====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፳፯።
******
በእንተ ፃዕሩ ወሞቱ ለኢየሱስ
፵፭፡ ወእምስሱ ሰዓት ጸልመ ኵሉ ዓለም እስከ ተሱዓት ሰዓት፡፡
******
፵፭፡ ከቀትር እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ጨለማ ሆነ፡፡
******
፵፮፡ ወጊዜ ተሱዓት ሰዓት ጸርሐ እግዚእ ኢየሱስ በቃል ዓቢይ፤
መዝ ፳፩፥፩፡፡
******
፵፮፡ በዘጠኝ ሰዓት ጊዜም ጌታ አሰምቶ ተናገረ፡፡
እንዘ ይብል ኤሎሄ ኤሎሄ ኤልማስ ለማ ሰበቅታኒ ዝ ውእቱ ብሂል
አምላኪየ አምላኪየ ለምንት ኀደገኒ
ኤሎሄ ኤሎሄ ያለውን አምላኪየ አለው ኤልማስ ያለውን ለምንትኑ
አለው ሰበቅታኒ ያለውን ኀደገኒ ብሎ ተረጐመው አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውከኝ አለ ኃደገ ብየ ሲል በኅዱጋኑ ተገብቶ ይጸልያል።
******
፵፯፡ ወሰሚዖሙ እለ ይቀውሙ ይቤሉ ኤልያስሃ ይጹውዕ ዝሰ።
******
፵፯፡ ከዚያ ቁመው ያሉት ኤሎሄ ኤሎሄ ሲል ሰምተው ይህስ ኤልያስን
ይጠራል አሉ።
******
፵፰፡ ወውእተ ጊዜ ሮፀ ፩ እምኔሆሙ ወነሥአ ሰፍነገ ወመልዓ
ብኂአ ወአሠረ ውስተ ህለት ወአስአዘዞ ውስተ አፉሁ ወአስተዮ።
******
፵፰፡ ያን ጊዜ ከእሳቸው አንዱ ፈጥኖ ሰፍነግ ወሰዶ መጣጣውን
መልቶ በዘንግ አሥሮ አጠጣው።
(ሐተታ) ሰፍነግ የጁህ ባዘቶ እንደ ዓይነ በጎ ያለ ውሀ የሚያነሳ
ቤት የሚጠርጉበት ነው።
******
፵፱፡ ወቦ እለ ይቤሉ ኅድጉ ንርአይ ለእመ ይመጽእ ኤልያስ ያድኅኖ።
******
፵፱፡ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ ተዉት እንይ ያሉ አሉ፡፡
******
፶፡ ወጸርሐ እግዚእ ኢየሱስ በዓቢይ ቃል።
******
፶፡ ጌታ አሰምቶ ተናገረ።
ወመጠወ ነፍሶ ወወጽአት መንፈሱ ሰቤሃ፡፡
ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡
ወመጽአ ፩ ወነሥአ ኵናተ ወረገዞ ገቦሁ ወውኅዘ ደም ወማይ፡፡
ቆመው ካሉት አንድ ሰው ጦሩን አንሥቶ ጎኑን ወጋው ውሀና ደም
ሳይቀላቀል ፈሰሰ፡፡
******
፶፩፡ ወተሠጠ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ አምላዕሉ እስከ ታሕቱ፡፡
፪፡ኅፁፃን ፫፥፲፬።
******
፶፩፡ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀደደ።
ወኮነ ፪ኤ ክፍለ።
ከሁለት ተከፈለ። ወመጽአ መልአክ ኅሩይ እማዕከለ ኵሎሙ መላእክት
እንዘ ይእኅዝ በእዴሁ ሰይፎ ክሡተ ከመ ያጥፍዖሙ ለዓላውያን ፍጡነ ወሶበ ከልዓቶ ምሕረቱ ለክርስቶስ ዘበጦ ዝኩ መልአክ በሰይፉ
ለመንጦላዕተ ምኵራብ ወሠጠጦ ወረስዮ ፪ተ እምላዕሉ እስከ ታሕቱ እንዲል። ኖራውን ሰነጠቀው።
አንድም አንዱን ዘሀ ከሁለት አደረገው።.
አድለቅለቀት ምድር።
ምድር ተናወጠ መርገመ ሥጋ ጠፋ።
ወነቅዓ ኰኵሕ።
አዕባን ተፈተቱ መርገመ ነፍስ ጠፋ።
******
፶፪፡ ወተከሥቱ መቃብራት።
******
፶፪፡ መቃብራት ተከፈቱ ሙስና መቃብር ጠፋ።
ወተንሥኡ ብዙኃን አብድንቲሆሙ ለጻድቃን።
የብዙ ጻድቃን በድን ማለት አምስት መቶ ሙታን ከመስቀል እግር
ተነሡ።
******
፶፫፡ ወቦኡ ውስተ ሀገር ቅድስት እምድኅረ ተንሥአ።
******
፶፫፡ ከተነሣም በኋላ ወደ ቅድስት ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም ገቡ።
ወአስተርአይዎሙ ለብዙኃን።
ለብዙ ሰዎች ታዩዋቸው አለ ለዘመዶቻቸው ሦስቱን ቀን ወዴት ኑረው
ቢሉ በደብረ ዘይት።
******
፶፬፡ ወመኰንነ ፻ሰ ወእለ ምስሌሁ የዓቅብዎ ለእግዚእ ኢየሱስ
ርእዮሙ ውእተ ድልቅልቀ ፈርሁ ጥቀ።
******
፶፬፡ የመቶ አዝማች ከእሱም ጋራ ጌታን ሲጠብቁት የዋሉት መናወጡን
ማለት የተደረገውን ተአምራት ባዩ ጊዜ ፈጽመው ፈሩ፡፡
ወይቤሉ አማን ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ፡፡
በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡
******
፶፭፡ ወሀለዋ ህየ ብዙኃት አንስት እለ ይሬእያ እምርኁቅ ኵሎ
ዘኮነ፡፡
******
፶፭፡ ከዚያም የተደረገውን ሁሉ ርቀው የሚያዩ ብዙ ሴቶች ነበሩ፡፡
ወውእቶን አለ ተለዋሁ ለእግዚእ ኢየሱስ እምገሊላ።
እሳቸውም ኢየሱስን ከገሊላ የተከተሉት።
እለ ይትለአካሁ።
የሚያገለግሉት ናቸው።
******
ወእማንቱ ማርያም መግደላዊት
******
፶፮፡ ብዙ ሴቶችም የተባሉ ማርያም መግደላዊ ናት መግደሎን ይባላል
አገሯ።
ወማርያም እመ ያዕቆብ ወእሙ ለዮሳ።
የዮሳና የያዕቆብ እናት ናት።
ወእሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ።
የዘብዴዎስ ልጆች እናት ማርያም ባውፍልያ ናት።
******
ዘከመ ተቀብረ ኢየሱስ።
፶፯፡ ወመስዮ መጽአ ብእሲ ባዕል እምአርማትያስ ዘስሙ ዮሴፍ።
******
፶፯፡ ሲመሽ በመሸ ጊዜ ዮሴፍ የሚባል ባለጸጋ ሰው መጣ።
ወውእቱ ይጸመዶ ለእግዚእ ኢየሱስ
ከጌታ ዘንድ ይማር ነበር።
******
፶፰፡ ወሖረ ኀበ ጲላጦስ ወሰአለ ሥጋሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
******
፶፰፡ ከጲላጦስ ሂዶ የጌታን ሥጋ ላውርድ ብሎ ለመነ፤
ወአዘዘ ጲላጦስ የሀብዎ።
ጲላጦስ ስጡት ብሎ አዘዘ።
******
፶፱፡ ወነሢኦ ሥጋሁ ዮሴፍ ገነዞ በሰንዱናት ንጹሕ።
******
፶፱፡ ዮሴፍ ሥጋውን አውርዶ በድርብ በፍታ ገነዘው።
******
፷፡ ወቀበሮ ውስተ መቃብር ሐዲስ ዘሎቱ አውቀረ ውስተ ኰኵሕ
******
፷፡ ለራሱ ብሎ በአሳነጸው በአዲስ መቃብር ቀበረው።
(ሐተታ) እንግዳ ሥራ እሠራላችኋለሁ ሲል።
አንድም እንደ ኤልሳዕ ገባሬ ተአምራት ነቢይ በተቀበረበት እንጂ
ቢቀበር አስነሣው አንዳይሉ።
ወአንኰርኰረ ዕብነ ዓቢየ ዲበ ኆኅተ መቃብር ወኃለፈ።
ታላቅ ደንጊያ አገላብጦ መቃብሩን ገጥሞት ሄደ።
******
፷፩፡ ወሀለዋ ህየ ማርያም መግደላዊት ወካልዕታሂ ማርያ ይነብራ
ኀበ መቃብር።
******
፷፩፡ ማርያም መግደላዊት ማርያም ባውፍልያ ከመቃብሩ ፊት ለፊት
ተቀምጠው ነበር።
******
፷፪፡ ወበሳኒታ እንተ ይእቲ እምድኅረ ዓርብ ተጋብኡ ሊቃነ ካህናት
ወፈሪሳውያን ኅበ ጲላጦስ።
******
፷፪፡ ያችም ከዓርብ ቀጥላ ናት በነጋው ቅዳሜ ፈሪሳውያንና ሊቃነ
ክሀናት ወደ ጲላጦስ ተሰብስበው።
******
ወይቤልዎ ተዘከርነ እግዚኦ ዘይቤ ዝኩ መስሐቲ አመ ሕያው ውእቱ
አመ ሣልስት ዕለት እትነሣእ።
******
፷፫፡ ያ መስሐቲ በሕይወተ ሥጋ ሳለ በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ ያለውን እናውቃለንና።
******
፷፬፡ አዝዝ እንከ ይዕቀቡ መቃብሪሁ እስከ ሠሉስ መዋዕል ከመ
ኢይምጽኡ አርዳኢሁ ወኢይሥርቅዎ ሌሊተ ወኢይበሉ ለሕዝብ ተንሥአ እምነ ሙታን።
******
፷፬፡ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሌሊት ሠርቀው ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
ብለው ለሕዝቡ እንዳያስተምሩ መቃብሩን እስከ ሦስት ቀን ይጠብቁ ዘንድ እዘዝ አሉት።
ወትከውን ደኃሪተ ጌጋዩ እንተ ተአኪ እምቀዳሚት።
የኋላ ስህተቱ ከቀደመው የጸና ይሆናል።
******
ወይቤሎሙ ጲላጦስ ንሥኡ ሠገራተ ሑሩ ወአጽንዑ መቃብሪሁ በከመ
ተአምሩ።
******
፷፭፡ ጲላጦስም ጭፍራ ወስዳችሁ እንደምታውቁ አጽንታችሁ አስጠብቁ
አላቸው።
******
ወሖሩ ወአጽንኡ ወቀተሩ መቃብሮ።
******
፷፮፡ ሂደው አጽንተው መቃብሩን ቈለፉት፡፡
ወኃተምዋ ለይእቲ ዕብን ምስለ ሠገራት።
ጭፍራውን ይዘው ቈለፉ።
(ሐተታ) በህልቀቱ ወበህልቀተ መገብቱ እንዲል ተጠራጥረዋል።
እሱ እሳቸውን ጠርጥሯቸዋልና በማተሚያው ያትማል፡፡ እሳቸው እሱን ጠርጥረውታልና በማተሚያቸው ያትማሉ።
******
በእንተ ትንሣኤሁ ለኢየሱስ።
ምዕራፍ ፳፰።
ወሠርከ ሰንበት ለጸቢሐ እሁድ መጽአት ማርያም መግደላዊት ወካልዕታኒ ማርያም ይርአያ መቃብረ። ማር ፲፮፥፭፡፡ ዮሐ ፳፥፲፩፡፡
፩፡ ቅዳሜ ማታ ለእሁድ አጥቢያ ማርያም መግደላዊት ሌላዪቱም ማርያም መቃብሩን ያዩ ዘንድ መጡ፡፡ ማርያም ባውፍልያ ናት።
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
03/11/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment