Thursday, August 15, 2019

የማርቆስ ወንጌል--------ምዕራፍ ፫።


በእንተ ዘየብሰት እዴሁ።

፩፡ ወቦአ ካዕበ ምኵራበ በሰንበት። ማቴ ፲፪፥፱። ሉቃ ፮፥፯።
፩፡ ሁለተኛ ወደ ምኵራብ ቅዳሜ ገባ፣
ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ ዘየብሰት እዴሁ።
ከዚያም እጁ የሰለለ ሰው ነበር፤
፪፡ ወይትዓቀብዎ ለእመ ይፌውሶ በሰንበት ከመ ያስተዋድይዎ።
፪፡ ሊያሳጡት ቅዳሜ ይፈውሰው እንደሆን ብለው ይጠብቁት ነበር።
፫፡ ወይቤሎ ለውእቱ ብእሲ ዘጽውስት እዴሁ ተንሥእ ወቁም ማዕከለ።
፫፡ ያን እጁ የሰለለች ሰው ተነሥተህ ከመካከል ቁም አለው፣
ወይቤሎሙ ይከውንኑ በሰንበት ገቢረ ሠናይ አው ገቢረ እኵይ።
ቅዳሜ በጎ ሥራ መሥራት ይሻላልን ወይም ክፉ ሥራ መሥራት
አሕይዎ ነፍስኑ ወሚመ ቀቲል።
የሚገባ ነፍስ መግደል ነውን ወይስ ማዳን አላቸው።
ወአርመሙ።
ዝም አሉ። ማቴዎስ ይከውንሁ ብለው እሳቸው ጠየቁት ይላል ማርቆስ እሱ ጠየቃቸው አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ይከውንሁ ብለው ቢጠይቁት ምሳሌ በግዕን ነግሮ ተንሥእ ወቁም ማዕከለ ብሎ ይከውንሁ አላቸው አርመሙ ዝም አሉ ስፋሕ እዴከ ይለዋል።
አንድም እንደ ማቴዎስ ይከውንሁ ቢሉት ተንሥእ ወቁም ማዕከለ ብሎ ምሳሌ በግዕን ነገራቸው ዝም አሉ ስፋሕ እዴከ ይለዋል።
አንድም እንደ ማቴዎስ ይከውንሁ ቢሉት መልሶ ይከውንሁ ገቢረ ሠናይ በሰንበት አሕይዎ ነፍስኑ ወሚመ ቀቲል አላቸው። ወአርመሙ ዝም አሉ ምሳሌ በግዕን ነግሮ ተንሥእ ወቁም ማዕከለ ብሎ ስፋሕ እዴከ ይለዋል።
፭፡ ወነጸሮሙ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ ይትመዓዕ ወይቴክዝ በእንተ ዑረተ ልቦሙ፣
፭፡ ስለ ልቡናቸው ድንቁርና እያዘነ ጌታ በቁጣ አያቸው።
ወእምዝ ይቤሎ ለውእቱ ብእሲ ስፋሕ እዴከ ወሰፍሐ እዴሁ።
ያን ሰው እጅህን ዘርጋ አለው እጁን ዘረጋ።
ወሐይወት ወኮነት ከመ ካልዕታ
ድና እንደ ሁለተኛዪቱ ሆነች፤
፮፡ ወወጺኦሙ ፈሪሳውያን ሶቤሃ ተማከሩ ምስለ ሰብአ ሄሮድስ ከመ ይቅትልዎ።
፮፡ ፈሪሳውያን ወጥተው ከሄሮድስ ስዎች ጋራ ሊገሉት ተማከሩ።
በእንተ ካልዓን ተአምራት ዘኢየሱስ።
፯፡ ወተግኅሠ እግዚእ ኢየሱስ ምስለ አርዳኢሁ መንገለ ባሕር።
፯፡ ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ባሕር ሄደ።
፰፡ ወተለውዎ ብዙኃን ጥቀ እምገሊላ ወእምይሁዳ ወእምኢየሩሳሌም
፰፡ ከይሁዳና ከገሊላ ከኢየሩሳሌም እጅግ ብዙ ሰዎች ተከተሉት።
ወእምኤዶምያስ ወእማዕዶተ ዮርዳኖስ።
ከዮርዳኖስ ማዶና ከኤዶምያስም።
ወእምጢሮስ ወእምሲዶና።
ከሲዶናና ከጢሮስም።
ወብዙኃን ጥቀ መጽኡ ኀቤሁ ሰሚዖሙ ኵሎ ዘገብረ።
ያደረገውን ሁሉ የሰሙ እጅግ ብዙ ሰዎች ናቸው።
፱፡ ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ያጽንሑ ሎቱ ሐመረ ከመ ኢይትጋፍዕዎ ሰብእ
፱፡ ሰዎች እንዳይገፉት ደቀ መዛሙርቱን መርከብ አቈዩኝ አላቸው።
፲፡ እስመ ለብዙኃን አሕየዎሙ
ብዙ ሰዎችን አድኖዋቸዋልና።
ወኮኑ ይትጋፍእዎ እስከ ይወድቁ ዲቤሁ።
ከላዩ ላይ እስቲወድቁ ይጋፉት ነበር፣
ወአስተብቊዕዎ ከመ ይግሥሥዎ ኵሎሙ ሕሙማን።
ሕሙማን ሁሉ ሊዳስሱት ይማልዱ ነበር።
፲፩፡ ወእለሂ እኁዛነ አጋንንት ርኵሳን እምከመ ርእይዎ ይሰግዳ ሎቱ፣
፲፩፡ ርኵሳን አጋንንት ያደሩባቸው ሁሉ ያዩት እንደሆነ ይሰግዱለት ነበር፤
ወእንዘ ይጸርሕ ወይብሉ አማን አንተ ውእቱ ወልደ እግዚአብሔር
ጩኸው የእግዚአብሔር ልጅ በእውነት አንተ ነህ አሉ፤
፲፪፡ ወኮነ ብዙኃ ይጌሥፆሙ ከመ ኢያግኅድዎ።
፲፪፡ እንዳይገልጡት፤
ወከመ ኢይክሥቱብሮ።
ሥራውንም እንዳይገልጡ ብዙ ገሠፃቸው

በእንተ ዘከመ ኀረዮሙ ለሐዋርያት።

፲፫፡ ወዓርገ ደብረ ወጸውአ እለ ፈቀደ። ማቴ ፥፩። ሉቃ ፮፥፫። ፱፥፩
፲፫፡ ከተራራ ወጥቶ የወደዳቸውን ጠራ ማለት ሹመት ሽረት አደረገ
ወመጽኡ ኀቤሁ።
ወደሱ ሄዱ።
ወኃረየ ወ፪ተ ወሰመዮሙ ሐዋርያተ።
አስራ ሁለቱን ሐዋርያት መረጠ።
ወረሰዮሙ ከመ የሀልዉ ምስሌሁ።
ከሱም ጋራ እንዲኖሩ አደረጋቸው።
(ሐተታ) ደጃዝማች በተሾመ ጊዜ ፈጥኖ እንዳይሄድ ወግ ታሪክ ሲያጠና እንዲሰነብት።
፲፬፡ ወፈነዎሙ ይስብኩ
፲፬፡ ያስተምሩ ዘንድ ላካቸው።
፲፭፡ ወአብሖሙ ያውጽኡ አጋንንተ ወይፈውሱ ዱያነ።
፲፭፡ አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ድውያንንም ይፈውሱ ዘንድ ሥልጣን ሰጣቸው።
፮፡ ወሰመዮሙ በበአስማቲሆሙ
፮፡ በየስማቸው ጠራቸው።
ወሰመዮ ለስምዖን ጴጥሮስ።
ስምዖንን ጴጥሮስ አለው።
፯፡ ወለያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ወለዮሐንስ እኍሁ ሰመዮሙ በአኔርጌስ።
፯፡ ያዕቆብንም የዘብዴዎስን ልጅ ዮሐንስንም የያዕቆብን ወንድም በአኔርጌስ አላቸው
ደቂቀ ነጐድጓድ ብሂል።
የነጐድጓጅ ልጆች ማለት ነው።
(ሐተታ) “በርጌስ” ማለት በዕብ ራይስጥ ልሳን ልጅ ማለትነው። “ጌስ” ደቂቀ ነጐድጓድ ማለት ነው። “አኔ” ትርፍ ቀለም ነው። እልመስጦአግያ እንደማለትእልም” ትምህርትስጦ” ትርፍአግያ” ኅቡአት እንደሆነ። ደቂቀ ነጐድጓድ አለ ደቂቀ ምሥጢር ደቂቀ መለኮት ሲል ነው። ደቂቀ ነጐድጓድ ማለቱ በምሳሌ ነው ርጡብ ጢስ ከርጡብ ምድር ይቡስ ጢስ ከይቡስ ምድር ወጥቶ አንድ ደመና ይሆናል ከውቅያኖስ ውሀ ጠልፎ ሲወጣ ነጐድጓድ ያሰማል፤ እኒህም ከቤተ ክህነት ከቤተ መንግሥት ተወልደው ሲያስተምሩ ተሰምተዋልና ደቂቀ ነጐድጓድ አላቸው።
፲፯፡ ወእንድርያስ።
፲፯፡ እንድርያስ
ወፊልጶስ።
ፊልጶስ፤
ወበርተሎሜዎስ፤
በርተሎሜዎስ
ወማቴዎስ
ማቴዎስ
ወቶማስ።
ቶማስም።
ወያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ።
የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ።
ወታዴዎስ።
ታዴዎስ።
ወስምዖን ቀነናዊ።
ቀነናዊ ስምዖን።
፲፱፡ ወይሁዳ አስቆሮታዊ ዘውእቱ ዘአግብኦ።
፲፱፡ የአስቆሮት ሰው የሚሆን ያሲያዘው ይሁዳ።
፳፡ ወበዊዖ ቤተ መጽኡዕበ ብዙኃን አሕዛብ እስከ ኢያበውህዎ ይብላዕ እክለ።
፳፡ ከቤት በገባ ጊዜ እንጀራ ይበላ ዘንድ እስኪሳነው ድረስ ብዙ አሕዛብ ሁለተኛ መጡ፥
ዘከመ አስተዋደይዎ ለኢየሱስ ከመ ያወጽእ አጋንንተ በብዔል ዜቡል።
፳፩፡ ወሰሚዖሙ አዝማዲሁ መጽኡ የአኀዝዎ
፳፩፡ ዘመዶቹም ሰምተው ሊይዙት መጡ።
እስመ ስሕወ ልቡ ይቤልዎ።
ልቡ አለው ብለዋልና።
፳፪ወጸሐፍትኒ እለ ወረዱ እምኢየሩሳሌም ይቤሉ ብዔል ዜቡል አኀዞ። ማቴ ፱፥፴፬።
፳፪፡ ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጸሐፍት ብዔል ዜቡል አድሮበታል
ወበመልአኮሙ ለአጋንንት ያወፅኦሙ ለአጋንንት።
በሰይጣን አለቃ ሰይጣናትን ያወጣል አሉ፤
፳፫፡ ወጸውዖሙ እግዚእ ኢየሱስ ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ እፎ ይክል ሰይጣን ለሰይጣን አውጽኦቶ፤
፳፫፡ ጌታ ጠርቶ ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደምን ይቻለዋል ብሎ ምሳሌ መስሎ ነገራቸው።
፳፬፡ ወመንግሥትኒ ዘበበይናቲሃ ትትናፈቅ ኢትቀውም ይእቲ መንግሥት።
፳፬፡ እርስ በርሱዋ የምትከፋፈል መንግሥት አትጸናም።
፭፡ ወእመኒ ቤት ተናፈቀት በበይናቲሃ ኢትቀውም ይእቲ ቤት
፭፡ ቤትም እርስ በርሷ ብትከፋፈል ያች ቤት አትጸናም።
፳፮፡ ወሰይጣንሂ ለእመ ተንሥአ በበይናቲሁ ወተናፈቀ ኢይቀውም።
፳፮፡ ሰይጣንም እርስ በእርሱ ቢጻላ ቢለያይም አይጠናም።
አላ ማኅለቅተ ይረክብ።
ተፍጻሜተ ሲል ነው። ፍጻሜ አለበት እንጅ።
፯፡ ወአልቦ ዘይክል በዊአ ቤተ ኃያል ወበርብሮተ ንዋዩ ለእመ ኢቀደመ አሢሮቶ ለኃያል
፯፡ ብርቱውን አስቀድሞ ካላሰረ ወደ ብርቱ ቤት መግባት ገንዘቡንም መዝረፍ የሚቻለው የለም።
ወእምዝ ይበረብር ቤቶ።
ከያዘው በኋላ ግን ቤቱን ይበዘብዛል፤
፳፰፡ አማን እብለክሙ ኵሉ ኃጢአት ወጽርፈት ይትኃደግ ለወልደ እጓለ እመሕያውማቴ ፲፪፥፴፩። ሉቃ ፲፪፲። ዮሐ ፫፥፲
፳፰፡ ኃጢአት ሁሉ ለሰው ልጅ እንዲሠረይ እውነት እነግራችኋለሁ
፱፡ ወዘሰ ጸረፈ ዲበ መንፈስ ቅዱስ ኢይትኃደግ ሎቱ ለዓለም ፱፡ መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ግን ለዘለዓለም ስርየት የለውም። ወይትኴነን በደይን ለዝለፉ።
በገሃነም የዘወትር ፍርድ ይፈረድበታል እንጂ።
፴፡ እስመ ይቤልዎ ጋኔን ርኵስ አኃዞ።
፴፡ ርኵስ ጋኔን አድሮበታል ብለውታልና።

በእንተ አዝማዲሁ ለኢየሱስ

፴፩፡ ወመጽኡ እሙ ወአኃዊሁ ወቆሙ አፍአ።
፴፩፡ ወንድሞቹና እናቱ መጥተው በውጭ ቆሙ እስመ ስህወ ልቡ ይቤሉ ይቤልዎሙ መጽኡ እሙ ወአኃዊሁ ብለህ ግጠም።
ወለአኩ ኀቤሁ ይጸውእዎ
ሊጠሩት ማለት ጥሩልን ብለው ላኩ።
ወይነብሩ ብዙኃን ሰብእ ምስሌሁ።
ብዙ ሰዎች ከእሱ ጋራ ተቀምጠው ነበር፤
፴፪፡ ወይልዎ ናሁ እምከኒ ወአኃዊከኒ አፍአ ይቀውሙ ወየኃሥሡከ።
፴፪፡ እነሆ እናትህና ወንድሞችህ በውጭ ቆመው ይሹሀል አሉት
፴፫፡ ወአውሥአ ወይቤሎሙ መኑ ይእቲ እምየ።
፴፫፡ እናቴ ማናት።
ወእለ መኑ እሙንቱ አኃውየ።
ወንድሞቼስ እነማናቸው ብሎ መለሰላቸው።
(ሐተታ) ማቴዎስ የነገረው አንድ ነው ይላል ማርቆስ ብዙ አለ እንደምነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር እንደ ማቴዎስ የነገረው አንድ ይሁዳ ነው። ማርቆስ ብዙ ማለቱ መናገር የሁሉ ፈቃድ ከሆነ ብሎ ነው።
፴፬፡ ወነጸሮሙ ለእለ ይነብሩ ዓውደ ወይቤሎሙ ነዮሙ እምየኒ ወአኃውየኒ።
፴፬፡ በዙሪያው ተቀምጠው ወደነበሩት አይቶ እነሆ እናቴም ወንድሞቼም አላቸው።
፴፭፡ እስመ ኵሉ ዘይገብር ፈቃዶ ለእግዚአብሔር ውእቱ እኍየኒ ወእኅትየኒ ወእምየኒ፤
፴፭፡ ወንድሜም እህቴም እናቴም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ነው።

No comments:

Post a Comment