====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ከመ
ተወለጠ ኢየሱስ በደብረ ታቦር።
ምዕራፍ
፲፯።
******
በእንተ
ወርኃዊ ዘይፄአር።
፲፬፡
ወበጺሖ ኀበ አሕዛብ ይቤሎሙ ምንትኑ ትትኀሠሥዎሙ፡፡ ማር ፪፥፲፮፡፡ ሉቃ ፱፥፴፰።
******
፲፬፡
ከሕዝቡ በደረሰ ጊዜ ለምን ታዳክሟቸዋላችሁ አላቸው።
(ሐተታ)
ስምንቱን መምሕራችሁ ወዴት ሄደ እያሉ ሲያደክሟቸው ቈይተዋል።
ወቀርበ
ኀቤሁ ብእሲ ወሰገደ ሎቱ እንዘ ይትመሐለል ወይብል ተሣሃል ሊተ ወልድየ።
ከነገር
ያልገባ ሰው ነው ለብቻው ቆይቶ ሰገደለት አቤቱ ልጄን አድንልኝ አለው።
እስመ
አኵይ ጋኔን አኃዞ
ቢስ
ጋኔን አድሮበታልና፡
ወበአርእስተ
አውራኅ ይሣቅዮ
ወርኅ
እያየ ይጥለዋልና ምልዓተ ወርኅ ሲሆን ደም ይመላል ብርድ ብርድ ይላል ደዌ ይቀሰቀሳልና ጨረቃ እንጂ ባታመልኩ ነው ለማለት።
ወመብዝኅቶሰ
ያወድቆ ውስተ እሳት ወቦ አመ ያወድቆ ውስተ ማይ።
ይልቁንም
ብዙ ጊዜ ከእሳት ከውሃ ይጥለዋል፡፡
******
፲፭፡
ወአምጻእክዎ ኀበ አርዳኢከ።
******
፲፭፡
ያድኑልኛል ብዬ ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት።
ወስዕኑ
ፈውሶቶ።
ማዳን
ተሳናቸው፤
******
፲፮፡
ወእምዝ አውሥአ እግዚእ ኢየሱስ፡
******
፲፮፡
ከዚህ በኋላ ጌታችን መለሰ
ወይቤ
ኦ ትውልድ ኢአማኒት ወዕሉት።
እንቢተኛ
አሉተኛ ትውልድ ሐዋርያት ።
እስከ
ማዕዜኑ እኄሉ ምስሌክሙ
እስከ
መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ
ወእስከ
ማዕዜኑ እትኤገሠክሙ
እስከ
መቼ ዝም እላችኋለሁ አላቸው።
(ሐተታ)
ንጉሥ በሌለበት ጊዜ ከንቲባ መሥራት መቅጻት እንዲገባው ባያውቁ መምሕራችን በሌለበት ጊዜ አይቻለንም ብለዋልና። እስከ መቼ ከናንተ
ጋራ እኖራለሁ ንጉሥ ባለ ጊዜ ከንቲባ መሥራት መቅጻት እንዳይገባው ባያውቁ መምራችን ሳለ ነው እንጂ ብለዋልና፡፡ እስከ መቼ ዝም
አላችኋለሁ ሳለሁማ እኔ አደርገው የለምን ሲል እንዲህ አለ።
አምጽእ
ሊተ ዝየ።
ወዲህ
አምጣልኝ አለ።
******
፲፯፡
ወገሠፆ እግዚአ ኢየሱስ።
******
፲፯፡
ጌታ ገሠፀው ማለት ፃዕ መንፈስ ርኩስ አለው።
ወወፅአ
ጋኔኑ እምላዕሌሁ።
ጋኔኑ
ከሱ ወጣ።
ወሐይወ
ወልዱ በይእቲ ሰዓት
ልጁ
በዚያች ሰዓት ዳነ።
******
፲፰፡
ወእምዝ ቀሪቦሙ አርዳኢሁ እንተ ባሕቲቶሙ ይቤልዎ ለእግዚአ ኢየሱስ በእንተ ምንት ንሕነ ስዕነ አውፅኦቶ።
******
፲፰፡
ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ቀርበው እኛ ማስወጣት ስለምን ተሣነን አሉት፡፡
******
፲፱፡
ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ በእንተ ሕፀተ ሃይማኖትክሙ፡፡ ሉቃ ፲፯፥፮፡፡
******
፲፱፡
ስለ ሃይማኖታችሁ ማነስ ማለት ሃይማኖት ባይኖራችሁ ነዋ አላቸው።
አማን
እብለክሙ እመ ብክሙ ሃይማኖት መጠነ ኀጠተ ሰናፔ።
አካሏን
አይሻም ፍጽምት ናት ፍጹም ሃይማኖት ቢኖራችሁ
ወትብልዎ
ለዝ ደብር ፍልስ እምዝየ ኀበ ከሀ ወይፈልስ
ይህን
ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ወዲያ ሂድ ብትሉት እንዲሄድ።
ወአልቦ
ዘይሰአነክሙ።
ቸግሯችሁ
የሚቀር እንደሌለ በእውነት እነግራችኋለሁ።
(ሐተታ)
ሊጻፍ ባይቻል ነው እንጂ በሱ ጊዜ ተደርጓል በሱ ጊዜስ አልተደረገም በአብርሃም ሶርያዊ ጊዜ የተደረገውን መናገር ነው፡፡ ለሊቀ
ጳጳሱ አንድ አይሁዳዊ ወዳጅ ነበረው ከንጉሠ ተንላት ወዳጆች ናቸው ያም ሊጠይቅ ያም ሊጠይቅ እየሄዱ ይገናኛሉ እየተከራከሩ ሊቀ
ጳጳስ አይሁዳዊን ምላሽ ያሳጣዋል ከዕለታት አንድ ቀን ለብቻው ገብቶ ነገር ሠራ የኒህ የክርስቲያን ሃይማኖታቸው እንጂ ደካማ ነው
አለው። እንኪያ እየተከራከሩ ምላሽ ያሳጣችኋልሳ አለው። ለዚህማ ምልክት እንጅል የምትባል መጽሐፍ አለቻቸው ለእመ ብክሙ ትላለች።
አድርጉ ብትላቸው አይሆንላቸውም አለው እሱን ሲያገኘው ነገሩን ያጣዋል ነገሩ ትዝ ሲለው እሱን ያጣዋል ከዕለታት ባንድ ቀን እሱ
ባለበት ነገሩ ትዝ አለው አባቴ የምጠይቅህ ኑሮኝ አንተን ሳገኝህ ነገሩን እያጣሁት ነገሩ ትዝ ሲለኝ አንተን እያጣሁህ ነበር። አሁን
ግን ነገሩም ትዝ ብሎኛል አንተም መጥተሃል አለው። ምንድነው አለው እንጅል የምትባል መጽሐፍ አለቻችሁን አለው። አዎን አለው እንዲህ
ትላለች አለው አዎን አለው ታደርጋላችሁን አለው አዎን አለው። ሚመጠን አእላፍ ክርስቲያን የዚህ ሁሉ ክርስቲያንማ ሃይማኖት ተራራ
አያህልምን እንኪያስ አድርገህ አሳየኝ አለው ቀን ስጠኝ አለው ሦስት ቀን ሰጠው ሂዶ ከእመቤታችን ሥዕል አመለከተ ልጄ እንዲህ ያለው
ላንተ አይደረግልህም የሚደረግለት ስምዖን ዘአሐቲ ዓይኑ አለ ተርታ ሰው መስሎ ከገበያ እንጨት ሲሸጥ ታገኘዋልህ ሂደህ ንገረው እኔን
አለችህ በለው፡፡ ያለዚያ በጅ አይልህም አለችው ቢሄድ እንደነገረችው አገኘው እየፈራ ሂዶ በስተኋላው ልብሱን ያዘው አወቀብኝ ብሎ
ተቆጣው ምን አድርግ ትለኛለህ በሀገርህ ድኃ አይኖርምን አለው እመቤታችን ልካኝ ነው ብሎ ነገሩን ገልጦ ነገረው። እንኪያስ እኔን
አትግለጠኝ ክርስቲያንን ባንድ ወገን አሕዛብን በአንድ ወጎን ሰብስበህ ካህናቱን ልብሰ ተክህኖ አልብሰህ ቈየኝ አንተ እኔ የምሠራውን
ሥራ እያየህ ሥራ ሕዝቡ አንተ የምትሠራውን እያዩ ይሥሩ፡፡ ፵፩ ኪርያላይሶን አድርሰው ሰግደው ሲነሱ ተራራው ተነሣ በውስጡ ተያዩ
ሲሰግዱ ይመለሳል ሲነሱ ይነሣል ሦስት ጊዜ አንዲሁ አድርገው በአራተኛው እየወጣ የሚያውካቸው ውሀ ነበር ሂደህ ተጋረድላቸው ብሎት
ቦታውን ለቆ ሂዶ ተጋርዶላቸዋል፡፡
አንድም
ለእመ ብክሙ ብለህ መልስ። ሰመዮ ደብረ በእንተ ትዕቢቱ ምንትኑ ዝ ደብር ቅድመ ዘሩባቤል እንዲል። ደብር የተባለ ዲያብሎስ ነው
ፍጹም ሃይማኖት ቢኖራችሁ ሰይጣንን ውጣ ብትሉት ይወጣል ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
******
፳፡
ወዝንቱ ዘመድ ኢይወፅእ ዘእንበለ በጾም ወበጸሎት።
******
፳፡
ይህ አብሮ አደግ ጋኔን ከአልጾሙ ከአልጸለዩ አይወጣም።
አንድም
ይህ ደካማ ባሕርያችሁ ካልጾመ ካልጸለየ ጋኔን አያወጣም።
አንድም
ወዘመደ ፍጥረትኒ መስዎ ለአስሐትያ እንዲል። ይህ የፍጥረት ወገን የሚሆን ሰይጣን ካልጾሙ ካልጸለዩ አይወጣም።
******
፳ወእንዘ
ያንሶሱ ውስተ ገሊላ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ያግብእዎ ውስተ እደ ሰብእ። ማቴ ፳፥፲፰፡፡ ማር ፱፥፴፡፡
ሉቃ ፱፥፵፬፡፡
******
፳፩፡
ጌታ በገሊላ ሲመላለስ የሰውን ልጅ ያሲዙት ዘንድ አላቸው ማለት እያዛለሁ።
******
፳፪፡
ወይቀትልዎ።
******
፳፪፡
እሞታለሁ።
ወአመ
ሣልስት ዕለት ይትነሣእ
በሦስት
ቀን እነሣለሁ አላቸው
ወተከዙ
ጥቀ አርዳኢሁ ሰሚፆሙ ዘንተ።
ደቀ
መዛሙርቱ ይኽን ሰምተው ፈጽመው አዘኑ።
******
በእንተ
ውሂበ ፀባሕት ።
፳፫፡
ወበጺሖሙ ቅፍርናሆም መጽኡ እለ ጸባሕተ ዲናር ይነሥኡ እምኀበ ጴጥሮስ።
******
፳፫፡
ቅፍርናሆም በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች መጡ።
ወይቤልዎ
ሊቅክሙሰ ኢይጸብሕኑ ጸባሕተ።
መምራችሁ
አይገብርም አሉት
******
፳፬፡
ወይቤ እወ።
******
፳፬፡
የኔ መምህር አዎን ይገብራል አዎን አይገብርም አላቸው።
ወበዊዖ
ውስተ ቤት አቅደመ እግዚእ ኢየሱስ ብሂሎቶ።
ከቤት
በገባ ጊዜ ጌታ አስቀድሞ ጠየቀው።
ምንተ
ትብል ኦ ስምዖን።
ስምዖን
ሆይ ምን ትፈርዳለህ
ነገሥተ
ምድር እምኀበ መኑ ይነሥኡ ጸባሕተ ወጋዳ
ነገሥታት
የዓመት ግብር እና እድ መንሻ ከማን ይቀበላሉ። -
እምኀበ
ውሉዶሙኑ ወሚመ እምኀበ ነኪር።
ከልጆቻቸውን
ነው ወይም ከሌላ አለው፡፡
******
፳፭፡
ወይቤ እምኀበ ነኪር፡፡
******
፳፭፡
ከሌላ ነው እንጅ ልጆቻቸውማ ይገብሩን ያስገብሩን አለው፡፡
ወይቤሎ
እግዚእ ኢየሱስ ውሉዶሙሰ እንጋ አግዓዝያንኑ እሙንቱ፡፡
እንኪያ
ልጆቻቸው ነጻ ናቸዋ አለው እኔም ነፃ ነኝ ሲል ነው እንከሰ ግዑዝ ውእቱ ወልድ ብሎታል ሊቁ፡፡
******
፳፮፡
ወባሕቱ ከመ ኢያጐንርጕሩ ሑር ውስተ ባሕር ወደይ መቃጥነ፡፡
******
፳፮፡
ነገር ግን እንዳያዝኑ ከባሕር ሂደህ መረብህን ጣል
ወዘቀዳሚ
አሥገርካ ዓሣ ንሣእ ወክሥት አፉሁ።
መጀመሪያ
የያዝኸውን ዓሣ ወስደህ አፉን ክፈት ማለት ሆዱን ቅደደው።
ወትረክብ
ውስቴቱ ሰጢጥራስ ዘውእቱ ፬ቱ ድርኀም።
በውሥጡም
አራት ድሪም ታገኛለህ።
ኪያሁ
ንሣእ ወሀቦመሙ ህየንቴየ ወህየንቴከ፡፡
እሱን
ወስደህ ፪ን ስለኔ ፪ን ስላንተ ስጣቸው አለው።
(ሐተታ)
ቀመቱ ፭ ፭ አይደለም ቢሉ በዘመን ብዛት ቀርቷል፡፡ ከገበረስ አጉድሎም አይገብር ብሎ የሚዛን ደግነት ነው፡፡ ባሕር የዚህ ዓለም
ሰጢጥራስ የወንጌል ምሳሌ ፬ት ድርሀም ፬ት ክፍል ሁና መጻፏን ያጠይቃል ወንጌልን ገንዘብ አድርገህ
ህየንቴየ
አሕዛብን
ህየንቴከ
እስራኤልን
አስተምር ሲል ነው፡፡ ከዚህም እንደ ሰውነቱ ገበረ እንደ አምላክነቱ ባሕርን አስገበረ።
******
በእንተ
ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ
፲፰።
፩፡
ወበይእቲ ሰዓት ቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
እንዘ
ይብሉ መኑ እንጋ የዓቢ በመንግሥተ ሰማያት። ማር ፱፥፴፫፡፡ ሉቃ ፱፥፵፮፡፡ ማቴ ፲፱፥፲፬፡፡
፩፡
ከዚያ ብፅዓን ሰጠው ከዚህ ገበረለት ሾመው እንጂ ሾመው ተባብለዋል። በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው በመንግሥተ ሰማይ በላይ
የሚሆን ማነው አሉት፡፡
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
15/09/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment