Tuesday, August 20, 2019

የማርቆስ ወንጌል------ምዕራፍ ፭።


፩፡ ወበጺሖሙ ማፅዶተ ባሕር ኀበ ብሔረ ጌርጌሴኖን። ማቴ ፰፥፳፰። ሉቃ ፰፥፳፮።
፩፡ በባሕር ማዶ ወዳለ ወደ ጌርጌሴኖን ደረሱ።
፪፡ ወወሪዶ እምሐመር ተቀበሎ ሶቤሃ ብእሲ ዘእኵይ ጋኔን ላዕሌሁ ወጺኦ እመቃብር።
፪፡ ከመርከቡ በወረደ ጊዜ ርኵስ ጋኔን የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ተገናኘው።
፫፡ ወይነብር ውስተ መቃብር።
፫፡ ከመቃብር ይኖር ነበር።
ወስዕንዎ አውጽኦቶ በመዋቅሕትኒ እንዘ ዘልፈ ይሞቅሕዎ
ዘወትር ሲያስሩት በሰንሰለት ስንኳ ማጽናት ተሳናቸው።
ወአልቦ ዘይክል አድክሞቶ።
የሚችለው አልነበረም።
፬፡ እስመ መዋቅሕተኒ ይሰብር
፬፡ እግርብረቱንም ይሰብረው ነበርና።
ወሰናስለኒ ይቀጠቅጥ።
ሰንሰለቱንም ያወልቅ ነበረና።
መያዓቅብዎ ደቅ።
ሕፃናት ይጠብቁት ነበር።
(ሐተታ) ግብረ አበር ናቸውና ብር ብር እያሉ።
አንድም ኃያል ሲል ነው። ለይትነሥኡ ደቅነ ወይትዋነዩ በቅድሜነ እንዲል።
፭፡ ወዘልፈ የዓወዩ መዓልተ ወሌሊተ በውስተ መቃብር ወበውስተ አድባር።
፭፡ ሁለጊዜም በመዓልትና በሌሊት በመቃብርና በተራራ ይጮህ ነበረ።
ወይጌምድ ሥጋሁ በዕብን።
ሥጋውንም በድንጊያ ይፈጨው ነበር።
፮፡ ወሶበ ርእዮ ለእግዚእ ኢየሱስ እምርኁቅ ሮፀ ወሰገደ ሎቱ።
፮፡ ጌታን በሩቅ ባየው ጊዜ መጥቶ ሰገደለት።
፯፡ ወጸርሐ በዓቢይ ቃል ወይቤ ምንት ብየ ምስሌከ ኢየሱስ ወልደ እግዚአብሔር ልዑል
፯፡ የልዑል የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ ከአንተ ጋራ ምን ጠብ አለኝ።
አምሕለከ በእግዚአብሔር ሕያው ከመ ኢትሣቅየኒ።
እንዳትሣቅየኝ በሕያው በእግዚአብሔር አምልሐለሁ ብሎ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ።
፰፡ እስመ ይቤሎ ለውእቱ ጋኔን እኵይ ፃዕ እምላዕሌሁ።
፰፡ ያን ርኵስ ጋኔን ውጣ ይለው ነበርና።
፱፡ ወተስእሎ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎ መኑ ስምከ።
፱፡ ኢየሱስም ስምህ ማነው ብሎ ጠየቀው።
ወይቤሎ ውእቱ ጋኔን ሌጌዎን ስምየ እስመ ብዙኃን ንሕነ
ያም ጋኔን ብዙ ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለ።
(ሐተታ) ቁጡ ማለት ነው። ዘበእንተ መዓቶሙ ተሰምዩ ሌጌዎነ እንዲል።
፲፡ ወአስተቊብዖ ብዙኃ ከመ ኢይስድዶ አፍአ እምብሔር።
፲፡ ከአገር ወደ ውጭ እንዳይሰዳቸው መላልሶ ለመነው።
፲፩፡ ወቦ ህየ መራዕየ አኅርው ብዙኃ ይትረዓይ መንገለ ደብር
፲፩፡ ከዚያ ብዙ የእሪያ መንጋ በተራራ አጠገብ ተሰማርቶ ነበር
፲፪፡ ወአስተብቊዕዎ ብዙኃ እሉ አጋንንት ወይቤልዎ እመሰ ታወጽአነ ፈንወነ ውስተ አኅርው ከመ ንባዕ ላእሌሆሙ።
፲፪፡ በእሪያዎች እንገባባቸው ዘንድ አሰናብተን ብለው ለመኑት።
፲፫፡ ወአብሖሙ እግዚእ ኢየሱስ።
፲፫፡ ጌታም ፈቀደላቸው።
ወወጺኦሙ እሙንቱ አጋንንት ቦኡ ላእለ አኅርው።
እኒያም አጋንንት ከሰዎቹ ወጥተው በእሪያዎች ገቡ።
ወዓብዱ እሙንቱ መራዕይ ወፀድፉ ውስተ ባሕር።
የእሪያውም መንጋ ሁሉ ሮጠው ከባሕር ወደቁ።
ወኮኑ መጠነ ፳፻።
ሁለት ሽህ ያህሉ ነበር።
ወሞቱ ውስተ ባሕር።
በባሕርም ውሥጥ ሞቱ።
፲፬፡ ወጐዩ ኖሎት ወዜነዉ ለአኅጕር ወለአዕፃዳት።
፲፬፡ እሪያ ጠባቆች ግን ሸሽተው በአደባባይና በሀገሩ አወሩ፤
ወወጽኡ ይርአዩ ዘኮነ፤
የሆነውንም ለማየት ወጡ፤
፲፭፡ ወርእዩ ወመጽኡ ኀበ እግዚእ ወረከብዎ ለዘጋኔን አኀዞ እንዘ ይነብር ድኁነ ወልቡሂ ገቢኦ ወልቡሰ ልብሶ ዝኩ ዘአኀዞ ሌጌዎን።
፲፭፡ ወደ ጌታም በመጡ ጊዜ ያ ጋኔን ያደረበትን ሰው አእምሮው ተመልሶ ልብሱን ለብሶ ከጌታ ጋራ ተቀምጦ አገኙት።
(ሐተታ) ማቴዎስ ሁለት ሰዎች ናቸው ይላል ማርቆስ አንድ ሰው አለ እንደምነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር አንደ ማቴዎስ ነው ሁለት ናቸው ማርቆስ አንድ ማለቱ ለመንገር ከበቃ ብሎ።
አንድም አንዱ የፀናበት አንዱ ያልፀናበት ነው። ማቴዎስ የጸናበትንም ያልጸናበትንም ቈጥሮ ሁለት አለ ማርቆስ ያልጠናበትን ትቶ አንድ አለ።
ወፈርሁ
ፈሩ።
፲፮፡ ወዜነውዎሙ እለ ርእዩ ዘከመ ኮነ ዘጋኔን ወዘበእንተ አኅርው።
፲፮፡ ጋኔን ያደረበት ሰው የሆነውን በእሪያዎችም የተደረገውን ያዩ ሰዎች ነገሩዋቸው።
፲፯፡ ወአኀዙ ያስተብቊዕዎ ከመ ይፃፅ እምደወሎሙ።
፲፯፡ ከአገራቸው ይሄድ ዘንድ ይለምኑት ጀመሩ።
፲፰፡ ወዓሪጎ ሐመረ ወአስተብቊዖ ውእቱ ዘጋኔን ይሑር ምስሌሁ
፲፰፡ ከመርከብ በወጣ ጊዜም ያ ጋኔን ያደረበት ሰው ከእሱ ጋራ ይሄድ ዘንድ ማለደው።
(ሐተታ) ምናኔ ሽቶ ይመለስብኛል ብሎ ፈርቶ።
፲፱፡ ወከልዖ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎ ሑር ውእቱ ቤተከ ኀበ እሊአከ።
፲፱፡ ጌታ ከለከለው ምናኔ ሽቶ ላለው እጣህ ምናኔ አይደለም ወደ ቤትህ ወደ ወገኖችህ ሂድ አለው።
፳፡ ወንግር ኵሎ ዘገብረ ለከ እግዚአብሔር።
፳፡ እግዚአብሔር ያደረገልህን አስተምር አለው።
(ሐተታ) ይመለስብኛል ብሎ ፈርቶ ላለው አይዞህ አይመለስብህም ከቤትህ ሂደህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ተአምራት አስተምር አለው።
ወዘከመ ተሣሃለከ።
ይቅርም እንዳለህ ተናገር።
፳፩፡ ወሖረ ወአኃዘ ይስብክ በዓሥሩ አኅጕር ኵሎ ዘገብረ ሎቱ ኢየሱስ።
፳፩፡ ጌታ ያደረገለትን ሁሉ በአሥሩ አገር ያስተምር ጀመረ።
ወአንከሩ ኵሎሙ።
ሁሉም አደነቁ።

ዘከመ ፈወሶን ለእንተ ደም ይውኅዛ ወለወለተ ኢያኢሮስ

፳፩፡ ወካዕበ ዓደወ እግዚእ ኢየሱስ በሐመር ማዕዶተ
፳፩፡ ዳግመኛም ጌታ በመርከብ ወደ ማዶ ተሻገረ።
ወተጋብኡ ብዙኃን ሰብእ ኀቤሁ ኀበ ሐይቀ ባሕር
በባሕር አጠገብ ሳለ ብዙ ሰዎች ወደእሱ ተሰበሰቡ
፳፪፡ ወመጽአ ኀቤሁ ፩ ብእሲ መጋቤ ምኵራብ ዘስሙ ኢያኢሮስ
፳፪፡ የምኵራብ ሹም ኢያኢሮስ የሚባል አንድ ሰው ወደእሱ መጣ።
ወሶበ ርእዮ ሰገደ ሎቱ ታሕተ እገሪሁ።
በአየውም ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገደለት
፳፫፡ ወብዙ አስተብቊዖ።
፳፫፡ እጅግም ለመነው።
ወይቤ ወለትየ አልጸቀት ትሙት።
ልጄ ልትሞት ቀርባለች።
ወባሕቱ ነዓ ደይ እዴከ ላዕሌሃ ወተሐዩ።
ነገር ግን መጥተህ አጅህን ጫንባት ትድናለች።
፳፬፡ ወሖረ እግዚእ ኢየሱስ ምስሌሁ ወተለውዎ ብዙኃን ሰብእ
፳፬፡ ብዙ ሰው ተከተሉት ከእሱ ጋራ ሔደ።
ወተጋፍዕዎ።
ያጫንቁት ነበር።
፳፭፡ ወመጽአት ብእሲት እንተ ደም ይውኅዛ እምነ ፲ወ፪ ክረምት።
፳፭፡ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት መጣች።
፳፮፡ ወብዙኃ አሕመምዋ ብዙኃን ዓቀብተ ሥራይ እንዘ ይፌውስዋ።
፳፮፡ እናድናታለን እያሉ ብዙ ባለ መድኃኒቶች ብዙ አደከሟት።
ወአስተዋጽአት ኵሎ ንዋያ ወአኅለቀት።
ገንዘቧን ሁሉ አውጥታ ጨረሰች።
ወአልቦ ዘበቊዓ ዘእንበለ ዳዕሙ ዘአልሀማ።
እየጸናባት ከመሄድ በቀር የረባት የጠቀማት የለም። ሰብእ ጥቀ እኵይ ውእቱ ወአርዌ ምድር ይልሕም እከየ እንዲል። ዘእንበለ ዘብእሳ ዘእንበለ ዘተወሰከ ሕማም ይላል እየባሰባት እየታከለባት ከመሄድ በቀር የጠቀማት የለም።
፳፯፡ ወሰሚዓ በእንተ እግዚእ ኢየሱስ መጽኣት ወቦአት ማዕከለ ሰብእ ወገሠሠት ጽንፈ ልብሱ እንተ ድኅሬሁ።
፳፯፡ የጌታን ነገር በሰማች ጊዜ መጥታ ከሰው መካከል ገብታ በኋላ የልብሱን ዘርፍ ዳሰሰች።
፳፰፡ እንዘ ትብል እምከመ ገሠሥኩ ጽንፈ ልብሱ አሐዩ እምደዌየ
፳፰፡ የልብሱን ዘርፍ የያዝኩ እንደሆነ እድናለሁ ብላ፣
፳፱፡ ወሶቤሃ ነጽፈ ነቅዓ ደማ።
፳፱፡ ያን ጊዜውንም የደሟ ምንጭ ደረቀ።
ወአንከረት ርእሳ ወሐይወት እምደዌሃ፣
ከደዌዋ እንደዳነች እሷ አደነቀች።
አንድም ወአእመረት ርእሳ ጥዒና ተሰማት።
፴፡ ወአእመረ እግዚእ ኢየሱስ ከመ ወጽአ ኃይል እምኔሁ ወተመይጦ ኀበ ሰብእ ይቤሎሙ መኑ ገሠሠኒ ጽንፈ ልብስየ።
፴፡ ጌታም ኃይል ከእሱ እንደወጣ አውቆ ወደ ሰዎቹ ተመልሶ የልብሴን ዘርፍ የያዘኝ ማነው አላቸው።
፴፩፡ ወይቤልዎ አርዳኢሁ ኢትሬኢኑ ሰብእ እንዘ ይትጋፍዓከ አንተ ትብል መኑ ገሠሠኒ ጽንፈ ልብስየ።
፴፩፡ ደቀ መዛሙርቱ ሰው ሲያጫንቅህ አታይምን የልብሴን ዘርፍ ማን ዳሠሠኝ ትላለህ አሉት።
፴፪፡ ወተመይጠ ከመ ይርአይ ዘገብረ ዘንተ።
፴፪፡ ይህን ያደረገን ሊያይ ተመለሰ።
፴፫፡ ወፈርሃት ይእቲ ብእሲት።
፴፫፡ ያች ሴት ፈራች።
ወርእደት ጥቀ።
እጅግ ተጨነቀች።
እስመ አእመረት ዘኮነ ላዕሌሃ
የተደረገባትን ስላወቀች።
ወመጽአት ኀበ እግዚእ ኢየሱስ ወሰገደት ሎቱ ታሕተ እገሪሁ።
ወደ ጌታ መጥታ ሰገደችለት
ወነገረቶ ኵሎ ጽድቀ
እውነቱንም ሁሉ ነገረችው።
፴፬፡ ወይቤላ ወለትየ ሃይማኖትኪ አሕየወተኪ እትዊ በሰላም።
፴፬፡ ልጄ ሃይማኖትሽ አድኖሻልና በደህና ሂጅ አላት።
ወሕየዊ እምደዌ።
ከደዌሽም ተፈወሽ አላት።
፴፭፡ ወእንዘ ይትናገር ምስሌሃ መጽኡ ምስሌሃ ኀበ መጋቤ ምኵራብ ወይቤልዎ ወለትከሰ ሞተት ወኢታፃምዎ እንከ ለሊቅ፣
፴፭፡ ከእሷ ጋራ ሲናገር ሰዎች ወደሹሙ መጥተው ልጅህስ ሞታለች ከእንግዲህስ ወዲህ መምህርን አታድክመው አሉት።
(ሐተታ) ማቴዎስ ወለትየ ሞተት አለው ይላል። ማርቆስ አልፀቀት ትሙት አለው አለ እንደምነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር እንደ ማቴዎስ ነው። ወለትየ ሞተት ብሎታል ሞተች አልክ ቢለው ደንግጦ አልፀቀት ትሙት ብሎታል እንደ ማርቆስ ይህን ተካፍለው ጽፈዋል።
አንድም ነገር እንደ ማርቆስ ነው አልፀቀት ትሙት ብሎታል ዝግጥግጥ ቢልበት ፈጥኖ ይሄድልኛል ብሎ ወለትየ ሞተት ይለዋል ይህን ተካፍለው ጽፈዋል።
አንድም አልፀቀት ትሙት ብሎታል ብላቴኖች መጥተው ወለትከሰ ሞተት ኢታፃምዎ እንከ ለሊቅ አሉት የብላቴኖቹን ቃል ይዞ ሞተት ብሎታል። የፊተኛውን ማርቆስ የኋለኛውን ማቴዎስ ጻፉ ነገር እንደ ማቴዎስ ነው።
፴፮፡ ወሰሚዖ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ ይትናገርዎ ይቤሎ ለመጋቤ ምኵራብ ኢትፍራህ ተአመን ዳዕሙ ተሐዩ ወለትከ።
፴፮፡ ጌታ ግን ሲነግሩት ሰምቶ የምኵራቡን ሹም እመን እንጂ አትፍራ ልጅህም ትድናለች አለው።
፴፯፡ ወከልዓ ከመ አልቦ ዘይተልዎ ዘእንበለ ጴጥሮስ ወያዕቆብ ወዮሐንስ እኍሁ ለያዕቆብ።
፴፯፡ ከያዕቆብ ከጴጥሮስ ከያዕቆብ ወንድም ከዮሐንስም በቀር የሚከተለው እንዳይኖር ከለከለ።
፴፰፡ ወቦአ ቤቶ ለመጋቤ ምኵራብ
፴፰፡ ከምኵራብ ሹም ቤት ገባ።
ወረከቦሙ እንዘ ይትሐወኩ ወይበክዩ ወየአወይዉ ብዙኃ።
ሲያለቅሱና ሲታወኩ በብዙም ሲጮሁ አገኛቸው።
፴፱፡ ወቦአ ወይቤሎሙ ለምንት ትትሐወኩ።
፴፱፡ ገብቶ ለምን ትታወካላችሁ አላቸው።
ወትበክዩ።
ለምን ታለቅላላችሁ።
ሕፃንሰ ኢሞተት።
ብላቴናይቱስ አልሞተችም አላቸው።
አላ ትነውም።
ተኝታለች እንጂ አላቸው
፵፡ ወሰሐቅዎ።
፵፡ ሳቁበት።
ወእምዝ ሰደደ ኵሎ ወነሥኦሙ ለአቡሃ ወለእማ ለሕፃን ወእለ ምስሌሆሙ ወቦአ ኀበ ሀለወት ሕፃን።
ከዚህ በኋላ ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን እናትና አባት ከእሱም ጋራ የነበሩትን ይዞ ብላቴናይቱ ካለችበት ገባ
፵፩፡ ወአኀዛ እዴሃ ለሕፃን
፵፩፡ የብላቴናይቱን እጁዋን ያዛት።
ወይቤላ ጣቢታ ቁሚ።
ጣቢታ ቁሚ አላት።
ተንሥኢ ወለትየ ብሂል በትርትሜሁ
ትርጓሜው ልጄ ተነሽ ማለት ነው።
፵፪፡ ወተንሥአት ሶቤሃ ይእቲ ወለት ወአንሶሰወት።
፵፪፡ ያችም ብላቴና ፈጥና ተነሥታ ሄደች።
ወ፲ ወ፪ቱ ክረምታ
አሥራ ሁለት ዓመት ሁኑዋት ነበር።
ወደንገጹ ሶቤሃ ዓቢየ ድንጋፄ
ያን ጊዜም ታላቅ ድንጋፄ ደነገጡ።
፵፫፡ ወገሠጾሙ ለአቡሃ ወለእማ ብዙኃ ከመ አልቦ ዘየአምር ዘንተ
፵፫፡ ይህን ማንም ማን የሚያውቀው እንዳይኖር እናት አባቷን ብዙ ገሠጻቸው።
ወአዘዘ የሀብዋ ዘትበልዕ።
የምትበላውም ስጧት አለ።

No comments:

Post a Comment