====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ
፩።
******
፲፪፡
ወእምድኅረ ፍልሰተ ባቢሎን ኢኮንያንኒ ወለደ ሰላትያልሃ።
******
፲፪፡
የኢየሩሳሌም ሰዎች ተማርከው ባቢሎን ከወረዱ በኋላም ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ። ሐተታ ምነዋ ኢየዓርግ ብእሲ እምውስተ ዘርኡ ዘይነብር
ዲበ መንበሩ ይል የለምን ቢሉ። አይነግሥም አለ እንጂ አይወለድም አለ። ያውስ ቢሆን አይነግሥም ያለው ሴዴቅያስ ኢኮንያንን ነው
እንጂ ኤልያቄም ኢኮንያንን ነውን። ወሰላትያልኒ ወለደ ዘሩባቤልሃ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፡፡
******
፲፫፡
ወዘሩባቤልኒ ወለደ አብዩድሃ፡፡
፲፫፡
ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ።
******
ወአብዩድኒ
ወለደ ኤልያቄምሃ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ።
ወኤልያቄምኒ
ወለደ አዛርሃ።
ኤልያቄምም
አዛርን ወለደ።
******
፲፬፡
ወአዛርኒ ወለደ ሳዶቅሃ።
፲፬፡
አዛርም ሳዶቅን ወለደ።
******
ወሳዶቅኒ
ወለደ አኪንሃ።
ሳዳዶቅም
አኪንን ወለደ።
ወአኪንኒ
ወለደ ኤልዩድሃ።
አኪንም
ኤልዩድን ወለደ።
******
፲፭፡
ወኤልዩድኒ ወለደ አልዓዛርሃ፡፡
፲፭፡
ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፡፡
******
ወአልዓዛርኒ
ወለደ ማትያንሃ አልዓዛርም ማትያንን ወለደ፡፡
ወማትያንኒ
ወለደ ያዕቆብሃ።
ማትያንም
ያዕቆብን ወለደ።
******
፲፮፡
ወያዕቆብኒ ወለደ ዮሴፍሃ ፈኃሪሃ ለማርያም እንተ እምኔሃ ተወልደ እግዚእ ኢየሱስ ዘተብህለ ክርስቶስ።
******
፲፮፡
ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስ ከስዋ የተወለደ የእመቤታችን እጮኛ የሚሆን ዓቃቤሃ ተለአኪሃ አገልጋይዋ ጠባቂዋ የሚሆን ዮሴፍን
ወለደ፡፡ መገናኛው ጉንዱ አልዓዛር ነው አልአዛር ማትያንንና ቅስራን ይወልዳል ማትያን ያዕቆብን ያዕቆብ ዮሴፍን ይወልዳል ቅስራ
ኢያቄምን ኢያቄም እመቤታችንን በሀገራቸው ሴትና ወንድ አቀላቅሎ መቊጠር የለምና ሥርዓት አፈረሰ ይሉኛል ብሎ በዮሴፍ አንጻር ቈጠረ፡፡
እስዋንም እንዳትቀር በቅጽል አመጣት፡፡ ሐተታ በ፫ ቤት እንድትታጭ ማድረጉ ስለ ምን ቢሉ በልማድ፡፡ አዋልደ ሰለጳድ ከሙሴ ዘንድ
ሄደው አባታችን የሞተ በበደሉ ነው እኛ ከነገር አልገባንምና ርስት አካፍለን ስሙን እናጸራው አሉት፡፡ ወደ አግዚአብሔር ቢያመለክት
ርቱዓ ይቤላ አዋልደ ሰለጳድ ሀቦን መክፈልቶን ማዕከለ አኃዊሆን አለው።
እስራኤል ይኸነን ሰምተው ሴት የያዘችው ነገር ከሁሉ ይደርሳል ከእንግዴህ ወዲህ ርስት ከርስት ትውልድ ከትውልድ እንደተፋለሰ ዕወቅ
አሉት፡፡ ሁለተኛ አመለከተ። አስተዋስቦን ዘእምቅሩቦን ባባታቸው ወገን በሶስት በሶስት ቤት እየተጋቡ እንዲወርሱ አድርግ ብሎታልና
በነዚያ ልማድ።
አንድም
ፄዋዌ ቢጸናባቸው ወንዱ ለሴቲቱ ሴቲቱ ለወንዱ የማያዝኑ ሁነዋል በተዘምዶተ ሥጋ ላይ የግቢ ተዘምዶ የተጨመረ እንደሆነ ጥሏት አይሄድም
ያዝንላታል ብለው የሚያጋቧቸው ሁነዋልና በዚያ ልማድ በዚያስ ላይ እንድትታጭ ማድረጉ ስለ ምን ቢሉ፡፡ ኃይል አርያማዊት ባሏት ነባርና
ወንድ ከወንድ ተገኘ ባሉ ነበርና ከመ በብሂሎቱ ፍሕርተ ብእሲ ያግኅድ ከመ እግዝአትነ ማርያም በአማን ብእሲት ይእቲ እንዲል፡፡
አንድም
ፅንስን ከአጋንንት ለማሳሳት አውቀው ቢሆን ብዙ ፅንስ ባበላሹ ነበርና።
አንድም
መስተመይናን ዝሁላነ አእምሮ አይሁድ ሰብሳብ ርኩስ ይላሉና። ንጹሕ እንደሆነ ለማጠየቅ።
አንድም
በመከራዋ ጊዜ ሊከተላት ከርስት ገብቶ ሊቆጠርላት ከውግረት ሊያድናት። ዮሴፍ ምክንያት ባይኖራት በድንጊያ ወግረው በገደሏት ነበርና።
ከፅዕለትም ሊያድናት ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለ፩ ብእሲ ወይብላሁ እክለ ዚአነ ንሴሰይ ወልብሰ ዚአነ ንትዔረዝ ዳዕሙ ይሰመይ ስምከ
በላዕሌነ ወአኅድገነ ዘንተ ፅዕለተ እንዲል። ይህንም ፪ ሊቃውንት አመሩ ፈቃደ ዮሴፍ ወሠለስቱ ሊቃውንት አመሩ ፈቃደ ሥላሴ ይላል።
ሁለቱ ሊቃውንት የተባሉ ዮሴፍ ለጊዜው አገባለሁ መስሎት ነበር ብለው የጻፉ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ያዕቆብ ዘሮሃ ናቸው። ፫ቱ ሊቃውንት
የተባሉ ሥላሴ ንጽሕናውን ባወቁ አስጠብቀውታል ብለው የጻፉ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ዮሐንስ አፈወርቅ ናቸው። ዘተብለ
ክርስቶስ አለ ይህም ስም ብቻ የትስብእት ብቻ የመለኮት አይደለም። ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢሆን
የወጣለት ስም ነው እንጂ ወእነግር አነሂ ከመ ኢመፍትው እስምዮ ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእንበለ ትስብእት፤ ወኢ ለትስብእት
ዘእንበለ መለኮት ክርስቶስሃ ይሰመይ ወእምቅድመ ትሥጉት አልቦ ዘይሰምዮ በዝንቱ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ እንዲል፡፡ በዝንቱ
ስም ተሰምዩ ነቢያት ቅቡዓነ እስመ ስመ ክርስቶስ ይትበሃል ላዕለ ብዙኅ ፆታ ከመ ነገሥተ እስራኤል ወካህናቲሆሙ ከመ አሮን ወዳዊት
ወዘኃረዮሂ ከመ ሥርዓተ ቂሮስ ውእቱ ይላልሳ ቢሉ። ይኽንም እንጂ ወተቀበዖሰ በመንፈስ ከመ ካህናተ ሐዲስ ውእቱ። ወላዕለ ዘተወልደ
እምእግዝእትነ ማርያም ይትበሀል እንበይነ ተዋሕዶ ኮነ ለመለኮት በእንተ ዘተሠገወ እምድንግል ህየንተ ቅብዓተ ቅብዕ ባለው አፍርሶ
ታል። እንዲህ ከሆነ ማን ሲያይ ተናግሮታል ቢሉ አንዱን ሲያይ። ገብርኤል ስሙ ዘአምኃ ለማርያም ዘበትርጓሜሁ አምላክ ውእቱ እንዲል።
ኤልን ሲያይ። ይህም አምላክ ሰው ቢሆን የወጣለት ስም ነው። ወዝ ስም ዘውእቱ ክርስቶስ ወፍካሬሁ ቅብዓት ምስለ አምጣነ ትስብእቱ
ረከቦ ለዋህድ እንዲል። ከበረ መባሉም በሥጋ ነው። ወቅብዓቱሰ ዘተወክፋ በትስብእቱ ይእቲ ወኢኮነ ቅብዓቱ አምሳለ ቅቡዓን እስመ
እለ ይትቀብዑ ይፈቅዱ ቀሪበ ኀቤሁ ለከዊነ ወልድና ውእቱሰ አምላክ ውእቱ በጠባይዒሁ ዘአንበለ ፈቂድ እንዲል፡፡ ቦ አለ ይቤሉ እምቅድመ
ተዋሕይ ወቦ እለ ይቤሉ እምድኅረ ተዋሕዶ እንዲል። ወገባሪሁሰ ለውእቱ ሥጋ መንፈስ ቅዱስ እስመ ውእቱ ቀብዖ ወተዋሕደ ቦቱ አምላክ
ቃል ያለውን ይዘው ተቀብቶ ተዋሐደ የሚሉ አሉ፡፡ ተሠጊዎ ነሥአ ቅብዓተ በዘተሰብአ ተቀብዓ ያለውን ይዘው ሰው ሁኖ ተቀብቶ ተዋሐደ
የሚሉ አሉ። ነገር ግን እንዲህ አይደለም ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው። ከመ ቅፅበተ ዓይን። እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ተቀብዓ ቃል በሥጋሁ
ወእምአመ ኮነ ቃል ሥጋ አሜሃ አስተርአየ በመንፈስ ቅዱስ እንዲል።
******
፲፯፡
ወኵሎንኬ ትውልድ እምአብ ርሃሞ እስከ ዳዊት ፲ወ፬ቱ፡፡
፲፯፡
ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ ነው።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
19/06/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment