© መልካሙ በየነ
ግንቦት
23/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
በቅድሚያ ሰበር ዜና ይቅደም!
ግርማ እስቲያውቅ ይባላል
የጎንቻ ልጅ ነው፡፡ አእምሮው የተነካ ነው የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አገልጋይ ናቸው አባቱ እስቲያውቅ፡፡ ታዲያ የአእምሮ
በሽተኛ የሆነው ልጃቸው ግንቦት 19/2009 ዓ.ም አቡነ ማርቆስ ከሚባርኩት አዲሱ ህንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝቷል፡፡ “አባ ማርቆስ
ዲቁና ይስጡኝ፡፡ አርስዎ በመኪና እየተንፈላሰሱ እኔ በእግሬ እሄዳለሁ” አላቸው፡፡ ከዚያም ጥቂት ዝም ብሎ ቆየ፡፡ አቡነ ማርቆስ ቅዱስ እስጢፋኖስ ብለው ሲናገሩ
ሲሰማ “የባህርዳር እስጢፋኖስ ዲያቆን አድርገው ይሹሙኝ” አላቸው፡፡ ከዚያ እርሳቸውም “አንተ አውቆ አበድ ከእነርሱ ወገን ትሆናለህ፡፡
ቁጭ በል! ቁጭ በል በሉት እባካችሁ” አሉ “ከእነርሱ” የተባለ ከተዋሕዶ ልጆች ጋር ማለታቸው ነው፡፡ ከዚያም “ተው ተው” ተባለ
ዝም አለ፡፡ አቡነ ማርቆስ ጸበል ሊባርኩ ሲሄዱ መኪናቸውን መንገድ ዳር ያገኛታል፡፡ የዚህን ጊዜ ድንጋይ አንሥቶ በሹፌሩ በኩል
ያለውን መስታወት ያረግፈዋል፡፡ ምናልባትም ወደፊት የመኪና መግዣ በሚል ገንዘብ አዋጡ ልንባል እንደምንችል እገምታለሁ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 19/2009 ዓ.ም
ዕለተ ቅዳሜ የጎንቻ ሲሶ እነሴ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ዐዋጅ ታወጆባቸዋል፡፡ ዐዋጅ ዐዋጅ ዐዋጅ አሉ አቡነ ማርቆስ
ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም የኆህተ ሰማይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተሠርቶ ስለተጠናቀቀ ቅዳሴ
ቤቱን ስለምባርክ እዚህ ቦታ እንድትሰበሰቡ ይሁን የትም አጥቢያ ቢሆን የቅዳሜው ቅዳሴ ታጉሎ ሁሉም በተጠቀሰው ቦታ እንዲገኝ ይሁን
በማለት ዐወጁ፡፡ ሁሉም አጥቢያ በዐዋጁ መሠረት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ከዚህ አዲስ ህንጻ ቤተክርስቲያን ተሰብስቧል፡፡ በጎንቻ
ወረዳ የትም ቦታ ቅዳሴ ታጉሏል ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም፡፡
ሥርዓቱ ተፈጽሞ ቅዳሴ ቤቱ
ተባርኮ ሁሉም ካህናት እና ምእመናን በተገኙበት አቡነ ማርቆስ ትምህርተ ወንጌል የሚመስል ትምህርተ ወንጀልን ሲያስተምሩ አረፈዱ፡፡
በዋናነት የትምህርተ ወንጀላቸው ቀስት የተቃጣው በታላቁ ገዳም በዲማ ጊዮርጊስ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በሚመራው እና በሚተዳደረው በማኅበረ ቅዱሳን፣ በተዋሕዶ
እምነታችን ላይ ተቀጽላ የሆነውን የቅብአት እምነትን አጥብቃችሁ ያዙ በሚል፣ መምህር ሰሎሞን አሥራቴን ደብድቡት የሚል ነው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን
መናፍቅ አታላይ ሌባ በማለት መድረክ ላይ ሲዘልፉ ይሰማል፡፡ የወንጌል አባት ናቸው በማለት የሚሟገቱላቸው ሰዎች በእውነት ወንጌል
“አፈር ብላ፣ አታላይ ሌባ፣ ቀጣፊ፣ አፈር ያብላህ፣ እርጉምማ እርጉም ነህ፣ በለው ደብድበው” እያለ ያስተምራልን? በእውነት ይህ
አንድ አባት ነኝ ከሚል ያውም ከሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ ንግግር ነውን? መምህር ሰሎሞን አሥራቴ ምንድን ነው ጥፋታቸው? ዲማ መሄዳቸው
ነው ነውሩ? ተዋሕዶን ማስተማራቸው ተምረው ያመኑትንም ማጥመቃቸው ነው ጥፋታቸው? ይቅርታ ካልጠየቀኝ ንስሐ ካልገባ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲን
እንዳይንቀሳቀስ ነው የማደርገው የሚሉስ በእውነት ከማን ዘንድ ንስሐ እንዲገቡ ፈልገው ይሆን? መድረክ ላይ አፈር ብላ ከሚል ደብድቡት
ከሚል ስለእስጢፋኖስ ብንማማር አይገባንም በማለት ስለ ግብርና ቃለ መጠይቅ ከሚያደርጉት ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ነውን ወይስ ከማን ዘንድ
ይግቡ? ተዋሕዶን በመስበኬ ተጸጽቻለሁ ዲማም በመሄዴ አፍሬያለሁ የልጅነትን ጥምቀት በማጥመቄም ተሳስቻለሁ እንዲሉ ነው የተፈለገው?
አ..ይ..ደ..ረ..ግ..ም! ራስዎ ፊሽካውን ነፍተው ያስጀመሩትን
እግር ኳስ ተጫውተን ስንሸነፍ ያኔ ይህን ያደርጉት ይሆናል ግን አ..ን..ሸ..ነ..ፍ..ም፡፡ ምናልባት መምህር ሰሎሞንን ለጊዜው
ከደመወዝ ያግዷቸው ከሥራ ያሰናብቷቸው ይሆናል ሃይማኖታቸውን ግን ማስቀየር የሚችሉበት ኃይል የለዎትም፡፡
ከሥራ እንዲታገዱ ብዙ ጥረቶችን
አድርገዋል በዚህም መሠረት የወረዳ ቤተክህነቱ ትናንት በላክሁላችሁ መረጃ መሠረት ከሥራ እንዲታገዱ አድርገዋል፡፡ የተጻፈው ደብዳቤ
ለመምህር ሰሎሞን የደረሳቸው በግልባጭ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ለሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ነው፡፡ ሰበካ ጉባኤው ይህንን ደብዳቤ
ተመልክቶ የሰጠው ምላሽ ስለመኖር አለመኖሩ አይታወቅም ሆኖም ግን ወረዳ ቤተክህነቱ ስላዘዘ ብቻ ተፈጻሚ እንደሚደረግ የታወቀ ነው፡፡ ከላይ አባ ማርቆስ ከሥር
ዓይነኩሉ ካሳ (የገብርኤል አስተዳዳሪ) እና ሊቀኅሩያን መምህር ዕዝራ አሰፋ (የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ)
በነገሩ እጃቸውን አስገብተዋልና፡፡ እኛ ይህን የድምጽ እና የምስል መረጃ ለሚመለከተው ሁሉ እናሰራጫለን፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳት ጋር
የቅርብ ግንኙነት ያላችሁ ግለሰቦችም ይህንን መረጃ እያወረዳችሁ አሳዩልን አሰሙልን፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዲማ ጊዮርጊስ ለአቡነ ማርቆስ
የእግር እሳት ነው፡፡ ዲማን ታሪክ አልባ እና ቅርስ አልባ የማድረግ ተልእኮ አንግበው መሥራት የጀመሩት ዛሬ አይደለም ገና መንበረ
ጵጵስናውን በተቀመጡበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዲማ ጋር በደብዳቤም በቃልም በማስፈራራትም በማስጠንቀቅም ብዙ ውዝግቦችን አሳልፈዋል፡፡
ይህ የውዝግብ ደብዳቤም መረጃው ደርሶኛል፡፡ ቀስ በቀስ እየመጠን ወደ ፊት እንመለከተዋለን፡፡ አሁን ትግላችን ስለ አንድ ገዳም
ስለዲማ ጊዮርጊስ ብቻ አይደለም ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ነው እንጅ፡፡ ተዋሕዶ ያስተማረችንን እናስተምራለን ተዋሕዶ አድርጉ ያለችንን
እናደርጋለን ተዋሕዶ ሁኑ ያለችንን እንሆናለን፡፡ ከአቡነ ማርቆስ ጋር መግባባት የማንችለው በዚህ ጉዳይ ነው፡፡ እርሳቸው አባትነታቸውን
ለጥቂቶች ብቻ አድርገዋልና፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የቅብአትን እምነት ለማስፋፋት
ብዙ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህም አሁን በቅርቡ በፈቃቸው የታተሙትን መጻሕፍት መመልከቱ ከበቂ በላይ ነው፡፡ በዚህ
ቪዲዮ ላይ እንደምትሰሟቸው “ጎንቻን የምታስደፍሩ እናንተ ናችሁ” በማለት የጎንቻን ህዝብ ለራሳቸው መጠቀሚያ ለማድረግ ሲጥሩ ይስተዋላሉ፡፡
ይባስ ብለውም የቅብአት መጻሕፍቱ የታተሙበትን ቦታ “ቆጋ ኪዳነ ምህረትን” ከሌሎች ሁሉ ከፍ በማድረግ ሲጠሩ ተሰምተዋል “ወዲህም
ቆጋ ወዲያም ጎንቻ ነው” በማለት፡፡ እርግጥ ነው ቦታው ገዳሙ የእኛ የራሳችን ነው፡፡ በአግባቡ ባለመጠበቃችን የማንም ወሮ በላ
እየገባ ምንፍቅናውን የሚዘራበት ሆነ እንጅ፡፡ ሌላው አቡነ ማርቆስ የተምታታባቸው ነገር አለ፡፡ እርሱም ምግባር እና ሃይማኖት ነው፡፡
“ከሞጣ እስከ ሰኞ ገበያ ድረስ የመናንያን ቦታ ነው” ብለዋል፡፡ ሞጣ አስተውል ጎንቻ ልብ በል እነብሴ ነቃ በል! ሦስቱ እነሴዎችን
ለራሳቸው መጠቀሚ ለማድረግ ሌት ከቀን እየደከሙ ናቸው፡፡ ቦታችሁ የመናንያን ቦታ ነው ስለተባለላችሁ ልባችሁ በሐሴት አይሞላ፡፡
ምነና ዓለምን ንቆ መተው ነው አቡነ ማርቆስ ደግሞ እምነትን ንቆ መተውን ነው ምነና የሚሉት፡፡ እርሳቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ባለ ሐገረ ስብከት ላይ ነው ሊቀጳጳስ ሆነው የተሾሙት፡፡ ነገር ግን አንድ ቀንም ቢሆን “ተዋሕዶ” ሲሉ
ተሰምተው አያቁም ኦርቶዶክስ ብቻ ነው የሚሉ፡፡ ምነናው የሚመጣ እኮ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከተማሩ ካወቁ ከተጠመቁ በኋላ እንጅ በምንፍቅና እንደጀቦኑ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ምግባርን ከሃይማኖት
ለይተው ያስተምሩ እንበላቸው፡፡ መጾም መጸለይ መስገድ መመጽት ብቻውን ያድናል ካሉን እሰየው አዲስ እንግዳ ትምህርትን አስተማሩን
ብለን ወይ እንከተልዎታለን ወይም እንሸሽወታለን፡፡ “በቀን አንድ ጊዜ የሚበሉ ቅዱሳን ነበሩበት፤ ዳዊቱን ከገበታ እስከ ገበታ በቃላቸው
የሚያደርሱ ቅዱሳን ነበሩበት” በማለት ቅድስና በዘር ይወረስ ይመስል በቀላሉ የማይታለሉትን ጎንቻዎችን ለማታለል ሞክረዋል፡፡ የጎንቻ
ህዝብ ግን እንዲህ በቀላሉ ከነፈሰው ጋር አብሮ የሚነፍስ ሳይሆን እውነቱን ተረድቶ የሚከተል ምእመናን ያሉበት ቦታ ነው፡፡ መርጡለ
ማርያሞችን በአዲሱ ህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ የተነሣ አሥረው ይዘዋቸዋል፡፡ “እኔ ከሌለው ህንጻው ይቋረጣል በማለት” ህዝቡን
ለራሳቸው መጠቀሚያ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ከህንጻ ግንባታው በስተጀርባ ማን ምን ያህል ገንዘብ ሰጠ ማንስ ወሰደው ለማንስ ጥቅም
ላይ ዋለ ብላችሁ ፈትሹ፡ አሁን መርጡለ ማርያሞች ይህን በህንጻው ስም የሚሰበሰበውን ገንዘብ በመቆጣጠር ላይ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሣ
ከአቡነ ማርቆስ ጋር ትንሽም ቢሆን ውዝግብ ቢጤ ላይ ናቸው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሌላው በዚህ ቪዲዮ ላይ አቡነ
ማርቆስ አፋቸውን የከፈቱበት “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው፡፡ እርሳቸው ቢሞቱ “ማኅበረ ቅዱሳን” ብለው አፋቸውን ተስቷቸው እንኳ አይጠሩትም፡፡
እዚህ ቪዲዮ ላይ ግን “ማኅበረ አጋንንት” በማለት “ቅዱሳን” የሚለውን “አጋንንት” በማለት ለውጠው ጠርተውታል፡፡ ምናልባትም ለአቡነ
ማርቆስ “ቅዱሳን” ማለት “አጋንንት” ማለት ሆኖላቸው ሊሆን ይችላል የቅኔ ሊቅ ስለሆኑ ማለቴ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን የማስተዋወቅ
ሥራ አልሰራም ዓላማየም ስላልሆነ፡፡ ባልለውማ ማኅበረ ቅዱሳንን እኔ አስተዋውቄ ማኅበር ላደርገው ኖሯል እንጅ፡፡ ማኅበሩ በማእበል
መካከል የሚጓዝ መርከብ እኮ ነው፡፡ በቃ ጸጥ ረጭ ብሎ ሥራውን ብቻ የሚሠራ የሥራ ማኅበር የተዋሕዶ አርበኛ ነው፡፡ ማኅበሩ ሥራውን
የጀመረው ዝም ብሎ በዘፈቀደ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ፈቅዶ በዘመኑ ለሚነሡት የቤተክርስቲያናችን ጠላቶች እንዲመክት በቅዱስ ሲኖዶስ
ታውቆ መተዳደሪያ ደንቡ ጸድቆለት የተመሠረተ ማኅበር ነው፡፡ ታዲያ የሲኖዶስ አባላት በሙሉ ፊርማቸው ያረፈበት መተዳደሪያ ደንብ
ያለው ማኅበር “ማኅበረ አጋንንት” ብሎ መሳደብ ምናልባትም የሲኖዶሱን ቅድስና መጠራጠር ይሆናል፡፡ የአቡነ ማርቆስ ፊርማ ግን እዚያ
መተዳደሪያ ደንብ ላይ በባትሪም ተፈልጎ አይገኝም፡፡ የዚያ የፊርማው ጊዜ አሜሪካ ለቢዝነስ ሥራ ሂደው ነበር መሰለኝ፡፡ ደግሞም
ለመናፍቃን የእግር እሳት የሆነባቸው ማኅበር ስለሆነ ለአቡነ ማርቆስም የእግር እሳት ሆኖባቸዋል ያ ማለት ከመናፍቃኑ ጋራ ግብር
ያገናኛቸዋል ማለት ነው፡፡ አሁን በቅርቡ በወጣ መረጃ መሠረት የተሐድሶ አቀንቃኞች እነ በጋሻው ደሳለኝ እና እነ አሰግድ ሳህሉ
ከፕሮቴስታንቶች ጋራ ባደረጉት ውይይት “አቡነ ማርቆስም በሐገረ ስብከታቸው የተነሣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማረጋጋት በግል ሥራቸው
ላይ ተጠምደዋል በዚህም የተነሣ ልናገኛቸው አልቻልንም” ብለዋል፡፡ ያ ማለት አንድ መሥመር አላቸው ማለት ነው የግብር መስመር፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንን “የማኅበር ሃይማኖት” ነው ብለዋል፡፡ በእውነት ተዋሕዶን መስበክ ተዋሕዶን ማስተማር “ማኅበረ አጋንንት” ነው
ያሰኛልን? አዲስ ሃይማኖት የሰበከ አዲስ እምነትን ያስተማረ ይመስል ከማኅበሩ ጋር እንዲህ መፋጠጥ የጀመሩ ለምን ይሆን?
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
“ጎንቻን ተጠመቁ የሚሉ ማኅበሮች
አሉ” ብለዋል አቡነ ማርቆስ፡፡ ጎንቻን ተጠመቁ የሚል ማነው? ማንም አላለም እኮ፡፡ እርሳቸው ግን ያለ ስም ስም መሥጠት ግብራቸው
ሆኖ ይህንን የንግግራቸው ሁሉ መጀመሪያ አድርገውታል፡፡ ማን ነው ማንን አስገድዶ ተጠመቅ የሚል? ተዋሕዶን እናስተምራለን ተዋሕዶን
ተምሮ ለሚቀበል ሰው ደግሞ የተዋሕዶን ሥርዓት እንፈጽምለታለን እናስፈጽምለታለን፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 3 ቁ 24 ላይ የሚገኝ
ስለሆነ፡፡ ከመጽሐፍ ውጭ የሆነውን ሁሉ እንቃወማለን እንታገልማለን፡፡ ማዕርጉን እናከብራለን ማዕርጉ የማይገባው ሰው በማዕርግ ተደብቆ
ቢመጣ እንታገለዋለን ይህ ግድ ነውና፡፡ በሃይማኖታችን ላይ ቀልድ ድርድር የለም፡፡ ጎንቻዎች የአገራችን ልጅ ናቸው ብላችሁ አትሸፋፍኗቸው
ችግራቸውን ንገሯቸው፡፡ እናንተ ከእኛ ይበልጥ በቅርበት ስለምታውቋቸው በደንብ ንገሯቸው፡፡ “ጎንቻ ጎንቻ” በማለት የጎንቻን ህዝብ
ተቀባይነት በማግኘት በምሥራቅ ጎጃም ዘንድ ብጥብጥን ለመፍጠር ጥረት ማድረጋቸው በጣም ያሳዝናል፡፡ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማስተማር
“መርዝ መርጨት ነው” በማለት ሲያስተምሩ ዝም ብለህ ከሰማህ በእውነት ጎንቻ አይደለህም፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከሥራ እንዲታገዱ ብዙ ጥረቶችን
አድርገዋል በዚህም መሠረት የወረዳ ቤተክህነቱ ትናንት በላክሁላችሁ መረጃ መሠረት ከሥራ እንዲታገዱ አድርገዋል፡፡ የተጻፈው ደብዳቤ
ለመምህር ሰሎሞን የደረሳቸው በግልባጭ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ለሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ነው፡፡ ሰበካ ጉባኤው ይህንን ደብዳቤ
ተመልክቶ የሰጠው ምላሽ ስለመኖር አለመኖሩ አይታወቅም ሆኖም ግን ወረዳ ቤተክህነቱ ሌላው አቡነ ማርቆስ ያነሡት
“የፌስቡክ ጉዳይ” ነው፡፡ መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን
መናፍቅ አታላይ ሌባ በማለት መድረክ ላይ ሲዘልፉ ይሰማል፡፡ የወንጌል አባት ናቸው በማለት የሚሟገቱላቸው ሰዎች በእውነት ወንጌል
“አፈር ብላ፣ አታላይ ሌባ፣ ቀጣፊ፣ አፈር ያብላህ፣ እርጉምማ እርጉም ነህ፣ በለው ደብድበው” እያለ ያስተምራልን? በእውነት ይህ
አንድ አባት ነኝ ከሚል ያውም ከሊቀ ጳጳስ የሚጠበቅ ንግግር ነውን? መምህር ሰሎሞን አሥራቴ ምንድን ነው ጥፋታቸው? ዲማ መሄዳቸው
ነው ነውሩ? ተዋሕዶን ማስተማራቸው ተምረው ያመኑትንም ማጥመቃቸው ነው ጥፋታቸው? ይቅርታ ካልጠየቀኝ ንስሐ ካልገባ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲን
እንዳይንቀሳቀስ ነው የማደርገው የሚሉስ በእውነት ከማን ዘንድ ንስሐ እንዲገቡ ፈልገው ይሆን? መድረክ ላይ አፈር ብላ ከሚል ደብድቡት
ከሚል ስለእስጢፋኖስ ብንማማር አይገባንም በማለት ስለ ግብርና ቃለ መጠይቅ ከሚያደርጉት ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ነውን ወይስ ከማን ዘንድ
ይግቡ? ተዋሕዶን በመስበኬ ተጸጽቻለሁ ዲማም በመሄዴ አፍሬያለሁ የልጅነትን ጥምቀት በማጥመቄም ተሳስቻለሁ እንዲሉ ነው የተፈለገው?
አ..ይ..ደ..ረ..ግ..ም! እኔ አሉ አቡነ ማርቆስ “እኔ ፌስቡክን ፌን ፈ ብላችሁ ቀይሩት ብያለሁ፡፡ ፈ ብየ ቀይሬ ስሙን እንዳልጠራላችሁ
ጸያፍ ነው” አሉ፡፡ አይ አንች ቤተክርስቲያን እነዲዎስቆሮስ ጥርሳቸውን እስኪረግፍ ድረስ ተደብድበው ያስተማሩሽ ጽሕማቸው እስኪነጭ
ድረስ የተጎተቱልሽ ዛሬ ግን መድረክሽ “ፌስ ቡክን” “ፈስ ቡክ” በሉት ገባችሁ እየተባለ የሚቀለድብሽ ሆንሽ፡፡ ልጅ አልሆንሽ ስንል
ምን ታደርጊ አንችማ!!! በፌስቡክ ፓትርያርኩን ይሳደባሉ ጳጳሱን ይሳደባሉ በማለትም ለፓትርያርኩ አጋዥ ሆነው ታይተዋል፡፡ ጥፋት
ካጠፋ እንኳን ፓትርያርክ መልአክም ቢሆን ይወቀሳል፡፡ ፓትርያርኩን አላያችሁም እንዴ ሰዓሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን መቅደስ ውስጥ
ቁጭ ብለው የማንም ወመኔ ፕሮቴስታንት አስገብተው ሲያስቀቡ እና ሲያቀባቡ እኮ ነው የዋሉ፡፡ ለማንኛውም ግን ማዕርግ ጥፋትን ሊሸፍን
አይችልም፡፡ አቡናርዮስ የሎዶቅያ ጳጳስ ነበረ ነገር ግን “አብ እና ወልድ መንፈስ ቅዱስም አንድ ገጽ ናቸው” በማለት አንድ ገጽ
ብሎ አስተማረ፡፡ ንስጥሮስ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ነበረ ነገር ግን “ወልድ ከነቢያት እንደ አንዱ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ
በዮርዳኖስ ባደረበት ጊዜ በጸጋ አምላክ ሆነ” በማለት ካደ፡፡ ፎጢኖስ የበሚርና ጳጳስ ነበረ ነገር ግን “የወልድ ሕልውና ከማርያም
ከተወለደ ወዲህ ነው” በማለት ካደ፡፡ ሳዊሮስ የሕንድ ቴዎዶስዮስ ደግሞ የእስክንድርያ ጳጳስ ነበሩ ነገር ግን “የእግዚአብሔር ልጅ
ያለፈቃዱ በግድ ሞተ” ብለው ካዱ፡፡ ልዮን የሮሜ ሊቀ ጳጳስ ነበረ ነገር ግን “ሥጋ ከመለኮት ያንሣል” በማለት ካደ፡፡ የኬልቄዶን
ማኅበርተኞች ከ500 እስከ 600 የሚደርሱ ጳጳሳት ነበሩ ነገር ግን “መለኮት እና ሥጋ በሁለት መንገድ በሁለት ሥርዓት ናቸው”
ብለው ካዱ፡፡ እነዚህን ታዲያ በፌስቡክ ቀርቶ ሌላ አማራጭስ ቢገኝ ቢጋለጡ ቢወቀሱ ቢሰደቡ ምኑ ነው ጥፋቱ? ላለመሰደብ ከነቀፋ
ነጻ መሆን ብቻ ነው ምርጫው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
“የኢትዮጵያ ቤተክርስቲን
አንዲት ናት አንድ ነው ጳጳሱ አንድ ነው ቤተክህነቱ ምንድን ነው ሁለት ማለት” በማለት የማይገባ ንግግር ተናገሩ፡፡ “ተዋሕዶ”
የምትለዋን ቃል ሽሽት ሲሉ አጉል ስህተት ውስጥ ወደቁ፡፡ በምን መሥፈርት ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንዲት የምትሆን ጳጳሷስ
አንድ የሚሆን በምን መሥፈርት ነው፡፡ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት” ቢሉን ኖሮ አዎን ብለን በተቀበልንዎ
ነበር እርስዎ ግን “ተዋሕዶ” የሚለውን ስም ላለመጥራት ሲሸሹ “የካቶሊካዊት” “የወንጌላዊት” እና “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ” ቤተክርስቲያናት
እንዳሉ እያወቅን በኢትዮጵያ አንዲት ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ሊሉን አይችሉም፡፡ እርስዎ አሁን እያስተማሩት ያለው የቅብአት እምነት
እና የእኛ የተዋሕዶ እምነት የሰማይ እና የምድር ያህል እንደሚለያይ ከበቂው በላይ አውቀነዋል ተረድተነውማል፡፡
ሌላው በጣም የሚያስቀው ነገር
መምህር የሚሾሙ መምህር የሚቀጥሩ በአገር ልጅነት መሆኑን አርስዎ
በቃልዎ መናገርዎ በጣም ይገርማል፡፡ ዓይነኩሉ የዚሁ አካባቢ ልጅ ነው ብሎ ነው ያቀረበልኝ እኔም እንደዛ ከሆነማ ብየ ነው የቀጠርሁት
አሉ መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን፡፡ በአገር ልጅነት እና በጥቅማጥቅሞች ተመርኩዘው በርካታ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን እንዲሁም
ካህናትን እና ዲያቆናትን በየቦታው እንዳስቀመጡ እናውቃለን፡፡ እስከጊዜው ድረስ እስኪ ይበሉ ይግፉበት፡፡ መምህር ሰሎሞን ዐሥራቴን
አቡነ ማርቆስ መናፍቅ ብለው ሲሰድቧቸው “እውነቱ ለሕዝቡ መገለጥ አለበት” በማለት ሲጠይቁ ነበር ግን ማን ይስማቸው በዘመድ ተደራጅተው
የመጡት አቡነ ማርቆስ “ዝም በል ዝም በል” አስባሉላቸው እንጅ፡፡ እውነቷ ልትፈርጥ ጫፍ ድርሳ ነበር እኮ!!!!
ዲማ መሄድ ኃጢአት እና ወንጀል
የሆነበት ዘመነ ጵጵስና!!!
No comments:
Post a Comment