Wednesday, July 10, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 132

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ትንሣኤሁ ለኢየሱስ።
ምዕራፍ ፳፰።
                    ******
፩፡ ወሠርከ ሰንበት ለጸቢሐ እሁድ መጽአት ማርያም መግደላዊት ወካልዕታኒ ማርያም ይርአያ መቃብረ። ማር ፲፮፥፭፡፡ ዮሐ ፳፥፲፩፡፡
                    ******
፩፡ ቅዳሜ ማታ ለእሁድ አጥቢያ ማርያም መግደላዊት ሌላዪቱም ማርያም መቃብሩን ያዩ ዘንድ መጡ፡፡ ማርያም ባውፍልያ ናት።
                    ******
፪፡ ወናሁ ኮነ ድልቅልቅ ዓቢይ።
                    ******
፪፡ ታላቅ ንውጽውጽታ ተደረገ።
እስመ መልአከ እግዚአብሔር ወረደ እምሰማይ ወቀርበ ወአንኰርኰራ ለይእቲ ዕብን እምአፈ መቃብር ወነበረ ዲቤሃ፡፡
መልአኩ ከሰማይ ወርዶ ደንጊያውን ከመቃብር ላይ አንስቶ ተቀምጦበት ነበርና።
                    ******
፫፡ ወራአዩ ከመ ዘመብረቅ።
                    ******
፫፡ መልኩ እንደ ፀሐይ ብሩህ ነው፡፡ ኢትርአይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ እንዲል፡፡
ወልብሱ ፀዓዳ ከመ በረድ።
ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነው፡፡ ወርኃ ትፍሥሕት ወርኃ ተድላ ነው ሲል።
                    ******
፬፡ ወእምግርማሁ ተሀውኩ እለ የዓቅቡ መቃብረ ወኮኑ ከመ አብድንት።
                    ******
፬፡ እሱን ከመፍራታቸው የተነሣ መቀብሩን የሚጠብቁት ደንግጠው እንደ በድን ሆኑ።
(ሐተታ) ነፍስ አልተለያቸውምና ከመ አብድንት አለ።
                    ******
፭፡ ወአውሥአ ውእቱ መልአክ ወይቤሎን ለአንስት እለ ይቀውማ ኢትፍርሃ አንትንሰ።
                    ******
፭፡ መልአኩ ሴቶችን እናንተ አትፍሩ አላቸው።
እስመ አአምር ከመ ኢየሱስሃ ዘተሰቅለ ተኃሥሣ።
የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና።
                    ******
፮፡ ኢሀሎ ዝየሰ።
                    ******
፮፡ ከዚህ ግን የለም።
ዳዕሙ ተንሥአ በከመ ይቤ።
እነሣለሁ እንዳለ ተነሥቷል  እንጂ።
ወባሕቱ ነዓ ርእያ መካኖ ኀበ ተቀብረ።
ነገር ግን የተቀበረበትን ቦታ መጥታችሁ እዩ።
                    ******
፯፡ ወፍጡነ ሑራ ወንግራሆሙ ለአርዳኢሁ ከመ ተንሥአ እምነ ምውታን።
                    ******
፯፡ ፈጥናችሁ ሂዳችሁ ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሯቸው።
ወናሁ ይቀድመክሙ ገሊላ።
በገሊላ ይቀድማችኋል ማለት መታየትን በገሊላ ይጀምርላችኋል፡፡
ወበህየ ትሬእይዎ።
በገሊላ ታዩታላችሁ።
ናሁ አይዳዕኩክን።
እነሆ ነገርኋችሁ፡፡
                    ******
፰፡ ወኃለፋ ፍጡነ እልኩ አንስት እምኀበ መቃብር በፍርሃት ወበረዓድ ወበፍሥሐ ዓቢይ
                    ******
፰፡ በታላቅ ደስታና በፍርሃት ከመቃብሩ ፈጥነው ሄዱ።
(ሐተታ) መልአክ አይተዋልና በፍርሃት ትንሣኤውን ሰምተዋልና ደስ ብሏቸው ሄዱ።
ወሮፃ ይንግራሆሙ ለአርዳኢሁ።
ለደቀ መዛሙርቱ ሊነግሯቸው ፈጥነው ሄዱ።
                    ******
፱፡ ወእንዘ የሐውራ ይንግራሆሙ ተራክቦን እግዚእ ኢየሱስ በፍኖት።
                    ******
፱፡ ሊነግሯቸው ሲሄዱ ጌታ ከመንገድ ታያቸው።
ወይቤሎን በሀክን፣
እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ አላቸው
ወቀሪቦን ወአኃዛ እገሪሁ ወሰገዳ ሎቱ
ቀርበው እግሩን ይዘው እጅ ነሡት ሰገዱለት
                    ******
፲፡ ወእምዝ ይቤሎን እግዚእ ኢየሱስ ኢትፍርሃ፤
                    ******
፲፡ ከዚህ በኋላ ጌታ አትፍሩ አላቸው
ሑራ ንግራሆሙ ለአኃውየ ከመ ይሑሩ ገሊላ
ገሊላ ይሄዱ ዘንድ ለወንድሞቼ ሄዳችሁ ንገሯቸው፡፡
ወበህየ ይሬእዩኒ፡፡
በገሊላ ያዩኛል፡፡
                    ******
ዘከመ ኄጥዎሙ።
፲፩፡ ወኃሊፎን እማንቱ አተዉ ሠገራት ሀገረ ወነገሩ ለሊቃነ ካህናት ኵሎ ዘከመ ኮነ።
                    ******
፲፩፡ ሴቶች ከሄዱ በኋላ ጭፍሮች ከከተማ ገብተው የተደረገውን ሁሉ እንደተደረገ ለሊቃነ ካህናት ተናገሩ፡፡
                    ******
ወተጋብኡ ወተማከሩ ምስለ ሊቃውንት ወወሀብዎሙ ብዙኃ ወርቀ ለሠገራት።
                    ******
፲፪፡ ተሰብስበው ከአለቆች ጋራ መክረው ለጭፍሮች ብዙ ወርቅ ሰጧቸው።
                    ******
ወይቤልዎሙ በሉ አርዳኢሁ ሌሊተ መጽኡ ወሠረቅዎ እንዘ ንነውም ንሕነ።
                    ******
፲፫፡ እኛ ተኝተን ሳለን ሌሊት መጥተው ደቀ መዛሙርቱ ሠርቀው ወሰዱት በሉ አሏቸው።
                    ******
፲፬፡ ወእምከመ ተሰምዓ ነገር በኀበ መልአከ አሕዛብ ንሕነ ነአምኖ፡፡
                    ******
፲፬፡ ይህ ነገር በጲላጦስ ዘንድ የተሰማ እንደሆነ እኛ እናስረዳዋለን፡፡
ወለክሙሰ ናድኅነክሙ።
እንናተንም ከቅጣት እናድናችኋለን።
ወናጸድቅ ነገረክሙ
ነገራችሁንም እናስረዳለን፡፡
ወዘእንበለ ኃዘን ንሬስየክሙ።
ደስ እናሰኛችኋለን አሏቸው።
                    ******
፲፭፡ ወነሢኦሙ ሠገራት ውእተ ወርቀ ገብሩ በከመ መሐርዎሙ።
                    ******
፲፭፡  ጭፍሮች ገንዘቡን ተቀብለው እንደነገሯቸው አደረጉ ማለት ሠርቀው ወሰዱት አሉ።
ወወጽአ ዝንቱ ነገር በኃበ አይሁድ እስከ ዮም።
እስካሁን ድረስ በአይሁድ ዘንድ ሠርቀው ወሰዱት ተብሎ ሲነገር ይኖራል።
(ሐተታ) አለቆቻቸው አራት ናቸው እየራሳቸው ጠይቀዋቸዋል አንዱን ቢጠይቁት አሥራ አንዱ ደቀመዛሙርቱ ሠርቀው ወሰዱት አለ፡፡  አንዱ መቶ ሀያው ቤተሰቡ ሰርቀው ወሰዱት አለ፡፡ አንዱ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሠርቀው ወሰዱት አለ። አንዱ እኔ ተኝቼ ነበር ሁሉንም አላየሁም አለ፡፡ ከመዝኑ ኮነ ነገርክሙ ዝርዙረ ወዝርወ ብሎ በሰይፍ አስፈጅቷቸዋል።
                    ******
፲ወአርዳኢሁሰ ፲ቱ ወ፩ዱ ሖሩ ውስተ ገሊላ ኀበ ደብር ዘአዘዞሙ እግዚእ ኢየሱስ።
                    ******
፲፮፡  አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርቱ ግን ሂዱ ወዳላቸው ቦታ ወደ ገሊላ ሄዱ።
                    ******
፲፯፡ ወሶበ ርእይዎ ሰገዱ ሎቱ።
                    ******
፲፯፡ ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት።
ወመንፈቆሙሰ ናፈቁ።
እኩሌቶቹ ተጠራጠሩ አለ ቶማስን ሲያይ። ወንፍቃ ለሌሊት እንዲል።
                    ******
፲፰፡ ወቀርበ እግዚእ ኢየሱስ ወተናገሮሙ እንዘ ይብል ተውህበኒ ሥልጣነ ሰማይ ወምድር።
                    ******
፲፰፡ ጌታ ቀርቦ ሰማይን ምድርን የማሳልፍበት ሥልጣን ተሰጠኝ ብሎ ነገራቸው።
(ሐተታ) ነፍሱና ሥጋው ተለያይተው ነበርና፡፡ የእኒያን ተዋሕዶ ሲያይ ተውህበ ሊተ አለ እንጂ የተሰጠው በማኅፀን ሲዋሐድ ነው።
በከመ ፈነወኒ አቡየ አነኒ እፌንወክምሙ።
እኔን አባቴ ላስተምር እንደላከኝ እናንተንም እልካችኋለሁ፡፡
                    ******
፲፱፡ ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ። ማር ፲፮፥፵፡፡
                    ******
፲፱፡ ሄዳችሁ ሰውን ሁሉ አስተምሩ።
ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብላችሁ አጥምቋቸው።
                    ******
፳፡ ወመሐርዎሙ ኵሎ ይዕቀቡ ኵሎ ዘአዘዝኵክሙ።
                    ******
፳፡ መሐርዎሙ ዘአዘዝኵክሙ ይዕቀቡ ዘአዘዝኵክሙ ብለህ ግጠም ያዘዝኋችሁን ሁሉ አስተምሯቸው።
ወናሁ አነ እሄሉ ምስሌክሙ በኵሉ መዋዕል እስከ ኅልፈተ ዓለም።
እኔም እነሆ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ባላችሁበት ዘመን አድሬባችሁ እኖራለሁ በሐዋርያት መላውን መናገር ነው።
                    ******
መልዓ ጽሕፈተ ብስራቱ ለማቴዎስ ሐዋርያ ፩ዱ እም ፲ወ፪ቱ ሐዋርያት።
ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ማቴዎስ የጻፈው ወንጌል ደረሰ ተፈጸመ፡፡
ወኮነ ጸሐፎ በፍልስጥኤም በአስተሐምሞ መንፈስ ቅዱስ እምድኅረ ዕርገቱ ለእግዚእነ ውስተ ሰማይ ዘበአጶሮግዮ በሰማኒት ዓመት።
ጌታ በሥጋ ወደ ሰማይ ከዐረገ በኋላ በስምንተኛው ዓመት መንፈስ ቅዱስ እያተጋው በፍልስጥኤም የጻፈው።
ወበቀዳሚት ዓመተ መንግሥቱ ለቀላውዴዎስ ቄሣር።
ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት።
ወስብሐት ለእግዘአብሔር።
አስጀምሮ ላስጨረሰን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን።
                    ******
ጥር 28/2011 ዓ.ም የጀመርነው የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ በዚህ ተፈጸመ፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
04/11/2011 ዓ.ም