Friday, August 23, 2019

የማርቆስ ወንጌል-----ምዕራፍ ፰።


በከመ አብዝኀ ኅብስተ ዳግመ።

፩፡ ወይእተ አሚረ ካዕበ ብዙኅ ሰብእንዘ ሀሎ አልቦሙ ዘይበልዑማቴ ፲፭፥፴፪።
፩፡ በዚያም ወራት ብዙ ሰው ሳለ የሚበሉት አልነበራቸውም
፪፡ ወጸውዖሙ ለአርዳኢሁ ወይቤሎሙ ያምሕሩኒ እሉ ሰብእ
፪፡ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ እኒህ ሰዎች ያሳዝኑኛል አላቸው።
ናሁ ሣልሶሙ ዮም እንዘ ይጸንሑኒ።
ሲጠብቁኝ ሦስተኛ ቀናቸው ነውና።
ወአልቦሙ ዘይበልዑ።
የሚበሉትም የላቸውም
፫፡ ወእመኒ ሠዓርክዎሙ ርኍባኒሆሙ ይእትው አብያቲሆሙ ይደክሙ በፍኖት።
፫፡ ወደቤታቸውም ይገቡ ዘንድ ተርበውም ባሰናብታቸው በመንገድ ይደክማሉ።
ወእለሂ መጽኡ እምርኍቅ
ከሩቅም የመጡ አሉ።
፬፡ ወይቤልዎ አርዳኢሁ መኑ ዘይክል በዝየ በገዳም አጽግቦቶሙ ኅብስተ ለዝንቱ ኵሉ ሕዝብ
፬፡ ደቀ መዛሙርቱ በዚህ በገዳም ይህን ሁሉ ሕዝብ ማጽገብ የሚቻለው ማነው አሉ።
፭፡ ወይቤሎሙ ሚ መጠን ኅብስት ብክሙ።
፭፡ ምን ያህል እንጀራ አላችሁ አላቸው።
ወይቤልዎ ሰብኡ፤
ሰባት ነው አሉት።
፮፡ ወአዘዞሙ ለሰብእ ይርፍቁ ዲበ ምድር።
፮፡ ሰዎቹን ከምድር ይቀመጡ ዘንድ አዘዛቸው
ወነሥኦን ለሰብኡ ኅብስት፤
ሰባቱንም እንጀራ ያዘ።
ወአዕኰተ።
አመሰገነ።
ወፈተተ።
ቈረሰ።
ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ ያቅርቡ ሎሙ ለሕዝብ።
ያቀርቡላቸው ዘንድ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው።
ወአቅረቡ ለሰብእ።
ለሰዎችም አቀረቡ፣
፯፡ ወቦሙ ዓሣኒ ኅዳጥ።
፯፡ ጥቂት ዓሣም ነበራቸው።
ወባረከ ኪያሁኒ
ያንም ባረከው።
ወይቤሎሙ አቅርቡ ሎሙ ዘኒ
ይህን አቅርቡላቸው አላቸው።
፰፡ ወበልዑ ወጸግቡ።
፰፡ በልተውም ጸገቡ።
ወዘአግኃሡ ዘተርፈ ፍተታተ መልዓ ፯ተ አስፈሬዳተ።
ያነሱት የቊራሽ ትራፊ ሰባት እንቅብ መላ።
፱፡ ወእለሰ በልዑ የአክሉ ፵፻።
፱፡ የበሉትም አራት ሽህ ያህላሉ
ወእምዝ ፈነዎሙ ሶቤሃ ይሑሩ
ከዚህም በኋላ ይሄዱ ዘንድ አሰናበታቸው።
፲: ወእምዝ ዓርገ ሐመረ ምስለ አርዳኢሁ ወበጽሐ ውስተ ደወለ ድልማኑታ።
፲: ከዚህም በኋላ ከመርከብ ገብቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ድልማኑታ ሄደ።

ዘከመ ኀሠሡ ትእምርተ እምሰማይ።

፲፩፡ ወወጽኡ ፈሪሳውያን። ማቴ ፲፮፥፩። ሉቃ ፲፩፥፶፬።
፲፩፡ ፈሪሳውያንም ወጡ።
አኃዙ ይትኀሠሥዎ።
ይከራከሩትም ጀመር።
ወሰአልዎ ትእምርተ እምሰማይ እንዘ ያሜክርዎ።
ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት ለመኑት።
፲፪፡ ወተከዘ በመንፈሱ።
፲፪፡ በልቡም ተቈረቈረ።
ወይቤ ምንትኑ ተኃሥሥ ትእምርተ ዛቲ ትውልድ።
ይች ትውልድ ለምን ምልክት ትሻለች
፲፫፡ አማን እብለክሙ ከመ ኢይትወሀባ ለዛቲ ትውልድ ትእምርት።
፲፫፡ ለዚህች ትውልድ ምልክት አይሰጣትም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
ወኃደጎሙ ወዓርገ ካዕበ ሐመረ ወሖረ ማዕዶተ።
ትቷቸው ሁለተኛ በመርከብ ተጭኖ ወደ ማዶ ሄደ።
፲፬፡ ወረስዑ ነሢአ ኅብስት። ማቴ ፲፮፥፭።
፲፬፡ እንጀራ መውሰድን ረሱ፤
ወአልቦሙ ዘእንበለ አሐቲ ኅብስት ምስሌሆሙ ውስተ ሐመር
እርሳቸውም ከአንዲት እንጀራ በቀር በመርከብ አልነበራቸውም።
(ሐተታ) ማቴዎስ ዘእንበለ አሐቲ አላለም ማርቆስ ዘእንበለ አሐቲ አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ከአነሰ ዘንድ የለም ማለት ልማድ ነውና። ማቴዎስ ዘእንበለ አሐቲ አላለም ወበውስተ ውሁድኒ ንብል አልቦ እንዲል።
አንድም ማርቆስ አንዲት ሳትቀር ሲል ነው። አግብኡ ሊተ ንዋይየ ዘእንበለ ብእሲትየ እንዲል።
፲፭፡ አዘዞሙ ወይቤሎሙ ዑቁ ወተዓቀቡ እምነ ብኍዓ ፈሪሳውያን ወእምነ ብኍኦሙ ለሄሮድሳውያን።
፲፭፡ ከሄሮድሳውያንና ከፈሪሳውያን እርሾ አስተውላችሁ ተጠበቁ ብሎ አዘዛቸው።
፲፮፡ ወሐለዩ በበይናቲሆሙ።
፲፮፡ እርስ በርሳቸው አሰቡ።
ወይቤሉ እስመሁ ኅብስተ ኢነሣእነ፤
እንጀራ ስለአልያዝን ነውን አሉ
፲፯፡ ወአእመሮሙ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎሙ ምንተ ትሔልዩ በልብክሙ።
፲፯፡ ጌታም አውቆባቸው በልባችሁ ምን ታስባላችሁ አላቸው።
እስመሁ ኅብስት አልብክሙ።
እንጀራ የላችሁምና ነው።
ዓዲኑ ተአምሩ ወኢትሌብዉ።
ገና አላወቃችሁም ልብ አላረጋችሁም።
ልብክሙኑ ጽሉል።
ልባችሁ ደንቆሮ ነውን
፲፰፡ ወአዕይንት ብክሙ ወኢትሬእዩ። ማር ፮፥፵፩። ዮሐ ፮፥፲፩
፲፰፡ ዓይን አላችሁ አታዩም፤
ወዕዝን ብክሙ ወኢትሰምዑ
ጆሮም አላችሁ አትሰሙም።
ወኢትዜክሩኑ።
አታስቡምን።
፱፡ ዘአመ ኃምስ ኅብስት ፈተትኩ ለ፶፻ ብእሲ።
፱፡ ለአምስት ሽህ ሰው አምስት እንጀራ በቈረስኩ ጊዜ።
ሚመጠነ አግኃሥክሙ አክፋረ ዘመልዓ ፍተታተ ዘተርፈ።
የተረፈውን ቁራሽ ምን ያህል ቅርጫት የመላ አነሳችሁ አላቸው።
ወይቤልዎ ፲ተ ወ፪ተ።
አሥራ ሁለት ነው አሉት።
፳፡ ወይቤሎሙ አመኬ ሰብዑ ኅብስተ ለ፵፻ ብእሲ ሚመጠነ አግኃሥክሙ አስፈሬዳተ ዘመልዓ ፍተታተ ዘተርፈ።
ለአራት ሽህ ሰው ሰባት እንጀራ በቈረስኩ ጊዜ የተረፈውን ቁራሽ ስንት እንቅብ የመላ አነሳችሁ።
ወይቤልዎ ሰብዑ።
ሰባት ነው አሉት።
፳፩፡ ወይቤሎሙ እፎ እንከ ዘኢትሌብዉ።
፳፩፡ እንኪያ አለማስተዋላችሁ እንደምን ነው አላቸው።

በእንተ ዕውር ዘቤተ ሳይዳ።

፳፪፡ ወበጺሖሙ ቤተ ሳይዳ አምጽኡ ኅቤሁ ዕውረ።
፳፪፡ ወደ ቤተ ሳይዳም በደረሱ ጊዜ ዕውርን ወደሱ አመጡ፣
ወአስተብቊዕዎ ይግሥሦ።
ይዳስሰው ዘንድ ማለዱት።
፳፫፡ ወአኃዞ በእዴሁ ለውእቱ ዕውር ወአውጽኦ አፍአ እምሀገር።
፳፫፡ ያን ዕውር በእጁ ይዞ ከሀገርም አፍአ አወጣው።
ወተፍዓ ውስተ አዕይንቲሁ።
በዓይኑም ተፋበት።
ወገሠሦ።
ዳሰሰውም።
ወይቤሎ ምንተ ትሬኢ።
ምን ታያለህ አለው።
፳፬፡ ወነጸረ ወይቤ እሬኢ ሰብአ ከመ ዕፀው ያንሶስዉ።
፳፬፡ አይቶ ሰዎች እንደዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ።
(ሐተታ) ዕውር ሆኖ ተወልዷል ያሉ እንደሆነ በምን አውቆ ቢሉ በበትሩ። ከተወለደ በኋላ ታውሯል ያሉ እንደሆነ የተመቸ።
፳፭፡ ወገሠሦ አዕይንቲሁ ካዕበ።
፳፭፡ ሁለተኛ አይኑን ዳሰሰው።
ወርአየ ዳኅነ።
ፍጹም ብርሃን አየ።
ወነጸረ ኵሎ ብሩሃ።
ሁሉን ገልጦ አየ።
፮፡ ወፈነዎ ቤቶ።
፮፡ ወደ ቤቱም ሰደደው።
ወይቤሎ ኢትባዕ ውስተ አዕፃዳት።
ወደ መንደርም አትግባ
ወአልቦ ዘትነግር በውስተ ሀገርኒ፤
በመንደርም ለማንም አትናገር አለው።
(ሐተታ) ዕውር የባሕታውያን ምሳሌ። ጥቂት ጸጋ የተሰጣቸው እንደሆነ ሰውን ሁሉ በግዕዘ እንስሳ ያዩታል። ሁለተኛ ቢዳስሰው ፈጽሞ እንደአየ ፍጹም ጸጋ የተሰጣቸው እንደሆነ ኃጥእ ጻድቅ አማኒ መናፍቅ ሳይለዩ ሁሉን ይወዳሉና።

በእንተ ተአምኖተ ጴጥሮስ።

፳፯፡ ወሖረ እግዚአ ኢየሱስ ወአርዳኢሁ ውስተ አኅጉረ ቂሣርያ ዘፊልጶስ። ማቴ ፮፥፲፫። ሉቃ ፱፥፲፰።
፳፯፡ ጌታ ወደ ፊልጶስ አገር ወደ ቂሣርያ መንደሮች ሄደ።
ወተስእሎሙ ለአርዳኢሁ በፍኖት መነ ይብለኒ ሰብእ ከመ አነ ውእቱ።
እኔ እንደሆንኩ ሰው ማን ይለኛል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በመንገድ ጠየቃቸው።
፳፰፡ ወይቤልዎ ዮሐንስሃ መጥምቀ
፳፰፡ ዮሐንስ መጥምቅን ይሉሃል።
አው ኤልያስሃ።
ወይም ኤልያስን፥
አው ፩ዱ እምነቢያት፣
ወይም ከነቢያት አንዱን ይሉሃል አሉት፣
፱፡ ወይቤሎሙ አንትሙኬ መነ ትብሉኒ።
፱፡ እናንተስ ማነው ትሉኛላችሁ አላቸው።
ወተሠጥዎ ጴጥሮስ ወይቤሎ አንተ ውእቱ ክርስቶስ፣
ጴጥሮስም አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰ።
፴፡ ወገሠፆሙ ከመ ኢይንግሩ ወኢለመኑሂ በእንቲአሁ።
፴፡ ለማንም ለማን እንዳይናገሩ ገሠፃቸው።

በእንተ ትንቢት ዘሕማማት

፴፩፡ ወአኀዘ ይምሐሮሙ ከመ ሐለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ብዙኃ ያሕምምዎ ወያመክርዎ ረበናት ወሊቃነ ከህናት።
፴፩፡ ጌታም ሽማግሎች የካህናት አለቆች ይፈትኑት ዘንድና ብዙ መከራ ያመጡበት ዘንድ እንዳለው ያስተምራቸው ጀመር
ወይቀትልዎ።
እንዲገድሉት።
ወይትነሣእ በሣልስት ዕለት።
በሦስተኛውም ቀን እንዲነሳ፣
፴፪፡ ወገሃደ ነገሮሙ ዘንተ ነገረ።
፴፪፡ ይህንም ነገር ገልጦ ነገራቸው
ወአኀዘ ይገሥፆ
ይቆጣውም ጀመር ነበር።
፴፫፡ ወተመይጠ ወነጸረ ኀበ አርዳኢሁ።
፴፫፡ ተመልሶም ወደ ደቀ መዛሙርቱ አየ።
ወገሠፆ ለጴጥሮስ።
ጴጥሮስንም ተቆጣው
ወይቤሎ ሑር እምድኅሬየ ሰይጣን።
አንተ ሰይጣን ከኋላዬም ሂድ አለው
እስመ ኢትሄሊ ዘእግዚአብሔር ዘእንበለ ዘእጓለ እመሕያው
የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስበምና።
በእንተ ኀዲገ ርእስ ዘክርስቲያን።
፴፬፡ ወጸውኦሙ ለሕዝብ ምስለ አርዳኢሁ። ማቴ ፲፥፴፰። ሉቃ ፱፥፳፫። ፲፬፥፳፰።
፴፬፡ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጠራቸው።
ወይቤሎሙ ዘይፈቅድ ይጸመደኒ ይጽልዓ ለነፍሱ ወያጥብዕ ወይንሣእ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ
ሊያገለግለኝም የሚወድ ጨክኖ የሞትን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ አላቸው፣
፴፭፡ ዘይፈቅድ ያድኅና ለነፍሱ ለይግድፋ። ሉቃ ፲፯፥፴፫። ዮሐ ፲፪፥፳፭።
፴፭፡ ነፍሱን ሊያድናት የወደደ ይጣላት።
ወዘገደፋ ለነፍሱ በእንቲአየ ወበእንተ ወንጌል ይረክባ
ስለእኔ ስለ ወንጌልም ነፍሱን የጣለ ያገኛታል ማለት ያድናታል።
፴፮፡ ወምንት ይበቊዖ ለሰብእ ለእመ ኵሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኃጕለ።
፴፮፡ ነፍሱን ከአጣ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ለሰው ምን ይረባዋል።
፴፯፡ ወምንት እምወሀበ ሰብእ ቤዛሃ ለነፍሱ
፴፯፡ ወይስ ለነፍሱ ቤዛ ሰው ምን በሰጠ።
፴፰፡ ወዘኒ ኃፈረኒ ወኃፈረ ቃልየ በዛቲ ትውልድ ዘማ ወኃጥእት። ማቴ ፲፥፴፫። ሉቃ ፱፥፳፮። ፲፪፥፱።
፴፰፡ ዘማ ኃጢአተኛም በምትሆን በዚህች ትውልድ ያፈረኝን በነገሬም ያፈረውን፤
ወልደ እጓለ እመሕያውኒ የኃፍሮ አመ ይመጽእ በስብሐተ አቡሁ ምስለ መላእክቲሁ ቅዱሳን።
ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስም በአባቱ ምስጋና ከቅዱሰን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ ያፍረዋል።