ብዙዎች የተጣመሩባት ለእምነታቸው መሠረት ያደረጓት እንደ ጥያቄ እንደ መልስም የሚጠቅሷት ብቸኛ ጥቅስ ናት ሮሜ 8÷34 :: ቃሉ “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ
ነው” ይላል:: “የሚማልደው” የሚለውን ቃል ይዘው ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ:: ( ሎቱ ስብሐት) አለማስተዋል ካልሆነ በቀር በዚህ የሚሳሳት ሰው አለ ለማለት
አያስደፍርም ምክንያቱም ከላይ ስናነብ የምናገኘው የዚህ ተቃራኒ ነውና:: ከቁጥር 33 ጀምረን እንመልከት “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል የሚያጸድቅ
እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ... ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” አእምሮ ላለው ይህን መረዳት
በጣም ቀላል ነው:: የሚያጸድቅ ክርስቶስ ነው የሚኮንንም ክርስቶስ ነው
የሚማልደው ማነው? ማንንስ ይማልዳል? የሚያጸድቅ ማለት አንተ ቅዱስ ነህና መንግሥተ ሰማያት ግባ
የሚል እውነተኛና የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጥ ማለት ነው የሚኮንን ሲል ደግሞ አንተ ኃጥእ ነህና ገሃነመ እሳት ግባ የሚል እውነተኛ ፍርድ የሚፈርድ
ማለት ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ ፈራጅነቱን ሲያጎላ መጥቶ በእርግጠኝነት “ስለኛ የሚማልደው” ብሎ አይደመድምም:: ነገር ግን እኛ በራሳችን መንገድ መሄድ ስንሻ ያጣመምነው ቃል እንደሆነ
ግን እንረዳለን:: ቅዱሳንን የሚንቁ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት
የሚጠራጠሩ ሰዎች አምላካቸውን ያከበሩ እየመሰላቸው አማላጅ ነው ይሉታል:: ትክክለኛ ቃሉ “ስለእኛ የሚፈርደው” የሚል ነው:: ከላይም የተጻፈው ይህንኑ ነው የሚገልጸው:: መጽሐፉን በሙሉ መመልከት ትልቅ መልስ ይስገኛል:: ቃሉን በትክክል ለመረዳት ከላይም ከታችም የተጻፈውን ማብራሪያ
በሚገባ ማንበብ ያስፈልጋል:: አንድ ጥቅስ ዝም ብሎ ከመካከል
መዝዞ አይነበብም ምክንያቱም ቃሉን ለመረዳት አስቸጋሪ በመሆኑ:: ክርስቶስን በተጻፈው መሠረት አማላጅ ነው ብንል እንኳ (ሎቱ ስብሐት) ሌሎች ጥቅሶችንም ማንሣት እንሻለን:: እሽ እኛ በምንጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ስለ እኛ የሚማልደው” ይላል ስለዚህ “ኢየሱስ አማላጅ
ነው” የምትሉ ሰዎች እስኪ በማስተዋል ሁኑና የሚከተሉትን ጥቅሶች፡-
v ሮሜ8÷26 ላይ “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ
ድካማችንን ያግዛል እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” ይላል:: ከዚህ እንደምንረዳው መናፍቃንም ይህንን ጥቅስ ይዘው መንፈስ ቅዱስ ይማልዳል ማለት አለባቸው ማለት ነው::
v ኤር7÷25 “አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር
ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር” ይላል:: እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚለው አብን ነው ከላይ ጀምራችሁ ተመልከቱት:: ስለዚህ በመናፍቃን አስተሳሰብ
መሠረት አሁንም አብ ይማልዳል ማለት ነው::
አሁን ከእነዚህ ጥቅሶች በመነሣት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ
ቅዱስ ሁሉም ይማልዳሉ ልንል ነው ማለት ነው? ጥሬ ቃል ይዘን የምንሮጥ ከሆነ ከዚህ የዘለለ
ድምዳሜ አይኖርም፡፡ ስለዚህ አብም ይማልዳል፤ ወልድም ይማልዳል፤ መንፈስ ቅዱስም ይማልዳል ማለት ነው (ሎቱ ስብሐት)፡፡ በፍጹም እኛ የእነአትናቴዎስና የእነቄርሎስ ልጆች እንዲህ ብለን አናምንም የሉተር ልጆች ግን ያምናሉ:: እኛ አምላካችንን አማላጅ አንለውም:: እኛ የምናመልከው እግዚአብሔር ተማላጅ ነው:: አማላጆቻችንም ቅዱሳን ናቸው:: “ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን
የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ
ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ ክርስቶስ በእኛ እንደሚማለድ ስለክርስቶስ
መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለክርስቶስ እንለምናለን” 2ኛቆሮ 5÷18-21 የማስታረቅ አገልግሎት ወይም ምልጃ ለቅዱሳን እንደ ተሰጠ በግልጽ አስቀምጧል:: ቅዱሳን የምልጃ አገልግሎት እንደሚሰጡ በግልጽ እንረዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የባሕርይ
አምላክ ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ ሮሜ 9÷5 “ክርስቶስ በሥጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው” እንዲሁም ሮሜ 14÷10 ላይ “ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ
ወንበር ፊት እንቆማለንና” ይላል ፈራጅነቱን ሲገልጥ፡፡ ቅዱሳን በአፀደ ሥጋም በአፀደ ነፍስም የማማለድ ሥራ
እንደሚሠሩ ድውይ እንደሚፈውሱ ሙትም እንደሚያነሡ የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡፡ 1ኛ17÷22 ላይ
“እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰማ የብላቴናው ነፍስ ወደርሱ ተመለሰች ርሱም ዳነ” 2ኛ ነገ4÷35 ላይ “ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ
በሕጻኑ ላይ ተጋደመ ሕጻኑም ዐይኖቹን ከፈተ” 2ኛነገ13÷21 “ሰዎችም አንድ
ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ” ሐዋ3÷7 “…በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው በዚያን ጊዜም
ቁርጭምጭሚቱ ጸና” ይላል እናንተ ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ እየጀመራችሁ ሙሉ ታሪኩን ተመልከቱት፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም የሚል የዘንዶው ደጋፊ ካለ ደግሞ ዮሐ 1÷1 -5 ፣ ሮሜ 9÷5፣1ኛ ዮሐ 5÷20 ያንብብ::
bicha bereketih yidiresegn tsegawun yabizaleih
ReplyDelete