Saturday, May 25, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 102

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
                    ******     
በእንተ ምሳሌ አግብርት ወፈድዮተ ዕዳ።
፳፫፡ ወበእንተዝ እብለክሙ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ንጉሠ ዘፈቀደ ይትሀሰቦሙ ለአግብርቲሁ።
                    ******     
፳፫፡ ንስሐ የሚገባ ስለሆነ መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል፡ ሕገ ወንጌል ተስፋ፣ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብላቴኖቹን ሊቆጣጠራቸው የወደደ ንጉሥን ትመስላለች።
                    ****** 
፳፬፡ ወሶበ አኃዘ ተሀስቦቶሙ አምጽኡ ሎቱ አሐደ ዘይፈድዮ ዕልፈ መካልየ፣
                    ******     
፳፬፡ በተቆጣጠራቸው ጊዜ የዕልፍ ወቄት ባለዳ አመጡለት።
                    ******     
፳፭፡ ወኃጢኦ ዘይፈድዮ አዘዘ እግዚኡ ይሢጥዎ ምስለ ብእሲቱ ወምስለ ውሉዱ።
                    ******     
፳፭፡  የሚክፍለው ቢያጣ ከልጆቹና ከሚስቱ ጋራ ሽጡት ብሎ አዘዘ። በወንጌልስ መሸጥም የለ ተገዝቶ ደመወዝ አውጥቶ ይክፈለኝ ሲል ነው።
                    ******     
፳፮፡ ወኵሎ ዘቦ እስከ ይፈዲ።
                    ******     
፳፮፡ ዕልፍ ወቄት አስኪከፍል ድረስ።
ወወድቀ እንከ ውእቱ ገብር ወሰገደ ሎቱ ወአስተብቊዖ።
ያ ባሪያ ወድቆ ማለደው።
እንዘ ይብል እግዚኦ ተዓገሠኒ
አቤቱ ታገሠኝ።
ወኵሎ እፈድየከ።
ዕልፍ ወቄት እከፍልሃለሁ ብሎ
                    ******     
፳፯፡ ወምህሮ እግዚኡ ለውእቱ ገብር ወዕዳሁኒ ኀደገ ሎቱ፡፡
                    ******     
፳፯፡ ለዚያ ባሪያ ጌታው አዘነለት ዕዳውን ሁሉ ተወለት።
                    ******     
፳፰፡ ወወጺኦ ውእቱ ገብር ረከበ አሐደ ገብረ እምነ አብያጺሁ  ዘይፈድዮ ዕልፈ ዲናረ።
                    ******     
፳፰፡ ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ወገን የመቶ ወቄት ባለዕዳ አገኘ።
ወአኀዞ ወኀነቆ እንዘ ይብል ሀበኒ ዘትፈድየኒ።
ገንዘቤን ስጠኝ ብሎ አስጨንቆ ያዘው።
                    ******     
፳፱፡ ወወድቀ ውእቱ ገብር ታሕተ እገሪሁ ወአስተብቊዖ እንዘ ይብል ተዓገሠኒ።
                    ******     
፳፱፡ ያ የጌታ ባርያ ታገሠኝ ማለት ቀን ስጠኝ ብሎ ወድቆ ማለደው፡፡
ወኵሎ እፈድየከ።
ጥቂት ጥቂት እያልሁ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፣
                    ******     
ወዓበዮ ወሖረ ወሞቅሖ፡
                    ******     
፴፡ ብትከፍለኝ ክፈለኝ ያለዚያ አይሆንም ብሎ አሥሮ አጋዘው
እስከ ይፈድዮ፣
እስኪከፍለው ድረስ።
                    ******     
፴፩፡ ወርእዮሙ አግብርተ እግዚኡ ዘገብረ ተከዙ ጥቀ፣
                    ******     
፴፩፡ የጌታው ባሮች ባልንጀሮቹ ያደረገውን አይተው ፈጽመው አዘኑ፣
ወሐዊሮሙ ነገርዎ ለእግዚኦሙ ኵሎ ዘገብረ
ሂደው ያደረገውን ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት ነገሩት፡፡
                    ******     
፴፪፡ ወእምዝ ጸውዖ እግዚኡ ኦ ገብር እኵይ ኵሎ ዕዳ ኀደጉ
ለከ።
                    ******     
፴፪፡ ከዚህ በኋላ ጌታው ጠርቶ አንት ክፉ ባርያ ዕዳህን ሁሉ ተውሁልህ።
                    ******     
፴፫፡ እስመ አስተብቋዕከኒ።
                    ******     
፴፫፡ ማልደኸኛልና ስለ ማለድኸኝ
አኮሁ መፍትው አንተሂ ትምሀር ውእተ ገብረ ቢጸከ በከመ አነ መሀርኩከ።
እኔ ዕልፍ ወቄት እንደተውኩልህ አንተስ ልትተው አይገባህም ነበርን።
                    ******     
፴፬፡ ወተምዓ እግዚኡ ወመጠዎሙ ለእለ ይሣቅይዎ።
                    ******     
፴፬፡ ጌታው ተቆጥቶ እሱ ለሰው ካላዘነ ብሎ መከራ ሥቃይ ለሚያጸኑበት ሰጠው።
እስከ አመ ይሤልጥ ኵሎ ዘይፈድዮ።
ዕልፍ ወቄት አስኪከፍለው ድረስ።
                    ******     
፴፭፡ ከማሁኬ አቡየኒ ሰማያዊ ይገብር ለክሙ እመ ኢኃደግሙ አበሳሆሙ ለቢጽክሙ እምኵሉ ልብክሙ።
                    ******     
፴፭፡ እንደዚህም ሁሉ የወንድዎቻችሁን ኃጢአት በፍጹም ልቡናችሁ ይቅር ካላላችሁ ሰማያዊ አባቴም እንዲህ ያደርግባችኋል።
አንድም ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብለህ መልስ። መንግሥተ ሰማያት አብ መላአክትን ሊቆጣጠራቸው የወደደ ንጉሥን ትመስላለች አለ እሱ ነው ማለት ነው።
ወሶበ አኀዘ ተሀስቦቶሙ።
በተቆጣጠራቸው ጊዜ ፍጹም ኃጢአት የሠራ አዳምን አመጡለት።
ወኃጢኦ ዘይፈደዮ።
ሃይማኖት ምግባር ቢያጣበት።
አዘዘ ይሢጥዎ
በእሱ በሔዋን በልጆቹ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስን ፈረደባቸው። በአዳም ሁሉን መናገር ነው፡፡
አንድም መምህረ ንስሐ ነው፡፡
አዘዘ ይሢጥዎ
በሕዋሳቱ ደዌያትን ፈረደበት
ወኵሎ ዘቦ
ቀኖናውን እስኪፈጽም ድረስ።
ወወድቀ ወአስተብቊዖ
በድዬሃለሁ ይቅር በለኝ።
ወኵሎ እፈድየከ
ቀኖናዬን እፈጽማለሁ አለው።
ወምህሮ
አዘነለት ኃጢአቱን አስተስረየለት፡፡
ወወፂኦ
ኃጢአቱ ከተሰረየለት በኋላ ከሕዝቡ አንድ ተነሳሂ አገኘ።
ወአኃዞ ወሐነቆ
መጽሐፍ ያዘዘውን ፈጽም ብሎ አስጨንቆ ያዘው።
ወወድቀ ወአስተብቊዖ
ቀኖናዬን ልፈጽም ብሎ ማለደው፡፡
ወአበዮ ወሞቅሖ
ብትፈጽም ፈጽም አለዚያ አይሆንም ብሎ አወገዘው።
እስከ ይፈደዮ
ቀኖናውን እስኪፈጽም ድረስ።
ወርእዮሙ አብያጺሁ
መላእክት አይተው ፈጽመው አዘኑ ሰው ለሰው እንዲህ ይጨክናል ብለው።
ወሐዊሮሙ ነገርዎ
ሂደው የሠራውን ሥራ ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት።
(ሐተታ) መንገሩስ የለም የነገሩት አውቆ ሥራ እንዲሠራ አውቆ ሥራ መሥራቱን መናገር ነው።
ወእምዝ ጸውዖ
ከዚህ በኋላ በደዌ ጸራው።
ወይቤሎ
አንተ ክፉ ቄስ እኔ ኃጢአትህን ሁሉ አስተሰረይኩልህ።
እስመ አስተብቋዕከኒ፡፡
ማልደኸኛልና ስለማለድኸኝ።
አኮሁ መፍትው
እኔ ይቅር እንዳልኩህ አንተስ የወንድምህን ኃጢአት ልታስተሰርይለት አይገባሕምን። ተመየጥ አንተ ወአነ ተወከፍኩ ህየንቴከ ሞተ በከመ ተወክፈ ክርስቶስ ሞተ ህየንቴየ ወህየንተ ኵሎሙ ልትለው አይገባህም ነበር አለው።
ወተምዓ ወመጠዎ
ፈርዶ መከራ ለሚያጸኑበት ለደዌያት ሰጠው።
እስከ ይፈዲ
ቀኖናውን እስኪፈጽም ድረስ።
ወከማሁኬ
የወንድማችሁን ኃጢአት በፍጹም ልቡናችሁ ይቅር ካላላችሁ ሰማያዊ አባታትሁ አሁን እንደተናገርሁት ያደርግባችኋል።
                    ******     
በእንተ ዘተግኅሠ ኢየሱስ እምኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ ፲፱፡፡
፩፡ ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ ተንሥአ እምገሊላ ወሖረ ወበጽሐ ውስተ ብሔረ ይሁዳ ማዕዶተ ዮርዳኖስ። ማር ፲፥፩፡፡
፩፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ነገር አስተምሮ ከፈጸመ በኋላ ከገሊላ ወጥቶ የዮርዳኖስ ማዶ ወደሚሆን ወደምድረ ይሁዳ ደረሰ።
                        ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
18/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment