Saturday, May 25, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 102

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
                    ******     
በእንተ ምሳሌ አግብርት ወፈድዮተ ዕዳ።
፳፫፡ ወበእንተዝ እብለክሙ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ንጉሠ ዘፈቀደ ይትሀሰቦሙ ለአግብርቲሁ።
                    ******     
፳፫፡ ንስሐ የሚገባ ስለሆነ መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል፡ ሕገ ወንጌል ተስፋ፣ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብላቴኖቹን ሊቆጣጠራቸው የወደደ ንጉሥን ትመስላለች።
                    ****** 
፳፬፡ ወሶበ አኃዘ ተሀስቦቶሙ አምጽኡ ሎቱ አሐደ ዘይፈድዮ ዕልፈ መካልየ፣
                    ******     
፳፬፡ በተቆጣጠራቸው ጊዜ የዕልፍ ወቄት ባለዳ አመጡለት።
                    ******     
፳፭፡ ወኃጢኦ ዘይፈድዮ አዘዘ እግዚኡ ይሢጥዎ ምስለ ብእሲቱ ወምስለ ውሉዱ።
                    ******     
፳፭፡  የሚክፍለው ቢያጣ ከልጆቹና ከሚስቱ ጋራ ሽጡት ብሎ አዘዘ። በወንጌልስ መሸጥም የለ ተገዝቶ ደመወዝ አውጥቶ ይክፈለኝ ሲል ነው።
                    ******     
፳፮፡ ወኵሎ ዘቦ እስከ ይፈዲ።
                    ******     
፳፮፡ ዕልፍ ወቄት አስኪከፍል ድረስ።
ወወድቀ እንከ ውእቱ ገብር ወሰገደ ሎቱ ወአስተብቊዖ።
ያ ባሪያ ወድቆ ማለደው።
እንዘ ይብል እግዚኦ ተዓገሠኒ
አቤቱ ታገሠኝ።
ወኵሎ እፈድየከ።
ዕልፍ ወቄት እከፍልሃለሁ ብሎ
                    ******     
፳፯፡ ወምህሮ እግዚኡ ለውእቱ ገብር ወዕዳሁኒ ኀደገ ሎቱ፡፡
                    ******     
፳፯፡ ለዚያ ባሪያ ጌታው አዘነለት ዕዳውን ሁሉ ተወለት።
                    ******     
፳፰፡ ወወጺኦ ውእቱ ገብር ረከበ አሐደ ገብረ እምነ አብያጺሁ  ዘይፈድዮ ዕልፈ ዲናረ።
                    ******     
፳፰፡ ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ወገን የመቶ ወቄት ባለዕዳ አገኘ።
ወአኀዞ ወኀነቆ እንዘ ይብል ሀበኒ ዘትፈድየኒ።
ገንዘቤን ስጠኝ ብሎ አስጨንቆ ያዘው።
                    ******     
፳፱፡ ወወድቀ ውእቱ ገብር ታሕተ እገሪሁ ወአስተብቊዖ እንዘ ይብል ተዓገሠኒ።
                    ******     
፳፱፡ ያ የጌታ ባርያ ታገሠኝ ማለት ቀን ስጠኝ ብሎ ወድቆ ማለደው፡፡
ወኵሎ እፈድየከ።
ጥቂት ጥቂት እያልሁ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፣
                    ******     
ወዓበዮ ወሖረ ወሞቅሖ፡
                    ******     
፴፡ ብትከፍለኝ ክፈለኝ ያለዚያ አይሆንም ብሎ አሥሮ አጋዘው
እስከ ይፈድዮ፣
እስኪከፍለው ድረስ።
                    ******     
፴፩፡ ወርእዮሙ አግብርተ እግዚኡ ዘገብረ ተከዙ ጥቀ፣
                    ******     
፴፩፡ የጌታው ባሮች ባልንጀሮቹ ያደረገውን አይተው ፈጽመው አዘኑ፣
ወሐዊሮሙ ነገርዎ ለእግዚኦሙ ኵሎ ዘገብረ
ሂደው ያደረገውን ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት ነገሩት፡፡
                    ******     
፴፪፡ ወእምዝ ጸውዖ እግዚኡ ኦ ገብር እኵይ ኵሎ ዕዳ ኀደጉ
ለከ።
                    ******     
፴፪፡ ከዚህ በኋላ ጌታው ጠርቶ አንት ክፉ ባርያ ዕዳህን ሁሉ ተውሁልህ።
                    ******     
፴፫፡ እስመ አስተብቋዕከኒ።
                    ******     
፴፫፡ ማልደኸኛልና ስለ ማለድኸኝ
አኮሁ መፍትው አንተሂ ትምሀር ውእተ ገብረ ቢጸከ በከመ አነ መሀርኩከ።
እኔ ዕልፍ ወቄት እንደተውኩልህ አንተስ ልትተው አይገባህም ነበርን።
                    ******     
፴፬፡ ወተምዓ እግዚኡ ወመጠዎሙ ለእለ ይሣቅይዎ።
                    ******     
፴፬፡ ጌታው ተቆጥቶ እሱ ለሰው ካላዘነ ብሎ መከራ ሥቃይ ለሚያጸኑበት ሰጠው።
እስከ አመ ይሤልጥ ኵሎ ዘይፈድዮ።
ዕልፍ ወቄት አስኪከፍለው ድረስ።
                    ******     
፴፭፡ ከማሁኬ አቡየኒ ሰማያዊ ይገብር ለክሙ እመ ኢኃደግሙ አበሳሆሙ ለቢጽክሙ እምኵሉ ልብክሙ።
                    ******     
፴፭፡ እንደዚህም ሁሉ የወንድዎቻችሁን ኃጢአት በፍጹም ልቡናችሁ ይቅር ካላላችሁ ሰማያዊ አባቴም እንዲህ ያደርግባችኋል።
አንድም ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብለህ መልስ። መንግሥተ ሰማያት አብ መላአክትን ሊቆጣጠራቸው የወደደ ንጉሥን ትመስላለች አለ እሱ ነው ማለት ነው።
ወሶበ አኀዘ ተሀስቦቶሙ።
በተቆጣጠራቸው ጊዜ ፍጹም ኃጢአት የሠራ አዳምን አመጡለት።
ወኃጢኦ ዘይፈደዮ።
ሃይማኖት ምግባር ቢያጣበት።
አዘዘ ይሢጥዎ
በእሱ በሔዋን በልጆቹ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስን ፈረደባቸው። በአዳም ሁሉን መናገር ነው፡፡
አንድም መምህረ ንስሐ ነው፡፡
አዘዘ ይሢጥዎ
በሕዋሳቱ ደዌያትን ፈረደበት
ወኵሎ ዘቦ
ቀኖናውን እስኪፈጽም ድረስ።
ወወድቀ ወአስተብቊዖ
በድዬሃለሁ ይቅር በለኝ።
ወኵሎ እፈድየከ
ቀኖናዬን እፈጽማለሁ አለው።
ወምህሮ
አዘነለት ኃጢአቱን አስተስረየለት፡፡
ወወፂኦ
ኃጢአቱ ከተሰረየለት በኋላ ከሕዝቡ አንድ ተነሳሂ አገኘ።
ወአኃዞ ወሐነቆ
መጽሐፍ ያዘዘውን ፈጽም ብሎ አስጨንቆ ያዘው።
ወወድቀ ወአስተብቊዖ
ቀኖናዬን ልፈጽም ብሎ ማለደው፡፡
ወአበዮ ወሞቅሖ
ብትፈጽም ፈጽም አለዚያ አይሆንም ብሎ አወገዘው።
እስከ ይፈደዮ
ቀኖናውን እስኪፈጽም ድረስ።
ወርእዮሙ አብያጺሁ
መላእክት አይተው ፈጽመው አዘኑ ሰው ለሰው እንዲህ ይጨክናል ብለው።
ወሐዊሮሙ ነገርዎ
ሂደው የሠራውን ሥራ ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት።
(ሐተታ) መንገሩስ የለም የነገሩት አውቆ ሥራ እንዲሠራ አውቆ ሥራ መሥራቱን መናገር ነው።
ወእምዝ ጸውዖ
ከዚህ በኋላ በደዌ ጸራው።
ወይቤሎ
አንተ ክፉ ቄስ እኔ ኃጢአትህን ሁሉ አስተሰረይኩልህ።
እስመ አስተብቋዕከኒ፡፡
ማልደኸኛልና ስለማለድኸኝ።
አኮሁ መፍትው
እኔ ይቅር እንዳልኩህ አንተስ የወንድምህን ኃጢአት ልታስተሰርይለት አይገባሕምን። ተመየጥ አንተ ወአነ ተወከፍኩ ህየንቴከ ሞተ በከመ ተወክፈ ክርስቶስ ሞተ ህየንቴየ ወህየንተ ኵሎሙ ልትለው አይገባህም ነበር አለው።
ወተምዓ ወመጠዎ
ፈርዶ መከራ ለሚያጸኑበት ለደዌያት ሰጠው።
እስከ ይፈዲ
ቀኖናውን እስኪፈጽም ድረስ።
ወከማሁኬ
የወንድማችሁን ኃጢአት በፍጹም ልቡናችሁ ይቅር ካላላችሁ ሰማያዊ አባታትሁ አሁን እንደተናገርሁት ያደርግባችኋል።
                    ******     
በእንተ ዘተግኅሠ ኢየሱስ እምኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ ፲፱፡፡
፩፡ ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ ተንሥአ እምገሊላ ወሖረ ወበጽሐ ውስተ ብሔረ ይሁዳ ማዕዶተ ዮርዳኖስ። ማር ፲፥፩፡፡
፩፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ነገር አስተምሮ ከፈጸመ በኋላ ከገሊላ ወጥቶ የዮርዳኖስ ማዶ ወደሚሆን ወደምድረ ይሁዳ ደረሰ።
                        ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
18/09/2011 ዓ.ም

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 101

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
                    ******     
በእንተ ዘከመ ይደልዎሙ ለአኃው ተገሥጾ።
፲፭፡ ወእመኒ አበሰ ለከ እኁከ ሑር ወገሥፆ ለባሕቲትከ፡፡ ዘሌዋ ፲፱፥፲፯፡፡ ሲራ ፲፱፥፲፫፡፡ ሉቃ ፲፯፥፫፡፡ ያዕ ፭፥፲፱፡፡
                    ******     
፲፭፡ ወንድምህ ቢበድልህ በብቻህ ሁነህ በብቻው አድርገህ ለባሕቲትከ ለባሕቲቱ ለብቻህ ሁነህ ለብቻው አድርገህ ብቻህን ሁነህ ብቻውን አድርገህ ምከረው።
ወእመ ሰምዓከ ረባሕኮ ለእኁከ።
የተቀበለህ እንደሆነ ረባኸው ጠቀምኸው።
                    ******     
፲፮፡ ወእመሰ ኢሰምዓከ ንሣእ ምስሌከ በዳግም አሐደ። ዘዳ ፲፥፮፡፡ ዮሐ ፰፥፲፯፡፡ ፪፡ቆሮ ፲፫፥፩፡፡ ዕብ ፲፥፳፰።
                    ******     
፲፮፡ ባይቀበልህሀ ግን በሁለተኛው አንድ ሰው ጨምረህ ምከረው።
አው ፪ተ።
እናንተን ባይቀበል ሁለት ሰው ጩጨምረህ አንተ ሦስተኛ ሁነህ ምከረው።
እስመ በአፈ ፪ቱ ወ፫ቱ ሰማዕት ይቀውም ኵሉ ነገር።
በሁለት ምስክር ነገር ይጸናልና።
ንሣእ አሐደ
በሦስት ምስክር ነገር ይጸናልና፡፡
አንድም በአምስት ምስክር ነገር ይጸናልና፡፡ ንሣአ ፪ተ አው ፫ተ።
                    ******     
፲፯፡ ወእመሰ ኢሰምዖሙ ሎሙሂ ንግራ ለቤተ ክርስቲያን። ፩፡ቆሮ ፭፥፱፡፡ ፪፡ተሰሎ ፫፥፲፫፡፡
                    ******     
፲፯፡ እሳቸውንም ባይቀበል ንግሩ ለጉባዔ ይላል የፍርድ መጣፍ ባንድ ደወል ለሚሰበሰቡ ንገሩ እኒያን ባይቀበል ለቤተ ክርስቲያን ንገሩበት።
ወእመሰ ለቤተ ክርስቲያን ኢሰምዓ ይኩን ከመ አረማዊ ወመጸብሐዊ።
ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት እንደ አረማዊ እንደ መጸብሐዊ ይሁን ማለት ይለይ።
(ሐተታ) ወንድሙን ቢበድል እግዚአብሔርን የካደ ይመስል ይለይ ማለቱ ስለምነው ቢሉ። ወንድሙን ከበደለ ከሥጋው ከደሙ ይከለከላል ከሥጋው ከደሙ ከተከለከለ እንደ አረማዊ እንደ መጸብሐዊ መሆኑ ነውና፡፡
አንድም የሚያየውን ወንድሙን መበደሉ እግዚአብሔርን መበደሉ ነውና።
                    ******     
፲፰፡ አማን እብለክሙ ዘአሠርክሙ በምድር ይኩን እሱረ በሰማያት። ዮሐ ፳፥፳፫።
                    ******     
፲፰፡ ከምድራውያን ነገሥታት ከሌዋውያን ካህናት ወገን ያይደለን መለየቱ እንደምን ይሆናል ትሉኝ እንደሆነ በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ እንዲሆን።
ወዘፈታሕክሙ በምድር ይከውን ፍቱሐ በሰማያት።
በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ እንዲሆን በእውነት እነግራችኋለሁ። እንዳለፈው ም፲፮ ቊጥር ፲፱።
                    ******     
፲፱፡ ወዓዲ እብለክሙ ለእመ ኃብሩ ፪ አው ፫ እምኔክሙ በውስተ ምድር በእንተ ኵሉ ግብር ዘሰአሉ ይትገበር ሎሙ በኃበ አቡየ ዘበሰማያት።
                    ******     
፲፱፡ ያውስ ቢሆን ጥቂት ነን ብዙ አይደለን መለየቱ እንደምን ይሆንልናል ትሉኝ እንደሆነ ከእናንተ ወገን ስለሚሹት ነገር በዚህ ዓለም ሁለቱ ወይም ሦስቱ አንድ ቢሆኑ በሰማይ አባቴ ዘንድ የሚሹት ነገር ይደረግላቸዋል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡
                    ******     
፳፡ እስመ ኀበ ሀለዉ ፪ቱ ወ፫ቱ ጉቡዓነ በስምየ ህየ እሄሉ አነ ማዕከሎሙ።
                    ******     
፳፡ ሁለቱ ሦስቱ በስሜ አምነው አንድ ቢሆኑ አንድ በሆኑበት እኖራለሁ ማለት አድሬባቸው እኖራለሁና።
(ሐተታ) ሠለስቱ የተባሉ አንባቢ ተርጓሜ መጽሐፍ ናቸው።
አንድም ናዛዚ ተናዛዚ ኄር ላእክ ናቸው።
አንድም ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና ናቸው። ሃይማኖት ትውክልት ተፋቅሮ ናቸው ።
                    ******     
፳፩፡ ወእምዝ ቀርበ ጴጥሮስ ወይቤሎ እግዚኦ ሚመጠነ አመ አበሰ ሊተ እኁየ እኅድግ ሎቱ፡፡ ሉቃ ፲፯፥፬፡፡
                    ******     
፳፩፡ ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ አቤቱ ወንድሜ ምን ያህል ቢበድለኝ ይቅር ልበለው።
እስከ ስብዕኑ
እስከ ሰባት ድረስ ነውን አለው፡፡
                    ******     
፳፪፡ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ ኢይብለከ እስከ ስብዕ።
                    ******     
፳፪፡ እስከ ሰባት አልልህም
አላ እስከ ሰብዓ በበስብዕ
ሰባቱን አንድ ሰባቱን አንድ እያልክ እስክ ሰባ ነው እንጂ
አንድም እስከ ስብዕ በበሰብዓ
ሰባውን አንድ እየልክ እስከ ሰባት ነው እንጂ አለው።
                    ******     
በእንተ ምሳሌ አግብርት ወፈድዮተ ዕዳ።
፳፫፡ ወበእንተዝ እብለክሙ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ንጉሠ ዘፈቀደ ይትሀሰቦሙ ለአግብርቲሁ።
፳፫፡ ንስሐ የሚገባ ስለሆነ መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል፡ ሕገ ወንጌል ተስፋ፣ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብላቴኖቹን ሊቆጣጠራቸው የወደደ ንጉሥን ትመስላለች።
                    ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
17/09/2011 ዓ.ም

Friday, May 24, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 100

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
                    ******     
፩፡ ወበይእቲ ሰዓት ቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
እንዘ ይብሉ መኑ እንጋ የዓቢ በመንግሥተ ሰማያት። ማር ፱፥፴፫፡፡ ሉቃ ፱፥፵፮፡፡ ማቴ ፲፱፥፲፬፡፡
                    ******     
፩፡ ከዚያ ብፅዓን ሰጠው ከዚህ ገበረለት ሾመው እንጂ ሾመው ተባብለዋል። በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው በመንግሥተ ሰማይ በላይ የሚሆን ማነው አሉት፡፡     
                    ******     
፪፡ ወጸውዓ ሕፃነ ወአቀመ ማዕከሎሙ።
                    ******     
፪፡ ብላቴና ጠርቶ አቆመው።
                    ******     
፫፡ ወይቤ አማን እብለክሙ እመ ኢተመየጥክሙ ዝንቱ ሕፃን ኢትበውኡ ውስተ መንግሥተ ሰማያት። ፩፡ቆሮ ፲፬፥፳፡፡
                    ******     
፫፡ ተመልሳችሁ ከየውሃት ጠባይዓዊ ደርሳችሁ እንደዚህ ሕፃን ካልሆናችሁ መንግሥተ ሰማይ እንዳትገቡ በእውነት እነግራችኋለሁ።
                    ******     
፬፡ ወዘአትሐተ ርእሶ ከመ ዝንቱ ሕፃን ውእቱ የዓቢ በመንግሥተ ሰማያት።
                    ******     
፬፡ በመካከላቸው እንደዚህ ሕፃን ሁኖ ራሱን ያዋረደ የመንግሥተ ሰማይ ባለቤት ይሆናል። ይህም ትሕትና የሚያስተምርበት ሕፃን አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ነው። በአንጾኪያ የጴጥሮስ ሦስተኛ ሁኖ ተሹማል።
                    ******     
፭፡ ወዘሂ ተወክፈ ፩ደ ሕፃነ ዘከመዝ በስምየ ኪያየ ተወክፈ
                    ******     
፭፡ እንደዚህ ሕፃን የሆነውን በእኔ ስም የተቀበለ እኔን ተቀበለ ማለት እኔ አድርበታለሁ።
                    ******     
በእንተ ዘተናገረ ኢየሱስ በላዕለ ዕቅፍት።
ወዘሂ አስሐቶ ለ፩ዱ እምእሉ ንዑሳን እለ የአምኑ ብየ ይኄይሶ ከመ ይዕሥሩ በክሣዱ ማኅረፀ አድግ ወያስጥምዎ ውስተ ልጐተ ባሕር።
                    ******     
፮፡ በእኔ ከአመኑ ምዕመናን አንዱን ያሳተ አህያ በመዘውር የሚፈጭባትን ወፍጮ ከአንገቱ አሥሮ ከጥልቅ ባሕር ቢያሰጥሙት ይሻለዋል።
አንድም ጽኑ ቀኖና ሰጥተው በአንብዓ ንስሐ ቢያሰጥሙት ይሻለዋል።
                    ******     
፯፡ አሌ ሎቱ ለዓለም እመንሱት ዘይመጽእ።
                    ******     
፯፡ ከሚመጣው መከራ የተነሣ ለሰው ሁሉ ወዮለት።
እስመ ግብር ይመጽእ መንሱት
መከራ ግድ ይመጣልና።
ወባሕቱ አሌ ሎቱ ለውእቱ ብእሲ ዘያመጽኣ ለመንሱት።
ነገር ግን ዋዛ ፈዛዛ ተጫውቶ መከራን ለሚያመጣት ለይሁዳ ወዮለት።
                    ******     
፰፡ ወእመኒ እዴከ አው እግርከ ታስሕተከ ምትራ ወግድፋ እምላዕሌከ። ማቴ ፭፥፴፡፡ ማር ፱፥ሣ፪።
                    ******     
፰፡ እጅህም ብትሆን ወይም እግርህ ብታስትህ ከአንተ ቈርጠህ ጣላት።
እስመ ይኄይሰከ ትባእ ውስተ ሕይወት ሐንካሳከ ወጽውሰከ እምእንዘ ብከ ፪ አዕዳው ወ፪ አእጋር ትትወደይ ውስተ እሳት ዘለዓለም።
ሁለት እጅ ሁለት እግር ኑሮህ ወደ ዘለዓለም እሳት ስትገባ አንካሳ ልምሾ ሁነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሸልሃልና።
                    ******     
፱፡ ወእመሂ ዓይንከ ታስሕተከ ምልሓ ወአውጽኣ እምላዕሌከ
                    ******     
፱፡ ዓይንህ ብታስትህ አውጥተህ ጣላት።
                    ******     
እስመ ይኄይሰከ ነቋረከ ትባዕ ውስተ ሕይወት እምትባዕ ምስለ ፪ሆን አዕይንቲከ ውስተ እሳተ ገሃነም።

ሁለት ዓይን ኑሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትገባ አንድ ዓይን ኑሮህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ይሸልሃልና፡፡
አንድም ወእመሂ ዓይንከ ብለህ መልስ፡፡ ኤጲስ ቆጶስህን ብትነቅፈው ሻረው፡፡ እስመ ይኄይሰከ የነቀፍከውን ኤጲስ ቆጶስ ሹመህ ኑረህ ኋላ ገሃነመ እሳት ከምትገባ የነቀፍኸውን ኤጲስ ቆጶስ ሽረህ ኑረህ ኋላ መንግሥተ ሰማይ ብትገባ ይሻልሃልና፡፡
                    ******     
፲፡ ዑቁ ኢታስተኃቅርዎሙ ለ፩ እምእሉ ንዑሳን፡፡ መዝ ፴፫፥፯፡፡
                    ******     
፲፡  ከአመኑ ምዕመናን አንዱን እንዳትንቁ እንዳታቃልሉ አስተውሉ፡፡
እብለክሙ ከመ መላእክቲሆሙ በሰማያት ወትረ ይሬእዩ ገጾ ለአቡየ ዘበሰማያት።
መላአክት ዑቃቤዎቻቸው ያባቴን ፊት ዘወትር ያያሉ ማለት መላእክተ ዑቃቤዎቻቸው በባለሟልነት እንዳሉ እነግራችኋለሁ እንዳይቀስፏችሁ ማለት ነው።
አንድም መላአክተ ዑቃቤዎቻቸው በባለሟልነት እንዳሉ እሳቸውም በባለሟልነት እንዳሉ እነግራችኋለሁ እንዳያስፈርዱባችሁ ማለት ነው።
                    ******     
በእንተ በግዕት ዘተሐጕለት።
፲፩፡ እስመ መጽአ ወልደ እጓለ እመሕያው ይኅሥሥ ወያድኅን ዘተኃጕለ። ሉቃ ፲፱፥፲።
                    ******     
፲፩፡ ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስ የጠፋውን ሊሻ የተጐዳውን ሊያድን ሰው ሁኑዋልና።
                    ******     
፲፪፡ ምንተ ትብሉ። ሉቃ ፲፫፥፬።
                    ******     
፲፪፡ አንቀጸ ንስሐ ነው ምን ትፈርዳላችሁ።
እመቦ ብእሲ ዘቦቱ ፻ አባግዕ።
መቶ በግ ያለው ሰው ቢኖር
ወእመ ተገድፎ ፩ እምኔሆሙ፡፡
ከመቶው አንዱ ቢጠፋበት።
አኮሁ የኃድግ ፺ወ፱ተ ውስተ ገዳም።
ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ።
ወየሐውር ይኅሥሥ ዘተገድፎ
የጠፋበትን ሊፈልግ ይሄድ የለምን።
                    ******     
፲፫፡ ወእምከመ ረከቦ አማን እብለክሙ ከመ ይትፌሣሕ በእንቲአሁ ፈድፋደ እም ፺ወ፱ እለ ኢተገድፉ።
                    ******     
፲፫፡ ያገኘው እንደሆነ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ ጠፍቶ በተገኘው ደስ ይለዋል ብዬ ደስ እንዲለው በእውነት እነግራችኋለሁ።
                    ******     
፲፬፡ ከማሁኬ ኢይፈቅድ አቡየኒ ዘበሰማያት ከመ ይትኃጐል ፩ዱ እምእሉ ንዑሳን።
                    ******     
፲፬፡ እንደዚህም ሁሉ ሰማያዊ አባቴ ከተነሣሕያን አንዱ ሊጐዳ አይወድም።
አንድም ምንተ ትብሉ ብለህ መልስ። መቶ በጎች የተባሉ መቶ ነገደ መላእክት ናቸው ከመቶው አንዱ ዲያብሎስ ቢወጣ በሱ ስፍራ አዳም ቢገባ አዳም ቢወጣ አኮሁ የኃድግ ባሕርየ መላእክትን ትቶ ባሕርየ አዳምን ገንዘብ ማድረጉን መናገር ነው። ኢነሥኦ ለዘነሥኦ እመላእክት ዘእንበለ ዳዕሙ እምዘርዓ አብርሃም እንዲል። ወእምከመ ረከበ አዳምን ንስሐ ገብቶ ቢያገኘው አማን እብለክሙ ንስሐ ከማያሻቸው ከመላእክት ይልቅ ንስሐ በሚያሻው በአዳም መመለስ ደስ ይለዋል ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
ከማሁኬ ኢይፈቅድ አቡየኒ ዘበሰማያት ከመ ይትኃጐል ፩ዱ እምእሉ ንዑሳን፡፡
አሁን እንደ ተናገርነው ሰማያዊ አባቴ ከተነሳሕያን አንዱ ሊጐዳ አይወድም።
                    ******     
በእንተ ዘከመ ይደልዎሙ ለአኃው ተገሥጾ\።
፲፭፡ ወእመኒ አበሰ ለከ እኁከ ሑር ወገሥፆ ለባሕቲትከ፡፡ ዘሌዋ ፲፱፥፲፯፡፡ ሲራ ፲፱፥፲፫፡፡ ሉቃ ፲፯፥፫፡፡ ያዕ ፭፥፲፱፡፡
                    ******     
፲፭፡ ወንድምህ ቢበድልህ በብቻህ ሁነህ በብቻው አድርገህ ለባሕቲትከ ለባሕቲቱ ለብቻህ ሁነህ ለብቻው አድርገህ ብቻህን ሁነህ ብቻውን አድርገህ ምከረው።   ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
16/09/2011 ዓ.ም

Wednesday, May 22, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 99

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ከመ ተወለጠ ኢየሱስ በደብረ ታቦር።
ምዕራፍ ፲፯።
                    ******     
በእንተ ወርኃዊ  ዘይፄአር።
፲፬፡ ወበጺሖ ኀበ አሕዛብ ይቤሎሙ ምንትኑ ትትኀሠሥዎሙ፡፡ ማር ፪፥፲፮፡፡ ሉቃ ፱፥፴፰።
                    ******     
፲፬፡ ከሕዝቡ በደረሰ ጊዜ ለምን ታዳክሟቸዋላችሁ አላቸው።
(ሐተታ) ስምንቱን መምሕራችሁ ወዴት ሄደ እያሉ ሲያደክሟቸው ቈይተዋል።
ወቀርበ ኀቤሁ ብእሲ ወሰገደ ሎቱ እንዘ ይትመሐለል ወይብል ተሣሃል ሊተ ወልድየ።
ከነገር ያልገባ ሰው ነው ለብቻው ቆይቶ ሰገደለት አቤቱ ልጄን አድንልኝ አለው።
እስመ አኵይ ጋኔን አኃዞ
ቢስ ጋኔን አድሮበታልና፡
ወበአርእስተ አውራኅ ይሣቅዮ
ወርኅ እያየ ይጥለዋልና ምልዓተ ወርኅ ሲሆን ደም ይመላል ብርድ ብርድ ይላል ደዌ ይቀሰቀሳልና ጨረቃ እንጂ ባታመልኩ ነው ለማለት።
ወመብዝኅቶሰ ያወድቆ ውስተ እሳት ወቦ አመ ያወድቆ ውስተ ማይ።
ይልቁንም ብዙ ጊዜ ከእሳት ከውሃ ይጥለዋል፡፡
                    ******     
፲፭፡ ወአምጻእክዎ ኀበ አርዳኢከ።
                    ******     
፲፭፡ ያድኑልኛል ብዬ ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት።
ወስዕኑ ፈውሶቶ።
ማዳን ተሳናቸው፤
                    ******     
፲፮፡ ወእምዝ አውሥአ እግዚእ ኢየሱስ፡
                    ******     
፲፮፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን መለሰ
ወይቤ ኦ ትውልድ ኢአማኒት ወዕሉት።
እንቢተኛ አሉተኛ ትውልድ ሐዋርያት ።
እስከ ማዕዜኑ እኄሉ ምስሌክሙ
እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ
ወእስከ ማዕዜኑ እትኤገሠክሙ
እስከ መቼ ዝም እላችኋለሁ አላቸው።
(ሐተታ) ንጉሥ በሌለበት ጊዜ ከንቲባ መሥራት መቅጻት እንዲገባው ባያውቁ መምሕራችን በሌለበት ጊዜ አይቻለንም ብለዋልና። እስከ መቼ ከናንተ ጋራ እኖራለሁ ንጉሥ ባለ ጊዜ ከንቲባ መሥራት መቅጻት እንዳይገባው ባያውቁ መምራችን ሳለ ነው እንጂ ብለዋልና፡፡ እስከ መቼ ዝም አላችኋለሁ ሳለሁማ እኔ አደርገው የለምን ሲል እንዲህ አለ።
አምጽእ ሊተ ዝየ።
ወዲህ አምጣልኝ አለ።
                    ******     
፲፯፡ ወገሠፆ እግዚአ ኢየሱስ።
                    ******     
፲፯፡ ጌታ ገሠፀው ማለት ፃዕ መንፈስ ርኩስ አለው።
ወወፅአ ጋኔኑ እምላዕሌሁ።
ጋኔኑ ከሱ ወጣ።
ወሐይወ ወልዱ በይእቲ ሰዓት
ልጁ በዚያች ሰዓት ዳነ።
                    ******     
፲፰፡ ወእምዝ ቀሪቦሙ አርዳኢሁ እንተ ባሕቲቶሙ ይቤልዎ ለእግዚአ ኢየሱስ በእንተ ምንት ንሕነ ስዕነ አውፅኦቶ።
                    ******     
፲፰፡ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ቀርበው እኛ ማስወጣት ስለምን ተሣነን አሉት፡፡
                    ******     
፲፱፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ በእንተ ሕፀተ ሃይማኖትክሙ፡፡ ሉቃ ፲፯፥፮፡፡
                    ******     

፲፱፡ ስለ ሃይማኖታችሁ ማነስ ማለት ሃይማኖት ባይኖራችሁ ነዋ አላቸው።
አማን እብለክሙ እመ ብክሙ ሃይማኖት መጠነ ኀጠተ ሰናፔ።
አካሏን አይሻም ፍጽምት ናት ፍጹም ሃይማኖት ቢኖራችሁ
ወትብልዎ ለዝ ደብር ፍልስ እምዝየ ኀበ ከሀ ወይፈልስ
ይህን ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ወዲያ ሂድ ብትሉት እንዲሄድ።
ወአልቦ ዘይሰአነክሙ።
ቸግሯችሁ የሚቀር እንደሌለ በእውነት እነግራችኋለሁ።
(ሐተታ) ሊጻፍ ባይቻል ነው እንጂ በሱ ጊዜ ተደርጓል በሱ ጊዜስ አልተደረገም በአብርሃም ሶርያዊ ጊዜ የተደረገውን መናገር ነው፡፡ ለሊቀ ጳጳሱ አንድ አይሁዳዊ ወዳጅ ነበረው ከንጉሠ ተንላት ወዳጆች ናቸው ያም ሊጠይቅ ያም ሊጠይቅ እየሄዱ ይገናኛሉ እየተከራከሩ ሊቀ ጳጳስ አይሁዳዊን ምላሽ ያሳጣዋል ከዕለታት አንድ ቀን ለብቻው ገብቶ ነገር ሠራ የኒህ የክርስቲያን ሃይማኖታቸው እንጂ ደካማ ነው አለው። እንኪያ እየተከራከሩ ምላሽ ያሳጣችኋልሳ አለው። ለዚህማ ምልክት እንጅል የምትባል መጽሐፍ አለቻቸው ለእመ ብክሙ ትላለች። አድርጉ ብትላቸው አይሆንላቸውም አለው እሱን ሲያገኘው ነገሩን ያጣዋል ነገሩ ትዝ ሲለው እሱን ያጣዋል ከዕለታት ባንድ ቀን እሱ ባለበት ነገሩ ትዝ አለው አባቴ የምጠይቅህ ኑሮኝ አንተን ሳገኝህ ነገሩን እያጣሁት ነገሩ ትዝ ሲለኝ አንተን እያጣሁህ ነበር። አሁን ግን ነገሩም ትዝ ብሎኛል አንተም መጥተሃል አለው። ምንድነው አለው እንጅል የምትባል መጽሐፍ አለቻችሁን አለው። አዎን አለው እንዲህ ትላለች አለው አዎን አለው ታደርጋላችሁን አለው አዎን አለው። ሚመጠን አእላፍ ክርስቲያን የዚህ ሁሉ ክርስቲያንማ ሃይማኖት ተራራ አያህልምን እንኪያስ አድርገህ አሳየኝ አለው ቀን ስጠኝ አለው ሦስት ቀን ሰጠው ሂዶ ከእመቤታችን ሥዕል አመለከተ ልጄ እንዲህ ያለው ላንተ አይደረግልህም የሚደረግለት ስምዖን ዘአሐቲ ዓይኑ አለ ተርታ ሰው መስሎ ከገበያ እንጨት ሲሸጥ ታገኘዋልህ ሂደህ ንገረው እኔን አለችህ በለው፡፡ ያለዚያ በጅ አይልህም አለችው ቢሄድ እንደነገረችው አገኘው እየፈራ ሂዶ በስተኋላው ልብሱን ያዘው አወቀብኝ ብሎ ተቆጣው ምን አድርግ ትለኛለህ በሀገርህ ድኃ አይኖርምን አለው እመቤታችን ልካኝ ነው ብሎ ነገሩን ገልጦ ነገረው። እንኪያስ እኔን አትግለጠኝ ክርስቲያንን ባንድ ወገን አሕዛብን በአንድ ወጎን ሰብስበህ ካህናቱን ልብሰ ተክህኖ አልብሰህ ቈየኝ አንተ እኔ የምሠራውን ሥራ እያየህ ሥራ ሕዝቡ አንተ የምትሠራውን እያዩ ይሥሩ፡፡ ፵፩ ኪርያላይሶን አድርሰው ሰግደው ሲነሱ ተራራው ተነሣ በውስጡ ተያዩ ሲሰግዱ ይመለሳል ሲነሱ ይነሣል ሦስት ጊዜ አንዲሁ አድርገው በአራተኛው እየወጣ የሚያውካቸው ውሀ ነበር ሂደህ ተጋረድላቸው ብሎት ቦታውን ለቆ ሂዶ ተጋርዶላቸዋል፡፡
አንድም ለእመ ብክሙ ብለህ መልስ። ሰመዮ ደብረ በእንተ ትዕቢቱ ምንትኑ ዝ ደብር ቅድመ ዘሩባቤል እንዲል። ደብር የተባለ ዲያብሎስ ነው ፍጹም ሃይማኖት ቢኖራችሁ ሰይጣንን ውጣ ብትሉት ይወጣል ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
                    ******     
፳፡ ወዝንቱ ዘመድ ኢይወፅእ ዘእንበለ በጾም ወበጸሎት።
                    ******     
፳፡ ይህ አብሮ አደግ ጋኔን ከአልጾሙ ከአልጸለዩ አይወጣም።
አንድም ይህ ደካማ ባሕርያችሁ ካልጾመ ካልጸለየ ጋኔን አያወጣም።
አንድም ወዘመደ ፍጥረትኒ መስዎ ለአስሐትያ እንዲል። ይህ የፍጥረት ወገን የሚሆን ሰይጣን ካልጾሙ ካልጸለዩ አይወጣም።
                    ******     
፳ወእንዘ ያንሶሱ ውስተ ገሊላ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ያግብእዎ ውስተ እደ ሰብእ። ማቴ ፳፥፲፰፡፡ ማር ፱፥፴፡፡ ሉቃ ፱፥፵፬፡፡
                    ******     
፳፩፡ ጌታ በገሊላ ሲመላለስ የሰውን ልጅ ያሲዙት ዘንድ አላቸው ማለት እያዛለሁ።
                    ******     
፳፪፡ ወይቀትልዎ።
                    ******     
፳፪፡ እሞታለሁ።
ወአመ ሣልስት ዕለት ይትነሣእ
በሦስት ቀን እነሣለሁ አላቸው
ወተከዙ ጥቀ አርዳኢሁ ሰሚፆሙ ዘንተ።
ደቀ መዛሙርቱ ይኽን ሰምተው ፈጽመው አዘኑ።
                    ******     
በእንተ ውሂበ ፀባሕት ።
፳፫፡ ወበጺሖሙ ቅፍርናሆም መጽኡ እለ ጸባሕተ ዲናር ይነሥኡ እምኀበ ጴጥሮስ።
                    ******     
፳፫፡ ቅፍርናሆም በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች መጡ።
ወይቤልዎ ሊቅክሙሰ ኢይጸብሕኑ ጸባሕተ።
መምራችሁ አይገብርም አሉት
                    ******     
፳፬፡ ወይቤ እወ።
                    ******     
፳፬፡ የኔ መምህር አዎን ይገብራል አዎን አይገብርም አላቸው።
ወበዊዖ ውስተ ቤት አቅደመ እግዚእ ኢየሱስ ብሂሎቶ።
ከቤት በገባ ጊዜ ጌታ አስቀድሞ ጠየቀው።
ምንተ ትብል ኦ ስምዖን።
ስምዖን ሆይ ምን ትፈርዳለህ
ነገሥተ ምድር እምኀበ መኑ ይነሥኡ ጸባሕተ ወጋዳ
ነገሥታት የዓመት ግብር እና እድ መንሻ ከማን ይቀበላሉ። -
እምኀበ ውሉዶሙኑ ወሚመ እምኀበ ነኪር።
ከልጆቻቸውን ነው ወይም ከሌላ አለው፡፡
                    ******     
፳፭፡ ወይቤ እምኀበ ነኪር፡፡
                    ******     
፳፭፡ ከሌላ ነው እንጅ ልጆቻቸውማ ይገብሩን ያስገብሩን አለው፡፡
ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ ውሉዶሙሰ እንጋ አግዓዝያንኑ እሙንቱ፡፡
እንኪያ ልጆቻቸው ነጻ ናቸዋ አለው እኔም ነፃ ነኝ ሲል ነው እንከሰ ግዑዝ ውእቱ ወልድ ብሎታል ሊቁ፡፡
                    ******     
፳፮፡ ወባሕቱ ከመ ኢያጐንርጕሩ ሑር ውስተ ባሕር ወደይ መቃጥነ፡፡
                    ******     
፳፮፡ ነገር ግን እንዳያዝኑ ከባሕር ሂደህ መረብህን ጣል
ወዘቀዳሚ አሥገርካ ዓሣ ንሣእ ወክሥት አፉሁ።
መጀመሪያ የያዝኸውን ዓሣ ወስደህ አፉን ክፈት ማለት ሆዱን ቅደደው።
ወትረክብ ውስቴቱ ሰጢጥራስ ዘውእቱ ፬ቱ ድርኀም።
በውሥጡም አራት ድሪም ታገኛለህ።
ኪያሁ ንሣእ ወሀቦመሙ ህየንቴየ ወህየንቴከ፡፡
እሱን ወስደህ ፪ን ስለኔ ፪ን ስላንተ ስጣቸው አለው።
(ሐተታ) ቀመቱ ፭ ፭ አይደለም ቢሉ በዘመን ብዛት ቀርቷል፡፡ ከገበረስ አጉድሎም አይገብር ብሎ የሚዛን ደግነት ነው፡፡ ባሕር የዚህ ዓለም ሰጢጥራስ የወንጌል ምሳሌ ፬ት ድርሀም ፬ት ክፍል ሁና መጻፏን ያጠይቃል ወንጌልን ገንዘብ አድርገህ
ህየንቴየ
አሕዛብን
ህየንቴከ
እስራኤልን አስተምር ሲል ነው፡፡ ከዚህም እንደ ሰውነቱ ገበረ እንደ አምላክነቱ ባሕርን አስገበረ።
                    ******     
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
፩፡ ወበይእቲ ሰዓት ቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
እንዘ ይብሉ መኑ እንጋ የዓቢ በመንግሥተ ሰማያት። ማር ፱፥፴፫፡፡ ሉቃ ፱፥፵፮፡፡ ማቴ ፲፱፥፲፬፡፡
፩፡ ከዚያ ብፅዓን ሰጠው ከዚህ ገበረለት ሾመው እንጂ ሾመው ተባብለዋል። በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው በመንግሥተ ሰማይ በላይ የሚሆን ማነው አሉት፡፡
                    ******     
   ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
15/09/2011 ዓ.ም