Tuesday, February 26, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 19


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ ፩።
                  ******
፲፪፡ ወእምድኅረ ፍልሰተ ባቢሎን ኢኮንያንኒ ወለደ ሰላትያልሃ።
                  ******
፲፪፡ የኢየሩሳሌም ሰዎች ተማርከው ባቢሎን ከወረዱ በኋላም ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ። ሐተታ ምነዋ ኢየዓርግ ብእሲ እምውስተ ዘርኡ ዘይነብር ዲበ መንበሩ ይል የለምን ቢሉ። አይነግሥም አለ እንጂ አይወለድም አለ። ያውስ ቢሆን አይነግሥም ያለው ሴዴቅያስ ኢኮንያንን ነው እንጂ ኤልያቄም ኢኮንያንን ነውን። ወሰላትያልኒ ወለደ ዘሩባቤልሃ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፡፡
                  ******
፲፫፡ ወዘሩባቤልኒ ወለደ አብዩድሃ፡፡
፲፫፡ ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ።
                  ******
ወአብዩድኒ ወለደ ኤልያቄምሃ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ።
ወኤልያቄምኒ ወለደ አዛርሃ።
ኤልያቄምም አዛርን ወለደ።
                  ******
፲፬፡ ወአዛርኒ ወለደ ሳዶቅሃ።
፲፬፡ አዛርም ሳዶቅን ወለደ።
                  ******
ወሳዶቅኒ ወለደ አኪንሃ።
ሳዳዶቅም አኪንን ወለደ።
ወአኪንኒ ወለደ ኤልዩድሃ።
አኪንም ኤልዩድን  ወለደ።
                  ******
፲፭፡ ወኤልዩድኒ ወለደ አልዓዛርሃ፡፡
፲፭፡ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፡፡
                  ******
ወአልዓዛርኒ ወለደ ማትያንሃ አልዓዛርም ማትያንን ወለደ፡፡
ወማትያንኒ ወለደ ያዕቆብሃ።
ማትያንም ያዕቆብን  ወለደ።
                  ******
፲፮፡ ወያዕቆብኒ ወለደ ዮሴፍሃ ፈኃሪሃ ለማርያም እንተ እምኔሃ ተወልደ እግዚእ ኢየሱስ ዘተብህለ ክርስቶስ።
                  ******
፲፮፡ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስ ከስዋ የተወለደ የእመቤታችን እጮኛ የሚሆን ዓቃቤሃ ተለአኪሃ አገልጋይዋ ጠባቂዋ የሚሆን ዮሴፍን ወለደ፡፡ መገናኛው ጉንዱ አልዓዛር ነው አልአዛር ማትያንንና ቅስራን ይወልዳል ማትያን ያዕቆብን ያዕቆብ ዮሴፍን ይወልዳል ቅስራ ኢያቄምን ኢያቄም እመቤታችንን በሀገራቸው ሴትና ወንድ አቀላቅሎ መቊጠር የለምና ሥርዓት አፈረሰ ይሉኛል ብሎ በዮሴፍ አንጻር ቈጠረ፡፡ እስዋንም እንዳትቀር በቅጽል አመጣት፡፡ ሐተታ በ፫ ቤት እንድትታጭ ማድረጉ ስለ ምን ቢሉ በልማድ፡፡ አዋልደ ሰለጳድ ከሙሴ ዘንድ ሄደው አባታችን የሞተ በበደሉ ነው እኛ ከነገር አልገባንምና ርስት አካፍለን ስሙን እናጸራው አሉት፡፡ ወደ አግዚአብሔር ቢያመለክት ርቱዓ ይቤላ አዋልደ ሰለጳድ ሀቦን መክፈልቶን ማዕከለ አኃዊሆን  አለው። እስራኤል ይኸነን ሰምተው ሴት የያዘችው ነገር ከሁሉ ይደርሳል ከእንግዴህ ወዲህ ርስት ከርስት ትውልድ ከትውልድ እንደተፋለሰ ዕወቅ አሉት፡፡ ሁለተኛ አመለከተ። አስተዋስቦን ዘእምቅሩቦን ባባታቸው ወገን በሶስት በሶስት ቤት እየተጋቡ እንዲወርሱ አድርግ ብሎታልና በነዚያ ልማድ።
አንድም ፄዋዌ ቢጸናባቸው ወንዱ ለሴቲቱ ሴቲቱ ለወንዱ የማያዝኑ ሁነዋል በተዘምዶተ ሥጋ ላይ የግቢ ተዘምዶ የተጨመረ እንደሆነ ጥሏት አይሄድም ያዝንላታል ብለው የሚያጋቧቸው ሁነዋልና በዚያ ልማድ በዚያስ ላይ እንድትታጭ ማድረጉ ስለ ምን ቢሉ፡፡ ኃይል አርያማዊት ባሏት ነባርና ወንድ ከወንድ ተገኘ ባሉ ነበርና ከመ በብሂሎቱ ፍሕርተ ብእሲ ያግኅድ ከመ እግዝአትነ ማርያም በአማን ብእሲት ይእቲ እንዲል፡፡
አንድም ፅንስን ከአጋንንት ለማሳሳት አውቀው ቢሆን ብዙ ፅንስ ባበላሹ ነበርና።
አንድም መስተመይናን ዝሁላነ አእምሮ አይሁድ ሰብሳብ ርኩስ ይላሉና። ንጹሕ እንደሆነ ለማጠየቅ።
አንድም በመከራዋ ጊዜ ሊከተላት ከርስት ገብቶ ሊቆጠርላት ከውግረት ሊያድናት። ዮሴፍ ምክንያት ባይኖራት በድንጊያ ወግረው በገደሏት ነበርና። ከፅዕለትም ሊያድናት ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለ፩ ብእሲ ወይብላሁ እክለ ዚአነ ንሴሰይ ወልብሰ ዚአነ ንትዔረዝ ዳዕሙ ይሰመይ ስምከ በላዕሌነ ወአኅድገነ ዘንተ ፅዕለተ እንዲል። ይህንም ፪ ሊቃውንት አመሩ ፈቃደ ዮሴፍ ወሠለስቱ ሊቃውንት አመሩ ፈቃደ ሥላሴ ይላል። ሁለቱ ሊቃውንት የተባሉ ዮሴፍ ለጊዜው አገባለሁ መስሎት ነበር ብለው የጻፉ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ያዕቆብ ዘሮሃ ናቸው። ፫ቱ ሊቃውንት የተባሉ ሥላሴ ንጽሕናውን ባወቁ አስጠብቀውታል ብለው የጻፉ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ዮሐንስ አፈወርቅ ናቸው። ዘተብለ ክርስቶስ አለ ይህም ስም ብቻ የትስብእት ብቻ የመለኮት አይደለም። ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢሆን የወጣለት ስም ነው እንጂ ወእነግር አነሂ ከመ ኢመፍትው እስምዮ ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእንበለ ትስብእት፤ ወኢ ለትስብእት ዘእንበለ መለኮት ክርስቶስሃ ይሰመይ ወእምቅድመ ትሥጉት አልቦ ዘይሰምዮ በዝንቱ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ እንዲል፡፡ በዝንቱ ስም ተሰምዩ ነቢያት ቅቡዓነ እስመ ስመ ክርስቶስ ይትበሃል ላዕለ ብዙኅ ፆታ ከመ ነገሥተ እስራኤል ወካህናቲሆሙ ከመ አሮን ወዳዊት ወዘኃረዮሂ ከመ ሥርዓተ ቂሮስ ውእቱ ይላልሳ ቢሉ። ይኽንም እንጂ ወተቀበዖሰ በመንፈስ ከመ ካህናተ ሐዲስ ውእቱ። ወላዕለ ዘተወልደ እምእግዝእትነ ማርያም ይትበሀል እንበይነ ተዋሕዶ ኮነ ለመለኮት በእንተ ዘተሠገወ እምድንግል ህየንተ ቅብዓተ ቅብዕ ባለው አፍርሶ ታል። እንዲህ ከሆነ ማን ሲያይ ተናግሮታል ቢሉ አንዱን ሲያይ። ገብርኤል ስሙ ዘአምኃ ለማርያም ዘበትርጓሜሁ አምላክ ውእቱ እንዲል። ኤልን ሲያይ። ይህም አምላክ ሰው ቢሆን የወጣለት ስም ነው። ወዝ ስም ዘውእቱ ክርስቶስ ወፍካሬሁ ቅብዓት ምስለ አምጣነ ትስብእቱ ረከቦ ለዋህድ እንዲል። ከበረ መባሉም በሥጋ ነው። ወቅብዓቱሰ ዘተወክፋ በትስብእቱ ይእቲ ወኢኮነ ቅብዓቱ አምሳለ ቅቡዓን እስመ እለ ይትቀብዑ ይፈቅዱ ቀሪበ ኀቤሁ ለከዊነ ወልድና ውእቱሰ አምላክ ውእቱ በጠባይዒሁ ዘአንበለ ፈቂድ እንዲል፡፡ ቦ አለ ይቤሉ እምቅድመ ተዋሕይ ወቦ እለ ይቤሉ እምድኅረ ተዋሕዶ እንዲል። ወገባሪሁሰ ለውእቱ ሥጋ መንፈስ ቅዱስ እስመ ውእቱ ቀብዖ ወተዋሕደ ቦቱ አምላክ ቃል ያለውን ይዘው ተቀብቶ ተዋሐደ የሚሉ አሉ፡፡ ተሠጊዎ ነሥአ ቅብዓተ በዘተሰብአ ተቀብዓ ያለውን ይዘው ሰው ሁኖ ተቀብቶ ተዋሐደ የሚሉ አሉ። ነገር ግን እንዲህ አይደለም ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ  ነው። ከመ ቅፅበተ ዓይን። እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ተቀብዓ ቃል በሥጋሁ ወእምአመ ኮነ ቃል ሥጋ አሜሃ አስተርአየ በመንፈስ ቅዱስ እንዲል።
                  ******
፲፯፡ ወኵሎንኬ ትውልድ እምአብ ርሃሞ እስከ ዳዊት ፲ወ፬ቱ፡፡
፲፯፡ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ ነው።
                  ******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
19/06/2011 ዓ.ም

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 18


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ ፩።
                  ******
፲፩፡ ወኢዮስያስኒ ወለደ ኢኮንያንሃ ወአኃዊሁ አመ ፍልሰተ ባቢሎን፡፡
                  ******
፲፩፡ የባቢሎን ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም በዘመቱ ጊዜ የኢየሩላሌም ሰዎች ተማርከው ወደ ባቢሎን በወረዱ ጊዜ ኢዮስያስም ኢኮንያንን ወንድሞቹን ወለደ፡፡ ሐተታ ወንጌላዊ ስቶን ዘንግቶ የልጅ ልጁን ልጁ ብሎ አጎቶቹን ወንድሞቹ ብሎ እንደነገሠ ጊዜ የተደረገውን ለልደቱ ሰጥቶ ተናገረ ቢሉ ስቶም ዘንግቶም አይደለ፡፡ ልማድ ይዞ ነው እንጂ የልጅ ልጁን ልጁ አለ ልማድ ይዞ፡፡ ያዕቆብ ከላባ ኮብልሎ ሚስቶቹን ልጆቹን ይዞ በመጣ ጊዜ ላባ ሦስት ቀን የሄደውን አንድ ቀን ገሥግሦ ደርሶ ለምንት ትሰርቀኒ ደቂቅየ ወአዋልድየ ከመ ዘበኵናት ፄወወ ወሚመ ኢይደልወኒኑ አስዓም ደቂቅየ ወአዋልድየ ብሎታል፡፡ አጎቶቹንም ወንድሞቹ አለ ልማድ ይዞ የአብርሃም ቤተሰቦችና የሎጥ ቤተሰቦች በሣር በውኃ ምክንያት ቢጣሉ ለምንት ንትዔመፅ እንዘ አኃው ንሕነ በበይናቲነ ለእመ አነ የማን ሔር አንተ ፀጋመ ወለእመ ፀጋም አነ ሑር አንተ የማነ ብሎታል፡፡
እንደ ነገሠ የተደረገውን ለልደቱ ሰጥቶ ተናገረ። ይህንም ልማድ ይዞ ነው፡፡ ደቂቅከ ይነብሩ ፈላስያነ ብሔሩ ነኪር ወይቀንይዎሙ ግብጽ ፬ተ ፻ተ ዓመተ እንዳለ፡፡ በግብጽ የሚኖሩት ሁለት መቶ ዐሥራ አምስት ዘመን ሲሆን በከነዓን የሚኖሩትን ደርቦ ስደቱን ከሰሙት ብሎ እንደተናገረ። አሁንም ፄዋዌውን ከሰሙት ብሎ እንደ ነገሠ ጊዜ የተደረገውን ለልደቱ ሰጥቶ ተናገረ።
ታሪክ ኢዮስያስ በነገሠ ባሥራ ሦስት ዓመት ኤልያቄም ኢኮንያንን ይወልዳል። በዚህ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ይህ ልጅ በነገሠ ጊዜ ፄዋዌ ይደረጋል ብሎ ትንቢት ተናግሯል፡፡ የኢዮስያስ መላ ዘመነ መንግሥቴ ሠላሳ አንድ ነው። ኢኮንያን በተወለደ ባሥራ ስምንት ኢዮስያስ በነገሠ በሠላሳ አንድ ዓመት ፈርዖን ኒካዑ ዘመተ፡፡ ኒካዑ ማለት አንካሳ ማለት ነው። ስለ ምን ዘመተ ቢሉ ንጉሠ በብነግን ለመውጋት።
አንድም መንግሥት ለማዳረስ፡፡ ከመ ያብጽሕ እዴሁ ላዕለ ፈለገ አፍራጢን እንዲል፡፡ ቀድሞ የሀገራችን ነገሥታት መንግሥት ለማዳረስ አኵሱም ይወጡ እንደነበረ መጥቶ ሰፈረ። ንጉሠ እስራኤል ካንት ፀብ የለኝምና መንገድ ሰጠኝ አለው። ለሕዝቡ ቢነግራቸው እኛስ ሀገራችንን የአሕዛብ መገሥገሻ አናደርጋትም አሉት። አይሆንም በሌላ መንገድ ሂድ አለው፡፡ እንግዲያውማ የመጣሁበትን ሳላደርግ የምመለስ ነኝ ብሎ ኃይለኛ ንጉሥ ነውና ተጋፍቶ ሄደ፡፡ ኢዮስያስም ሰልፎ ቆየው ኢዮስያስ በነፍጥ ተመቶ ወደቀ አስከሬናቸውን ይዘው ወደ አምባ ተጠጉ፡፡ እሱም ፀብ የለውምና አልፎ ሄደ አምባ ገብተው ኢዮስያስን ቀብረው ልጁን ዮአክስን አንግሠው ተቀመጡ፡፡ ንጉሠ በብነግን ወግቶ ሦስት ወር ኑሮ ግብሩን ተገብሮ ወደ ኢየሩሳሌም ቢመለስ አገሪቱን ጫ ብላ አገኛት፡፡ የዚህች ሀገር ኃያላን እንደ ቀትር ንብ ይናደፉ ነበረ ወዴት ሄደዋል ብሎ ጠየቀ፡፡
አንድም የቀሩት መጥን ሲያገቡልኝ እነዚህ የማያገቡልኝ በምን ምክንያት ነው ብሎ ጠየቀ። አንድም የዚች አገር ንጉሥ ተመቶ ነበር አለን ሞተ ብሎ ጠየቀ። እሱማ ሙቶ አምባ ገብተው እሱን ቀብረው ልጁን ዮአክስን አንግሠው ተቀምጠዋል ብለው ነገሩት። በሀገራቸው ሥርዓት ፈሊጥ የለም የገደለ ያንግሥ የዘመተ ይመለስ አይሉም ብሎ አምባውን ሰብሮ ዮአክስን አሥሮ ኤልያቄምን አንግሦላቸው ሄድዋል፡፡ ኤልያቄም ማለት ቆመ ለነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኢቆመ ለክሙ ሲል ኢዮአቄም ብሎታል፡፡ ግብጽ ከሄደ በኋላ ሦስት ዓመት ይገብርለታል፡፡ ወተቀንየ ኢዮአቄም ንጉሠ ይሁዳ ለንጉሠ ግብጽ ሠልስተ ዓመተ እንዲል። በአራተኛው ዓመት ናቡከደነጾር ዳር ዳር መውጋት ጀመረ መንገድ ተያዘብኝ ብሎ ግብር ነሣ ባምስተኛው ዓመት መጥቶ ገብር አለው። ንጉሥ ፍርድ ልበስ ፈርኦን ኒካዑ አባቴን ገድሎ ወንድሜን አስሮ እኔን አንግሦ ግብሩን ተገብሮ ሄደ፡፡ አንድ ባሪያ ለሁለት ጌታ መገዛት እንደምን ይሆንለታል አለው፡፡ አሕዛብ ፍርድ ጠነቀቅን ባዮች ናቸውና የዚያን ያንካሳ መዳረሻ ሳላሳይህ የዕለት ራት የጣት ቀለበት ልትለኝ አይገባህም ብሎ ግብጽ ወርዶ ፈርኦን ኒካዑን ገድሎ ሦስት ዓመት ኑሮ ባቢሎን ዘግብጽ አሰኝቷት ተመልስዋል፡፡ ከተመለሰም በኋላ ለሦስት ዓመት ይገብርለታል አሥር አንድ ዓመት ይሆናል ከዚህ በኋላ ሞት ቢያምረው በሰማይ የለ ዱር በእሥራኤል የለ ግብር ብሎ ግብር ነሣው፡፡ እሱም ተክል ለማየት ወጥቶ ሳለ ከለዳውያን ገድለውታል።
አንድም በእደ እግዚአብሔር ታሞ ሙቷል፡፡ ልጁን ኢኮንያንን አነገሡ ኢኮንያን ሦስት ወር እንደ ነገሠ ናቡከደነጾር ተመልሶ መጣ ይተወኛል መስሎት ወባት ገባ፡፡ እሱን አስሮ  ሕዝቡን ማርኮ ሲሄድ እናቱ ናታን ከመንገድ ቆይቶ ልጅ ሳለሁ የልጅ ልጅ አዋቂ ሳለሁ አላዋቂ  ታላቅ ሳለሁ ታናሽ አንግሠውብኝ ነበር የዚህን ግፍ አይቶ እግዚአብሔር መንግሥትን ላንተ አሳልፎ ከሰጠህ ንጉሥ ፍርድ ልበስ አለው፡፡ ምን ላድርግልህ አለው፡፡ አንግሠኝ አለው፡፡ ሕዝቡን ማርኬ እወስዳቸዋለሁ በማን አነግሥሃለሁ አለው፡፡ በሀገሬ እኔ አውቃለሁ ተክል በሚኩተኵቱት በገበራርት አንግሠኝ አለው፡፡ አንግሦት ሄዷል ስሙን ሴዴቅስያስ አለው። ባትከደኝ ማለት ነው። እሱም አምባውን እያጸና ግብሩን እየሰደደ ስምንት ዓመት ኖረ፡፡ በዘጠነኛው ዓመት እንደ ወንድሙ ሞት ቢያምረው በእሥራኤል የለ ግብር በሰማይ የለ ዱር ብሎ ግብር ነሣው። አስቀድሞ ፀባኢተ ሞዓብን ፀባኢተ ሶርያን ስዶ አስከበበው ኋላም እሱ ፪ት ዓመት ከ፮ ወር ይከበዋል፡፡ ወተገፍትዓት ሀገር ይላል የዘመነ ረኃብ ሰው ቀዩ ይጠቁራል ጥቁሩ ይነጣልና። አንድም እኩሉ እንገብር እኩሉ እንዋጋ በማለት ተለያዩ። ናቡከደነጾር ሥርዓት ሠርቶላቸው ነበር ሰው የሞተባቸው እንደሆነ መቃብር አይከልከሉ እያወጡ በየርስታቸው ይቅበሩ ብሎ በዚያ ልማድ ዋይ ሸሸ ተበላሸ ብላችሁ ይዛችሁኝ ውጡ አላቸው። ዋይ ሸሸ ተበላሸ እያሉ ይዘውት ሲሄዱ ያ ምንድነው ብሎ ጠየቀ። በምን አውቆ ቢሉ ሰው በዝቶ ነበርና።
አንድም ፍርድ ያደላባት ሴት ነግራበት የእሥራኤል ንጉሥ ሞቶ በሠራህላቸው ሥርዓት ሊቀብሩት ይወስዱታል አሉት። የወዳጅ እንጂ አስከሬን አጥቦ ገንዞ መቅበር ይገባል ወደኔ አምጡት ብሎ አስመጥቶ መግነዙን ፈተው ቢያዩት ዓይኑ ቆለል ቆለል ሲል ተገኝቷል ወተናገሮ ፍትሐ እንዲል ወቀሰው። መርጬ ባነግሥህ ምነው ከዳኸኝ። ከከዳኸኝስ በኋላ ወይ እችላለሁ ብለህ አትዋጋ ወይ አልችልም ብለህ አትገብር በዚያውስ ላይ እኔን ከዚህ አኑረሀ ወዴት ልትሄድ ኖሯል ብሎ መኳንንቱን ፍረዱልኝ አላቸው። እችላለሁ ብሎ አይዋጋ አልችልም ብሎ አይገብር ሞት ይገባዋል አሉ፡፡ ፍርድስ አላወቃችሁም ሞቱ ለብእሲ ዕረፍቱ ሞትማ ዕረፍት አይደለምን እኔ አውቃለሁ ብሎ ፯ ለመንግሥት የደረሱ ልጆች ነበሩት ከፊቱ በሠይፍ አስመታቸው፡፡ እሱንም ክፉ ባየበት ዓይኑ በጎ አይይበት ብሎ ሁለት ዓይኖቹን በፍላት አውጥቶ ትብትብ አሸክሞ ዱር ለዱር በፈረስ ጭራ እያስጎተተ ባቢሎን ይዞት ወርዷል፡፡ ከዚያም ባቄላ ሲፈጭ ከወፍጮ ስር ልቡ ፈርሶ ሞቱዋል ወይከውን መቃብሪከ ታኅተ እግረ ማኅረፅ ያለው የነቢዩ ቃል ይደርስ ይፈጸም ዘንድ፡፡ የዮአክስ ሦስት ወር የኢኮንያን ሦስት ወር ከመንፈቅ የሴዴቅያስ ዓሥር ዓመት ከመንፈቅ አሥራ አንድ ዓመት የኤልያቄም ዓሥራ አንድ። የኢዮስያስ ዓሥራ ስምንት እርባ ይሆናል፡፡ ይኸ ሁሉ ዘመን እያለ ፄዋዌውን ሰሙት ብሎ እንደ ነገሠ ጊዜ የተደረገውን ለልደቱ ሰጥቶ ተናገረ አንድም ከዚህ ሁሉ ሐተታ ለመዳን ዘአመ ፍልሰተ ባቢሎን የሚል ይገኛል እሥራኤል ተማርከው ባቢሎን በወረዱ ጊዜ የነገሠ ኢኮንያንን ወለደ ይህ አያሳስትም። ፄዋዌ ሥጋው ለፄዋዌ ነፍሱ ምልክት እንደሆነ ሚጠተ ሥጋው ለሚጠተ ነፍስ ምልክት ነውና። እሥራኤል ተማርከው ባቢሎን መውረዳቸው ነፍሳት ገሃነም ለመውረዳቸው ምሳሌ ነውና፡፡ እሥራኤል ከባቢሎን መውጣታቸው ነፍሳት ከሲኦል ከገሃነም ለመውጣቸው ምሳሌ ነውና። ኤልያቄምን የሚጽፈውም የሚተወውም አለ፡፡ የተወው እንደ ሆነ መጽሐፈ ኤርምያስን አቃጥሎ ነበርና በመጽሐፍ መጻፍ አይገባውም ብሎ። ይኸማ እንዳይሆን ጌታ ግብር ይጸየፋል እንጂ ባሕርይ ይጸየፋልን ብሎ ለቊጥር ይመቸኛል ብሎ ያውስ ቢሆን በሱ ዕጣ ወጥቶበታልን ብሎ። ግድፈተ ጸሐፊ ነው ይህን ለምን ይሻዋል ቢሉ እሳቸው ከሠሩላቸው ሥርዓት ካስተማሯቸው ትምህርት ቢወጡ እንዲህ ያለ መከራ አገኛቸው። እናንተም ከሠራንላችሁ ሥርዓት ካስተማርናችሁ ትምህርት ብትወጡ እንዲህ ያለ መከራ ያገኛችኋል ለማለት፡፡
                  ******
፲፪፡ ወእምድኅረ ፍልሰተ ባቢሎን ኢኮንያንኒ ወለደ ሰላትያልሃ።
፲፪፡ የኢየሩሳሌም ሰዎች ተማርከው ባቢሎን ከወረዱ በኋላም ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ።
                  ******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
17/06/2011 ዓ.ም

Friday, February 22, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 17


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ ፩።
                  ******
፮፡ ወዳዊትኒ ንጉሥ ወለደ ሰሎሞንሃ እምነ ብእሲተ ኦርዮ።
               (፪፡ነገ ፪፥፳፬)
                  ******
፮፡ ዳዊት ንጉሥም ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ሰሎሞንን ወለደ። እሊያስ ሴቶቹ ከአረማውያን ወገን ቢሆኑ ነው እነዚህማ እሱ ዕብራዊ እሱዋ ዕብራዊት ስለምን እንዲህ አለ ቢሉ። ዳዊትማ ጐልማሳ አስገድሎ የጐልማሳ ሚስት ቀምቶ ማማውን ግርማውን ቢፈራ ኃጢአቱን ሳይገልጽበት ቀረ እንዳይሉት። ሐዋርያ መምሕር ወመገሥፅ ዘኢያደሉ ለገጽ እንደሆነ ለማጠየቅ።
አንድም በተነሳሕያን ፍርሃት እንደሌለባቸው ለማጠየቅ። አዳምን ያህል ሰው በድሎ ንስሐ ቢገባ ተማረ። ዳዊትን ያህል ሰው በድሎ ንስሐ ቢገባ ተማረ። ጴጥሮስን ያሀል ሰው ክዶ ንስሐ ቢገባ ተማረ እናንተም ንስሐ ብትገቡ ትድናላችሁ ለማለት።
አንድም በዓቂበ ሕግ ይመካሉና እናንተስ የሕግ አፍራሽ ልጆች አይደላችሁምን ለማለት። ክርስቶስ በዳዊት ከበረ ይላሉና ዳዊት በክርስቶስ ከበረ እንጂ እሱማ ጐልማሳ አስገድሎ የጐልማሳ ሚስት ቀምቶ አልነበረም ለማለት።
                  ******
፯፡ ወሰሎሞንኒ ወለደ ሮብዓምሃ
     (፫፡ነገ ፪፥፴፫። ፲፬፥፴፩። ፲፭፥፰።)
                  ******
፯፡ ሰሎሞንም ሮብአምን ወለደ።
ወሮብዓምኒ ወለደ አብያሃ።
ሮብዓምም አብያን ወለደ።
ወአብያኒ ወለደ አሳፍ።
አብያም አሳፍን ወለደ።
                  ******
፰፡ ወአሳፍኒ ወለደ ኢዮሳፍጥሃ።
                  ******
፰፡አሳፍም ኢዮሳፍጥን ወለደ።
ወኢዮሳፍጥኒ ወለደ ኢዮራምሃ፡፡
ኢዮሳፍጥም ኢዮራምን ወለደ፡፡
ወኢዮራምኒ ወለደ አካዝያስሃ፡፡
ኢዮራምም አካዝያስን ወለደ፡፡
ወአካዝያስኒ ወለደ ኢዮአስሃ፡፡
አካዝያስም ኢዮአስን ወለደ፡፡
ወኢዮአስኒ ወለደ አሜስያስሃ፡፡
ኢዮአስም አሜስያስን ወለደ፡፡
ሐተታ። አካዝያስን ኢዮአስን አሜስያስን የሚጽፍም የማይጽፍም ይገኛል። የጻፈ እንደሆነ የተመቸ። የተወ እንደሆነ በሀገራቸው አንድ አ እንጂ ሁለት አ አይገኝምና አና አ አሳስቶት በሀገራቸውስ ስንኳን ሁለት አ አራት አ ይገኛል ብሎ ዝያና ዝያ አሳስቶት። አንድም መምለክያነ ጣዖት ናቸውና ስማቸው በመጽሐፍ መጻፍ አይገባውም ብሎ። ይህማ እንዳይሆን ጌታ ግብር ይጸየፋልን ብሎ። ለቊጥር ይመቸኝ ብሎ። ለቊጥርስ ይመቸኝ ቢል በኒህ ዕጣ መጥቶባቸዋልን ቢሉ።ግድፈተ ጸሐፊ ነው።
ወአሜስያስኒ ወለደ ኦዝያንሃዘተሰምየ አዛርያስ፡፡
አሜስያስም አዛርያስ የተባለ ዖዝያንን ወለደ። ሕዝቡ በፍና ተሣልቆ በማይገባ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ማዕጠንተ ወርቅ ይዞ ከቤተ እግዚአብሔር ገብቶ ቢያጥኑ አዛርያስ ይባሉ ብለውታልና በፍና ተሣልቆ ስለተናገሩ አዛርያስ የተባለ አለ።
አንድም አዛርያስ በሉኝ ያለ ዖዝያንን ወለደ። የአዛርያስን ሥራ ልሥራ ማለት አዛርያስ በሉኝ ማለት ነውና። በዘመኑ ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ይባላል በቀኙ ይቀመጣል ምነው ይለዋል ወካህን ይነብር በየማኑ እንጂ ይላል ይለዋል። ፍርዱን ይገሥበታል ምነው ይለዋል። እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት እንጂ ይላል ይለዋል። ከሱ የሚበልጥ ልብስ ይለብሳል ምነው ይለዋል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ እንጂ ይላል ይለዋል። በባቴ ከቤተ መንግሥት ብወለድ በናቴ ከቤተ ክህነት እወለድ የለምን ብሎ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ማዕጠንተ ወርቅ ይዞ ሊያጥን ሲገባ ሕዝቡ ተው አይገባም አይሆንም አሉት። ንጉሥ ነውና ተጋፍቶ ገባ ሲያጥን ጢሰ ቅታሬው ቢነካው ከግንባሩ ለምፅ ወጣበት በሻሽ ቢሸፍነው ከሻሹ ላይ ወጣ። እስራኤል ለምፅ የያዘውን ስንኳን ሊያነግሡት ሊገናኙት አይወዱምና ወአውፅእዎ ለዖዝያን ውስተ ቤተ ሐፍሶት እንዲል። ቀሳ አወጡት ወኢዮአታም ወልዱ የዓቅብ ቤተ መንግሥት ወይኴንን ሕዝበ ምድር እንዲል ልጁን ኢዮአታምን አንግሠዋል ይህንንስ ለምን ይሻዋል ቢሉ። ሐተታ እሱ ካስተማሩት ትምህርት ከሠሩለት ሥርዓት ቢወጣ እንዲህ ያለ መከራ አገኘው። እናንተም ካስተማርናችሁ ትምህርት ከሠራንላችሁ ሥርዓት ብትወጡ እንዲህ ያለ መከራ ያገኛችኋል ለማለት።
                  ******
፱፡ ወዖዝያንኒ ወለደ ኢዮአታምሃ፡፡
                  ******
፱፡ ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ።
ወኢዮአታምኒ ወለደ አካዝሃ፡፡
ኢዮአታምም አካዝን ወለደ።
ወአካዝኒ ወለደ ሕዝቅያስሃ።
አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ።
                  ******
፲፡ ወሕዝቅያስኒ ወለደ ምናሴሃ።
                  ******
፲፡ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ።
ወምናሴኒ ወለደ አሞፅሃ።
ምናሴም አሞፅን ወለደ።
ወአሞፅኒ ወለደ ኢዮስያስሃ።
አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ።
                  ******
፲፩፡ ወኢዮስያስኒ ወለደ ኢኮንያንሃ ወአኃዊሁ አመ ፍልሰተ ባቢሎን፡፡
                  ******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
16/06/2011 ዓ.ም