====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ
፩።
******
፮፡
ወዳዊትኒ ንጉሥ ወለደ ሰሎሞንሃ እምነ ብእሲተ ኦርዮ።
(፪፡ነገ ፪፥፳፬)
******
፮፡
ዳዊት ንጉሥም ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ሰሎሞንን ወለደ። እሊያስ ሴቶቹ ከአረማውያን ወገን ቢሆኑ ነው እነዚህማ እሱ ዕብራዊ እሱዋ
ዕብራዊት ስለምን እንዲህ አለ ቢሉ። ዳዊትማ ጐልማሳ አስገድሎ የጐልማሳ ሚስት ቀምቶ ማማውን ግርማውን ቢፈራ ኃጢአቱን ሳይገልጽበት
ቀረ እንዳይሉት። ሐዋርያ መምሕር ወመገሥፅ ዘኢያደሉ ለገጽ እንደሆነ ለማጠየቅ።
አንድም
በተነሳሕያን ፍርሃት እንደሌለባቸው ለማጠየቅ። አዳምን ያህል ሰው በድሎ ንስሐ ቢገባ ተማረ። ዳዊትን ያህል ሰው በድሎ ንስሐ ቢገባ
ተማረ። ጴጥሮስን ያሀል ሰው ክዶ ንስሐ ቢገባ ተማረ እናንተም ንስሐ ብትገቡ ትድናላችሁ ለማለት።
አንድም
በዓቂበ ሕግ ይመካሉና እናንተስ የሕግ አፍራሽ ልጆች አይደላችሁምን ለማለት። ክርስቶስ በዳዊት ከበረ ይላሉና ዳዊት በክርስቶስ ከበረ
እንጂ እሱማ ጐልማሳ አስገድሎ የጐልማሳ ሚስት ቀምቶ አልነበረም ለማለት።
******
፯፡
ወሰሎሞንኒ ወለደ ሮብዓምሃ
(፫፡ነገ ፪፥፴፫። ፲፬፥፴፩። ፲፭፥፰።)
******
፯፡
ሰሎሞንም ሮብአምን ወለደ።
ወሮብዓምኒ
ወለደ አብያሃ።
ሮብዓምም
አብያን ወለደ።
ወአብያኒ
ወለደ አሳፍ።
አብያም
አሳፍን ወለደ።
******
፰፡
ወአሳፍኒ ወለደ ኢዮሳፍጥሃ።
******
፰፡አሳፍም
ኢዮሳፍጥን ወለደ።
ወኢዮሳፍጥኒ
ወለደ ኢዮራምሃ፡፡
ኢዮሳፍጥም
ኢዮራምን ወለደ፡፡
ወኢዮራምኒ
ወለደ አካዝያስሃ፡፡
ኢዮራምም
አካዝያስን ወለደ፡፡
ወአካዝያስኒ
ወለደ ኢዮአስሃ፡፡
አካዝያስም
ኢዮአስን ወለደ፡፡
ወኢዮአስኒ
ወለደ አሜስያስሃ፡፡
ኢዮአስም
አሜስያስን ወለደ፡፡
ሐተታ።
አካዝያስን ኢዮአስን አሜስያስን የሚጽፍም የማይጽፍም ይገኛል። የጻፈ እንደሆነ የተመቸ። የተወ እንደሆነ በሀገራቸው አንድ አ እንጂ
ሁለት አ አይገኝምና አና አ አሳስቶት በሀገራቸውስ ስንኳን ሁለት አ አራት አ ይገኛል ብሎ ዝያና ዝያ አሳስቶት። አንድም መምለክያነ
ጣዖት ናቸውና ስማቸው በመጽሐፍ መጻፍ አይገባውም ብሎ። ይህማ እንዳይሆን ጌታ ግብር ይጸየፋልን ብሎ። ለቊጥር ይመቸኝ ብሎ። ለቊጥርስ
ይመቸኝ ቢል በኒህ ዕጣ መጥቶባቸዋልን ቢሉ።ግድፈተ ጸሐፊ ነው።
ወአሜስያስኒ
ወለደ ኦዝያንሃዘተሰምየ አዛርያስ፡፡
አሜስያስም
አዛርያስ የተባለ ዖዝያንን ወለደ። ሕዝቡ በፍና ተሣልቆ በማይገባ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ማዕጠንተ ወርቅ ይዞ ከቤተ እግዚአብሔር ገብቶ
ቢያጥኑ አዛርያስ ይባሉ ብለውታልና በፍና ተሣልቆ ስለተናገሩ አዛርያስ የተባለ አለ።
አንድም
አዛርያስ በሉኝ ያለ ዖዝያንን ወለደ። የአዛርያስን ሥራ ልሥራ ማለት አዛርያስ በሉኝ ማለት ነውና። በዘመኑ ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ
ይባላል በቀኙ ይቀመጣል ምነው ይለዋል ወካህን ይነብር በየማኑ እንጂ ይላል ይለዋል። ፍርዱን ይገሥበታል ምነው ይለዋል። እምነ መንግሥት
የዓቢ ክህነት እንጂ ይላል ይለዋል። ከሱ የሚበልጥ ልብስ ይለብሳል ምነው ይለዋል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ እንጂ ይላል ይለዋል።
በባቴ ከቤተ መንግሥት ብወለድ በናቴ ከቤተ ክህነት እወለድ የለምን ብሎ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ማዕጠንተ ወርቅ ይዞ ሊያጥን ሲገባ
ሕዝቡ ተው አይገባም አይሆንም አሉት። ንጉሥ ነውና ተጋፍቶ ገባ ሲያጥን ጢሰ ቅታሬው ቢነካው ከግንባሩ ለምፅ ወጣበት በሻሽ ቢሸፍነው
ከሻሹ ላይ ወጣ። እስራኤል ለምፅ የያዘውን ስንኳን ሊያነግሡት ሊገናኙት አይወዱምና ወአውፅእዎ ለዖዝያን ውስተ ቤተ ሐፍሶት እንዲል።
ቀሳ አወጡት ወኢዮአታም ወልዱ የዓቅብ ቤተ መንግሥት ወይኴንን ሕዝበ ምድር እንዲል ልጁን ኢዮአታምን አንግሠዋል ይህንንስ ለምን
ይሻዋል ቢሉ። ሐተታ እሱ ካስተማሩት ትምህርት ከሠሩለት ሥርዓት ቢወጣ እንዲህ ያለ መከራ አገኘው። እናንተም ካስተማርናችሁ ትምህርት
ከሠራንላችሁ ሥርዓት ብትወጡ እንዲህ ያለ መከራ ያገኛችኋል ለማለት።
******
፱፡
ወዖዝያንኒ ወለደ ኢዮአታምሃ፡፡
******
፱፡
ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ።
ወኢዮአታምኒ
ወለደ አካዝሃ፡፡
ኢዮአታምም
አካዝን ወለደ።
ወአካዝኒ
ወለደ ሕዝቅያስሃ።
አካዝም
ሕዝቅያስን ወለደ።
******
፲፡
ወሕዝቅያስኒ ወለደ ምናሴሃ።
******
፲፡
ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ።
ወምናሴኒ
ወለደ አሞፅሃ።
ምናሴም
አሞፅን ወለደ።
ወአሞፅኒ
ወለደ ኢዮስያስሃ።
አሞፅም
ኢዮስያስን ወለደ።
******
፲፩፡
ወኢዮስያስኒ ወለደ ኢኮንያንሃ ወአኃዊሁ አመ ፍልሰተ ባቢሎን፡፡
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
16/06/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment