Sunday, July 7, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 129

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፳፯።
                    ******
፩፡ ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ወሊቃናተ ሕዝብ ይቅትልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ።
                    ******
፩፡ ሲነጋ በነጋ ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝቡም አለቆች ጌታን ሊገሉት እንግደለው ብለው መከሩ።
                    ******
፪፡ ወአሢሮሙ ወሰድዎ ወመጠውዎ ለጲላጦስ መስፍን። ማር ፲፭፥፩። ሉቃ ፳፫፥፩። ዮሐ ፲፰፥፳፰።
                    ******
፪፡ አስረው ወስደው ለጲላጦስ ሰጡት።
(ሐተታ) አዳምን ለመኰንነ ገሃነም አሳልፎ ሰጥቶ ነበርና ለእሱ ካሣ ሊሆን።
                    ******
በእንተ ቀቢፀ ተስፋ ዘይሁዳ፡፡
፫-፬፡ ወእምዝ ሶበ ርእየ ይሁዳ ዘአግብኦ ከመ አስርህዎ አግብአ ውእተ ፴ ብሩረ ለሊቃነ ካህናት ወለሊቃውንተ ሕዝብ እንዘ ይብል አበስኩ ዘአግባዕኩ ደመ ንጹሐ ወአቅተልኩ ብእሴ ጻድቀ።
                    ******
፫-፬፡ ከዚህ በኋላ ያሲያዘው ይሁዳ አስርህዎ እንዳደከሙት አርስህዎ ኃጥእ ብለው እንደፈረዱበት ከመ ረስሐ ወከመ ተኰነነ ኃጥእ ተብሎ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ። ኦሪት ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ። ያለችውን አፍርሼ ንጹሕ ደም ያስፈሰስኩ ደግ ሰው ያስገደልኩ አላበጀሁም ብሎ ያን ሠላሳ ብር ለሊቃነ ካህናት ለሕዝቡ አለቆች መልሶ ወስዶ ሰጠ፡፡
(ሐተታ) እሱም በተአምራቱ ይድናል። እኔም ገንዘቤን እንደያዝኩ እቀራለሁ ብሎ ሸጦት ነበርና።
ወይቤልዎ ሚ ላዕሌነ ወሚ ላዕሌከ።
ይሁዳ የወደድነውን ሰጠኸን የወደድከውን ሰጠንህ ከእንግዲ ወዲህ ለአንተ ከእኛ ምን አለህ ለእኛስ ከአንተ ምን አለን።
ለሊከ አእምር ለርእስከ።
አንተ ለራስህ ዕወቅ አሉት።
                    ******
፭፡ ወገደፈ ውእተ ብሩረ ውስተ ምኵራብ ወሖረ ወተሐንቀ ወሞተ። ግብ ፩፥፲፰።
                    ******
፭፡ ያን ብር ከምኵራብ ደጅ አፍሶት ሄዶ ታንቆ ሞተ
                    ******
፮፡ ወነሥኡ ሊቃነ ካህናት ውእተ ብሩረ ወይቤሉ ኢይደልወነ ንደዮ ውስተ ወርቀ መባዕ እስመ ሤጠ ደም ውእቱ
                    ******
፮፡ ሊቃነ ካህናት ያን ብር አንስተው የደም ዋጋ ነውና ከመባዕ ልንጨምረው አይገባንም አሉ።
(ሐተታ) በሀገራቸው የደም ዋጋ ሤጠ ከልብ አስበ ደነስ ከመባዕ አያገቡም ነበርና፡፡
                    ******
፯፡ ወተማኪሮሙ ተሣየጡ ቦቱ ገራህተ ለብሐዊ ለመቃብረ እንግዳ
                    ******
፯፡ ለመፃተኛ ለስደተኛ መቀበሪያ ሊሆን መክረው ቦታ ገዙበት
(ሐተታ) ከጣዖት ከኃጢአት ፈልሶ ለመጣ መከበሪያ ሊሆን ምዕመናን ጥምቀትን ገንዘብ ማድረጋቸውን መናገር ነው፤
                    ******
፰፡ ወተሰምየ ውእቱ ገራኅት ገራኅተ ደም እስከ ዮም፡፡ ግብ ፩፥፲፱፡፡
                    ******
፰፡ ያ ቦታ እስከአሁን ድረስ የደም ምድር ሲባል ይኖራል፤
                    ******
፱፡ ወይእተ አሚረ በጽሐ ቃለ ኤርምያስ ነቢይ ዘይቤ ነሥኡ ፴ ብሩረ ሤጦ ለክቡር ዘአክበርዎ እምደቂቀ እስራኤል ወወሀብዎ ለገራህት ለብሐዊ፡፡ ዘካ ፲፩፥፲፪፡፡
                    ******
፱፡ ደቂቀ እስራኤል በሆሣዕና ያከበሩትን ከደቂቀ እስራኤል ተለይተው የክቡርን ዋጋ፡፡
አንድም ዘተከሀሉ ይላል ደቂቀ እስራኤል የተስማሙበትን ለገራህተ ለብሐዊ የሰጡትን የክብሩን ዋጋ ወሰዱ ብሎ ኤርምያስ የተናገረው ደረሰ ተፈጸመ።
                    ******
፲፡ በከመ አዘዘኒ እግዚአብሔር ወወሀብዎ ለገራህተ ለብሐዊ
                    ******
፲፡ ማለትን እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እናገራለሁ አለ። የማይገባ ማለት ነው።
                    ******
ዘከመ ቆመ እግዚእ ኢየሱስ ቅድመ ጲላጦስ፣
፲፩፡ ወቆመ እግዚእ ኢየሱስ ቅድሜሁ ለመስፍን፡፡ ማር ፲፭፥፪፡፡ ሉቃ ፳፫፥፫፡፡ ዮሐ ፲፰፥፴፫።
                    ******
፲፩፡ ጌታ ከጲላጦስ ፊት ቆመ።
ወሐተቶ ወተስእሎ መስፍን።
ጲላጦስ ጠየቀው።
ወይቤሎ አንተኑ ንጉሦሙ ለአይሁድ።
የአይሁድ ንጉሣቸው አንተ ነህን አለው፡፡
ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ አንተ ትቤ።
አንተ ትላለህ አለው፡፡
አንድም አንተ የአንድ መንደር ንጉሥ ታደርገኛለህ።
                    ******

፲፪፡ ወእንዘ ያስተዋድይዎ ሊቃነ ካህናት ወሊቃውንተ ሕዝብ አልቦ ዘያወሥኦሙ ወኢምንተኒ።
                    ******
፲፪፡ የሕዝቡ አለቆችና የካህናት አለቆች ሲያሳጡት ሲያጣሉት ምንም ምን የመለሰላቸው ምላሽ የለም፡፡
                    ******
፲፫፡ ወእምዝ ይቤሎ ጲላጦስ ኢትሰምዕኑ እንዘ መጠነዝ ያስተዋድዩከ።
                    ******
፲፫፡ ይህን ያህል ሲያሳጡህ ሲያክስሱህ አትሰማምን አለው።
                    ******
፲፬፡ ወኢያውሥአ ወኢ አሐተሂ ቃለ፤
                    ******
፲፬፡ ጥቂት ስንኳን አልመለሰለትም፡፡
(ሐተታ) እንዳለፈው።
እስከ ያነክር መልአክ።
ጲላጦስ ይህን ያህል ትእግሥት ብሎ እስኪያደንቅ ድረስ
                    ******
ዘከመ ኃረይዎ ለበርባን እምነ ኢየሱስ ወከመ ኰነንዎ።
፲፭፡ ወቦ ልማድ ለመስፍን ያሕዩ ለሕዝብ ፩ደ እምውስተ ሙቁሐን ዘፈቀዱ።
                    ******
፲፭፡ ከታሠሩት የወደዱትን ይፈታላቸው ዘንድ ለጲላጦስ ልማድ ነበረው።
አንድም ቦሙ ልማድ ይላል በዓመት በዓመት ለበዓለ ፋሲካ ከእስር ቤት ገብተው የወደዱትን ይፈቱ ዘንድ ለሕዝቡ ልማድ ነበራቸው።
(ሐተታ) በግብፅ ሳሉ ሁለት እስሮች ነበሯቸው እነዚያን ፈተው ይዘው ወጥተዋልና። በግብፅ ሳሉማ ምን ዕሥር ነበራቸው ብሎ በግብፅ መኖራቸውን እንደ መታሰር። ከግብፅ መውጣታቸውን እንደ መፈታት አድርገውት በበዓል አንድ አንድ እሥር ይፈቱ ነበርና በዚያ ልማድ።
                    ******
፲፮፡ ወቦ አሜሃ ሙቁሕ ዘስሙ በርባን ስሙዕ።
                    ******
፲፮፡ ያን ጊዜ በርባን የሚባል የታወቀ እስር ነበር
ወየአምሮ ኵሉ።
ወንበዴ መሆኑን ሁሉ ያውቀዋል።
                    ******
፲፯፡ ወእንዘ ጉቡዓን እሙንቱ ይቤሎሙ ጲላጦስ ለሕዝብ መነ ትፈቅዱ አሕዩ ለክሙ።
                    ******
፲፯፡ እሳቸው በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ ማን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ፡፡
በርባንሃኑ።
በርባንን ነውን።
ወሚመ ኢየሱስሃኑ ዘይብልዎ ክርስቶስ  .
ወይም ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ነው አላቸው።
                    ******
፲፰፡ እስመ የአምር ከመ በቅንዓቶሙ አግብእዎ።
                    ******
፲፰፡ ጠልተው ተመቅኝተው ቀንተው ለሕማም ለሞት አሳልፈው እንደሰጡት ያውቃልና።
                    ******
፲፱፡ ወእንዘ ይነብር ጲላጦስ ዓውዶ ለአከት ኀቤሁ ብእሲቱ።
                    ******
፲፱፡ በአደባባይ ተቀምጦ ነገር ሲሰማ ሚስቱ ላከችበት አብሮቅላ ትባላለች።
እንዘ ትብል ዑቅአ ኢተአብስ ላዕለ ውእቱ ጻድቅ።
ያን ደግ ሰው እንዳትበድል አስተውል ብላ።
እስመ ብዙኃ ሐመምኩ በዛቲ ሌሊት በሕልምየ በእንቲአሁ
በዚች ሌሊት በሱ ምክንያት በሕልሜ ብዙ ሥቃይ ሳይ አድሬአለሁና።
(ሐተታ) ምን ስታይ አድራለች ቢሉ እሱን ዘንዶ ሲውጠው እሷን በእሳት አለንጋ ሲገርፏት አይታለች ይህን ልካበታለች። አብረው አድረው አልነበረም ቢሉ እነግረዋለሁ ስትል አንበሳ መደብ ወጣ፤ ሲመለስ እነግረዋለሁ ስትል ጩኸት ሰምቶ ወጣ በዚያው እንደወጣ ቀርቷል፡፡
አንድም ዶርታ መከራ የሚባሉ ከተወለዱ ጀምሮ ተናግረው ሰምተው የማያውቁ ልጆች ነበሯቸው ንጹሕ ደም ለሚያፈስ ለዚያ ለባልሽ ወዮለት ብለዋታል ይኸን ልካበታለች።
                    ******
፳፡ ሊቃነ ካህናትሰ ወሊቃውንተ ሕዝብ ኄጥዎሙ ለሕዝብ ወኦሆ አበልዎሙ ከመ በርባንሃ ያሕዩ ሎሙ ይስአሉ ወኢየሱስሃ ይቅትሉ፡፡ ማር ፲፭፥፲፩፡፡ ሉቃ ፳፫፥፲፰፡፡ ዮሐ ፲፰፥፵፡፡ ግብ ፫፥፲፬።
                    ******
፳፡ የሕዝቡ አለቆችና ሊቃነ ካህናት ግን በርባንን አድንልን ኢየሱስን ስቀልልን ብለው ይለምኑ ዘንድ ሕዝቡን አባበሏቸው እሽ በጄ አሰኝዋቸው።
                    ******
፳፩፡ ወአውሥአ መስፍን ወይቤሎሙ መነ ትፈቅዱ እም፪ሆሙ አሕዩ ለክሙ።
                    ******
፳፩፡ ጲላጦስ መለሰ ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ አላቸው።
ወይቤሉ በርባንሃ።
በርባንን ነው አሉ።
                    ******
፳፪፡ ወይቤሎሙ ጲላጦስ ምንተ እንከ እሬስዮ ለኢየሱስ ዘተብህለ ክርስቶስ።
                    ******
፳፪፡ ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ምን አደርገዋለሁ።
አንድም እረስዮ ይላል ምን ላድርገው አላቸው፡፡
                    ******
፳፫፡ ወይቤሎሙ ኵሎ ስቅሎ።
                    ******
፳፫፡ ሁሉም ስቀለው አሉ።
ወይቤሎሙ መስፍን ምንተ እኵየ ገብረ።
ምን ክፉ ሥራ ሠራ አላቸው፡፡
ወአፈድፈዱ ጸሪሃ እንዘ ይብሉ ስቅሎ ስቅሎ።
ስቀለው ብንልህ ስቀለው አሉ።
                    ******
፳፬፡ ወእምዝ ሶበ ርእየ ጲላጦስ ከመ አልቦ ዘይበቁዕ ዘእንበለ ዳዕሙ ዘይበዝኅ ሀከክ።
                    ******
፳፬፡ ጸብዕ ክርክር እየጸና ከመሄድ በቀር የሚረባው የሚጠቅመው ነገር እንደሌለ ጲላጦስ ባየ ጊዜ
ነሥአ ማየ ወተሐፅበ እዴሁ በቅድሜሆሙ ለሕዝብ እንዘ ይብል ንጹሕ አነ እምደሙ ለዝ ብእሲ ጻድቅ።
ውሀ አስመጥቶ በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ንጹሕ ነኝ ብሎ በአደባባይ እጁን ታጠበ በአዕሩገ እስራኤል ልማድ።
(ታሪክ) ከሀገርና ከሀገር መካከል ሰው ሙቶ የተገኘ እንደሆነ ያሰው ለሞተበት አቅራቢያ ለሚሆን አገር ሰዎች ውሀ በመንቀል ይዘው ጊደር ነድትው ከበረሀ ይወርዳሉ ቋንጃዋን ይመቷታል ትወድቃለች የዚህን ሰው ደም አላፈሰስንም ያፈሰሰውንም አላየንም ብለው ይታጠባሉ ከገዳዩ ወገን ሲደርስ መወየብ ይጀምራል እሱ ሲሆን ፈጽሞ ደም ይሆንበታል። ምዕመናን ጥምቀትን ገንዘብ ማድረጋቸውን መናገር ነው።
አንትሙ ለሊክሙ አእምሩ።
እናንት ለራላችሁ እወቁ።
                    ******
፳፭፡ ወአውሥኡ ኵሉ ሕዝብ ወይቤሉ ደሙ ላዕሌነ ወላዕለ ውሉድነ፡፡
፳፭፡ ደሙ በእኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ፤
                    ******
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
01/11/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment