የካቲት
20/ 2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
በመጀመሪያ ( facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም
facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ ከዚያ ጽሑፉን ያንብቡ ቀጥለውም ጽሑፉን SHARE, COMMENT,
LIKE ያድርጉ፡-
==============================================
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውስጥ እንደ ትኋን ተጣብቀው
ከሀሊበ ጸጋዋ እየተጎነጩ በክህደት በዘረዘረ ጥፍራቸው የሚባጭሩ፤ በምንፍቅና በበለዘው ጥርሳቸው የሀሊብ ምንጮቿን የሚነክሱ የጨለማ
ልጆች (ውሉደ ጽልመት) ከላይ ስማቸውን የጠራናቸውን ሊቃውንት በመጥቀስ እየተጓዙበት ያለውን የጥፋት ጎዳና እንዳቀኑላቸው ይናገራሉ፡፡
“ዝክሪ እና ጳውሊ በብራና መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለውልሃል” እያሉ በእነዚህ ሊቃውንት ስም የሚቀልዱ “ወልድ በቅብአተ መንፈስ
ቅዱስ ከበረ” የሚሉ የካቶሊክ ቅርንጫፎች እያቆጠቆጡ ናቸው፡፡ ለዚህ ማቆጥቆጣቸው ምክንያት ደግሞ ሰይጣን ለራሱ ስራ እና ዓላማ
ማስፈጸሚያነት በአንዳንድ ገዳማት እና አድባራት ላይ ያስቀመጣቸው ምሥጢር ያልተገለጠላቸው በፈለገ አርዮስ የሚፈስሱ “መምህራን” ናቸው፡፡ በቅርቡ ልባቸውን ሞልተው፣ ደረታቸውን ነፍተው፣ ሽንጣቸውን
ገትረው፣ ዓይናቸውን አፍጥጠው፣ ጥርሳቸውን አግጥጠው “ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ቅብአትነት ከበረ፤ አብ በቀደመ መውለዱ በማኅጸነ ማርያም
ዳግመኛ ወልድን ወልዶታል” እያሉ አርዮስ “ወልድ ፍጡር” ማለቱ ስህተት እንዳልሆነ አብዝተው ይጮኸሉ፡፡ ይህንን ክህደታቸውንም “ወልደ
አብ” የሚል ስም በመስጠት መጽሐፍ እስከማሳተም እንደደረሱ ከዚህ በፊት መረጃውን አቅርበናል፡፡ ይህ መጽሐፍ እርስ በርሱ የሚጋጭ
አስተምህሮ የያዘ ከንቱ መጽሐፍ እንደሆነ ከዚህ በፊት ከ10 በላይ ትምህርቶችን አስተላልፈናል፡፡ አሁን የምንመለከተው አንዳንድ
የዚህ እምነት አስተምሮ በትክክል ሳይገባቸው ገብቶናል ስለሚሉ ወጣቶች ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች የጎንቻው መምህራቸው “ሄኖክ” በሚበርርበት
የክህደት ክንፍ የሚበርሩ ናቸው፡፡ ማስረጃ አይጠቅሱም መምህር አይጠይቁም እነርሱ በጭፍኑ ብቻ ይከራከራሉ፡፡ በተለይ ከላይ ስማቸውን የጠቀስናቸውን ሊቃውንት ለራሳቸው የክህደት
አካሄድ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በእውነት ዝክሪ እና ጳውሊ ግን “በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ” ብለዋልን?
ስለእነዚህ ሊቃውንት መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ
በጻፉት “መድሎተ አሚን” ላይ በመቅድም ገጻቸው ይናገራሉ፡፡ ሊቁ በመቅድማቸው ኹለተኛ ክፍል ላይ “ይህ የካቶሊክ ባህል ወደ ኢትዮጵያ
በምን ጊዜ እንደመጣና የኢትዮጵያ ሊቃውንት በምን ዓይነት እንደተቃወሙት የሚገልጽ ታሪክ” በማለት ጽፈዋል ይህንን ክፍል እነሆ መልካም
ንባብ!
ኢትዮጵያን ግራኝ መሀመድ በወረራት ጊዜ ዐፄ ልብነ
ድንግል ከፖርቹጊዝ መንግሥት እርዳታ ጠይቀው እርሳቸው ከሞቱ በኋላ በፖርቹጊዞች እርዳታ ግራኝ ድል ሆኖ ኢትዮጵያ ሙሉ ነጻነቷን
አግኝታ መንግሥቷን በትክክል ማቋቋሟ የታወቀ ነው፡፡
በዚህ ጊዜ ከኢትዮጵያ ተልኮ ፖርቹጊዞችን ለእርዳታ
ያመጣው ቤርሙዲዝ ከኢትዮጵያ ግዛት ገሚሱ ለፖርቹጊዝ መንግሥት ይሰጥ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ከእንግዲህ ወዲያ አቡን ከእስክንድርያ
መምጣቱ ቀርቶ ከሮም ይምጣ እኔም ለኢትዮጵያ አንደኛ መጀመሪያ ሮማዊ ጳጳስ ልሁን ብሎ ዐፄ ገላውዴዎስን ጠየቀ፡፡ ዐፄ ገላውዴዎስም
ሊቃውንቱን ሰብስበው ምን እናድርግ ብለው ጠየቁ፡፡ የኢትዮጵያ ሊቃውንትም ፍርድ በቃ ይስጡን እንከራከርና ሮማውያን ቢረቱን እንልቀቅላቸው
ብንረታቸው ይልቀቁልን አሏቸው፡፡ ንጉሡም ፈቅደው ጉባዔ ተደረገ ለኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጉባኤ ዝክሪና ጳውሊ ኾኑ፡፡
ዝክሪና ጳውሊም በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በዲማ ቅዱስ
ጊዮርጊስ አጠገብ የሚገኝ የደብረ ጽሙና ገዳም ሊቃውንት ናቸው፡፡
ኢትዮጵያውያን ሮማውያንን ሀገራችሁ ወዴት ነው ሃይማኖታችሁ
ምንድን ነው ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ ሮማውያን ሲመልሱ ሀገራችን ሮም ነው፤ ሃይማኖታችንም ኹለት ባሕርይ ኹለት ጠባይዕ አንዱ የመለኮቱ
አንዱ የትስብእቱ እንላለን፡፡ ኹለተኛም ወልድ ከአብ ያንሳል መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል እንላለን አሏቸው፡፡
ኢትዮጵያውያን ሲመልሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ
የሚል ምን አለ እስኪ አስረዱን አሏቸው፡፡
ሮማውያን ሲመልሱ እርሱው ራሱ ወልድ ደቀመዛሙርቱ
ሕልፈተ ዓለም የሚሆነው መቼ ነው ብለው ቢጠይቁት መላእክትም ቢሆኑ ወልድም ቢሆን ከአብ በቀር ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የሚያውቃት
የለም ብሏል፡፡ ስለዚህ አብ መለኮት ስለሆነ ያውቃል ወልድ መንፈስ ቅዱስ ግን መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም እንላለን እናንተ ይህን
ነገር ምን ትሉታላችሁ አሉ፡፡
አባ ዝክሪ ሲመልስ ሦስቱን አካላት አብ ወልድ መንፈስ
ቅዱስን አንድ አምላክ የምንላቸው አብን ልብ ወልድን ቃል መንፈስ ቅዱስን እስትንፋስ ብለን በአብ ልብነት ያስባሉ ያውቃሉ፤ በወልድ
ቃልነት ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንስነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ ለየራሳቸው ልብ ቃል እስትንፋስ የላቸውም በማለት ነው፡፡
ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ ያለው አንድ ሰው በልቡ አስቦት አውቆት ለመናገር ጊዜው ባለመድረሱ ሰዓት እየጠበቀለት ሰውሮ የያዘውን ነገር
ጊዜው ባለመድረሱ ምክንያት በቃሉ ሳይናገረው ቢቆይ ቢጠየቅም ዛሬ አልናገረውም ቢል አያውቅም እንደማይባል ወልድም ያችን ዕለት ያችን
ሰዓት የምትገለጽበት ጊዜው እስኪደርስ በልቤ በአብ ሰውሬ አቆያታለሁ እንጅ ዛሬ በቃልነቴ አውጥቼ አልናገራትም ማለቱ ነው እንጅ
የማያውቃት ሆኖ አይደለም፡፡ እንዲህስ ባይሆን የከዊን ስማቸውና ግብራቸው ተፋልሶ አብ ቃል፤ ወልድ ልብ በተባሉ ነበረ አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ሮማውያን መልስ አጥተው ዝም አሉ፡፡
ኹለተኛ ጥያቄ
ይቀጥላል…. ይቆየን!!!
No comments:
Post a Comment