Wednesday, July 10, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 131

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፳፯።
                    ******
በእንተ ፃዕሩ ወሞቱ ለኢየሱስ
፵፭፡ ወእምስሱ ሰዓት ጸልመ ኵሉ ዓለም እስከ ተሱዓት ሰዓት፡፡
                    ******
፵፭፡ ከቀትር እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ጨለማ ሆነ፡፡
                    ******
፵፮፡ ወጊዜ ተሱዓት ሰዓት ጸርሐ እግዚእ ኢየሱስ በቃል ዓቢይ፤
መዝ ፳፩፥፩፡፡
                    ******
፵፮፡ በዘጠኝ ሰዓት ጊዜም ጌታ አሰምቶ ተናገረ፡፡
እንዘ ይብል ኤሎሄ ኤሎሄ ኤልማስ ለማ ሰበቅታኒ ዝ ውእቱ ብሂል አምላኪየ አምላኪየ ለምንት ኀደገኒ
ኤሎሄ ኤሎሄ ያለውን አምላኪየ አለው ኤልማስ ያለውን ለምንትኑ አለው ሰበቅታኒ ያለውን ኀደገኒ ብሎ ተረጐመው አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውከኝ አለ ኃደገ ብየ ሲል በኅዱጋኑ ተገብቶ ይጸልያል።
                    ******
፵፯፡ ወሰሚዖሙ እለ ይቀውሙ ይቤሉ ኤልያስሃ ይጹውዕ ዝሰ።
                    ******
፵፯፡ ከዚያ ቁመው ያሉት ኤሎሄ ኤሎሄ ሲል ሰምተው ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ።
                    ******
፵፰፡ ወውእተ ጊዜ ሮፀ ፩ እምኔሆሙ ወነሥአ ሰፍነገ ወመልዓ ብኂአ ወአሠረ ውስተ ህለት ወአስአዘዞ ውስተ አፉሁ ወአስተዮ።
                    ******
፵፰፡ ያን ጊዜ ከእሳቸው አንዱ ፈጥኖ ሰፍነግ ወሰዶ መጣጣውን መልቶ በዘንግ አሥሮ አጠጣው።
(ሐተታ) ሰፍነግ የጁህ ባዘቶ እንደ ዓይነ በጎ ያለ ውሀ የሚያነሳ ቤት የሚጠርጉበት ነው።
                    ******
፵፱፡ ወቦ እለ ይቤሉ ኅድጉ ንርአይ ለእመ ይመጽእ ኤልያስ ያድኅኖ።
                    ******
፵፱፡ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ ተዉት እንይ ያሉ አሉ፡፡
                    ******
፶፡ ወጸርሐ እግዚእ ኢየሱስ በዓቢይ ቃል።
                    ******
፶፡ ጌታ አሰምቶ ተናገረ።
ወመጠወ ነፍሶ ወወጽአት መንፈሱ ሰቤሃ፡፡
ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡
ወመጽአ ፩ ወነሥአ ኵናተ ወረገዞ ገቦሁ ወውኅዘ ደም ወማይ፡፡
ቆመው ካሉት አንድ ሰው ጦሩን አንሥቶ ጎኑን ወጋው ውሀና ደም ሳይቀላቀል ፈሰሰ፡፡
                    ******
፶፩፡ ወተሠጠ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ አምላዕሉ እስከ ታሕቱ፡፡ ፪፡ኅፁፃን ፫፥፲፬።
                    ******
፶፩፡ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀደደ።
ወኮነ ፪ኤ ክፍለ።
ከሁለት ተከፈለ። ወመጽአ መልአክ ኅሩይ እማዕከለ ኵሎሙ መላእክት እንዘ ይእኅዝ በእዴሁ ሰይፎ ክሡተ ከመ ያጥፍዖሙ ለዓላውያን ፍጡነ ወሶበ ከልዓቶ ምሕረቱ ለክርስቶስ ዘበጦ ዝኩ መልአክ በሰይፉ ለመንጦላዕተ ምኵራብ ወሠጠጦ ወረስዮ ፪ተ እምላዕሉ እስከ ታሕቱ እንዲል። ኖራውን ሰነጠቀው።
አንድም አንዱን ዘሀ ከሁለት አደረገው።.
አድለቅለቀት ምድር።
ምድር ተናወጠ መርገመ ሥጋ ጠፋ።
ወነቅዓ ኰኵሕ።
አዕባን ተፈተቱ መርገመ ነፍስ ጠፋ።
                    ******
፶፪፡ ወተከሥቱ መቃብራት።
                    ******
፶፪፡ መቃብራት ተከፈቱ ሙስና መቃብር ጠፋ።
ወተንሥኡ ብዙኃን አብድንቲሆሙ ለጻድቃን።
የብዙ ጻድቃን በድን ማለት አምስት መቶ ሙታን ከመስቀል እግር ተነሡ።
                    ******
፶፫፡ ወቦኡ ውስተ ሀገር ቅድስት እምድኅረ ተንሥአ።
                    ******
፶፫፡ ከተነሣም በኋላ ወደ ቅድስት ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም ገቡ።
ወአስተርአይዎሙ ለብዙኃን።
ለብዙ ሰዎች ታዩዋቸው አለ ለዘመዶቻቸው ሦስቱን ቀን ወዴት ኑረው ቢሉ በደብረ ዘይት።
                    ******
፶፬፡ ወመኰንነ ፻ሰ ወእለ ምስሌሁ የዓቅብዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ርእዮሙ ውእተ ድልቅልቀ ፈርሁ ጥቀ።
                    ******
፶፬፡ የመቶ አዝማች ከእሱም ጋራ ጌታን ሲጠብቁት የዋሉት መናወጡን ማለት የተደረገውን ተአምራት ባዩ ጊዜ ፈጽመው ፈሩ፡፡
ወይቤሉ አማን ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ፡፡
በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
                    ******
፶፭፡ ወሀለዋ ህየ ብዙኃት አንስት እለ ይሬእያ እምርኁቅ ኵሎ ዘኮነ፡፡
                    ******
፶፭፡ ከዚያም የተደረገውን ሁሉ ርቀው የሚያዩ ብዙ ሴቶች ነበሩ፡፡
ወውእቶን አለ ተለዋሁ ለእግዚእ ኢየሱስ እምገሊላ።
እሳቸውም ኢየሱስን ከገሊላ የተከተሉት።
እለ ይትለአካሁ።
የሚያገለግሉት ናቸው።
                    ******
ወእማንቱ ማርያም መግደላዊት
                    ******
፶፮፡ ብዙ ሴቶችም የተባሉ ማርያም መግደላዊ ናት መግደሎን ይባላል አገሯ።
ወማርያም እመ ያዕቆብ ወእሙ ለዮሳ።
የዮሳና የያዕቆብ እናት ናት።
ወእሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ።
የዘብዴዎስ ልጆች እናት ማርያም ባውፍልያ ናት።
                    ******
ዘከመ ተቀብረ ኢየሱስ።
፶፯፡ ወመስዮ መጽአ ብእሲ ባዕል እምአርማትያስ ዘስሙ ዮሴፍ።
                    ******
፶፯፡ ሲመሽ በመሸ ጊዜ ዮሴፍ የሚባል ባለጸጋ ሰው መጣ።
ወውእቱ ይጸመዶ ለእግዚእ ኢየሱስ
ከጌታ ዘንድ ይማር ነበር።
                    ******
፶፰፡ ወሖረ ኀበ ጲላጦስ ወሰአለ ሥጋሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
                    ******
፶፰፡ ከጲላጦስ ሂዶ የጌታን ሥጋ ላውርድ ብሎ ለመነ፤
ወአዘዘ ጲላጦስ የሀብዎ።
ጲላጦስ ስጡት ብሎ አዘዘ።
                    ******
፶፱፡ ወነሢኦ ሥጋሁ ዮሴፍ ገነዞ በሰንዱናት ንጹሕ።
                    ******
፶፱፡ ዮሴፍ ሥጋውን አውርዶ በድርብ በፍታ ገነዘው።
                    ******
፷፡ ወቀበሮ ውስተ መቃብር ሐዲስ ዘሎቱ አውቀረ ውስተ ኰኵሕ
                    ******
፷፡ ለራሱ ብሎ በአሳነጸው በአዲስ መቃብር ቀበረው።
(ሐተታ) እንግዳ ሥራ እሠራላችኋለሁ ሲል።
አንድም እንደ ኤልሳዕ ገባሬ ተአምራት ነቢይ በተቀበረበት እንጂ ቢቀበር አስነሣው አንዳይሉ።
ወአንኰርኰረ ዕብነ ዓቢየ ዲበ ኆኅተ መቃብር ወኃለፈ።
ታላቅ ደንጊያ አገላብጦ መቃብሩን ገጥሞት ሄደ።
                    ******
፷፩፡ ወሀለዋ ህየ ማርያም መግደላዊት ወካልዕታሂ ማርያ ይነብራ ኀበ መቃብር።
                    ******
፷፩፡ ማርያም መግደላዊት ማርያም ባውፍልያ ከመቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር።
                    ******
፷፪፡ ወበሳኒታ እንተ ይእቲ እምድኅረ ዓርብ ተጋብኡ ሊቃነ ካህናት ወፈሪሳውያን ኅበ ጲላጦስ።
                    ******
፷፪፡ ያችም ከዓርብ ቀጥላ ናት በነጋው ቅዳሜ ፈሪሳውያንና ሊቃነ ክሀናት ወደ ጲላጦስ ተሰብስበው።
                    ******
ወይቤልዎ ተዘከርነ እግዚኦ ዘይቤ ዝኩ መስሐቲ አመ ሕያው ውእቱ አመ ሣልስት ዕለት እትነሣእ።
                    ******
፷፫፡ ያ መስሐቲ በሕይወተ ሥጋ ሳለ በሦስተኛው ቀን  እነሣለሁ ያለውን እናውቃለንና።
                    ******
፷፬፡ አዝዝ እንከ ይዕቀቡ መቃብሪሁ እስከ ሠሉስ መዋዕል ከመ ኢይምጽኡ አርዳኢሁ ወኢይሥርቅዎ ሌሊተ ወኢይበሉ ለሕዝብ ተንሥአ እምነ ሙታን።
                    ******
፷፬፡ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሌሊት ሠርቀው ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ብለው ለሕዝቡ እንዳያስተምሩ መቃብሩን እስከ ሦስት ቀን ይጠብቁ ዘንድ እዘዝ አሉት።
ወትከውን ደኃሪተ ጌጋዩ እንተ ተአኪ እምቀዳሚት።
የኋላ ስህተቱ ከቀደመው የጸና ይሆናል።
                    ******
ወይቤሎሙ ጲላጦስ ንሥኡ ሠገራተ ሑሩ ወአጽንዑ መቃብሪሁ በከመ ተአምሩ።
                    ******
፷፭፡ ጲላጦስም ጭፍራ ወስዳችሁ እንደምታውቁ አጽንታችሁ አስጠብቁ አላቸው።
                    ******
ወሖሩ ወአጽንኡ ወቀተሩ መቃብሮ።
                    ******
፷፮፡ ሂደው አጽንተው መቃብሩን ቈለፉት፡፡
ወኃተምዋ ለይእቲ ዕብን ምስለ ሠገራት።
ጭፍራውን ይዘው ቈለፉ።
(ሐተታ) በህልቀቱ ወበህልቀተ መገብቱ እንዲል ተጠራጥረዋል። እሱ እሳቸውን ጠርጥሯቸዋልና በማተሚያው ያትማል፡፡ እሳቸው እሱን ጠርጥረውታልና በማተሚያቸው ያትማሉ።
                    ******
በእንተ ትንሣኤሁ ለኢየሱስ።
ምዕራፍ ፳፰።
ወሠርከ ሰንበት ለጸቢሐ እሁድ መጽአት ማርያም መግደላዊት ወካልዕታኒ ማርያም ይርአያ መቃብረ። ማር ፲፮፥፭፡፡ ዮሐ ፳፥፲፩፡፡
፩፡ ቅዳሜ ማታ ለእሁድ አጥቢያ ማርያም መግደላዊት ሌላዪቱም ማርያም መቃብሩን ያዩ ዘንድ መጡ፡፡ ማርያም ባውፍልያ ናት።
                    ******
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
03/11/2011 ዓ.ም

Monday, July 8, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 130

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፳፯።
                    ******
፳፭፡ ወአውሥኡ ኵሉ ሕዝብ ወይቤሉ ደሙ ላዕሌነ ወላዕለ ውሉድነ፡፡
                    ******
፳፭፡ ደሙ በእኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ፤
(ሐተታ) እንዲህ ብለው የተናገሩበት አንደበታቸው የሚሸት የሚከረፋ ሁኑዋል ልጆቻቸውም ወንድ የሆነ እንደሆነ በእጁ ደም ጨብጦ በአፉ ደም ጎርሶ የሚወለድ ሁኑዋል። ሴት የሆነች እንደሆነ በተፈትሆ የምትወለድ ሁናለች።
                    ******
፳፮፡ ወእምዝ አሕየወ ሎሙ በርባንሃ።
                    ******
፳፮፡ ከዚህ በኋላ በርባንን ፈታላቸው።
ወቀሠፎ ለእግዚእ ኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ።
ጌታን ገርፎ ስቀሉ ብሎ ሰጣቸው።
(ሐተታ) ካልቀረስ በምር ደስ ይበላቸው ብሎ።
አንድም ራርተው ይተውታል መስሎት።
አንድም ወመጠውኩ ዘባንየ ለቅሥፈት ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም።
አንድም ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡናውን እየገረፈ ገሃነም አውርዶት ነበርና ለዚያ ካሳ ሊሆን፡፡
አንድም በጌታ የግፍ ድርብ ይደረግበታልና ለልማዱ የሚሰቀል አይገረፍም የሚገረፍ አይሰቀልም ነበር። እሱን ግን ገርፈው የሚሰቅሉት ነውና።
                    ******
ዘከመ ተሣለቁ በላዕለ ኢየሱስ።
፳፯፡ ወእምዝ መስተራትዓተ ሐራ ነሥእዎ ለእግዚእ ኢየሱስ እምውስተ ዓውድ ወወሰድዎ ኀበ ምኵናን። መዝ ፳፩፥፲፯። ማር ፲፭፥፲፮።
                    ******
፳፯፡ ከዚህ በኋላ ጭፍራውን የሚሠሩ የሚያቅናኑ ከአደባባይ ወደሚፈረድበት ቦታ ይዘውት ሄዱ።
(ሐተታ) ቤተ አንሳ ቤተ አይጥ የሚባሉ ሰቃይ ቈራጭ ባለወጎች በቤተ መንግሥት እንዳሉ።
ወአስተጋብኡ ኵሎ ሠርዌ ሐራ
አለቆች ጭፍራቸውን ሰበሰቡ፡፡
አንድም ኵሎ ሠርዌ ሐራ ጭፍሮች አለቆችን።
አንድም ወአስተጋብኡ ኵሎ ሠርዌ ሐራ ብለህ አናበህ ጭፍሮች ያሏቸው አለቆች ሕዝቡን ሰበሰቡ።
ወሰለብዎ አልባሲሁ።
ልብሱን ገፈፉት።
(ሐተታ) የአዳም ልጅነት እንደሄደበት ያጠይቃል።
                    ******
፳፰፡ ወአልበስዎ ከለሜዳ ዘለይ።
                    ******
፳፰፡ ቀይ ግምጃ አለበሱት። ደምህ ይፈሳል ሲሉ።
አንድም ደማችንን በአርባ ዘመን በጥጦስ ታፈሰዋለህ ሲሉ።
                    ******
፳፱፡ ወጸፈሩ ሐራ አክሊለ ዘሦክ ወአስተቀጸልዎ ዲበ ርእሱ። ዮሐ ፲፱፥፪።
                    ******
፳፱፡ ጭፍሮች የእሾህ አክሊል ታተው ደፉለት።
(ሐተታ) አነገሥንህ ብለውታልና በፍና ተሣልቆ።
አንድም ወወደዩ ጌራ መድኃኒት ዲበ ርእሱ በአክሊል ዘአስተቀጸለቶ እሙ ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ድርሳነ መድኃኔ ዓለም ሽህ ጥቃቅን ሰባ ታላላቅ እሾህ ያለው የብረት ዘውድ ነው ይላል፡፡ እንደ ምን ነው ቢሉ ነገር እንደዚህ ነው ያስ ቢሆን ኢትስብሩ ዓፅሞ ያለው በፈረሰ ነበር፡፡
ወአስተአኃዝዎ ህለተ ውስተ የማኑ።
በቀኝ እጁ ዘንግ አስያዙት አነገሥንህ ብለውታልና በፍና ተሣልቆ
አንድም ብርዓ ይላል አብነት፡፡ ብርዕ አስያዙት ሥራ ፈት ነህ ሲሉ፡፡ ጽሕፈትንማ ርእሰ ጥበባት እንጅ ይለዋል ብሎ ኃጢአታችንን በፍዳ ታጽፍብናለህ ሲያሰኛቸው ነው፡፡
ወአስተብረኩ ቅድሜሁ፡፡
ሰገዱለት፡፡
ወተሣለቁ ላዕሌሁ
ዘበቱበት፡፡
ወይቤልዎ በሀ ንጉሠ አይሁድ፤
የአይሁድ ንጉሣቸው ቢሰኛህን ጠበኛህን አያውለው አያሳድረው አሉት፡፡ ከእነሱ ሌላ ቢሰኛ ጠበኛ አለውን አያውለን አያሳድረን ሲያሰኛቸው ነው።
                    ******
፴፡ ወይወርቁ ላዕሌሁ።
                    ******
፴፡ በፊቱ ተፉበት።
(ሐተታ) እንዳለፈው።
ወነሥኡ ህለተ ወኰርዕዎ ርእሶ።
ያስያዙትን ዘንግ ተቀብለው ራሱን መቱት፡፡
(ሐተታ) እንዳለፈው፡፡
                    ******
፴፩፡ ወተሣሊቆሙ ላዕሌሁ ሰለብዎ ውእተ ከለሜዳ ዘለይ፡፡
                    ******
፴፩፡ ከዘበቱበት በኋላ ያለበሱትን ቀይ ግምጃ ገፈፉት።
ወአልበስዎ አልባሲሁ።
የጥንት ልብሱን አለበሱት የአዳም ልጅነት እንደተመለሰለት ያጠይቃል።

ወወሰድዎ ይስቅልዎ።
ሊሰቅሉት ይዘውት ሄዱ።
                    ******
ወእንዘ ይወጽኡ ረከቡ ብእሴ ቀሬናዊ ዘስሙ ሰምዖን እትወቶ እምሐቅል። ማር ፲፭፥፳፩፡፡ ሉቃ ፳፫፥፳፮።
                    ******
፴፪፡ ሊሰቅሉት ይዘውት ሲሄዱ ስምዖን የሚባል የቀራንዮ ሰው ከተሠወረበት ሲመለስ አገኙ፤
ወአበጥዎ ይፁር መስቀሎ፡፡
መስቀሉን ይሸከም ዘንድ ጎተቱት
(ሐተታ) ነገር ፈርቶ ተሰውሮ ውሏል ነገር ተፈጽሟል ብሎ ሲወጣ አገኙት አንተም የእሱ ወገን ነህ መስቀሉን ተሸከም ብለው አሸክመውታል፡፡ ምሥጢሩ ግን ጌታ ከበረከተ መስቀሉ እንዳሳተፈው ያጠይቃል፡፡
                    ******
ወበጺሖሙ ብሔረ ዘስሙ ጎልጎታ ዘበትርጓሜሁ ቀራንዮ። ማር ፲፭፥፳፪። ሉቃ ፳፫፥፴፫፡፡ ዮሐ ፲፱፥፲፯።
                    ******
፴፫፡ በአንዱ ልሳን ቀራንዮ ወደሚሉት ጎልጎታ በደረሱ ጊዜ።
                    ******
፴፬፡ ወወሀብዎ ይስተይ ወይነ ወሐሞተ ድሙረ
                    ******
፴፬፡ ሐሞት የተቀላቀለበት ወይን ይጠጣ ዘንድ ሰጡት፡፡
ወጥዒሞ ዓበየ ሰትየ።
ቀምሶ አልጠጣም አለ።
                    ******
ዘከመ ተሰቅለ አ.የሱስ
፴፭፡ ወእምዝ ሰቀልዎ፡፡ ማር ፲፭፥፳፬፡፡ ሉቃ ፳፫፥፴፬። ዮሐ ፲፱፥፳፫፡፡ መዝ ፳፩፥፲፱።
                    ******
፴፭፡ ከዚህ በኋላ ሰቀሉት።
ወተካፈሉ አልባሲሁ እንዘ ይትዓፀዉ።
ልብሱን በዕፃ ተካፈሉ፡፡ በከመ ጽሑፍ ወተካፈሉ አልባስየ ለርእሶሙ ወተዓፀዉ ዲበ አራዝየ ተብሎ በነቢይ እንደ ተጻፈ፡፡
                    ******
፴፮፡ ወነበሩ የዓቅብዎ ህየ
                    ******
፴፮፡ ሲጠብቁት ዋሉ፡፡
                    ******
፴፯፡ ወአንበሩ መልዕልተ ርእሱ ጽሒፎሙ መጽሐፈ ጌጋዩ ዘይብል ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሦሙ ለአይሁድ፡፡
                    ******
፴፯፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሣቸው ነው የሚል በደሉን የሚነግር ደብዳቤ ከራሱ በላይ ከመስቀሉ ትርፍ ጠርቀው ተውት፣
                    ******
፴፰፡ ወእምዝ ሰቀሉ ምስሌሁ ፪ተ ፈያተ፡፡
                    ******
፴፰፡ ከዚህ በኋላ ሁለት ወንበዶች ከእሱ ጋራ ሰቀሉ፡፡
አሐደ በየማኑ
አንዱን በቀኙ
ወአሐደ በጸጋሙ
አንዱን በግራው፡፡ አነገሥንህ ብለውታልና በፍና ተሣልቆ
(ሐተታ) ቀኝ አዝማችና  ግራ አዝማች ቢትወደድ ግራ ቢትወደድ ሾምንልህ ሲሉ፡፡
አንድም ለማሳሳት በቀኝ በግራ የመጣው ያ ምንድ ነው፤ ወንበዴ ይሉታል፡፡ ያሳ የመከከለኛው ይላል ያስ ከዚህን ልዩ ነው ለማለት፡፡
አንድም ተኆለቈ ምስለ ጊጉያን ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም፤ ይህንም ሊቁ ከመ ይደምረነ ምስለ ነፍሰ ጻድቃን ብሎ ተርጕሞታል ምሥጢሩን ግን እኛን ኃጥአንን በግራ ታቆመናለህ ሲያሰኛቸው ነው፣
                    ******
፴፱፡ ወእለሂ የኃልፉ ይጸርፉ ላዕሌሁ እንዘ የሐውሱ ርእሶሙ
                    ******
፴፱፡ የሚያልፉ የሚያገድሙት ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበር፡፡
                    ******
፵፡ ወይብሉ ኦ ዘይነሥቶ ለቤተ መቅደስ ወየሐንፆ በሣልስት ዕለት አድኅን ርእሰከ። ዮሐ ፪፥፲፱፡፡
                    ******
፵፡ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስተኛው ቀን እሰራዋለሁ የምትል ራስክን አድን እያሉ።
እመሰ አማን ወልደ እግዚአብሔር አንተ ረድ እመስቀልከ
የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ከመስቀልህ ውረድ።
                    ******
፵፩፡ ወከማሁ ሊቃነ ካህናት ይሣለቁ ምስለ ጸሐፍት ወሊቃናት።
                    ******
፵፩፡ እኒያ እንደሰደቡት ሊቃነ ካህናትም ከጸሐፍትና ከአለቆች
ጋራ ሰደቡት።
                    ******
፵፪፡ እንዘ ይብሉ ባዕደ ያድኅን ወርእሶ ኢይክል አድኅኖ፡፡ ማቴ ፪፥፲፰፡፡
                    ******
፵፪፡ ሌላውን ያድናል ራሱን ማዳን አይቻለውም እያሉ።
እመሰ ንጉሠ እስራኤል ውእቱ ለይረድኬ ይእዜ እምነ መስቀሉ ንርአይ ወንእመን ቦቱ።
የእስራኤልስ ንጉሥ ከሆነ ከመስቀሉ ይውረድና አይተን እንመንበት።
(ሐተታ) ወርዶም ቢሆን ፈርቶ ነው ባሉ ነበር እንጂ ባላመኑትም ነበር፡፡ ሶበሰ ወረደ እግዚእነ እምነ መስቀሉ እመርሀ ከመ ውእቱ ፈርሀ እሞት እንዲል፡፡
                    ******
፵፫፡ እመሂ ተአመነ በእግዚአብሔር ናሁ ይእዜ ያድኅኖ። መዝ ፳፩፥፰።
                    ******
፵፫፡ በእግዚአብሔር ከታመነ ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ እነሆ ዛሬ ያድነው።
አመ ይፈቅዶ።
ስንኳን ይወልደው ይወደው እንደሆነ።
እስመ ይብል ወልደ እግዚአብሔር አነ።
የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ይላልና።
                    ******
ወከማሁ ፈያትኒ እለ ተሰቅሉ ምስሌሁ ይዘነጕግዎ፡፡
                    ******
፵፬፡ እነዚያ እንደሰደቡት፤ ከእሱ ጋራ የተሰቀሉ ወምበዶችም ሰደቡት፤ ፈያታይ ዘየማንም ቢሉ ፀሐይን አይቶ እስኪመለስ ድረስ ጥቂት ጥቂት ያደራርግ ነበር።
                    ******
በእንተ ፃዕሩ ወሞቱ ለኢየሱስ
፵፭፡ ወእምስሱ ሰዓት ጸልመ ኵሉ ዓለም እስከ ተሱዓት ሰዓት፡፡
፵፭፡ ከቀትር እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ጨለማ ሆነ፡፡
                    ******
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
02/11/2011 ዓ.ም