====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
******
፩፡ ወበይእቲ ሰዓት ቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ለእግዚእ ኢየሱስ
እንዘ ይብሉ መኑ እንጋ የዓቢ በመንግሥተ ሰማያት። ማር ፱፥፴፫፡፡ ሉቃ ፱፥፵፮፡፡ ማቴ ፲፱፥፲፬፡፡
******
፩፡ ከዚያ ብፅዓን ሰጠው ከዚህ ገበረለት ሾመው እንጂ ሾመው ተባብለዋል። በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው በመንግሥተ ሰማይ በላይ የሚሆን ማነው አሉት፡፡
******
፪፡ ወጸውዓ ሕፃነ ወአቀመ ማዕከሎሙ።
******
፪፡ ብላቴና ጠርቶ አቆመው።
******
፫፡ ወይቤ አማን እብለክሙ እመ ኢተመየጥክሙ ዝንቱ ሕፃን ኢትበውኡ ውስተ መንግሥተ ሰማያት። ፩፡ቆሮ ፲፬፥፳፡፡
******
፫፡ ተመልሳችሁ ከየውሃት ጠባይዓዊ ደርሳችሁ እንደዚህ ሕፃን ካልሆናችሁ መንግሥተ ሰማይ እንዳትገቡ በእውነት እነግራችኋለሁ።
******
፬፡ ወዘአትሐተ ርእሶ ከመ ዝንቱ ሕፃን ውእቱ የዓቢ በመንግሥተ ሰማያት።
******
፬፡ በመካከላቸው እንደዚህ ሕፃን ሁኖ ራሱን ያዋረደ የመንግሥተ ሰማይ ባለቤት ይሆናል። ይህም ትሕትና የሚያስተምርበት ሕፃን አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ነው። በአንጾኪያ የጴጥሮስ ሦስተኛ ሁኖ ተሹማል።
******
፭፡ ወዘሂ ተወክፈ ፩ደ ሕፃነ ዘከመዝ በስምየ ኪያየ ተወክፈ
******
፭፡ እንደዚህ ሕፃን የሆነውን በእኔ ስም የተቀበለ እኔን ተቀበለ ማለት እኔ አድርበታለሁ።
******
በእንተ ዘተናገረ ኢየሱስ በላዕለ ዕቅፍት።
ወዘሂ አስሐቶ ለ፩ዱ እምእሉ ንዑሳን እለ የአምኑ ብየ ይኄይሶ ከመ ይዕሥሩ በክሣዱ ማኅረፀ አድግ ወያስጥምዎ ውስተ ልጐተ ባሕር።
******
፮፡ በእኔ ከአመኑ ምዕመናን አንዱን ያሳተ አህያ በመዘውር የሚፈጭባትን ወፍጮ ከአንገቱ አሥሮ ከጥልቅ ባሕር ቢያሰጥሙት ይሻለዋል።
አንድም ጽኑ ቀኖና ሰጥተው በአንብዓ ንስሐ ቢያሰጥሙት ይሻለዋል።
******
፯፡ አሌ ሎቱ ለዓለም እመንሱት ዘይመጽእ።
******
፯፡ ከሚመጣው መከራ የተነሣ ለሰው ሁሉ ወዮለት።
እስመ ግብር ይመጽእ መንሱት
መከራ ግድ ይመጣልና።
ወባሕቱ አሌ ሎቱ ለውእቱ ብእሲ ዘያመጽኣ ለመንሱት።
ነገር ግን ዋዛ ፈዛዛ ተጫውቶ መከራን ለሚያመጣት ለይሁዳ ወዮለት።
******
፰፡ ወእመኒ እዴከ አው እግርከ ታስሕተከ ምትራ ወግድፋ እምላዕሌከ። ማቴ ፭፥፴፡፡ ማር ፱፥ሣ፪።
******
፰፡ እጅህም ብትሆን ወይም እግርህ ብታስትህ ከአንተ ቈርጠህ ጣላት።
እስመ ይኄይሰከ ትባእ ውስተ ሕይወት ሐንካሳከ ወጽውሰከ እምእንዘ ብከ ፪ አዕዳው ወ፪ አእጋር ትትወደይ ውስተ እሳት ዘለዓለም።
ሁለት እጅ ሁለት እግር ኑሮህ ወደ ዘለዓለም እሳት ስትገባ አንካሳ ልምሾ ሁነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሸልሃልና።
******
፱፡ ወእመሂ ዓይንከ ታስሕተከ ምልሓ ወአውጽኣ እምላዕሌከ
******
፱፡ ዓይንህ ብታስትህ አውጥተህ ጣላት።
******
እስመ ይኄይሰከ ነቋረከ ትባዕ ውስተ ሕይወት እምትባዕ ምስለ ፪ሆን አዕይንቲከ ውስተ እሳተ ገሃነም።
ሁለት ዓይን ኑሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትገባ አንድ ዓይን ኑሮህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ይሸልሃልና፡፡
አንድም ወእመሂ ዓይንከ ብለህ መልስ፡፡ ኤጲስ ቆጶስህን ብትነቅፈው ሻረው፡፡ እስመ ይኄይሰከ የነቀፍከውን ኤጲስ ቆጶስ ሹመህ ኑረህ ኋላ ገሃነመ እሳት ከምትገባ የነቀፍኸውን ኤጲስ ቆጶስ ሽረህ ኑረህ ኋላ መንግሥተ ሰማይ ብትገባ ይሻልሃልና፡፡
******
፲፡ ዑቁ ኢታስተኃቅርዎሙ ለ፩ እምእሉ ንዑሳን፡፡ መዝ ፴፫፥፯፡፡
******
፲፡ ከአመኑ ምዕመናን አንዱን እንዳትንቁ እንዳታቃልሉ አስተውሉ፡፡
እብለክሙ ከመ መላእክቲሆሙ በሰማያት ወትረ ይሬእዩ ገጾ ለአቡየ ዘበሰማያት።
መላአክት ዑቃቤዎቻቸው ያባቴን ፊት ዘወትር ያያሉ ማለት መላእክተ ዑቃቤዎቻቸው በባለሟልነት እንዳሉ እነግራችኋለሁ እንዳይቀስፏችሁ ማለት ነው።
አንድም መላአክተ ዑቃቤዎቻቸው በባለሟልነት እንዳሉ እሳቸውም በባለሟልነት እንዳሉ እነግራችኋለሁ እንዳያስፈርዱባችሁ ማለት ነው።
******
በእንተ በግዕት ዘተሐጕለት።
፲፩፡ እስመ መጽአ ወልደ እጓለ እመሕያው ይኅሥሥ ወያድኅን ዘተኃጕለ። ሉቃ ፲፱፥፲።
******
፲፩፡ ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስ የጠፋውን ሊሻ የተጐዳውን ሊያድን ሰው ሁኑዋልና።
******
፲፪፡ ምንተ ትብሉ። ሉቃ ፲፫፥፬።
******
፲፪፡ አንቀጸ ንስሐ ነው ምን ትፈርዳላችሁ።
እመቦ ብእሲ ዘቦቱ ፻ አባግዕ።
መቶ በግ ያለው ሰው ቢኖር
ወእመ ተገድፎ ፩ እምኔሆሙ፡፡
ከመቶው አንዱ ቢጠፋበት።
አኮሁ የኃድግ ፺ወ፱ተ ውስተ ገዳም።
ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ።
ወየሐውር ይኅሥሥ ዘተገድፎ
የጠፋበትን ሊፈልግ ይሄድ የለምን።
******
፲፫፡ ወእምከመ ረከቦ አማን እብለክሙ ከመ ይትፌሣሕ በእንቲአሁ ፈድፋደ እም ፺ወ፱ እለ ኢተገድፉ።
******
፲፫፡ ያገኘው እንደሆነ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ ጠፍቶ በተገኘው ደስ ይለዋል ብዬ ደስ እንዲለው በእውነት እነግራችኋለሁ።
******
፲፬፡ ከማሁኬ ኢይፈቅድ አቡየኒ ዘበሰማያት ከመ ይትኃጐል ፩ዱ እምእሉ ንዑሳን።
******
፲፬፡ እንደዚህም ሁሉ ሰማያዊ አባቴ ከተነሣሕያን አንዱ ሊጐዳ አይወድም።
አንድም ምንተ ትብሉ ብለህ መልስ። መቶ በጎች የተባሉ መቶ ነገደ መላእክት ናቸው ከመቶው አንዱ ዲያብሎስ ቢወጣ በሱ ስፍራ አዳም ቢገባ አዳም ቢወጣ አኮሁ የኃድግ ባሕርየ መላእክትን ትቶ ባሕርየ አዳምን ገንዘብ ማድረጉን መናገር ነው። ኢነሥኦ ለዘነሥኦ እመላእክት ዘእንበለ ዳዕሙ እምዘርዓ አብርሃም እንዲል። ወእምከመ ረከበ አዳምን ንስሐ ገብቶ ቢያገኘው አማን እብለክሙ ንስሐ ከማያሻቸው ከመላእክት ይልቅ ንስሐ በሚያሻው በአዳም መመለስ ደስ ይለዋል ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
ከማሁኬ ኢይፈቅድ አቡየኒ ዘበሰማያት ከመ ይትኃጐል ፩ዱ እምእሉ ንዑሳን፡፡
አሁን እንደ ተናገርነው ሰማያዊ አባቴ ከተነሳሕያን አንዱ ሊጐዳ አይወድም።
******
በእንተ ዘከመ ይደልዎሙ ለአኃው ተገሥጾ\።
፲፭፡ ወእመኒ አበሰ ለከ እኁከ ሑር ወገሥፆ ለባሕቲትከ፡፡ ዘሌዋ ፲፱፥፲፯፡፡ ሲራ ፲፱፥፲፫፡፡ ሉቃ ፲፯፥፫፡፡ ያዕ ፭፥፲፱፡፡
******
፲፭፡ ወንድምህ ቢበድልህ በብቻህ ሁነህ በብቻው አድርገህ ለባሕቲትከ ለባሕቲቱ ለብቻህ ሁነህ ለብቻው አድርገህ ብቻህን ሁነህ ብቻውን አድርገህ ምከረው። ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
16/09/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment