Monday, June 5, 2017

የኮሚቴው ሪፖርት



© መልካሙ በየነ

ግንቦት *23*/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
ዕለቱ ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 19/2009 ዓ.ም ኆህተ ሰማይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወእስጢፋኖስ አዲስ ህንጻ ቤተክርስቲያን ምረቃ ነው፡፡ አቡነ ማርቆስ በቦታው ተገኝተዋል፡፡ እርሳቸውም በተከታታይ የለጠፍነውን ትምህርት አስተማሩ፡፡ ከዚያም ጸበሉን ሊባርኩ ሄዱ ከዚያም ተመልሰው መጡ እና የኮሚቴው ሪፖርት እንዲህ ቀረበ፡፡ “በመቀጠል ይህንን ሪፖርት እንዳቀርክ በብጹእ አባታችን በጎ ፈቃድና በህዝበ ክርስቲያኑ ስም አመሰግናለሁ፡፡ የሰላም የፍቅር የልማት አባት በሆኑት በብጹእ አባታችን አቡነ ማርቆስ… የካቲት 05/2008 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ መጣሉ ይታወቃል…” አለ፡፡ ቀጥሎም ሌሎችን ንግግሮች ተናገረ፡፡ ከዚያም ቤተክርስቲያኑን ለመሥራት የወጣውን ወጭ ይዘረዝራል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር የሰላም አባት የሚለው ነው፡፡ ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ደብዳቤ የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳድር ፀጥታ ዘርፍ ቀጥታ ለአቡነ ማርቆስ የጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡  ብጥብጥ እየፈጠሩ ስለሆነ ከዚህ ድርጊትዎ እንዲታቀቡ የሚል ደብዳቤ ነው፡፡ አንብቡት እሱን ለእናንተ ተውኩት እኔ ግን ወደ ሪፖርቱ ልገባ ነው፡፡
1.  ቆርቆሮ በብዛት 180 በ24 ብር ድምር 22320 (***የ24 ብር ቆርቆሮ አለ እንዴ???***)
2.  እንጨት 20000 ብር
3.  ድንጋይ በሜትር ኩብ 7 በ1400 በድምር 9800 ብር
4.  ሲሚንቶ 75 ኩንታል በ245 ብር በድምር 18376 ብር
5.  አሸዋ 2 ባጆ በ2240 ድምር 4800 (**የማባዛት ስህተት**)
6.  አሸዋ 1 ባጆ በሲኖ 5500 ብር 2000 ብር በነጻ
7.  ግንባታ ሰራተኛ 10000 ብር
8.  ለአናፂ 5000 ብር
9.  ለቤተክርስቲያን አናፂ 600 ብር
10. ምስማር 55 ኪሎ በ32 ብር በድምር 18700 ብር
11. ቀን ሰራተኛ 40 ሴት 40 ወንድ በ80 ብር በድምሩ 3200 ብር (** ይፈተሸ**)
12. ቀን ሰራተኛ 50 ሴት በ50 ብር በድምር 2500 ብር
13. የቀን ሰራተኞች 55 19 በ120 ብር በድምር 1800 (***ምን ማለት ነው**)
14. ኮርኒስ ቀለም ሰራተኛ 7020 ብር
15. መስኮት 6 በ1400 ብር በድምሩ 8400 ብር
16. በር መዝጊያ 2 በ3000 ብር በድምር 6000 ብር
17. በር መዝጊያ ጠበብ ያሉ 4 መስኮቶች በ2500 ብር በድምሩ 10000 ብር
18. ጉልላት 1500 ብር
19. ጉልላት ዝቅተኛ 1200 ብር
20. የህብረተሰብ ተሳትፎ ወደ 500 ሰው በ70 ብር 35000 ብር
21. ጽላት መግዣ 10000 ብር
22. ጽላት ማምጫ 10500 ብር
23. ከተለያዩ ግለሰቦች ለማስመረቂያ እና ለልዩ ልዩ ወጭ 21118 ብር
በጠቅላላ ድምር 211704 ብር፡፡
ብድር 21558 ብር፡፡
እዚህ ላይ በጣም የሚገርሙ ወጭዎችን ሰምተናል፡፡
1.  ጽላት መግዣ--- 10 ሺ ብር
2.  ጽላት ማምጫ 10 ሺ 500 ብር
3.  ማስመረቂያ ወጭ 21118 ብር
ጽላቱን ከማን ነው የገዙት? ከየትስ ነው የገዙት? ከየት ወዴት ለማጓጓዝ ነው 10 ሺ 500 ብር የሚፈጀው? ቪዲዮው ላይ እንደምትሰሙት ጽላት መግዣ--- 10 ሺ ብር ካለ በኋላ ማምጫ በል ተብሎ መሠለኝ ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ ጽላት ማምጫ ብሎ 500 ብር ጨምሮ 10500 ብር ብሏል፡፡ ጽላቱ ከአሜሪካ እንኳ ቢመጣ 10500 ብር በምን መልኩ ሊፈጅ ይችላል፡፡ ይች 10 ሺ ብር ማን ኪስ ገባች ብለህ ጎንቻ አፍጥጠህ ጠይቅ፡፡ ከመቼ ወዲህ ነው ጽላት ተገዝቶ የሚመጣ? ሌላው ለማስመረቂያ ወጣ የተባለው 21118 ብር ለምን አገልግሎት ዋለ ብለህ ጎንቻ ወትውት፡፡ ምናልባት አቡነ ማርቆስ እና አብረዋቸው የመጡት ሁለቱ መነኮሳት የተካፈሉት በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ከሆነ በግልጽ ጠይቅ በግልጽም ይመለስ፡፡ ሌላው 215580 ብር ብድር አለብን ያለው ኮሚቴ 21118 ብር ግን ለማስመረቂያ ብሎ አውጥቷል እንዴት ለምን ብለህ ጠይቅ ይህ ለጎንቻዎች ጥያቄ መሆን አለበት፡፡
ሌላው ኮሚቴው አቡነ ማርቆስ ሲሉት የዋሉትን የጥምቀት ጉዳይ እንደመፈክር ሲያሰማ ተሰምቷል፡፡ ዳግም ጥምቀት የፈቀደ ሰው ማነው ዳግምስ የተጠመቀ ማነው? በቅባት እምነት ውስጥ ያሉ ሁሉ ተምረው ተዋሕዶ ለመሆን ይጠመቃሉ አራት ነጥብ!!!!
ሌለው አቡነ ማርቆስ ስእለት አስገቡ ሲሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚያወራ ሰው ነበር፡፡ “አውቆ አበድ” ብለው የሰደቡት ማለት ነው፡፡ እሱ ነው ዲቁና ስጡኝ ያላቸው መኪናቸውንም መስታወቷን የሠበራት፡፡
ከዚህ ጉባዔ በኋላ ሞጣ ገብተዋል፡፡ ሞጣ ሄደውስ ምን አሉ???

No comments:

Post a Comment