© መልካሙ በየነ
ኅዳር 1/
2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
በመጀመሪያ ( facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም
facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ ከዚያ ጽሑፉን ያንብቡ ቀጥለውም ጽሑፉን SHARE, COMMENT,
LIKE ያድርጉ፡-
==============================================
“አውሎግሶን” ማለት “አቤቱ ክፈትልኝ፤ አቤቱ ግለጥልኝ” ማለት ነው፡፡ (ድርሳነ ሚካኤል ዘኅዳር)
ይህ ልመና እንደ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት ያለ ልመና ነው፡፡ ዳዊት “አቤቱ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ፡፡ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” መዝ 50 እንዳለው ያለ ማለት ነው፡፡
የልባችን ክፋት ሲያይልብን፣ ማሥተዋል ሲጎድለን፣ መረዳት ሲሳነን፣ ተስፋችን ሲሟጠጥ፣ ኅሊናችን ሲታወክ ወዘተ አውሎግሶን ማለት ይገባናል፡፡ የደነቆረ ልቡናችን፣ ማየት የቸገረው ዓይናችን፣ ማሰብ የተሳነው ልቡናችን፣ ለፈጣሪ የተገዛ እንዲሆንልን ቅዱሳንን አማላጆቼ እንዲልልን አሁንም አውሎግሶን እንበል፡፡ በዘመናችን ተገቢ ልመና ከፈጣሪ መታረቂያ ጸሎት አውሎግሶን ነው፡፡ የተዘጋው ሲከፈት የተሰወረው ሲገለጥ ሰይጣን የኃፍረት ካባ ሲጎናጸፍ ነፍሳችን ሥጋችንን ገዝታ በነፍስ ጎዳና ትመራታለች፡፡ የሥጋ ገበያ ይቀዘቅዛል የነፍስ በረከት ምድሪቱን ይሸፍናታል፡፡ የመላእክቱ ጠባቂነት ይበዛልናል ስለዚህ ትናንት አበው አውሎግሶን እንዳሉ ዛሬ እኛም እንዲሁ ብለን ለነገው ትውልድ የሚድንበትን መንገድ እንዲከፈት የተሠወረው እንዲገለጥ አውሎግሶን በሉ ብለን እናስተምር፡፡
ዳዊት “አቤቱ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ፡፡ የቀናውንም
መንፈስ በውስጤ አድስ” መዝ 50 ብሏል፡፡ ይህን የዳዊት ልመና እንደእኔ ዓይነቱ ሞኝ ዳዊት ድሮ የነበረውን
ወይም ቀድሞ የተፈጠረለትን ልብ ፈጣሪ በጥበቡ እንዲቀይርለት (እንዲለውጥለት) የለመነ ይመስለዋል፡፡ ግን አይደለም፡፡ ልቡናው በኃጢአት
ረክሷል፣ ልቡናው ሰው በመግደል አድፏል፣ ልቡናው የቀናውን መንፈስ ለማሰብ ተስኖታል፣ ልቡናው ጽድቅን እንዳያስብ ተዘግቷል፤ ልቡናው
የሰውን ሚስት በማስነወር ቆሽሿል፣ ልቡናው ያልተፈቀደለትን የካህናትን ምግብ በመመገብ ኃጢአት ሠርቷል፡፡ ስለዚህ ነው ይህንን በኃጢአት
የሚባዝነውን ልቡናየን ንጹሕ አድርግልኝ ማለቱ፡፡ ያለኝን ቀድሞ የፈጠርክልኝን ልብ በንስሐ ሳሙና ንጹህ አድርግልኝ ማለቱ ነው፡፡
ንስሐ እንድገባ በንስሐ እንድመላለስ በቅድስና እንድጓዝ አድርገኝ ሲል ነው፡፡ የእኛም ልመና ይኼ ነው መሆን ያለበት፡፡ እኛን ከፍጥረታት
ሁሉ አልቆ አብልጦ ፈጥሮናል ነገር ግን በማይገባ የኃጢአት ሥራ እየባዘንን እንሳሳትን እንመስላለን፡፡ በርግጥ ሰው እንስሳዊ ባሕርይ
አለው፡፡ እንስሳዊ ባሕርይውን ግን መቆጣጠር እንዲችል ሆኖ የተፈጠረ ድንቅ ፍጥረት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በሬ ሲያዩ
በሬ ባደረገኝ፣ ወፍ ሲያዩ ወፍ ባደረገኝ፣ አንበሳ ሲያዩ አንበሳ ባደረገኝ፣ ነብር ሲያዩ ነብር ባደረገኝ ወዘተ ይላሉ፡፡ የሚገርመው
ነገር ዳዊት ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ማለቱን አለማስተዋላችን ነው፡፡ ዳዊት ያለኝን የቆሸሸ ልቤን ንጹሕ አድርግልኝ አለ እንጅ የእንስሳትን
ልብ ስጠኝ አላለም፡፡ እኛም የሚያስፈልገን ይኼ ልመና ነው፡፡ ያለንን ነገር ቀድስልን ባርክልን ንጹሕ አድርግልን ማለት ያስፈልገናል፡፡
የሌለንን ነገር ምኑን እንዲባርክልን እንለምነዋን? አውሎግሶን በሉ እባካችሁ፡፡ ሁሉም ከተዘጋብን ሁሉም ከተሠወረብን ከዚህ የልመና
ቃል ውጭ ምንም አማራጭ የለንም፡፡ ልመናችንን እንድናስተካክል የተሠወረው እንዲገለጥልን የተዘጋው እንዲከፈትልን አውሎግሶን እንበል፡፡
ልቡናችን በኃጢአት ቁልፍ ተዘግቷል፤ የጽድቅ ጎዳና በዲያብሎስ ተንኮል ታጥሮብናል ተዘግቶብናል፤ የንስሐ ሳሙና ተደብቆብናል ስለዚህ
የተዘጋው እንዲከፈት የተሠወረው እንዲገለጥ አውሎግሶን እንበል፡፡
ጸሎት ለመጀመር በጣም የከበደ እንዲሆን
አድርጎ ሰይጣን በልባችን ገብቶ መጥፎ አረም ይዘራብናል፡፡
ለዚያም ነው ትንሿ ጸሎት ዳገት ሆና ለመጀመር የምትከብደን፡፡ አውሎግሶን ብለን
ጸሎት ስንጀምር ግን ዳገቱ ሁሉ የተስተካከለ ሜዳ ይሆንና ውዳሴዋን ስንጨርስ አንቀጸ ብርሃኗን፤ አንቀጸ ብርሃኗን ስንጨርስ ይዌድስዋ
መላእክትን፤ ያን ስንጨርስ አቡነ ዘበሰማያትን እርሱንም ስንጨርስ ቅዳሴዋን፣ መልክአዋን ሌሎችንም ለመጸለይ ልባችን ተከፍቶ በተመስጦ
እንድንጸልይ ብርታት እናገኛለን፡፡ ማንም ማረጋገጥ የሚችለው እውነት ነው፡፡ ትንሽ ጸሎት ብንጀምር ትልቁን ጸሎት እንድንጀምር ሰይጣን የመቃወም ኃይሉ ይቀንሳል፡፡
አማትበን አቡነ ዘበሰማያትን ስንጀምር ሰይጣን መሸሽ ይጀምራል፡፡ በዚያ ላይ ስግደት ስንጨምርበት በኖ ይጠፋል፡፡ አውሎግሶን!!!
No comments:
Post a Comment