====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፳፮።
******
፶፫፡ ይመስለክሙኑ ዘኢይክል አስተብቊዖቶ ለአቡየ ከመ ይፈኑ
ሊተ ዘይበዝኁ እም፲ቱ ወ፪ቱ ሠራዊተ መላእክት።
፶፫፡ ከአሥራ ሁለቱ ነገደ መላእክት የሚበዙትን ይልክልኝ ዘንድ
አባቴን መለመን መማለድ የማይቻለኝ ይመስላችኋልን
******
፶፬፡ ወባሕቱ እፎ ይትፈጸም ወይበጽሕ ቃለ መጽሐፍ ዘይቤ። ኢሳ
፶፫፥፲፡፡
******
፶፬፡ ነገር ግን መጽሐፍ የተናገረው እንደምን ይደርሳል ይፈጸማል
እኔ ካልሞትኩ ሲል ነው።
እስመ ከመዝ ሀለዎ ይኩን።
ይህ ይደረግ ዘንድ አለውና።
******
፶፭፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለሕዝብ ሶቤሃ ከመ ሠራቂኑ ትዴግኑኒ
መጻእክሙ በመጥባሕት ወበአብትር ተአኃዙኒ። ሰቆ ኤር ፬፥፳፡፡ ማር ፲፬፥፶፡፡ ሉቃ ፳፪፥፶፬፡፡ ዮሐ ፲፰፥፳፬።
******
፶፭፡ ሌባን አግባ መልስ ብሎ ቢጣላንሳ ብለው ሾተል ጎመድ ይዘው
በትኩስ ፍለጋ እንዲፈልጉት ሾተል ጎመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን አላቸው፡፡
ወዘልፈ እነብር ምስሌክሙ በምኵራብ ወእሜህር።
ዘወትር በምኵራብ ከእናንተ ጋራ ሳስተምር እኖር ነበር
በእፎ እንከ ኢአኃዝክሙኒ።
ለምን አልያዛችሁኝም።
******
፶፮፡ ወዝ ኵሉ ዘኮነ ከመ ይብጻሕ ወይትፈጸም ቃለ ነቢያት።
******
፶፮፡ ይህ ኵሉ የተደረገ ነቢያት የተናገሩት ነገር ይደርስ ይፈጸም
ዘንድ ነው።
ወእምዝ ኃደግዎ ኵሎሙ አርዳኢሁ ወጐዩ።
ከዘህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።
******
ዘከመ ቆመ ኢየሱስ በቅድመ ዓውድ።
፶፯፡ ወእለ አኃዝዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ወሰድዎ ኀበ ቀያፋ ሊቀ
ካህናት ኀበ ይትጋብኡ ጸሐፍት ወሊቃናት።
******
፶፯፡ ጌታን የያዙት ግን ሽማግሎች ወደ ተሰበሰቡበት የካህናት
አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ይዘውት ሄዱ፡፡
******
፶፰፡ ወተለዎ ጴጥሮስ እምርኁቅ እስከ ዓፀደ ሊቀ ካህናት።
******
፶፰፡ ጴጥሮስ እስከ ካህናት አለቃ ቦታ ድረስ በሩቅ ተከተለው።
ወቦአ ውሥጠ ወነበረ ምስለ መዓልት ይርአይ ማኅለቅቶ ለነገር።
የነገሩን ፍጸሜ ያይ ዘንድ ፩ዱን ቅጽር ገብቶ ተቀመጠ።
******
ወየኃሥሡ ሊቃነ ካህናት ወጸሐፍት ወሊቃናት ወኵሉ ዓውድ ሰማዕተ
ሐሰት በዘይሰቅልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ።
******
፶፱፡ ጸሐፍትና የካህናት አለቆች ሽማግሎችም ጌታን በሚገሉበት
ነገር ይገሉት ዘንድ የሐሰት መሳክርት ይሹ ነበረ።
******
፷፡ ወኢረከቡ ሎቱ ጌጋየ።
******
፷፡ አላገኙበትም።
ወመጽኡ ብዙኃን ሰማዕተ ሐሰት።
ብዙ የሐሰት ምስክሮች መጡ
ወስእኑ ቦቱ ነገረ።
መርታት ተሳናቸው ማለት ነውር አጡበት።
ወድኅረ መጽኡ ፪ቱ።
ከዚህ በኋላ ዕውነተኞች ናቸው የሚባሉ ሁለት ሰዎች መጡ
******
፷፩፡ ወይቤሉ ይቤ ዝንቱ እክል ነሢቶቶ ለቤተ እግዚአብሔር ወበሣልስት
ዕለት አኀንጾ፡፡ ፪፥፲፱፡፡
******
፷፩፡ ይህ ቤተ መቅደስን አፍርሼ በሦስተኛው ቀን አንጸዋለሁ
አለ አሉ።
******
፷፪፡ ወተንሥአ ሊቀ ካህናት ወይቤሎ ኢትሰምዕኑ እንዘ መጠነዝ
ያስተዋድዩከ እሉ።
******
፷፪፡ ሊቀ ካህናቱ ተነሥቶ ይህን ያህል ሲያጣሉህ ሲያካስሱህ
አትሰማምን አለው፡፡
******
፷፫፡ ወኢያውሥአ እግዚእ ኢየሱስ
******
፷፫፡ ጌታ አልመለሰለትም።
(ሐተታ) ነገሩ ተርታ ቢሆንበት እንዳልፈራ ለማጠየቅ እንዳይቀርለት
ያውቃልና ለጥብዓት ለትአግሥት አብነት ለመሆን።
ወይቤሎ ሊቀ ካህናት አመሐልኩከ በእግዚአብሔር ሕያው ከመ ትንግረኒ
እመ አንተሁ ውእቱ ክርስቶስ ወልዱ ለእግዚአብሔር። እስከ ክርስቶስ ተብሎ የተነገረልህ የሕያው የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ አንተ
እንደሆንከ ትነግረኝ ዘንድ በሕያው እግዚአብሔር አማጽኜሀለሁ አለው።
******
፷፬፡ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ አንተ ትቤ። ማቴ ፲፮፥፳፯፡፡
ሮሜ ፲፬፥፲፡፡ ፩፡ተሰሎ ፬፥፲፭።
******
፷፬፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንተ ትላለሀ አለው።
ወባሕቱ እብለክሙ እምይእዜሰ ትሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው
እንዘ ይነብር በየማነ ኃይል።
ነበረ ካልኩ ብሎ የማን ብሏል እንጂ በክብር ሲል ነው ከአንግዲህስ
ወዲህ ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስን በአብ ዕሪና ታዩታላችሁ።
አንድም በየማነ ኃይል ዓለምን በማሳለፍ ኃይል ባለው ዕሪና
ወይመጽእ በደመና ሰማይ።
በባሕርይ ክብሩ መጥቶ ታዩታላችሁ።
(ሐተታ) የደብረ ታቦር የዕርገት የምጽአት ደመና የባሕርይ ክብሩ
ነው።
አንድም በሥጋ ማርያም መጥቶ ሰማይ ዳግሚት እንዲል።
አንድም በክበበ ትስብእት መጥቶ።
******
፷፭፡ ወሠጠጠ አልባሲሁ ሊቃነ ካህናት።
******
፷፭፡ በገዛ እጄ ፈጣሪዬን ላሰድብ ብሎ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን
ቀደደ።
(ሐተታ) በኃዘን ምክንያት ልብሱን የቀደደ ፊቱን የነጨ እንደሆነ
ይሽር ትላለች ኦሪት። ጌታ እንደ ተሾመበት እሱ እንደተሻረ ለማጠየቅ።
እንዘ ይብል ምንተ እንከ ትፈቅዱ ሎቱ ሰማዕተ።
ምን ምስክር ትሹለታላችሁ።
ናሁ ጸረፈ።
ይሳደባል ማለት እነሆ አምላክ ነኝ አለ።
ወሰማዕክሙ ጽርፈቶ።
አምላክ ነኝ ሲል ሰምታችኋል፡፡
******
፷፮፡ ምንተ እንከ ትብሉ። ኢሳ ፶፥፮። ማር ፲፬፥፷፭።
******
፷፮፡ ምን ትፈርዳላችሁ።
ወአውሥኡ ወይቤሉ ዝንቱ ድልው ለሞት።
ይህ ሞት ያገባዋል አሉ።
******
፷፯፡ ወእምዝ ተፍኡ ውስተ ገጹ።
******
፷፯፡ ከዚህ በኋላ በፊቱ ተፉበት፡፡
ወኢይትሀከዩ ወሪቀ ውስተ ገጽየ።
ወኢሜጥኩ ገጽየ እምኃፍረተ ምራቅ ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም።
አንድም አዳምን ዲያብሎስ በገጸ ልቡናው ምራቀ ምክሩን እየተፋ
ገሃነም አውርዶት ነበርና ለእሱ ካሣ ሊሆን።
******
፷፰፡ ወኰርዕዎ።
******
፷፰፡ ራሱን በዘንግ መቱት።
ወኵሉ ርእስ ለሕማም ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም። አንድም
ዲያብሎስ የአዳምን ርእሰ ልቡናውን በዘንግ እየመታ ገሃነም አውርዶት ነበርና ካሣ ሊሆን።
ወጸፍዕዎ
ፊቱን በሻሽ ሸፍነው መቱት
እንዘ ይብሉ መኑ ውእቱ ክርስቶስ ዘጸፍዓከ።
ክርስቶስ በጥፊ የመታህ ማነው ንገረን እያሉ።
(ሐተታ) አዳምና ሔዋን የአምላክነት ዕውቀት እንወቅ ብለው ገሃነም
ወርደው ነበርና ለእሳቸው ካሣ ሊሆን
******
በእንተ ክህደተ ጴጥሮስ።
፷፱፡ ወጴጥሮስ ሀሎ ይነብር አፍአ ውስተ ዓፀድ። ሉቃ ፳፪፥፶፫-፸፡፡
ዮሐ ፲፰፥፲፯።
******
፸፡ ጴጥሮስ ግን አንዱን ቅጽር ገብቶ ተቀምጦ ነበር
ወመጽአት ኀቤሁ አሐቲ ወለት ወትቤሎ አንተሂ ምስለ ኢየሱስ ገሊላዊ
ሀለውከ።
አንዲት ብላቴና መጥታ አንተም ከገሊላዊ ከኢየሱስ ጋራ ነበርክ
አለችው።
******
፸፡ ወክሕደ በቅድመ ኵሉ ሕዝብ አንሰ ኢየአምሮ ዘትብሊ።
******
፸፡ የምትዪውን አላውቀውም ብሎ በጉባዔ ካደ።
******
፸፩፡ ወወጺኦ ኖኅተ ርእየቶ ካልዕተ ወለት።
******
፸፩፡ አንዱን በር ወጥቶ ሳለ ሌላዪቱ አየችው።
ወትቤሎሙ ለእለ ይቀውሙ ዝኒ ሀሎ ምስለ ኢየሱስ ናዝራዊ።
ተቀምጠው ላሉት ይህም ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋራ ነበር አለቻቸው።
******
፸፪፡ ወክህደ ከዕበ።
******
፸፪፡ ሁለተኛ ካደ።
ወመሐለ ከመ ኢየአምሮ ለውእቱ ብእሲ።
ያን ሰው አላውቀውም እንዳላውቀው ብሎ ማለ፡፡
******
፸፫፡
ወጐንድዮ ሕቀ መጽኡ እለይቀውሙ።
******
፸፫፡ ጥቂት ቆይቶ የተቀመጡት መጡ።
ወይቤልዎ ለጴጥሮስ አማን አንተሂ እምኔሆሙ።
አንተም በእውነት ከእሳቸው ወገን ነህ አሉት።
ወነገርከ ያዔውቀከ።
በአነጋገርህ ትታወቃለህ።
******
፸፬፡ ወእምዝ መሐለ ወተረግመ ከመ ኢየአምሮ ለውእቱ ብእሲ።
******
፸፬፡ የያዘውን ጥሎ እንዲህ ይጣለኝ የእሱን ሞት ለእኔ ያድርገው
ያን ሰው አላውቀውም ብሎ ማለ፡፡
******
፸፭፡ ወተዘከረ ጴጥሮስ ቃሎ ለእግዚእ ኢየሱስ ዘይቤሎ ሥልሰ ትክህደኒ ዘእንበለ ይንቁ ዶርሆ
******
፸፭፡ ጴጥሮስም ጌታ ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለውን
አሰበ።
ወወፅአ አፍአ ወበከየ ብካየ መሪረ።
ከአፍአ ወጥቶ ጽኑ ኃዘን አዘነ፡፡
(ሐተታ) ከሁሉ ይልቅ እኔ እወደው ከሁሉ አስቀድሞ እኔ እክደው
ብሎ አዘነ። የአዳም የዳዊት የቅዱስ ጴጥሮስ ኃዘን አንድ ነው ሳይሰቀቁ እንባቸው እንደሰን ውሀ ይወርዳል።
******
ምዕራፍ ፳፯።
፩፡ ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ወሊቃናተ ሕዝብ ይቅትልዎ
ለእግዚእ ኢየሱስ።
፩፡ ሲነጋ በነጋ ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝቡም አለቆች ጌታን
ሊገሉት እንግደለው ብለው መከሩ።
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
27/10/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment