Saturday, May 25, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 101

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ክርስቲያናዊት ትሕትና፡፡
ምዕራፍ ፲፰።
                    ******     
በእንተ ዘከመ ይደልዎሙ ለአኃው ተገሥጾ።
፲፭፡ ወእመኒ አበሰ ለከ እኁከ ሑር ወገሥፆ ለባሕቲትከ፡፡ ዘሌዋ ፲፱፥፲፯፡፡ ሲራ ፲፱፥፲፫፡፡ ሉቃ ፲፯፥፫፡፡ ያዕ ፭፥፲፱፡፡
                    ******     
፲፭፡ ወንድምህ ቢበድልህ በብቻህ ሁነህ በብቻው አድርገህ ለባሕቲትከ ለባሕቲቱ ለብቻህ ሁነህ ለብቻው አድርገህ ብቻህን ሁነህ ብቻውን አድርገህ ምከረው።
ወእመ ሰምዓከ ረባሕኮ ለእኁከ።
የተቀበለህ እንደሆነ ረባኸው ጠቀምኸው።
                    ******     
፲፮፡ ወእመሰ ኢሰምዓከ ንሣእ ምስሌከ በዳግም አሐደ። ዘዳ ፲፥፮፡፡ ዮሐ ፰፥፲፯፡፡ ፪፡ቆሮ ፲፫፥፩፡፡ ዕብ ፲፥፳፰።
                    ******     
፲፮፡ ባይቀበልህሀ ግን በሁለተኛው አንድ ሰው ጨምረህ ምከረው።
አው ፪ተ።
እናንተን ባይቀበል ሁለት ሰው ጩጨምረህ አንተ ሦስተኛ ሁነህ ምከረው።
እስመ በአፈ ፪ቱ ወ፫ቱ ሰማዕት ይቀውም ኵሉ ነገር።
በሁለት ምስክር ነገር ይጸናልና።
ንሣእ አሐደ
በሦስት ምስክር ነገር ይጸናልና፡፡
አንድም በአምስት ምስክር ነገር ይጸናልና፡፡ ንሣአ ፪ተ አው ፫ተ።
                    ******     
፲፯፡ ወእመሰ ኢሰምዖሙ ሎሙሂ ንግራ ለቤተ ክርስቲያን። ፩፡ቆሮ ፭፥፱፡፡ ፪፡ተሰሎ ፫፥፲፫፡፡
                    ******     
፲፯፡ እሳቸውንም ባይቀበል ንግሩ ለጉባዔ ይላል የፍርድ መጣፍ ባንድ ደወል ለሚሰበሰቡ ንገሩ እኒያን ባይቀበል ለቤተ ክርስቲያን ንገሩበት።
ወእመሰ ለቤተ ክርስቲያን ኢሰምዓ ይኩን ከመ አረማዊ ወመጸብሐዊ።
ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት እንደ አረማዊ እንደ መጸብሐዊ ይሁን ማለት ይለይ።
(ሐተታ) ወንድሙን ቢበድል እግዚአብሔርን የካደ ይመስል ይለይ ማለቱ ስለምነው ቢሉ። ወንድሙን ከበደለ ከሥጋው ከደሙ ይከለከላል ከሥጋው ከደሙ ከተከለከለ እንደ አረማዊ እንደ መጸብሐዊ መሆኑ ነውና፡፡
አንድም የሚያየውን ወንድሙን መበደሉ እግዚአብሔርን መበደሉ ነውና።
                    ******     
፲፰፡ አማን እብለክሙ ዘአሠርክሙ በምድር ይኩን እሱረ በሰማያት። ዮሐ ፳፥፳፫።
                    ******     
፲፰፡ ከምድራውያን ነገሥታት ከሌዋውያን ካህናት ወገን ያይደለን መለየቱ እንደምን ይሆናል ትሉኝ እንደሆነ በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ እንዲሆን።
ወዘፈታሕክሙ በምድር ይከውን ፍቱሐ በሰማያት።
በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ እንዲሆን በእውነት እነግራችኋለሁ። እንዳለፈው ም፲፮ ቊጥር ፲፱።
                    ******     
፲፱፡ ወዓዲ እብለክሙ ለእመ ኃብሩ ፪ አው ፫ እምኔክሙ በውስተ ምድር በእንተ ኵሉ ግብር ዘሰአሉ ይትገበር ሎሙ በኃበ አቡየ ዘበሰማያት።
                    ******     
፲፱፡ ያውስ ቢሆን ጥቂት ነን ብዙ አይደለን መለየቱ እንደምን ይሆንልናል ትሉኝ እንደሆነ ከእናንተ ወገን ስለሚሹት ነገር በዚህ ዓለም ሁለቱ ወይም ሦስቱ አንድ ቢሆኑ በሰማይ አባቴ ዘንድ የሚሹት ነገር ይደረግላቸዋል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡
                    ******     
፳፡ እስመ ኀበ ሀለዉ ፪ቱ ወ፫ቱ ጉቡዓነ በስምየ ህየ እሄሉ አነ ማዕከሎሙ።
                    ******     
፳፡ ሁለቱ ሦስቱ በስሜ አምነው አንድ ቢሆኑ አንድ በሆኑበት እኖራለሁ ማለት አድሬባቸው እኖራለሁና።
(ሐተታ) ሠለስቱ የተባሉ አንባቢ ተርጓሜ መጽሐፍ ናቸው።
አንድም ናዛዚ ተናዛዚ ኄር ላእክ ናቸው።
አንድም ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና ናቸው። ሃይማኖት ትውክልት ተፋቅሮ ናቸው ።
                    ******     
፳፩፡ ወእምዝ ቀርበ ጴጥሮስ ወይቤሎ እግዚኦ ሚመጠነ አመ አበሰ ሊተ እኁየ እኅድግ ሎቱ፡፡ ሉቃ ፲፯፥፬፡፡
                    ******     
፳፩፡ ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ አቤቱ ወንድሜ ምን ያህል ቢበድለኝ ይቅር ልበለው።
እስከ ስብዕኑ
እስከ ሰባት ድረስ ነውን አለው፡፡
                    ******     
፳፪፡ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ ኢይብለከ እስከ ስብዕ።
                    ******     
፳፪፡ እስከ ሰባት አልልህም
አላ እስከ ሰብዓ በበስብዕ
ሰባቱን አንድ ሰባቱን አንድ እያልክ እስክ ሰባ ነው እንጂ
አንድም እስከ ስብዕ በበሰብዓ
ሰባውን አንድ እየልክ እስከ ሰባት ነው እንጂ አለው።
                    ******     
በእንተ ምሳሌ አግብርት ወፈድዮተ ዕዳ።
፳፫፡ ወበእንተዝ እብለክሙ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ንጉሠ ዘፈቀደ ይትሀሰቦሙ ለአግብርቲሁ።
፳፫፡ ንስሐ የሚገባ ስለሆነ መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል፡ ሕገ ወንጌል ተስፋ፣ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብላቴኖቹን ሊቆጣጠራቸው የወደደ ንጉሥን ትመስላለች።
                    ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
17/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment