Monday, June 5, 2017

የኮሚቴው ሪፖርት



© መልካሙ በየነ

ግንቦት *23*/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
ዕለቱ ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም ኆህተ ሰማይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወእስጢፋኖስ አዲስ ህንጻ ቤተክርስቲያን ምረቃ ነው፡፡ አቡነ ማርቆስ በቦታው ተገኝተዋል፡፡ እርሳቸውም በተከታታይ የለጠፍነውን ትምህርት አስተማሩ፡፡ ከዚያም ጸበሉን ሊባርኩ ሄዱ ከዚያም ተመልሰው መጡ እና የኮሚቴው ሪፖርት እንዲህ ቀረበ፡፡ “በመቀጠል ይህንን ሪፖርት እንዳቀርክ በብጹእ አባታችን በጎ ፈቃድና በህዝበ ክርስቲያኑ ስም አመሰግናለሁ፡፡ የሰላም የፍቅር የልማት አባት በሆኑት በብጹእ አባታችን አቡነ ማርቆስ… የካቲት 05/2008 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ መጣሉ ይታወቃል…” አለ፡፡ ቀጥሎም ሌሎችን ንግግሮች ተናገረ፡፡ ከዚያም ቤተክርስቲያኑን ለመሥራት የወጣውን ወጭ ይዘረዝራል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር የሰላም አባት የሚለው ነው፡፡ ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ደብዳቤ የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳድር ፀጥታ ዘርፍ ቀጥታ ለአቡነ ማርቆስ የጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡  ብጥብጥ እየፈጠሩ ስለሆነ ከዚህ ድርጊትዎ እንዲታቀቡ የሚል ደብዳቤ ነው፡፡ አንብቡት እሱን ለእናንተ ተውኩት እኔ ግን ወደ ሪፖርቱ ልገባ ነው፡፡
1.  ቆርቆሮ በብዛት 180 በ24 ብር ድምር 22320 (***የ24 ብር ቆርቆሮ አለ እንዴ???***)
2.  እንጨት 20000 ብር
3.  ድንጋይ በሜትር ኩብ 7 በ1400 በድምር 9800 ብር
4.  ሲሚንቶ 75 ኩንታል በ245 ብር በድምር 18376 ብር
5.  አሸዋ 2 ባጆ በ2240 ድምር 4800 (**የማባዛት ስህተት**)
6.  አሸዋ 1 ባጆ በሲኖ 5500 ብር 2000 ብር በነጻ
7.  ግንባታ ሰራተኛ 10000 ብር
8.  ለአናፂ 5000 ብር
9.  ለቤተክርስቲያን አናፂ 600 ብር
10. ምስማር 55 ኪሎ በ32 ብር በድምር 18700 ብር
11. ቀን ሰራተኛ 40 ሴት 40 ወንድ በ80 ብር በድምሩ 3200 ብር (** ይፈተሸ**)
12. ቀን ሰራተኛ 50 ሴት በ50 ብር በድምር 2500 ብር
13. የቀን ሰራተኞች 55 19 በ120 ብር በድምር 1800 (***ምን ማለት ነው**)
14. ኮርኒስ ቀለም ሰራተኛ 7020 ብር
15. መስኮት 6 በ1400 ብር በድምሩ 8400 ብር
16. በር መዝጊያ 2 በ3000 ብር በድምር 6000 ብር
17. በር መዝጊያ ጠበብ ያሉ 4 መስኮቶች በ2500 ብር በድምሩ 10000 ብር
18. ጉልላት 1500 ብር
19. ጉልላት ዝቅተኛ 1200 ብር
20. የህብረተሰብ ተሳትፎ ወደ 500 ሰው በ70 ብር 35000 ብር
21. ጽላት መግዣ 10000 ብር
22. ጽላት ማምጫ 10500 ብር
23. ከተለያዩ ግለሰቦች ለማስመረቂያ እና ለልዩ ልዩ ወጭ 21118 ብር
በጠቅላላ ድምር 211704 ብር፡፡
ብድር 21558 ብር፡፡
እዚህ ላይ በጣም የሚገርሙ ወጭዎችን ሰምተናል፡፡
1.  ጽላት መግዣ--- 10 ሺ ብር
2.  ጽላት ማምጫ 10 ሺ 500 ብር
3.  ማስመረቂያ ወጭ 21118 ብር
ጽላቱን ከማን ነው የገዙት? ከየትስ ነው የገዙት? ከየት ወዴት ለማጓጓዝ ነው 10 ሺ 500 ብር የሚፈጀው? ቪዲዮው ላይ እንደምትሰሙት ጽላት መግዣ--- 10 ሺ ብር ካለ በኋላ ማምጫ በል ተብሎ መሠለኝ ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ ጽላት ማምጫ ብሎ 500 ብር ጨምሮ 10500 ብር ብሏል፡፡ ጽላቱ ከአሜሪካ እንኳ ቢመጣ 10500 ብር በምን መልኩ ሊፈጅ ይችላል፡፡ ይች 10 ሺ ብር ማን ኪስ ገባች ብለህ ጎንቻ አፍጥጠህ ጠይቅ፡፡ ከመቼ ወዲህ ነው ጽላት ተገዝቶ የሚመጣ? ሌላው ለማስመረቂያ ወጣ የተባለው 21118 ብር ለምን አገልግሎት ዋለ ብለህ ጎንቻ ወትውት፡፡ ምናልባት አቡነ ማርቆስ እና አብረዋቸው የመጡት ሁለቱ መነኮሳት የተካፈሉት በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ከሆነ በግልጽ ጠይቅ በግልጽም ይመለስ፡፡ ሌላው 215580 ብር ብድር አለብን ያለው ኮሚቴ 21118 ብር ግን ለማስመረቂያ ብሎ አውጥቷል እንዴት ለምን ብለህ ጠይቅ ይህ ለጎንቻዎች ጥያቄ መሆን አለበት፡፡
ሌላው ኮሚቴው አቡነ ማርቆስ ሲሉት የዋሉትን የጥምቀት ጉዳይ እንደመፈክር ሲያሰማ ተሰምቷል፡፡ ዳግም ጥምቀት የፈቀደ ሰው ማነው ዳግምስ የተጠመቀ ማነው? በቅባት እምነት ውስጥ ያሉ ሁሉ ተምረው ተዋሕዶ ለመሆን ይጠመቃሉ አራት ነጥብ!!!!
ሌለው አቡነ ማርቆስ ስእለት አስገቡ ሲሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚያወራ ሰው ነበር፡፡ “አውቆ አበድ” ብለው የሰደቡት ማለት ነው፡፡ እሱ ነው ዲቁና ስጡኝ ያላቸው መኪናቸውንም መስታወቷን የሠበራት፡፡
ከዚህ ጉባዔ በኋላ ሞጣ ገብተዋል፡፡ ሞጣ ሄደውስ ምን አሉ???

“ስለ እስጢፋኖስ አይገባንም (ገ ላልቶ ይነበብ)”-- አቡነ ማርቆስ



© መልካሙ በየነ

ግንቦት 23/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


ስለ ሊቀዲያቆናት ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ መድረክ ላይ ቆሞ መናገር አይገባም (ገ ይላላ)፡፡ ዕለቱ ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም ኆህተ ሰማይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወእስጢፋኖስ አዲስ ህንጻ ቤተክርስቲያን ምረቃ ነው፡፡ አቡነ ማርቆስ በቦታው ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ቦታ የመገኘት ዋና ምክንያቱ ቅዳሴ ቤቱን ለመባረክ አይደለም፡፡ በምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት የተነሣባቸውን የምእመናን ተቃውሞ ይደግፉኛል ብለው ለሚተማመኑባቸው የጎንቻ ምእመናን ለማሳወቅ ነው፡፡ እርሳቸው በሦስቱ እነሴዎች ማለትም በጎንቻ ሲሶ እነሴ (ጉንደ ወይን) በሁለት እጁ እነሴ (ሞጣ) እና በእነብሴ ሣር ምድር (መርጡለ ማርያም) እየተዟዟሩ የህዝበ ክርስቲያኑን ይሁንታ በመለመን ላይ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የጎንቻን ህዝብ በሙሉ ከዚህ ከሚባረከው አዲሱ ህንጻ ቤተክርስቲያን እንዲገኝ ካደረጉ በኋላ የራሳቸውን መልእክት በሚገባ አስተላልፈዋል፡፡
ስለእስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማእትነት ሊቀ ዲያቆንነት ብነግራችሁ አይገባችሁም በማለት ለህዝቡ ይገባዋል (ገ ይላላ) ያሉትን የግብርና ሙያ ለአንድ አዛውንት ቃለ መጠይቅ በማድረግ ሲያስተምሩ ታይተዋል፡፡  እርሳቸው የተሾሙት የግብርና ሙያን ሊያስተምሩ ነውን?  የወንጌል አባት ናቸው በማለት የሚክቧቸው ወገኖችም ወንጌል ከቀዳሜ ሰማእት ከሊቀ ዲያቆን እስጢፋኖስ ይልቅ መሬት እንዴት እንደሚታረስ አብልጦ ከመሰከረ መረጃውን አሳዩን፡፡
ካህናቱን ስለእርሻ እንዳልጠይቃቸው የእነርሱ እርሻ የምእመናንን አእምሮ ማለስለስ እንጅ መሬትን ማለስለስ አይደለም፡፡ በዚያም ላይ እግዚአብሔር በጎቸን ጠብቀሀልን ብሎ እንጅ መሬትን ስለማለስለስ አይጠይቃቸውም፡፡ ይህንን የሚጠየቁ ገበሬዎች ናቸው በማለት ነው አንዱን አዛውንት እያስጨበጨቡ የጠሯቸው፡፡ አይ የወንጌል አባት! ካህኑን ሌላ ምእመኑን ሌላ የሚጠይቅ እግዚአብሔር ነው ያለን ማለት ነው ለካ፡፡ ካህኑን ስለእረኝነቱ ገበሬውን ስለ ሞዴል አርሶ አደርነቱ ነው የሚጠይቀው ብለውን አረፉት እኮ፡፡ ብራብ አላበላኸኝም፤ ብጠማ አላጠጣኸኝም፣ እንግዳ ብሆን አልተቀበልከኝም፤ ብታረዝ አላለበስከኝም፤ ብታሰር አላስፈታኸኝም፣ ብታመም አልጠየቅኸኝም ብሎ ይጠይቃል እንጅ መሬትህን ስንት ጊዜ አረስከው ብሎ ይጠይቃል የሚል ትምህርት ተምረንም ሰምተንም አናውቅም፡፡
አዛውንቱ ሲመጡ “አጨብጭቡላቸው” በማለት ህዝቡን በማይቋረጥ ጭብጨባ እንዲያጅቧቸው አደረጉ፡፡ የሆነ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የመጣ ነው የሚመስለው፡፡ “ተጨብጭቦላቸው አያውቅም ነበር የዓመቱን ነው ዛሬ የተጨበጨበላቸው” በማለትም ህዝቡን ፈገግ አደረጉ፡፡ ልብ በል ወገኔ ንቃ! ይህ አካሄድ የቤተክርስቲናችን አካሄድ አይደለም ሥርዓትም አይደለም፡፡ ይህ የመናፍቃን ድብቅ ተልእኮ ነው፡፡ መናፍቃኑ መድረክ ላይ ወጥተው ስለቅዱሳን ከመናገር ይልቅ የሆነ ያልሆነ ዋዛ ፈዛዛ ነገርን በመናገር በማሳቅ ጊዜን የሚያባክኑ ከንቱዎች ናቸው፡፡ እርሳቸውም ስለእስጢፋኖስ ከመናገር ከመማማር ይልቅ ስለግብርና እንማር በማለት ይህን መድረካችን ላይ መፈጸማቸው ተልእኳቸውን እንድናጤን በር ከፋች ነው፡፡ ለማንኛውም ቪዲዮውን ተመልከቱት፡፡ አስተያየታችሁንም ለግሱን!!!

“አታላይ ሌባ አንት ቀጣፊ አፈር ያብላህ ይህ ሌባ! እርጉምማ እርጉም ነህ!”-- አቡነ ማርቆስ



© መልካሙ በየነ

ግንቦት 23/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
በቅድሚያ ሰበር ዜና ይቅደም!
ግርማ እስቲያውቅ ይባላል የጎንቻ ልጅ ነው፡፡ አእምሮው የተነካ ነው የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አገልጋይ ናቸው አባቱ እስቲያውቅ፡፡ ታዲያ የአእምሮ በሽተኛ የሆነው ልጃቸው ግንቦት 19/2009 ዓ.ም አቡነ ማርቆስ ከሚባርኩት አዲሱ ህንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝቷል፡፡ “አባ ማርቆስ ዲቁና ይስጡኝ፡፡ አርስዎ በመኪና እየተንፈላሰሱ እኔ በእግሬ እሄዳለሁ” አላቸው፡፡  ከዚያም ጥቂት ዝም ብሎ ቆየ፡፡ አቡነ ማርቆስ ቅዱስ እስጢፋኖስ ብለው ሲናገሩ ሲሰማ “የባህርዳር እስጢፋኖስ ዲያቆን አድርገው ይሹሙኝ” አላቸው፡፡ ከዚያ እርሳቸውም “አንተ አውቆ አበድ ከእነርሱ ወገን ትሆናለህ፡፡ ቁጭ በል! ቁጭ በል በሉት እባካችሁ” አሉ “ከእነርሱ” የተባለ ከተዋሕዶ ልጆች ጋር ማለታቸው ነው፡፡ ከዚያም “ተው ተው” ተባለ ዝም አለ፡፡ አቡነ ማርቆስ ጸበል ሊባርኩ ሲሄዱ መኪናቸውን መንገድ ዳር ያገኛታል፡፡ የዚህን ጊዜ ድንጋይ አንሥቶ በሹፌሩ በኩል ያለውን መስታወት ያረግፈዋል፡፡ ምናልባትም ወደፊት የመኪና መግዣ በሚል ገንዘብ አዋጡ ልንባል እንደምንችል እገምታለሁ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 19/2009 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ የጎንቻ ሲሶ እነሴ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ዐዋጅ ታወጆባቸዋል፡፡ ዐዋጅ ዐዋጅ ዐዋጅ አሉ አቡነ ማርቆስ ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም የኆህተ ሰማይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተሠርቶ ስለተጠናቀቀ ቅዳሴ ቤቱን ስለምባርክ እዚህ ቦታ እንድትሰበሰቡ ይሁን የትም አጥቢያ ቢሆን የቅዳሜው ቅዳሴ ታጉሎ ሁሉም በተጠቀሰው ቦታ እንዲገኝ ይሁን በማለት ዐወጁ፡፡ ሁሉም አጥቢያ በዐዋጁ መሠረት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ከዚህ አዲስ ህንጻ ቤተክርስቲያን ተሰብስቧል፡፡ በጎንቻ ወረዳ የትም ቦታ ቅዳሴ ታጉሏል ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም፡፡
ሥርዓቱ ተፈጽሞ ቅዳሴ ቤቱ ተባርኮ ሁሉም ካህናት እና ምእመናን በተገኙበት አቡነ ማርቆስ ትምህርተ ወንጌል የሚመስል ትምህርተ ወንጀልን ሲያስተምሩ አረፈዱ፡፡ በዋናነት የትምህርተ ወንጀላቸው ቀስት የተቃጣው በታላቁ ገዳም በዲማ ጊዮርጊስ፣  በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በሚመራው እና በሚተዳደረው በማኅበረ ቅዱሳን፣ በተዋሕዶ እምነታችን ላይ ተቀጽላ የሆነውን የቅብአት እምነትን አጥብቃችሁ ያዙ በሚል፣ መምህር ሰሎሞን አሥራቴን ደብድቡት የሚል ነው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን መናፍቅ አታላይ ሌባ በማለት መድረክ ላይ ሲዘልፉ ይሰማል፡፡ የወንጌል አባት ናቸው በማለት የሚሟገቱላቸው ሰዎች በእውነት ወንጌል “አፈር ብላ፣ አታላይ ሌባ፣ ቀጣፊ፣ አፈር ያብላህ፣ እርጉምማ እርጉም ነህ፣ በለው ደብድበው” እያለ ያስተምራልን? በእውነት ይህ አንድ አባት ነኝ ከሚል ያውም ከሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ ንግግር ነውን? መምህር ሰሎሞን አሥራቴ ምንድን ነው ጥፋታቸው? ዲማ መሄዳቸው ነው ነውሩ? ተዋሕዶን ማስተማራቸው ተምረው ያመኑትንም ማጥመቃቸው ነው ጥፋታቸው? ይቅርታ ካልጠየቀኝ ንስሐ ካልገባ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲን እንዳይንቀሳቀስ ነው የማደርገው የሚሉስ በእውነት ከማን ዘንድ ንስሐ እንዲገቡ ፈልገው ይሆን? መድረክ ላይ አፈር ብላ ከሚል ደብድቡት ከሚል ስለእስጢፋኖስ ብንማማር አይገባንም በማለት ስለ ግብርና ቃለ መጠይቅ ከሚያደርጉት ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ነውን ወይስ ከማን ዘንድ ይግቡ? ተዋሕዶን በመስበኬ ተጸጽቻለሁ ዲማም በመሄዴ አፍሬያለሁ የልጅነትን ጥምቀት በማጥመቄም ተሳስቻለሁ እንዲሉ ነው የተፈለገው? አ..ይ..ደ..ረ..ግ..ም!  ራስዎ ፊሽካውን ነፍተው ያስጀመሩትን እግር ኳስ ተጫውተን ስንሸነፍ ያኔ ይህን ያደርጉት ይሆናል ግን አ..ን..ሸ..ነ..ፍ..ም፡፡ ምናልባት መምህር ሰሎሞንን ለጊዜው ከደመወዝ ያግዷቸው ከሥራ ያሰናብቷቸው ይሆናል ሃይማኖታቸውን ግን ማስቀየር የሚችሉበት ኃይል የለዎትም፡፡
ከሥራ እንዲታገዱ ብዙ ጥረቶችን አድርገዋል በዚህም መሠረት የወረዳ ቤተክህነቱ ትናንት በላክሁላችሁ መረጃ መሠረት ከሥራ እንዲታገዱ አድርገዋል፡፡ የተጻፈው ደብዳቤ ለመምህር ሰሎሞን የደረሳቸው በግልባጭ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ለሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ነው፡፡ ሰበካ ጉባኤው ይህንን ደብዳቤ ተመልክቶ የሰጠው ምላሽ ስለመኖር አለመኖሩ አይታወቅም ሆኖም ግን ወረዳ ቤተክህነቱ  ስላዘዘ ብቻ ተፈጻሚ እንደሚደረግ የታወቀ ነው፡፡ ከላይ አባ ማርቆስ ከሥር ዓይነኩሉ ካሳ (የገብርኤል አስተዳዳሪ) እና ሊቀኅሩያን መምህር ዕዝራ አሰፋ (የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ) በነገሩ እጃቸውን አስገብተዋልና፡፡ እኛ ይህን የድምጽ እና የምስል መረጃ ለሚመለከተው ሁሉ እናሰራጫለን፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳት ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላችሁ ግለሰቦችም ይህንን መረጃ እያወረዳችሁ አሳዩልን አሰሙልን፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዲማ ጊዮርጊስ ለአቡነ ማርቆስ የእግር እሳት ነው፡፡ ዲማን ታሪክ አልባ እና ቅርስ አልባ የማድረግ ተልእኮ አንግበው መሥራት የጀመሩት ዛሬ አይደለም ገና መንበረ ጵጵስናውን በተቀመጡበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዲማ ጋር በደብዳቤም በቃልም በማስፈራራትም በማስጠንቀቅም ብዙ ውዝግቦችን አሳልፈዋል፡፡ ይህ የውዝግብ ደብዳቤም መረጃው ደርሶኛል፡፡ ቀስ በቀስ እየመጠን ወደ ፊት እንመለከተዋለን፡፡ አሁን ትግላችን ስለ አንድ ገዳም ስለዲማ ጊዮርጊስ ብቻ አይደለም ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ነው እንጅ፡፡ ተዋሕዶ ያስተማረችንን እናስተምራለን ተዋሕዶ አድርጉ ያለችንን እናደርጋለን ተዋሕዶ ሁኑ ያለችንን እንሆናለን፡፡ ከአቡነ ማርቆስ ጋር መግባባት የማንችለው በዚህ ጉዳይ ነው፡፡ እርሳቸው አባትነታቸውን ለጥቂቶች ብቻ አድርገዋልና፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የቅብአትን እምነት ለማስፋፋት ብዙ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህም አሁን በቅርቡ በፈቃቸው የታተሙትን መጻሕፍት መመልከቱ ከበቂ በላይ ነው፡፡ በዚህ ቪዲዮ ላይ እንደምትሰሟቸው “ጎንቻን የምታስደፍሩ እናንተ ናችሁ” በማለት የጎንቻን ህዝብ ለራሳቸው መጠቀሚያ ለማድረግ ሲጥሩ ይስተዋላሉ፡፡ ይባስ ብለውም የቅብአት መጻሕፍቱ የታተሙበትን ቦታ “ቆጋ ኪዳነ ምህረትን” ከሌሎች ሁሉ ከፍ በማድረግ ሲጠሩ ተሰምተዋል “ወዲህም ቆጋ ወዲያም ጎንቻ ነው” በማለት፡፡ እርግጥ ነው ቦታው ገዳሙ የእኛ የራሳችን ነው፡፡ በአግባቡ ባለመጠበቃችን የማንም ወሮ በላ እየገባ ምንፍቅናውን የሚዘራበት ሆነ እንጅ፡፡ ሌላው አቡነ ማርቆስ የተምታታባቸው ነገር አለ፡፡ እርሱም ምግባር እና ሃይማኖት ነው፡፡ “ከሞጣ እስከ ሰኞ ገበያ ድረስ የመናንያን ቦታ ነው” ብለዋል፡፡ ሞጣ አስተውል ጎንቻ ልብ በል እነብሴ ነቃ በል! ሦስቱ እነሴዎችን ለራሳቸው መጠቀሚ ለማድረግ ሌት ከቀን እየደከሙ ናቸው፡፡ ቦታችሁ የመናንያን ቦታ ነው ስለተባለላችሁ ልባችሁ በሐሴት አይሞላ፡፡ ምነና ዓለምን ንቆ መተው ነው አቡነ ማርቆስ ደግሞ እምነትን ንቆ መተውን ነው ምነና የሚሉት፡፡ እርሳቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ባለ ሐገረ ስብከት ላይ ነው ሊቀጳጳስ ሆነው የተሾሙት፡፡ ነገር ግን አንድ ቀንም ቢሆን “ተዋሕዶ” ሲሉ ተሰምተው አያቁም ኦርቶዶክስ ብቻ ነው የሚሉ፡፡ ምነናው የሚመጣ እኮ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከተማሩ ካወቁ ከተጠመቁ  በኋላ እንጅ በምንፍቅና እንደጀቦኑ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ምግባርን ከሃይማኖት ለይተው ያስተምሩ እንበላቸው፡፡ መጾም መጸለይ መስገድ መመጽት ብቻውን ያድናል ካሉን እሰየው አዲስ እንግዳ ትምህርትን አስተማሩን ብለን ወይ እንከተልዎታለን ወይም እንሸሽወታለን፡፡ “በቀን አንድ ጊዜ የሚበሉ ቅዱሳን ነበሩበት፤ ዳዊቱን ከገበታ እስከ ገበታ በቃላቸው የሚያደርሱ ቅዱሳን ነበሩበት” በማለት ቅድስና በዘር ይወረስ ይመስል በቀላሉ የማይታለሉትን ጎንቻዎችን ለማታለል ሞክረዋል፡፡ የጎንቻ ህዝብ ግን እንዲህ በቀላሉ ከነፈሰው ጋር አብሮ የሚነፍስ ሳይሆን እውነቱን ተረድቶ የሚከተል ምእመናን ያሉበት ቦታ ነው፡፡ መርጡለ ማርያሞችን በአዲሱ ህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ የተነሣ አሥረው ይዘዋቸዋል፡፡ “እኔ ከሌለው ህንጻው ይቋረጣል በማለት” ህዝቡን ለራሳቸው መጠቀሚያ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ከህንጻ ግንባታው በስተጀርባ ማን ምን ያህል ገንዘብ ሰጠ ማንስ ወሰደው ለማንስ ጥቅም ላይ ዋለ ብላችሁ ፈትሹ፡ አሁን መርጡለ ማርያሞች ይህን በህንጻው ስም የሚሰበሰበውን ገንዘብ በመቆጣጠር ላይ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሣ ከአቡነ ማርቆስ ጋር ትንሽም ቢሆን ውዝግብ ቢጤ ላይ ናቸው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሌላው በዚህ ቪዲዮ ላይ አቡነ ማርቆስ አፋቸውን የከፈቱበት “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው፡፡ እርሳቸው ቢሞቱ “ማኅበረ ቅዱሳን” ብለው አፋቸውን ተስቷቸው እንኳ አይጠሩትም፡፡ እዚህ ቪዲዮ ላይ ግን “ማኅበረ አጋንንት” በማለት “ቅዱሳን” የሚለውን “አጋንንት” በማለት ለውጠው ጠርተውታል፡፡ ምናልባትም ለአቡነ ማርቆስ “ቅዱሳን” ማለት “አጋንንት” ማለት ሆኖላቸው ሊሆን ይችላል የቅኔ ሊቅ ስለሆኑ ማለቴ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን የማስተዋወቅ ሥራ አልሰራም ዓላማየም ስላልሆነ፡፡ ባልለውማ ማኅበረ ቅዱሳንን እኔ አስተዋውቄ ማኅበር ላደርገው ኖሯል እንጅ፡፡ ማኅበሩ በማእበል መካከል የሚጓዝ መርከብ እኮ ነው፡፡ በቃ ጸጥ ረጭ ብሎ ሥራውን ብቻ የሚሠራ የሥራ ማኅበር የተዋሕዶ አርበኛ ነው፡፡ ማኅበሩ ሥራውን የጀመረው ዝም ብሎ በዘፈቀደ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ፈቅዶ በዘመኑ ለሚነሡት የቤተክርስቲያናችን ጠላቶች እንዲመክት በቅዱስ ሲኖዶስ ታውቆ መተዳደሪያ ደንቡ ጸድቆለት የተመሠረተ ማኅበር ነው፡፡ ታዲያ የሲኖዶስ አባላት በሙሉ ፊርማቸው ያረፈበት መተዳደሪያ ደንብ ያለው ማኅበር “ማኅበረ አጋንንት” ብሎ መሳደብ ምናልባትም የሲኖዶሱን ቅድስና መጠራጠር ይሆናል፡፡ የአቡነ ማርቆስ ፊርማ ግን እዚያ መተዳደሪያ ደንብ ላይ በባትሪም ተፈልጎ አይገኝም፡፡ የዚያ የፊርማው ጊዜ አሜሪካ ለቢዝነስ ሥራ ሂደው ነበር መሰለኝ፡፡ ደግሞም ለመናፍቃን የእግር እሳት የሆነባቸው ማኅበር ስለሆነ ለአቡነ ማርቆስም የእግር እሳት ሆኖባቸዋል ያ ማለት ከመናፍቃኑ ጋራ ግብር ያገናኛቸዋል ማለት ነው፡፡ አሁን በቅርቡ በወጣ መረጃ መሠረት የተሐድሶ አቀንቃኞች እነ በጋሻው ደሳለኝ እና እነ አሰግድ ሳህሉ ከፕሮቴስታንቶች ጋራ ባደረጉት ውይይት “አቡነ ማርቆስም በሐገረ ስብከታቸው የተነሣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማረጋጋት በግል ሥራቸው ላይ ተጠምደዋል በዚህም የተነሣ ልናገኛቸው አልቻልንም” ብለዋል፡፡ ያ ማለት አንድ መሥመር አላቸው ማለት ነው የግብር መስመር፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን “የማኅበር ሃይማኖት” ነው ብለዋል፡፡ በእውነት ተዋሕዶን መስበክ ተዋሕዶን ማስተማር “ማኅበረ አጋንንት” ነው ያሰኛልን? አዲስ ሃይማኖት የሰበከ አዲስ እምነትን ያስተማረ ይመስል ከማኅበሩ ጋር እንዲህ መፋጠጥ የጀመሩ ለምን ይሆን?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
“ጎንቻን ተጠመቁ የሚሉ ማኅበሮች አሉ” ብለዋል አቡነ ማርቆስ፡፡ ጎንቻን ተጠመቁ የሚል ማነው? ማንም አላለም እኮ፡፡ እርሳቸው ግን ያለ ስም ስም መሥጠት ግብራቸው ሆኖ ይህንን የንግግራቸው ሁሉ መጀመሪያ አድርገውታል፡፡ ማን ነው ማንን አስገድዶ ተጠመቅ የሚል? ተዋሕዶን እናስተምራለን ተዋሕዶን ተምሮ ለሚቀበል ሰው ደግሞ የተዋሕዶን ሥርዓት እንፈጽምለታለን እናስፈጽምለታለን፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 3 ቁ 24 ላይ የሚገኝ ስለሆነ፡፡ ከመጽሐፍ ውጭ የሆነውን ሁሉ እንቃወማለን እንታገልማለን፡፡ ማዕርጉን እናከብራለን ማዕርጉ የማይገባው ሰው በማዕርግ ተደብቆ ቢመጣ እንታገለዋለን ይህ ግድ ነውና፡፡ በሃይማኖታችን ላይ ቀልድ ድርድር የለም፡፡ ጎንቻዎች የአገራችን ልጅ ናቸው ብላችሁ አትሸፋፍኗቸው ችግራቸውን ንገሯቸው፡፡ እናንተ ከእኛ ይበልጥ በቅርበት ስለምታውቋቸው በደንብ ንገሯቸው፡፡ “ጎንቻ ጎንቻ” በማለት የጎንቻን ህዝብ ተቀባይነት በማግኘት በምሥራቅ ጎጃም ዘንድ ብጥብጥን ለመፍጠር ጥረት ማድረጋቸው በጣም ያሳዝናል፡፡ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማስተማር “መርዝ መርጨት ነው” በማለት ሲያስተምሩ ዝም ብለህ ከሰማህ በእውነት ጎንቻ አይደለህም፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከሥራ እንዲታገዱ ብዙ ጥረቶችን አድርገዋል በዚህም መሠረት የወረዳ ቤተክህነቱ ትናንት በላክሁላችሁ መረጃ መሠረት ከሥራ እንዲታገዱ አድርገዋል፡፡ የተጻፈው ደብዳቤ ለመምህር ሰሎሞን የደረሳቸው በግልባጭ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ለሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ነው፡፡ ሰበካ ጉባኤው ይህንን ደብዳቤ ተመልክቶ የሰጠው ምላሽ ስለመኖር አለመኖሩ አይታወቅም ሆኖም ግን ወረዳ ቤተክህነቱ ሌላው አቡነ ማርቆስ ያነሡት “የፌስቡክ ጉዳይ” ነው፡፡ መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን መናፍቅ አታላይ ሌባ በማለት መድረክ ላይ ሲዘልፉ ይሰማል፡፡ የወንጌል አባት ናቸው በማለት የሚሟገቱላቸው ሰዎች በእውነት ወንጌል “አፈር ብላ፣ አታላይ ሌባ፣ ቀጣፊ፣ አፈር ያብላህ፣ እርጉምማ እርጉም ነህ፣ በለው ደብድበው” እያለ ያስተምራልን? በእውነት ይህ አንድ አባት ነኝ ከሚል ያውም ከሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ ንግግር ነውን? መምህር ሰሎሞን አሥራቴ ምንድን ነው ጥፋታቸው? ዲማ መሄዳቸው ነው ነውሩ? ተዋሕዶን ማስተማራቸው ተምረው ያመኑትንም ማጥመቃቸው ነው ጥፋታቸው? ይቅርታ ካልጠየቀኝ ንስሐ ካልገባ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲን እንዳይንቀሳቀስ ነው የማደርገው የሚሉስ በእውነት ከማን ዘንድ ንስሐ እንዲገቡ ፈልገው ይሆን? መድረክ ላይ አፈር ብላ ከሚል ደብድቡት ከሚል ስለእስጢፋኖስ ብንማማር አይገባንም በማለት ስለ ግብርና ቃለ መጠይቅ ከሚያደርጉት ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ነውን ወይስ ከማን ዘንድ ይግቡ? ተዋሕዶን በመስበኬ ተጸጽቻለሁ ዲማም በመሄዴ አፍሬያለሁ የልጅነትን ጥምቀት በማጥመቄም ተሳስቻለሁ እንዲሉ ነው የተፈለገው? አ..ይ..ደ..ረ..ግ..ም! እኔ አሉ አቡነ ማርቆስ “እኔ ፌስቡክን ፌን ፈ ብላችሁ ቀይሩት ብያለሁ፡፡ ፈ ብየ ቀይሬ ስሙን እንዳልጠራላችሁ ጸያፍ ነው” አሉ፡፡ አይ አንች ቤተክርስቲያን እነዲዎስቆሮስ ጥርሳቸውን እስኪረግፍ ድረስ ተደብድበው ያስተማሩሽ ጽሕማቸው እስኪነጭ ድረስ የተጎተቱልሽ ዛሬ ግን መድረክሽ “ፌስ ቡክን” “ፈስ ቡክ” በሉት ገባችሁ እየተባለ የሚቀለድብሽ ሆንሽ፡፡ ልጅ አልሆንሽ ስንል ምን ታደርጊ አንችማ!!! በፌስቡክ ፓትርያርኩን ይሳደባሉ ጳጳሱን ይሳደባሉ በማለትም ለፓትርያርኩ አጋዥ ሆነው ታይተዋል፡፡ ጥፋት ካጠፋ እንኳን ፓትርያርክ መልአክም ቢሆን ይወቀሳል፡፡ ፓትርያርኩን አላያችሁም እንዴ ሰዓሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን መቅደስ ውስጥ ቁጭ ብለው የማንም ወመኔ ፕሮቴስታንት አስገብተው ሲያስቀቡ እና ሲያቀባቡ እኮ ነው የዋሉ፡፡ ለማንኛውም ግን ማዕርግ ጥፋትን ሊሸፍን አይችልም፡፡ አቡናርዮስ የሎዶቅያ ጳጳስ ነበረ ነገር ግን “አብ እና ወልድ መንፈስ ቅዱስም አንድ ገጽ ናቸው” በማለት አንድ ገጽ ብሎ አስተማረ፡፡ ንስጥሮስ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ነበረ ነገር ግን “ወልድ ከነቢያት እንደ አንዱ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በዮርዳኖስ ባደረበት ጊዜ በጸጋ አምላክ ሆነ” በማለት ካደ፡፡ ፎጢኖስ የበሚርና ጳጳስ ነበረ ነገር ግን “የወልድ ሕልውና ከማርያም ከተወለደ ወዲህ ነው” በማለት ካደ፡፡ ሳዊሮስ የሕንድ ቴዎዶስዮስ ደግሞ የእስክንድርያ ጳጳስ ነበሩ ነገር ግን “የእግዚአብሔር ልጅ ያለፈቃዱ በግድ ሞተ” ብለው ካዱ፡፡ ልዮን የሮሜ ሊቀ ጳጳስ ነበረ ነገር ግን “ሥጋ ከመለኮት ያንሣል” በማለት ካደ፡፡ የኬልቄዶን ማኅበርተኞች ከ500 እስከ 600 የሚደርሱ ጳጳሳት ነበሩ ነገር ግን “መለኮት እና ሥጋ በሁለት መንገድ በሁለት ሥርዓት ናቸው” ብለው ካዱ፡፡ እነዚህን ታዲያ በፌስቡክ ቀርቶ ሌላ አማራጭስ ቢገኝ ቢጋለጡ ቢወቀሱ ቢሰደቡ ምኑ ነው ጥፋቱ? ላለመሰደብ ከነቀፋ ነጻ መሆን ብቻ ነው ምርጫው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
“የኢትዮጵያ ቤተክርስቲን አንዲት ናት አንድ ነው ጳጳሱ አንድ ነው ቤተክህነቱ ምንድን ነው ሁለት ማለት” በማለት የማይገባ ንግግር ተናገሩ፡፡ “ተዋሕዶ” የምትለዋን ቃል ሽሽት ሲሉ አጉል ስህተት ውስጥ ወደቁ፡፡ በምን መሥፈርት ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንዲት የምትሆን ጳጳሷስ አንድ የሚሆን በምን መሥፈርት ነው፡፡ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት” ቢሉን ኖሮ አዎን ብለን በተቀበልንዎ ነበር እርስዎ ግን “ተዋሕዶ” የሚለውን ስም ላለመጥራት ሲሸሹ “የካቶሊካዊት” “የወንጌላዊት” እና “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ” ቤተክርስቲያናት እንዳሉ እያወቅን በኢትዮጵያ አንዲት ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ሊሉን አይችሉም፡፡ እርስዎ አሁን እያስተማሩት ያለው የቅብአት እምነት እና የእኛ የተዋሕዶ እምነት የሰማይ እና የምድር ያህል እንደሚለያይ ከበቂው በላይ አውቀነዋል ተረድተነውማል፡፡
ሌላው በጣም የሚያስቀው ነገር መምህር የሚሾሙ መምህር የሚቀጥሩ በአገር ልጅነት  መሆኑን አርስዎ በቃልዎ መናገርዎ በጣም ይገርማል፡፡ ዓይነኩሉ የዚሁ አካባቢ ልጅ ነው ብሎ ነው ያቀረበልኝ እኔም እንደዛ ከሆነማ ብየ ነው የቀጠርሁት አሉ መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን፡፡ በአገር ልጅነት እና በጥቅማጥቅሞች ተመርኩዘው በርካታ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን እንዲሁም ካህናትን እና ዲያቆናትን በየቦታው እንዳስቀመጡ እናውቃለን፡፡ እስከጊዜው ድረስ እስኪ ይበሉ ይግፉበት፡፡ መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን አቡነ ማርቆስ መናፍቅ ብለው ሲሰድቧቸው “እውነቱ ለሕዝቡ መገለጥ አለበት” በማለት ሲጠይቁ ነበር ግን ማን ይስማቸው በዘመድ ተደራጅተው የመጡት አቡነ ማርቆስ “ዝም በል ዝም በል” አስባሉላቸው እንጅ፡፡ እውነቷ ልትፈርጥ ጫፍ ድርሳ ነበር እኮ!!!!
ዲማ መሄድ ኃጢአት እና ወንጀል የሆነበት ዘመነ ጵጵስና!!!

አስቸኳይ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ!


© መልካሙ በየነ
ግንቦት 22/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ


ጠፋህብን ጠፋህብን ያላችሁኝ ሁሉ አረ አለሁ ምን እጠፋለሁ! ይኼው መጣሁላችሁ፡፡ ብዙ መረጃዎች ከእጄ ላይ ገብተዋል! ያውም በድምጽ በምስል በቪዲዮ!!! አሁን ግን አስቸኳይ ስለሆነው ጉዳይ ብቻ ነው የማወራችሁ!
ብዙዎች የወንጌል አባት ናቸው በማለት ይሟገቱላቸዋል፡፡ ለምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ፡፡ በእውነት የወንጌል አባት ናቸው በማለት የሚሟገቱላቸው ወገኖች ምናልባትም በጥቅማጥቅሞች ታጥረው የሚገኙ የሥጋ ዘመዶቻቸው አልያም በገንዘብ የመምሪያ ኃላፊ የሆኑ ሆድ አደሮች መሆን አለባቸው፡፡ የወንጌል አባት ናቸው የምትሉ ሰዎች ቆም በሉ እና ይህን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡ ከዚህ ቪዲዮ ላይ በዋናነት ማሳየት የምፈልገው አስቸኳዩ ነገር ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛ የወንጌል አባት ናቸው የምትሉ ወገኖች ስለእስጢፋኖስ ብንማር አይገባንም በማለት ስለግብርና አንዱን አዛውንት አስነስተው ቃለ መጠይቅ ማድረጉ ትርጉሙ ምን ይሆን?
ቀጣዩ እና አስቸኳዩ ነገር ከዚህ ቃለመጠይቅ ከሚደረግላቸው አዛውንት በስተቀኝ በኩል የመጀመሪያው ሻሽ ጠምጥመው ቁጭ ያሉትን (አክሊል ከደፉት ካህን በስተግራ ያሉትን) መምህር የሚመለከት ነው፡፡
መምህሩ መምህር ሰሎሞን አሥራቴ ይባላሉ፡፡ አቡነ ማርቆስ ስለቅባት እምነት በይፋ ሲያስተምሩ መድረክ ላይ እያሉ የተቃወሙ የተዋሕዶ አርበኛ ናቸው፡፡ ታዲያ እነኚህ አባት አቡነ ማርቆስን በግልጽ በመቃወማቸው የስራ ዕገዳ ተደርጎባቸዋል፡፡ የሥራ ዕገዳው ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ነው፡፡ ዋና ነገሩ እንዲህ ይነበባል፡፡
ቁጥር፡134.09
ቀን፡ 07/09/09
ለደ/ብ/ሠፈረ ገነት ቅድስት ስላሴ ወገብርኤል ሠ/ጉ/ጽ/ቤት