በእንተ ፈሪሳውያን ወሥርዓቶሙ።
፩፡
ወተጋብኡ ኀቤሁ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መጺኦሙ እምኢየሩሳሌም።
፩፡
ጸሐፍት ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም መጥተው ወደእሱ ተሰ
በሰቡ።
፪፡
ወርእይዎሙ ለአርዳኢሁ እንዘ ይበልዑ እክለ ዘእንበለ ይትሐፀቡ እዴሆሙ። ማቴ ፲፭፥፪።
፪፡
ደቀ መዛሙርቱን እጃቸውን
ሳይታጠቡ ሲበሉ አዩዋቸው
፫፡
እስመ ፈሪሳውያንሰ ወኵሎሙ አይሁድ ለእመ በሕቁ ኢተሐፅቡ እደዊሆሙ ኢይበልዑ እክለ
፫፡
ፈሪሳውያን ግን አይሁድ ሁሉ እጃቸውን በጅጉ ሳይታጠቡ
አይበሉም ነበርና።
መላልሰው ደም እስኪሰርበው እስኪመለጥ ድረስ ካልታጠቡ አይበሉም
እስመ የዓቅቡ ሥርዓቶም ለረበናት።
የረበናትን ሥርዓት ይጠብቁ
ነበርና።
፬፡
ወዘሂ ተሣየጡ እምሥያጥ ኢይበልዑ ለእመ ኢያጥመቅዎ
፬፡
ከገበያ የተገዛውንም በውሀ
ካላጠቡ አይበሉም ነበር።
ወባዕደኒ ብዙኅ ኅርመተ ዘይትዓቀቡ።
ሌላም የሚጠብቁት ብዙ ሥርዓት አለ፤
ወያጠምቁ ጽዋዓተኒ፣
ጽዋውንም ያጥቡት ነበር።
ወቈሳቊሳተ፣
ብርቱን ድስቱን።
ወጽሕርታተ፤
ማድጋውን።
ወአራታተ።
አልጋውን።
፭፡
ወይቤልዎ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን ለምንት ኢየሐውሩ አርዳኢከ በከመ ሠርዑ ረበናት
፭፡
ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ደቀ መዛሙርትህ እንደ
ሽማግሎች ሥርዓት ለምን አይሄዱ አሉት፡
ወዘእንበለ ይትሐፀቡ እደዊሆሙ ይበልዑ እክለ።
እጃቸውንስ ሳይታጠቡ ለምን
እህል ይበላሉ።
፮፡
ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስወይቤሎሙ ኦ መደልዋን ሠናየ ተነበየ ኢሳይያስ ላዕሌክሙ እንዘ ይብል ዝ ሕዝብ በከናፍሪሆሙ ያከብሩኒ ወበልቦሙሰ ነዋኅ ይርኅቁ እምኔየ። ኢሳ ፳፱፥፲፫።
፮፡
እናንት ግብዞች ኢሳይያስ እኒህ ሕዝብ በከንፈራቸው ያከብሩኛል በልባቸው ግን ፈጽመው ከእኔ ይርቃሉ ብሎ ኢሳይያስ እውነት ተናግሮባችኋል።
ወከንቶ ያመልኩኒ።
በከንቱ ያመልኩኛል።
፯፡
እንዘ ይሜህሩ ሥርዓታተ ትእዛዛተ ሰብእ።
፯፡
በሰዎች ሥርዓት ትምህርት እያስተማሩ።
፰፡
ወየኃድጉ ትእዛዛተ እግዚአብሔር ወየዓቅቡ ትእዛዘ እጓለ እመሕያው።
፰፡
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትተው የሰውን ሥርዓት ይጠብቁ ነበረና።
ጥምቀተታተ ጽዋዓት ወቈሳቊሳተ
ጽዋውን ብርቱን ድስቱንም
ማጠብ።
ወጽርሐታተ።
ማድጋውን።
ወባዕደኒ ብዙኃ ዘይመስሎ ለዝንቱ፤
ሌላውንም ይህን የመሰለውን
ሁሉ፤
፱፡
ወይቤሎሙ ርቱዕኑ ትዕልዉ ትእዛዛተ እግዚአብሔር ከመ ትዕቀቡ ትእዛዘ ርእስክሙ።
፱፡
የራሳችሁን ትእዛዝ ትጠብቁ
ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ልታፈርሱ ይገባልን አላቸው
፲፡
ወሙሴ ይቤለክሙ አክብር አባከ ወእመከ። ዘፀ ፳፥፲፬። ዘዳ ፭፥፲፮። ኤፌ ፮፥፪። ዘፀ ፳፩፥፲፯። ዘሌ ፰፥፱። ምሳ ፳፥፳።
፲፡
ሙሴ እናትና አባትክን አክብር ብሏችኋል።
ወዘአኅሰመ ቃለ ላዕለ አቡሁ ወእሙ ሞተ ለይሙት።
አባትና እናቱንም የሰደበ ፈጽሞ ይሙት።
፲፩፡ ወአንትሙሰ ትብልዎ ዘይቤሎ ለአቡሁ።
፲፩፡ እናንተ ግን ለአባቱ የሚመልሰውን ትነግሩታላችሁ።
አው ለእሙ።
ወይም ለእናቱ የሚመልሰውን
ቊርባን ዘረባህከ እምኔየ ብሂል
ከእኔ ያገኘኸውን ቊርባን ነው ማለት ነው።
፲፪፡ ኢታበውህዎ ይግበር ምንተኒ ለአቡሁ ወለእሙ።
፲፪፡ ለአባትና ለእናቱ ምን ምን ያደርግ
ዘንድ አታሰናብቱትም።
፲፫፡ ወትሥዕሩ ቃለ እግዚአብሔር በእንተ ትእዛዝ
ዘሠራዕክሙ።
፲፫፡ ለሠራችሁት ሥርዓት የእግዚአብሔርን
ትእዛዝ ታፈርሳላችሁ።
ወዓዲ ብዙኅ በአምሳለ ዝንቱ ዘትገብሩ።
ዳግመኛም ሌላም የምትሠሩት ይህን የመሠለ
ብዙ አለ
፲፬፡ ወጸውዖሙ ካዕበ ለሕዝብ ወይቤሎሙ ስምዑ ኵልክሙ
ወለብዉ። ማቴ ፲፭፥፲።
፲፬፡ ሁለተኛ ሕዝቡን ጠርቶ ስሙ እወቁ አላቸው።
፲፭፡ አልቦ ዘይበውእ እምአፍአ ውስተ አፉሁ ለሰብእ
ዘይክል አርኵሶቶ።
፲፭፡ ከውጭ ወደ ሰው አፍ የሚገባው ሊያረክሰው
አይችልም፤
ዘእንበለ ዳዕሙ ዘይወፅእ እምልቡ ለሰብእ ውእቱ
ያረኵሶ ለሰብእ።
ከሰው ልብ የሚወጣ እሱ ያረክሰዋል እንጂ።
፲፮፡ ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማዕ
፲፮፡ ጆሮ ያለው ይስማ።
ወበዊኦ ቤተ እምኀበ ሕዝብ ተስእልዎ አርዳኢሁ ዘንተ
አምሳለ።
ከሕዝቡም ዘንድ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ደቀ
መዛሙርቱ ይህን ምሳሌ ጠየቁት።
፲፯፡ ወይቤሎሙ አንትሙኒ ከመዝኑ ኢትሌብዉ።
፲፯፡ እናንተም እንዲህ ገና አታውቁምን።
፲፰፡ ኢተአምሩኑ ከመ ኵሉ ዘእምአፍአ ይበውእ ውስተ
ሰብእ ኢይክል አርኵሶቶ።
፲፰፡ ከውጭ ወደ ሰው የሚገባው ሁሉ ሰውን
እንዳይጐዳው አታውቁምን።
፲፱፡ እስመ ኢይበውእ ውስተ ልቡ ዘእንበለ ውስተ
ከርሠ ክመ
፲፱፡ ወደ ሆዱ ብቻ ነው እንጂ ወደ ልቡ
አይገባምና።
ወጽመ ይትከዓው እንዘ ያነጽሕ ኵሎ መባልእተ።
መብሉን ሁሉ ሲያጠራ ቆይቶም ይወጣል።
፳፡ ወይቤሎሙ ዘይወጽእ እም አፋሁ ለሰብእ ውእቱ
ያረኵሶ ለሰብእ።
፳፡ ከሰው የሚወጣው እሱም ሰውን ይጐዳዋል።
፳፩፡ እስመ እምውሥጠ ልቡ ለሰብእ ይወጽእ ኵሉ
ሕሊና እኵይ።
፳፩፡ ከሰው ከልቡ ውሥጥ ክፉ አሳብ ሁሉ
ይወጣልና።
ዘውእቱ ዝሙት
ይህም ዝሙት ነው
ወቀቲል
መግደል
ወሥርቅ።
መስረቅ
፳፪፡ ወሐዊረ ብእሲተ ብእሲ
፳፪፡ ወደ ጐልማሳ ሚስት መሄድ
ወትዕግልት።
ቅሚያ
ወእከይ
ክፋት።
ወጕሕሉት
ክዳት
ወጽልሑት።
ሽንገላ።
ወምርዓት።
ድርዓት
ወጽርፈት
ስድብ።
ወትዕቢት።
ትዕቢት
ወሕመሜ ዓይን።
ምቀኝነት
ወዕበድ
ስንፍና።
፳፫፡ ዝንቱ ኵሉ እከይ ይወጽእ እምውሥጥ
፳፫፡ ይህ ሁሉ ክፉ ነገር ከውሥጥ ይወጣል
ወያረኵሶ ለሰብእ።
ሰውን ይጐዳዋል፤
በእንተ ከነናዊት።
፳፬፡ ወተንሢኦ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ሖረ ብሔረ
ጢሮስ ወሲዶና። ማቴ ፲፭፥፳፩።
፳፬፡ ጌታም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ
ሲዶና ሄደ።
ወቦአ ቤተ ወኢፈቀደ ያእምሮ መኑሂ።
ከቤትም ገባ ማንም ማን ሊያውቀው አልወደደም።
ወስእነ ተከብቶ።
መሠወርም አልተቻለውም
፳፭፡ ወእምዝ ሰምዓት በእንቲአሁ አሐቲ ብእሲት
እንተ ጋኔን እኵይ አኀዛ ለወለታ
፳፭፡ ከዚህም በኋላ ልጅዋን ርኵስ ጋኔን
የያዘባት አንዲት ሴት የሱን ነገር ሰማች።
ወቦአት ወሰገደት ሎቱ ታሕተ እገሪሁ።
ገብታም ከእግሩ በታች ሰገደችለት፤
፳፮፡ ወአረማዊት ይእቲ ብእሲት
፳፮፡ ያችም ሴት አረማዊት ናት።
ወሲሮፊኒቂሳዊት።
ሲሮፊኒቂሳዊትም ናት።
(ሐተታ) አረማዊት ከነናዊት ከንዓናዊት ጽርአዊት ሶርያዊት ሲሮፊኒቂሳዊት ይላታል ስምንት ጋጥ ያላት ናት የሰው ትውልድ ከብዙ ወገን ነውና።
ወሰአለቶ ያውጽእ ጋኔነ እምወለታ
ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው
፳፯፡ ወይቤላ እግዚአ ኢየሱስ ኅድጊ ቅድመ ምዕረ ይጽገቡ ውሉድ፤
፳፯፡ ጌታም ቈዪ ልጆች ይጽገቡ
አላት።
እስመ አኮ ሠናይ ነሢአ ኅብስተ ውሉድ ወውሂብ ለከለባት።
የልጆችን እንጀራ ነሥቶ ለውሾች መስጠት አይገባምና
፳፰፡ ወተሰጥወቶ።
መለሰችለት።
ወትቤሎ እወ እግዚኦ ከለባትኒ ይበልዑ በታሕተ ማዕድ ፍርፋራተ ዘያወድቁ ደቂቅ
፳፰፡
አዎን አቤቱ ውሻም ልጆች ከማዕድ የጣሉትን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው።
፳፱፡ ወይቤላ በዝንቱ ቃልኪ ሑሪ ወጽአ ውእቱ ጋኔን እምወለትኪ
፳፱፡ ስለዚህም ነገርሽ ሂጂ ጋኔኑም
ከልጅሽ ወጥቷል አላት።
፴፡
ወሖረት ወአተወት ቤታ።
፴፡
ወደቤቷም ተመለሰች።
ወረከበታ ለወለታ ልብስታ ወትነብር ዲበ ዓራታ።
ልጁዋን ልብሷንም ለብሳ በአልጋውም ተቀምጣ አገኘቻት
ወኃደጋ ጋኔና።
ጋኔኑዋም ተዋት
ዘከመ ፈወሶ ለበሐም ወጽሙም
፴፩፡
ወኃሊፎ ካዕበ እምጢሮስ ወሖረ እንተ ሲዶና ወባሕረ ገሊላ እንተ ፲ቱ አኅጉር።
፴፩፡ ዳግመኛ ከጢሮስ አልፎ በአሥሩ ሀገር መካከል ወደ ገሊላ
ባሕርና ወደ ሲዶና ሄደ።
፴፪፡ ወአምጽኡ ኀቤሁ በሐመ ወጽሙመ። ማቴ ፱፥፴፪። ሉቃ ፲፥፩-፲፬።
፴፪፡ ደንቆሮም ድዳም ይዘው ወደእሱ
መጡ።
ወአስተብቊዕዎ ከመ ይደይ እዴሁ ላዕሌሁ።
እጁንም ይጭንበት ዘንድ ማለዱት።
፴፫፡
ወአግኃሦ እምሰብእ ባሕቲቱ
፴፫፡
ብቻውንም ከሰው ለየው።
ወወደየ አፃብዒሁ ውስተ እዘኒሁ፤
ጣቱንም ከጆሮው ጫነበት ።
ወተፍአ
ምራቁንም ተፋበት፤
ወገሠሠ ልሳኖ፤
ምላሱንም ዳሰሰው፣
፴፬፡ ወነጸረ ሰማየ፤
፴፬፡ ወደሰማይ አየ፤
ወአስተምሐረ።
አዘነም፡
ወይቤ ኤፍታሔ ኤፍታሔ።
ኤፍታሔ ኤፍታሔ አለ።
ተረኀው ብሂል።
ተከፈት ማለት ነው።
፴፭፡ ወሶቤሃ ተከሥተ ዕዘኒሁ።
፴፭፡ ያንጊዜም ጆሮው ተከፈተ።
ወተፈትሐ ማዕሠረ ልሳኑ።
የምላሱም ዕሥራት ተፈታ።
ወተናግረ ርቱዓ
አቃንቶም ተናገረ።
፴፮፡
ወገሠፆሙ ኢይንግሩ ወኢለመኑሂ።
፴፮፡
ለማንም ለማን እንደይናገሩ ገሠፃቸው።
ወአምጣነ ይከልዖሙ ውእቱ ፈድፋደ ይነግሩ ሎቱ፤
እሳቸው ግን በከለከላቸው መጠን ይናገሩ ነበር።
፴፯፡ ወፈድፋደ ያነክርዎ ወእንዘ ይብሉ ሚ ሠናይ ኵሉ ዘገብረ ዝንቱ ብእሲ።
፴፯፡
ይህ ሰው የሠራው ምን ያምር እያሉ ፈጽመው ያደንቃሉ
ለጽሙማን ያሰምዖሙ።
ደንቆሮዎችን ያሰማቸዋል፤
ወለበሐማን ያነብቦሙ
ዲዳዎችን ያናግራቸዋል።
No comments:
Post a Comment