን ስህተቶች በማስረጃ አስደግፈን እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር አብሬ ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን በቤተክርስቲያናችን ትምህርት ልዩነት ያለውን ብቻ በማስረጃ እያስደገፍሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡



#እናምናለን_ምሥጢረ_ቅባት የሚል መዝሙር በጭፈራ መልኩ ሲዘመር የሚያሳይ መረጃ ከጉንደወይን ደርሶኛል፡፡ #በወልደ_አብ_መናፍቅ_አፈረ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ያወገዘውን መጽሐፍ ደግፈው ሲጨፍሩ አድረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ #በሃያ_ስምንት_መብላት_ተወገዘ ይላሉ፡፡ “ወልደ አብ” የታተመባትን ቆጋ ገዳምን #ቆጋ_ገዳም_የሃይማኖት_አገር በማለት ሲያሞካሹም ተደምጠዋል፡፡ #ሁለተኛ_ሻወር_መውሰድ_ቀረ በማለትም ጥምቀትን #ሻወር ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ #አክሲማሮስ_የቅባት_ምስክር በማለትም ሊቁ ኤጲፋንዮስ የጻፈልንን መጽሐፍ ለክህደታቸው #ምስክር ነው ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ተዋሕዶ ነን የሚሉ ካህናትንም በዚያ አካባቢ መከራ እንደሚያጸኑባቸውም በዕለቱ ትምህርት የሰጡት ሰው ተናግረዋል፡፡ ይህ ጉዳይ በዝምታ መታየት የለበትም፡፡ በቤተክርስቲያናችን ስም እየተሰባሰቡ ቤተክርስቲያናችንን ለማፍረስ እየሠሩ ያሉ ስለሆነ ጉዳዩን ወደ ህጋዊ አካል ማድረስ ቢቻል ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡፡

 

Thursday, November 9, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፪





፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከመጀመሪያው ገጽ ከምእራፍ አንድ ጀምረን እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር አብሬ ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን በቤተክርስቲያናችን ትምህርት ልዩነት ያለውን ብቻ በማስረጃ እያስደገፍሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡

Tuesday, November 7, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፩




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ቅባቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ኃፍረታቸውን የገለጡበት እጃቸውን የፈቱበት የመጀመሪያው የክህደት መጽሐፋቸው በሐምሌ ፲/ ፳፻፩ ዓ.ም በካሳሁን ምናሉ (0910581997) አዘጋጅነት የታተመው “መሠረተ ሃይማኖት” የተሰኘው ባለ ዐሥራ ሁለት ምእራፎች ባለ ሃምሳ አምስት ገጾች አነስተኛ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ከሽፋን ገጹ ጀምሮ በፊደል ግድፈቶች የተሞላ ነው፡፡ ምናልባትም ይህ የፊደል ግድፈት አንድም ከአዘጋጁ አንድም ከኮምፒዩተር ጸሐፊው ሊመጣ ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን መጽሐፍ ሲታተም የጽሑፉ ረቂቅ በሚገባ ተገምግሞ እና በድጋሜ ታይቶ ስህተቶች ግድፈቶች ተለቅመው ነው መዘጋጀት ያለበት፡፡ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ግን ምናልባትም የዚህ ዓይነቱ ክህደት በመጽሐፍ ሲታተም የመጀመሪያውም ስለሆነ በፍርሐት መካከል ስለሆነ የፊደል ግድፈቶችን ለቅሞ አላስተካከላቸውም፡፡ በውስጥ ገጾችም ስትመለከቱ እንዲሁ በፊደል ግድፈቶች የተሞላ ነው፡፡ በነገራችን ላይ “ወልደ አብ” ም ሆነ “ሚሥጢረ ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ” የተባሉት በቅርቡ የታተሙትም ቢሆኑ የፊደል ግድፈታቸው በጣም የበዛ ነው፡፡ ነገሩማ ክህደት እየተጻፈ በፊደል ግድፈቶች ማን ይጨነቃል ብላችሁ ነው እኛ ዓይን ስላየነው እንጅ፡፡





Monday, November 6, 2017

“በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም”




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
“መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፣ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል” እንዳለ ደራሲ መድኅን ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስለዓለም ኃጢአት ተሰቅሏል፡፡ በደሙ ፈሳሽነት ዓለምን ከኃጢአት ቆሻሻ ሊያነጻት በደል የሌለበት እርሱ በመስቀል ላይ ተቸነከረ፡፡ ስለእኛ ብሎ የማይታመመው ታመመ፤  የማይሞተው ሞተ፤ የማይቀበረው ተቀበረ፡፡ በዚህ ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን እመሕይወት ድንግል ማርያምን እናስባታለን፡፡ ጌታችን መታመሙን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን፣ ማረጉን የተመለከትነው ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ ነውና ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን፡፡
መድኃኔዓለም የዓለም ጌታ የዓለም መድኃኒት ሆይ! በደል ሳይኖርብህ እንደበደለኞች ከበደለኞች ጋራ በቀራንዮ ኮረብታ ላይ በእንጨት መስቀል ላይ የተሰቀልህ አንተ ስለእናትህ ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ስለንጽሕተ ንጹሐን ስለ ወላዲተ አምላክ ስለ ደንግል ማርያም ብለህ ይቀር በለኝ ማረኝ ራራልኝ እያልን እንለምነዋለን፡፡ ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ዘንድ ታማልደናለች፡፡ የዛሬ መናፍቃን “በለኒ መሐርኩከ በእንተ ኢየሱስ” እያሉ አምላካቸውን እንደ አማላጅ ሲያደርጉት ይታያሉ፡፡ ይህ በጣም ውርደት የውርደትም ውርደት ነው፡፡ ያልተማረ ሰው የሚናገረው ከንቱ ንግግር ነው፡፡ “መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፣ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ኢየሱስ” ቢባል ትርጉሙ ምንድን ነው? ትርጉም አልባ መሆኑን ልብ በሉ፡፡
መድኃኔዓለም የምንለው ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ ታዲያ “ስለኢየሱስ ክርስቶስ ብለህ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ ማረኝ ራራልኝ” ብለን እንጸልይ ዘንድ ማን ነው ይህን ከንቱ ፈራሽ ነገር በልቡናችን ውስጥ የተከለው? ኢየሱስ ከመድኃኔዓለም ይለምናል ማለት ነው? ኢየሱስ እና መድኃኔዓለም ይለያያሉ ማለት ነውን? በፍጹም አይለያዩም አንድ ናቸው፡፡ ይሄ በጣም ውርደት ነውና ፈራሽ የሆነ ከንቱ ነገርን ከምታመጡ ትክክለኛውን ልመና እንዲህ ብላችሁ ለምኑ “መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፣ በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል”፡፡ መናፍቃን ሆይ አትድከሙ የመዳናችን ምክንያት ድንግል ማርያም ናት፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ እስኪ ስለነገረ መስቀሉ እንነጋገር፡፡ ነገረ መስቀሉን ስናስብ የተደረገልንን የቤዛነት ሥራ ከማስታወሳችንም በተጨማሪ በግራና በቀኝ የተሰቀሉትን ወንበዴዎች እና ከእግረ መስቀሉ ሥር የቆሙትን ቅዱሳን እንዲሁም በሰማይና በምድር የተደረጉ ተአምራትን እናስብበታለን፡፡
በመጀመሪያ የተደረገልንን የቤዛነት ሥራ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ነገረ መስቀሉ በልባችን ጽላት ከተሳለ ኃጢአትን እናደርግ ዘንድ እጅ አንሰጥም፡፡ ምክንያቱም ለቤዛ ዓለም በመስቀል ላይ እጆቹን ዘርግቶ የተሰቀለውን ክርስቶስ በፊታችን እየተመለከትን ኃጢአትን የምናስብበት ጊዜ የለምና፡፡ ዮሐንስ ፊቱ ሳይፈታ ቁጽረ ገጽ ሆኖ ዘመኑን ሁሉ ያሳለፈው በመስቀሉ ሥር ቆሞ ለቤዛ ዓለም እጁ በመስቀል ላይ የተዘረጋውን ክርስቶስ ተመልክቶ ነው፡፡ እኛ ህግ ጥሰን ትእዛዝ አፍርሰን አምላክነትን ሽተን አትብሉ የተባልነውን በልተን ስለበድልነው ከሰማይ የወረደልን የፍቅር ባለቤት አምላካችን ፈጣሪያችን ጌታችን መድኃኒታችን እርሱ ነው ከመስቀሉ ላይ ዕርቃኑን ተሰቅሎ ያየነው፡፡ ሊቁ አባ ሕርያቆስ “ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት፤ የሰው ፍቅር ኃያል ወልድን ከሰማይ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው” ይላል፡፡ ለመስቀል ሞት ራሱን አሳልፎ የሰጠ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል እንደሆነ እናውቃለን፡፡ የእኛ ፍቅር አገብሮት አንዳች ኃጢአት ሳይኖርበት ሰማያዊ መለኮት ምድራዊውን ደካማ ሥጋ ተዋሕዶ የቤዛነት ሥራውን ሠርቷል፡፡ ይህን የቤዛነት ሥራ የፈጸመው በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ አደባባይ በተተከለው ዕፀ መስቀል ላይ እጅና እግሮቹን ተቸንክሮ ተሰቅሎ ሞቶ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት መዝ ፸፫÷፲፪ ላይ “ወገብረ መድኃኒተ በማእከለ ምድር፤ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ” እንዳለው በምድር ማእከል በሆነችው በቀራንዮ እጆቹን እና እግሮቹን ለችንካር  ጎኑንም ለጦር ሰጠ፡፡
“ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፤ የአባቶች ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ፡፡ የነጻነት አርማ መስቀልም በቀራንዮ አደባባይ ተተከለ” እንዲል ደራሲ (መልክአ ሥላሴ)፡፡ የነቢያት ትንቢት የአበው ተስፋ የተፈጸመው በንጽሕተ ንጹሐን በቅድስተ ቅዱሳን በእመ ብርሃን በወላዲተ አምላክ በድንግል ማርያም ነው፡፡ በቀራንዮ አደባበይ በተተከለው መስቀል ተሰቅሎ የተመለከትነው ከድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ ነውና የድኅነታችን መጀመሪያ ንጽሕት ዘር ድንግል ማርያም ናት፡፡
ነገረ መስቀሉን ስናስታውስ ድንግል ማርያምን ማስታወስ ግዴታችን ነው እርሷ ባትኖር ኖሮ ጌታ ሥጋን ተዋሕዶ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ባልተመለከትነውም ነበር፡፡ ስለዚህም “የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽህናችንም መሠረት አንች ነሽ” እያልን ቅዱስ ኤፍሬም እንዳመሰገናት እኛም እናመሰግናታለን፡፡ ስለዚህ ነው ነገረ መስቀሉን ስናስብ ይህን የተደረገልንን የቤዛነት ሥራ ማሰብ ይገባናል የምንለው፡፡ ጌታ ለመስቀል ሞት ቀራንዮ አደባባይ የደረሰው እንዲሁ በቀላሉ አልነበረም በርካታ ድብደባዎችን፣ ግርፋቶችን፣ እንግልቶችንና መከራዎችን ተቀብሎ ነው እንጅ፡፡ ሊቃውንቱ ጌታ የተቀበላቸውን መከራዎች “13ቱ ሕማማተ መስቀል” ብለው አስተምረውናል፡፡ እነዚህም ተአስሮ ድኅሪት፣ ተስሕቦ በሐብል፣ ወዲቅ ውስተ ምድር፣ ተከይዶ በእግረ አይሁድ፣ ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ፣ ተጸፍዖ መልታህት፣ ተወክፎ ምራቀ ርኩሳን፣ ተኮርዖተ ርእስ፣ አክሊለ ሶክ፣ ፀዊረ መስቀል፣ተቀንዎ በቅንዋት፣ ተሰቅሎ በዕፅ እና ሰሪበ ሐሞት ናቸው፡፡ እነዚህን መከራዎች ትኩሳቱን አብርዱልኝ መከራውን አስታግሱልኝ ሳይል ስለእኛ በትህትና እና በትዕግሥት የተቀበላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ በነገረ መስቀሉ ውስጥ ይህንን ሁሉ መከራ የተቀበለውን ኢየሱስ ክርሰቶስ እንመለከትበታለንና በሕይወት ለመጽናት ይጠቅመናል፡፡
ሌላው ነገረ መስቀሉን ስናስብ ግራና ቀኝ ያሉትን ወንበዴዎች ማሰብ ያስፈልገናል፡፡ እነዚህ ወንበዴዎች የኃጥአንና የጻድቃን ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በዓለም ፍጻሜ ጊዜ ኃጥአንን በግራው ጻድቃንን በቀኙ አቁሞ ዘለዓለማዊውን ፍርድ ይፈርዳልና በዚያ ምሳሌ እርሱ ባወቀ ይህን አድርጓል፡፡ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን ስናስብ በዓለም ፍጻሜ ጊዜ የሚጠብቀን ፍርድ ምን ይሆን “ሁሩ እምኔየ” እንባል ይሆን ወይስ ደግሞ “ንዑ ኀቤየ” እንባል ይሆን ብለን ነገረ ምጽአትን እናስታውስበታለንና በቤቱ ለመጽናት እንተጋለን፡፡ እዚህ ላይ በተለይ በቀኝ የተሰቀለውን ጥጦስ በምግባር በሃይማኖት እንመስለው ዘንድ ወደ ሰማይ ቀና ብለን ሦስቱን ወደ ምድርም ዝቅ ብለን አራት ተአምራትን ተመልክተን “ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ” ልንል ይገባናል፡፡ እነዚያ ሰባቱ ተአምራት ያለአንዳች ነገር እንዳልተደረጉ ራሳችንን ልናሳስበው ይገባናል፡፡ ይህን ሁሉ ተአምር ሳይከፈልብን እየተመለከትን እንደ ዳክርስ የጥፋት ዕቅዳችንን ማቀድ የለብንም፡፡ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን ስናስብ የተፈጸሙትን ተአምራትም ማስታወስ ይገባናል ማለት ነው፡፡
ሌላው ነገረ መስቀሉን ስናስብ ከእግረ መስቀሉ አጠገብ ሆነው ዓይናቸውን ወደ ላይ አቅንተው የተሰቀለውን ጌታ የሚመለከቱትን እና መከራ መስቀሉን አስበው ፊታቸውን በእንባ ያራሱ ቅዱሳንን ማሰብ አለብን፡፡ ዮሐ ፲፱÷፳፭ ላይ “በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፣ የእናቱም እኅት፣ የቀለዮጳም  ሚስት ማርያም፣ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር” ይላል፡፡ በእግረ መስቀሉ የቆሙት ወንጌላዊው ዮሐንስ እና እነዚህ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ለዚህ ክብር የደረሱት መከራውን ሁሉ ታግሰው ፍርሐታቸውን ሁሉ አርቀው ነው፡፡ እስከ ቀራንዮ አደባባይ መከራውን ታግሰን ፍርሐታችንን አርቀን ከእግረ መስቀሉ ሥር ካልተገኘን “እነኋት እናትህ” ዮሐ ፲፱÷፳፯ ለመባል አንችልምና እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ መጓዝ አለብን፡፡ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን ከልባችን ጽላት ልንጽፈው ያስፈልገናል፡፡
ሌላው ነገረ መስቀሉን ስናስታውስ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ያስፈልገናል፡፡ መምህረ አህዛብ ቅዱስ ጳውሎስ ፩ኛ ቆሮ ፩÷፲፰ ላይ “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው” ይለናል፡፡ ስለዚህ እነዚህን የመስቀሉ ላይ ቃሎች ሁልጊዜም ማስታወስ ማሰብ ይገባናል ማለት ነው ምክንያቱም ኃይለ እግዚአብሔር ነውና፡፡ ጌታችን በመስቀሉ ሳለ የተናገራቸው ለእኛ ብርታት ጽናት ድኅነት የሚሆኑ ፯ ቃላት አሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ አጽርሐ መስቀል በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነዚህም
፩. አምላኪየ አምላኪየ ነጽረኒ ወለምንት ኀደገኒ
፪. አባ ሥረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ
፫. ነዋ ወልድኪ ወነያ እምከ
፬. ኤሎሄ ኤሎሄ ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ
፭. ወአንተ ትቀድሞ ለአዳም በዊአ ውስተ ገነተ
፮. አባ አማሐፅን ነፍስየ ውስተ
፯. ተፈጸመ ኩሉ እነዚህን ሰባቱን በመስቀል ላይ ሆኖ ተናግሮ እራሱን ወደቀኝ ዘንበል አድርጎ ነፍሱን ከሥጋው በገዛ ሥላጣኑ ለየ፡፡ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን ስናስብ እነዚህን የርኅራኄ ቃላት ማስታወስ ይጠበቅብናል ማለት ነው፡፡
በመጨረሻም ክርስቶስን ለመከተል በቤቱም ለመጽናት የግድ መከራ መስቀሉን ማስታወስ እንደሚኖርብን ጌታችን የተናገረውን እንመለከታለን፡፡ ማቴ ፲፮÷፳፬ ላይ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ይለናል፡፡ ስለዚህ ነው ነገረ መስቀሉን ማሰብ በቤቱ እንድንጸና ይረዳናል ማለታችን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተልና በቤቱ ለመጽናት በመጀመሪያ ራስን መካድ ያስፈልጋል፡፡ ራስን መካድ የቀደሙትን አባቶችና እናቶች አብነት አድርጎ  እውቀቴ፣ ሀብቴ፣ ትምህርቴ፣ ወገኔ ዘመዴ፣ ገንዘቤ ንብረቴ ሳይሉ መድኃኔዓለም ክርስቶስንና ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን በመከተል ህገ እግዚአብሔርን ማክበር፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን መጠበቅና ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን መፈጸም፣ በጊዜውም ያለጊዜውም ፀንቶ መገኘት ነው፡፡ ሐዋርያት በዚያ ዓይነት መከራ ውስጥ ሳሉ ወንጌልን ያስተምሩ የነበረው ራሳቸውን ስለካዱ መስቀሉንም ስለተሸከሙ ነበር፡፡ ራሳቸውን ለሞት ሰጥተዋልና ሞትን አይፈሩም ነበር፡፡ ስለዚህ እኛም በቤቱ ለመጽናት ፈተናና መከራውን መሰቀቅ አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም እኔን መከተል የሚወድ ራሱን ይካድ ብሏልና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስንከተለው ምግቤ ምን ይሆን፣ ቤተሰቦቼስ እንዴት ይሆኑ ይሆን ሀብት ንብረቴስ እንዴት ይሆን እያልን ማሰብ የለብንም ለዚህ ነው በመጀመሪያ ራሳችንን መካድ የሚስፈልገው፡፡
ራሳችንን ከካድን በኋላ መስቀሉን እንሸከማለን፡፡ መስቀሉ መከራው ነው፤ መስቀሉ ስቃዩ ነው፤ መስቀሉ መራብ መጠማቱ ነው፤ መስቀሉ መታሰሩ ነው፤ መስቀሉ መደብደብ መገረፉ ነው፤ መስቀሉ ሥጋን ብቻ ለሚገድሉት ራስን ለሞት አሳልፎ መስጠቱ ነው፡፡ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን ስናስታውስ በቤቱ እንጸናለን ማለታችን በእነዚህ ነገሮች ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ “በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ” ገላ ፭÷፩ ላይ ይለናል፡፡ ስለዚህ በመስቀል ሞቶ ነጻነት የሰጠንን አምላክ በማስታወስ በባርነት ቀንበር ዳግም እንዳንያዝ በቤቱ መጽናት ይጠበቅብናል ማለት ነው፡፡ ይህን ማድረግ የምንችለው ወይም ዳግም በባርነት ቀንበር እንዳንያዝ፤ በሰይጣን ምክር ዳግም እንዳንታለል የምንሆነው፤ የምንበረታው ደግሞ ነገረ መስቀሉን ማሰብ ስንችል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ገላ ፫÷፩ ላይ “የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዐይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር ለእውነት እንዳትታዘዙ ዐዚም ያደረገባችሁ ማነው” ይላል፡፡ ስለዚህ ነገረ መስቀሉን ሁልጊዜም ማሰብ እንደሚገባን ቅዱሱ ሐዋርያ ያስተምረናል፡፡ ነገረ መስቀሉን እንዳናስብ የሚያደርገን ዐዚም እንደሆነ ነው የሚገልጽልን፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ ነገረ መስቀሉን ማሰብ ማስታወስ በቤቱ እንድንጸና እና ከቤቱ እንዳንወጣ ይጠቅመናል፡፡
ጌታ ሆይ ስለእናትህ ስለድንግል ማርያም ብለህ ማርሁህ ይቅርም አልሁህ በለኝ!!!
(አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምህ ከሚለው ያልታተመ መጽሐፌ የተወሰደ)
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
ጥቅምት ፳፯ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍