Tuesday, August 13, 2019

የማርቆስ ወንጌል -----ምእራፍ ፩።

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማርቆስ እንደ ጻፈው።
ብሥራተ ማርቆስ ረድእ ፩ዱ እም፸ ወ፪ቱ አርድእት ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ፍቁሩ ወልደ ማርያም ለዓለመ ዓለም አሜን።
ማርቆስ ማለት ንህብ ማለት ነው። ንህብ ከሁሉ እንዲቀስም አስቀድሞ ከክርስቶስ ኋላ ከሐዋርያት ተምሯልና።
አንበሳ ማለት ነው። አንበሳ ለላም ጌታው እንደሆነ እንዲሰብረው አምልኮተ ላሕምን ከግብፅ አጥፍቷልና።
አንድም ካህን ልዑክ ማለት ነው። ብሥራተ ማሪ ማርቆስ ይላል የተደራረበ ቀለም ነው። ሁሉም ካህን ማለት ነው እመልእክተ ሲኖዲቆስ ባለ ጊዜ መልእክትም ሲኖዲቆስም ክታብ ማለት እንደሆነ፤ ይህም ቃል የሠለስቱ ምዕት ነው እንደ ማቴዎስ ተርክ። ይህን ዓለም ዕጣ በዕጣ ብለው ተካፍለው ለማስተማር በሚወጡበት ጊዜ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሮም በዕጣ ደርሰዋለች አምስተኛ ግብፅን አንሥቷል። ይህስ አይደለም ብሎ ግብፅ በዕጣ ደረሰችው። አምስተኛ ሮምን አንሥቷል የንጉሠ ነገሥት መዲና ናትና እሱም ሊቀ ሐዋርያት ነውና። ለአርድዕት ግን ዕጣ የላቸውም አንድም ሁለትም እየሆኑ አንዱን ሐዋርያ አንዱም ሁለቱም አንዱን ሐዋርያ ተከትለው ሄደዋል። ማርቆስም ጴጥሮስን ተከትሎ ሄዷል። ግብፅን ለማርቆስ ሰጥቶት እርሱም ሮም ወርዷል ማርቆስ ከዚህ ገብቶ ጌታ ከፅንስ ጀምሮ ያደረገውን ተአምራት ያስተማረውን ትምህርት የሠራውን ትሩፋት ቢነግራቸው ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ተመለሱ አመኑ ተጠመቁ። ትምህርት ካልደረሰበት ለማዳረስ ወጥቶ በሚሄድበት ጊዜ አባታችን በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳልና ጻፍልን ብለው በዚያ ምክንያት ይጽፋል።
አንድም እሱ እንደ አባትነቱ ይጽፋል። መዋዕለ ጽሕፈት ሐተታ እንደ ማቴዎስ።
ጸሐፍቱም ሁለቱ ከሐዋርያት ሁለቱ ከአርድዕት ናቸው ሐዋርያት ጨርሰው እንዲጽፉት ያላደረገ ሁለቱን ከአድርዕት ያጻፈ ስለምን ቢሉ፤ ሐተታ እንደ ማቴዎስ።
አርድእት ጨርሰው እንዲጽፍት ያላደረገ ሁለቱን ከሐዋርያት ያጻፈ ስለምን ቢሉ ሐተታ እንደ ማቴዎስ።
ጸሐፍቱንስ ከፍ ብሎ አምስት ስድስት ዝቅ ብሎ ሁለት ሦስት ያላደረገ ስለምን ቢሉ። ሐተታ እንደ ማቴዎስ።
ሀገርም ልሳንም ሐተታ እንደ ማቴዎስ። ወንጌልሂ ብለህ አትት ይህን አርእስት ሠለስቱ ምዕት ሰጥተዋል ብለህ ጨርሰህ ተርክ። ልመናው ክብሩ ይደርብንና ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ማርቆስ የጻፈው ወንጌል ይህ ነው።

ምዕራፍ ፩።

በእንተ ስብከተ ዮሐንስ።

-፫፡ ቀዳሚሁ ለወንጌለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በከመ ጽሑፍ ውስተ መጽሐፈ ነቢያት ናሁ አነ እፌኑ መልአኪየ ቅድመ ገጽከ ዘይጸይሕ ፍኖተከ በቅድሜከ ቃለ ዓዋዲ ዘይሰብክ በገዳም ወይብል ጺሑአ ፍኖተ እግዚአብሔር ወአርዩ መጽያሕቶ። ኢሳ ፵፥፫። ማቴ ፫፥፫። ሉቃ ፫፥፬። ዮሐ ፩፥፳፫።
-፫፡ ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው የወንጌል ጥንቱ ጥምቀተ ዮሐንስ ስብከተ ዮሐንስ ነው። በከመ ጽሑፍ ውስተ መጻሕፍተ ነቢያት። ሚክ ፫፥፩። በመጻሕፍተ ነቢያት እንደተነገረ ዘንድ።
አንድም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው የወንጌል ጥንቱ በመጻሕፍተ ነቢያት እንደ ተነገረ ዘንድ ነው።
አንድም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው የወንጌል ጥንቱ አምላክ ሰው እንደሆነ ዘንድ ነው።
በከመ ጽሑፍ።
በመጸሕፍተ ነቢያት እንደተነገረ። እፌኑ ያለውን ይሻል።
አንድም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው የወንጌል ጥንቱ ሰው አምላክ እንደሆነ ዘንድ ነው። መልአኪየ ያለውን ይሻል። በከመ ጽሑፍ በመጻሕፍተ ነቢያት እንደተነገረ ዘንድ።
አንድም ቀዳሚሁ ለወንጌለ ኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ጥንቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በከመ ጽሑፍ በመጻሕፍተ ነቢያት እንደተነገረ ዘንድ።
(ሐተታ) መጻሕፍተ ነቢያት ያለ እንደሆነ አያሳትትም መጽሐፈ ነቢይ ያለ እንደሆነ እፌኑ መልአኪየ ያለ ሚልክያስ ቃለ ዓዋዲ ያለ ኢሳይያስ ነው። ምነው ነቢይ አለ ቢሉ ያንድ ገንዘብ ሽህ ያለዝብ እንዲሉ ነቢይ የሁሉ ስም ነውና መጽሐፈ ኢሳይያስ ይላል አብነት ኢሳይያስ እንደ አባት እንደመምህር ሚልክያስ እንደ ልጅ እንደ ደቀ መዝሙር ናቸውና።
፬፡ ወሀሎ ዮሐንስ ያጠምቅ በገዳም
፬፡ ዮሐንስ በምድረ በዳ ያስተምር ነበር።
ወይሰብክ ጥምቀተ ለንስሐ ወይትኃደግ ሎሙ ኃጢአቶሙ
ኃጢአታቸው ሊሠረይላቸው የንስሐ ጥምቀትን ያስተምር ነበር
፭፡ ወየሐውሩ ኀቤሁ ኵሎሙ ሰብአ ይሁዳ ወኢየሩሳሌም። ማቴ ፫፥፭።
፭፡ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ወደሱ ይሄዱ ነበር።
ወያጠምቆሙ ኵሎሙ በፈለገ ዮርዳኖስ እንዘ ይትአመኑ ኃጢአቶሙ።
ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ሁሉንም በዮርዳኖስ ወንዝ ያጠምቃቸው ነበር።
፮፡ ወልብሱ ለዮሐንስ ኮነ ዘጸጕረ ገመል። ማቴ ፫፥፬። ዘሌ ፲፩፥፴፪። ሉቃ ፫፥፲፮። ዮሐ ፩፥፳፮። ግብ ፯፥፭።
፮፡ የዮሐንስ ልብሱ የግመል ጸጕር ነበር።
ወቅናቱ ዘዓዲም ውስተ ሐቌሁ
በወገቡም የሚታጠቀው የነት መታጠቂያ ነበር።
ወሲሳዩ አንበጣ ወመዓረ ጸደና
ምግቡም የምድረ በዳ ማርና አንበጣ ነበር።
፯፡ ወሰበከ ወይቤ ይመጽእ እምድኅሬየ ዘይጸንዕ እምኔየ
፯፡ ከእኔ የበረታ ከእኔ በኋላ ይመጣል።
ወኢይደልወኒ እድንን ወእፍታሕ ቶታነ አሣዕኒሁ እምእገሪሁ
የጫማውን ጠፍር ተጐምብሼ እፈታ ዘንድ የማይገባኝ
(ሐተታ) እጹር ማቴዎስ እድንን ማርቆስ እፍታሕ ሉቃስ መገናኛው ዮሐንስ። እንዲህ ግን ስለሆነ እድንን ይቀድማል እፍታሕ ይከተላል እጹር በመጨረሻ ነው ይህን ተከፍለው ጽፈዋል።
፰፡ ወአንሰ አጠምቀክሙ በማይ።
፰፡ እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ።
ወውእቱሰ ያጠምቀክሙ በመንፈስ ቅዱስ።
እሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል።
በእንተ ጥምቀት ወተመክሮት ዘኢየሱስ።
፱፡ ወይእተ አሚረ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ እምናዝሬት ዘሀገረ ገሊላ።
፱፡ በዚያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ክፍል ከናዝሬት መጣ።
ወአጥመቆ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ።
በዮርዳኖስ ወንዝ ዮሐንስ አጠመቀው።
፲፡ ወወፂኦ እማይ ርእየ ተሰጥቀ ሰማይ። ሉቃ ፫፥፳፪። ዮሐ ፩፥፴፪።
፲፡ ከውኃውም በወጣ ጊዜ ሰማይ ሲቀደድ አየ።
(ሐተታ) ማቴዎስ ተርኅወ ይላል ከዚህ ማርቆስ ተሰጥቀ አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር እንደ ማቴዎስ ነው። ከዚህ ግን ማርቆስ ተሰጥቀ ማለቱ ስለ ክብረ መንፈስ ቅዱስ ነው።
ወወረደ መንፈስ ቅዱስ ከመ ርግብ ወነበረ ዲቤሁ።
መንፈስ ቅዱስም እንደ ርግብ ወርዶ ተቀመጠበት።
፲፩፡ ወመጽአ ቃል እምሰማይ ዘይብል አንተ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ወኪያኩ ሠመርኩ።
፲፩፡ ደስታዬን የማይብህ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ የሚል ድምጽ ከወደ ሰማይ ተሰማ።
(ሐተታ) ማቴዎስ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ አለው ይላል ማርቆስ አንተ ውእቱ ወልድየ አለው አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር እንደ ማቴዎስ ነው ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ብሎታል። ማርቆስ ወልድየ አንተ ያለው ትንቢት እንደ ተፈጸመለት ለማጠየቅ አንተ ውእቱ ወልድየ አለው አለ እንጂ።
አንድም ነገር እንደ ማርቆስ ከውኃው ሳለ አንተ ውእቱ ወልድየ ብሎታል። አሁን ወልድ የባሕርይ ልጅነቱን የማያውቅ ሁኖ አይደለም በወልድ ለዮሐንስ ለመናገር ነው እንጂ። አኮ ዘእስእለከ ከመ ትንሥኦሙ እምዓለም ዘእንበለ ዳዕሙ ከመ ትዕቀቦሙ እምእኵይ ባለ ጊዜ አብ የማያውቅ ሁኖ እንዳይይለ በአብ ለሐዋርያት ለመናገር እንደሆነ። ከውኃው ከወጣ በኋላ እንደ ማቴዎስ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ብሎታል በዮሐንስ ለሕዝቡ ለመናገር።
፲፪፡ ወአውፅኦ መንፈስ ሶቤሃ ገዳመ። ማቴ ፬፥፩። ሉቃ ፬፥፩።
፲፪፡ በዚያም ጊዜ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው።
፲፫፡ ወነበረ ሐቅለ መዓልተ ወ፵ ሌሊተ።
፲፫፡ በምድረ በዳም አርባ ሌሊትና አርባ መዓልት ተቀመጠ።
ወያሜክሮ ሰይጣን።
ሰይጣን ይፈታተነው ነበር።
ወነበረ ምስለ አራዊት።
ከአራዊት ጋራ ይኖር ነበር። ርኅቀተ መካኑን ያጠይቃል።
ወይትለአክዎ መላእክት።
መላእክትም ያገለግሉት ነበር።
ዘከመ አኀዘ ኢየሱስ ይስብክ ወይኅረይ ቀደምተ ሐዋርያተ።
፲፬፡ ወእምድኅረ አኃዝዎ ወሞቅሕዎ ለዮሐንስ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ ገሊላ ወሰበከ ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር። ማቴ ፬፥፲፪። ሉቃ ፬፥፲፬። ዮሐ ፬፥፵፫።
፲፬፡ ዮሐንስን ይዘው ከአሠሩት በኋላ ጌታ ወደገሊላ መጥቶ የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌልን አስተማረ።
፲፭፡ እንዘ ይብል በጽሐ ጊዜሁ።
ጊዜው ደረሰ።
ወቀርበት መንግሥተ ሰማያት
መንግሥተ ሰማያትም ቀረበች
ነስሑ ወአመኑ።
በወንጌል ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ።
፲፮፡ ወእንዘ የኃልፍ መንገለ ባሕረ ገሊላ ረከቦሙ ለስምዖን ወለእንድርያስ እኍሁ እንዘ ይወድዩ መርበብቶሙ ውስተ ባሕር። ማቴ ፬፥፲፰። ሉቃ ፭፥፪።
፲፮፡ በገሊላም ባሕር አጠገብ ሲሄድ ስምዖንን ወንድሙን እንድርያስንም መረባቸውን ከባሕር ሲጥሉ አገኛቸው።
እስመ መሠግራን እሙንቱ።
ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
፲፯፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ንዑ ትልዉኒ
፲፯፡ ጌታም ተከተሉኝ አላቸው።
ወእሬስየክሙ መሠግራነ ሰብእ
ሰውን እንድታጠምዱ አደርጋችኋለሁ።
፲፰፡ ወኃደጉ መሣግሪሆሙ ወተለውዎ ሶቤሃ።
፲፰፡ ያን ጊዜም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
፲፱፡ ወኃሊፎ ሕቀ እምህየ ረከቦሙ ለያዕቆብ ወለዮሐንስ እኍሁ ደቂቀ ዘብዴዎስ።
፲፱፡ ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብን ወንድሙን ዮሐንስንም አገኛቸው።
ወለሊሁኒ ምስሌሆሙ።
እሱም ከእሳቸው ጋራ ነበር።
እንዘ ይሠርዑ ወያስተሣንዩ መሣግሪሆሙ።
መረባቸውን ሲያበጁ ማለት ያደፈውን ሲያጥቡ የተቈረጠውን ሲቀጥሉ።
፳፡ ወጸውዖሙ በጊዜሃ። ወኃደጉ ዘብዴዎስሃ አባሆሙ ምስለ አሳቡ ውስተ ሐመር ወተለውዎ።
፳፡ ጠራቸው። አባታቸውን ዘብዴዎስን ከሟያተኞቹ ጋራ በታንኳ ትተውት ሄደው ተከተሉት ምስለ አሳቡ ብሎ በማርቆስ ያቀናዋል ያልነው ይህ ነው።
ዘከመ ፈወሶ ኢየሱስ በቅፍርናሆም ለዘቦቱ ጋኔን።
፳፩፡ ወሖሩ ቅፍርናሆም። ማቴ ፬፥፲፫። ሉቃ ፬፥፴፩።
፳፩፡ ቅፍርናሆም ሄዱ።
ወቦአ በሰንበት ምኵራበ ወአኀዘ ይምሀሮሙ፤
ቅዳሜ በምኵራብ ገብቶ ያስተምር ጀመረ።
፳፪፡ ወአንከሩ ምሕሮቶ። ማቴ ፯፥፳፰።
፳፪፡ ትምህርቱን አደነቁ።
እስመ ከመ መኰንን ይሜሕሮሙ ወአኮ ከመ ጸሐፍቶሙ
እንደ ጸሐፍት ያይደለ፤ ሥልጣን እንዳለው ያስተምራቸው ነበርና።
፳፫፡ ወሀሎ ብእሲ ዘጋኔን ውስተ ምኵራብ። ሉቃ ፬፥፴፫።
፳፫፡ ከምኵራብ ጋኔን ያደረበት ሰው ነበር።
፳፬፡ ወአውየወ ወይቤ ምንት ብየ ምስሌከ ኢየሱስ ናዝራዊ።
፳፬፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከአንተ ጋራ ምን ጠብ አለኝ።
መጸእከኑ ታጥፍአነ።
ልታጠፋን መጣህን
ነአምረከ ከመ አንተ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር።
የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ማንም እንደሆንህ እናውቅሀለን ብሎ ጮኸ።
፳፭፡ ወገሠፆ እግዚእ ኢየሱስ።
፳፭፡ ጌታም ገሠፀው።
ወይቤሎ ተፈጸም አፉከ
ዝም በል።
ወፃእ እምኔሁ።
ከእሱም ውጣ አለው።.
፳፮፡ ወአስተራገፆ ውእቱ ጋኔን እኵይ
፳፮፡ ቢስ ጋኔን አንዘፈዘፈው
(ሐተታ) ይሰማዋልና ጽንዓ ተአምራቱን ለማጠየቅ።
አንድም ውደቅ ሌባ ባሉት ጊዜ ከሳንቃው ከመድረኩ እየተማታ እንዲወጣ።
ወአውየወ በዓቢይ ቃል
በታላቅ ቃልም ጮኸ።
ወወፅአ እምኔሁ
ከእሱ ወጣ።
(ሐተታ) ምኵራቡ ያለ ከተራራ ላይ ነው ያሉ እንደሆነ ሲያስተምር ውሎ ጉባዔ ሲፈታ ከምኵራብ ገብቶ ፈውሶት ሂዷል። ምኵራቡ ከተራራው በታች ነው ያሉ እንደሆነ ሲያስተምር ውሎ ከተራራው ወርዶ ከምኵራቡ ገብቶ ፈውሶት ይሄዳል።
፳፯፡ ወደንገጹ ኵሎሙ እለ ርእዩ ዘንተ።
፳፯፡ ይህን ያዩ ሁሉ አደነቁ።
ወይቤሉ በበይናቲሆሙ ምንትኑ ዝንቱ ትምሕርት ሐዲስ
ይህ እንግዳ ትምህርት ምንድነው
እስመ በትእዛዝ ይኤዝዞሙ ለአጋንንት ርኩሳን ከመ ይፃዑ።
ርኵሳን አጋንንት ይወጡ ዘንድ ያዛቸዋልና።
አንድም ትእምርት ብለህ ይህ እንግዳ ምልክት ምንድር ነው በትእዛዝ ውጡ ብሎ አጋንንትን የሚያዛቸው።
ወይትኤዘዙ ሎቱ።
አጋንንትም የሚወጡለት ይህ እንግዳ ምልክት ምንድ ነው አሉ።
፳፰፡ ወተሰምዓ ነገሩ ውስተ ኵሉ በሐውርተ ገሊላ።
፳፰፡ ተአምራቱ በገሊላ አውራጃ ሁሉ ተሰማ።
በእንተ ሐማተ ጴጥሮስ ወካልዓን ሕሙማን እለ ተፈወሱ
፳፱፡ ወወፂኦ እምኵራብ ቦአ ቤተ ስምዖን። ማቴ ፰፥፲፬። ሉቃ ፬፥፴፬።
፳፱፡ ከምኵራብም ወጥቶ ከስምዖን ቤት ገባ።
ወምስሌሁ እንድርያስ ወያዕቆብ ወዮሐንስ።
ያዕቆብና እንድርያስ ዮሐንስም ከእሱ ጋራ ነበሩ።
፴፡ ወርእያ ሐማቱ ለስምዖን እንዘ ትፈጽን ወትሰክብ።
፴፡ የስምዖን አማት ምንሾ ታማ ነበረች።
ወነገርዎ በእንቲአሃ።
የእሷን ነገር ነገሩት።
፴፩፡ ወቀርበ ኀቤሃ ወአኀዘ እዴሃ ወአንሥኣ።
፴፩፡ ቀርቦ እጅዋን ይዞ አሥነሣት
ወኃደጋ ፈፀንታ ሶቤሃ።
ያን ጊዜ ሆድ ዝማዋ ፈጥኖ ተዋት።
ወተንሥአት ወተልእክቶሙ።
ተነሥታ አገለገለቻቸው። ማቴዎስ ነገርዎ አላለም ከዚህ ማርቆስ ነገርዎ አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም፤ ከመንገድ ሳለ ነግረውታል ከቤት ከገባ በኋላ አልነገሩትም። ያኑ ከመንገድ የነገሩትን ይዞ አድኑዋታል። ከቤት ከገባ በኋላ አለመንገራቸውን ሲያይ ማቴዎስ ነገርዎ አላለም። ከመንገድ መንገራቸውን ሲያይ ማርቆስ ነገርዎ አለ።
አንድም ነገር እንደ ማርቆስ። ከመንገድ ሳለ ነግረውታል። ከቤት ገብቶ ነገሩን እሳቸው ያንሱ ብሎ ዝም ብሏል ሁለተኛ ነግረውት ፈውሷታል ነገሩን ያንሱት ብሎ ዝም ስላለ ማቴዎስ ነገርዎ አላለም። ሁለተኛ መንገራቸውን ሲያይ ማርቆስ ነገርዎ አለ።
፴፪፡ ወመስዮ ጊዜ የዓርብ ፀሐይ አምጽኡ ኀቤሁ ኵሎ ድውያነ ወአለሂ እኁዛነ አጋንንት።
፴፪፡ ሲመሽ ፀሐይ በሚገባበት ጊዜ ድውያንን ሁሉ ጋኔን ያደረባቸውንም ወደእርሱ አመጧቸው።
፴፫፡ ወተጋብኡ ኵሎሙ ሰብአ ሀገር ኀበ አንቀጽ
፴፫፡ ሰዎች ሁሉ ከበር ተሰብስበው
፴፬፡ ወፈወሶሙ ለብዙኃን ድውያን ወሕሙማን። ሉቃ ፬፥፵፩።
፴፬፡ ብዙ ድውያንን አዳናቸው።
ወአውጽኦሙ ለብዙኃን አጋንንት።
ብዙ አጋንንትንም አወጣቸው
ወኢያብሖሙ ይንብቡ፤
ይናገሩ ዘንድ አላሰናበታቸውም ዝም በሉ አላቸው፤
እስመ አእመርዎ ከመ ውእቱ ክርስቶስ።
ክርስቶስ እንደ ሆነ ስላወቁት።
፴፭፡ ወበጽባሕ ተንሥአ ወአሌለየ ጥቀ ወወጺኦ ሖረ ሐቅለ ወጸለየ በህየ
፴፭፡ በድጅ ማለዳ ገሥግሦ ወጥቶ በረሃ ሂዶ በዚያ ጸለየ።
፴፮፡ ወዴገንዎ ስምዖን ወእለ ምስሌሁ
፴፮፡ ስምዖን ከእሱም ጋራ የነበሩት ተከተሉት።
፴፯፡ ወሶበ ረከብዎ ይብልዎ ኵሉ ሕዝብ የኃሥሡከ።
፴፯፡ ባገኙት ጊዜ ሁሉ ይሹሃል አሉት።
፴፰፡ ወይቤሎሙ መልዑ ንሑር ካልአተኒ አኅጉረ።
፴፰፡ ወደሌላውም አገር ተነሡ እንሂድ አላቸው፤
ከመ በህየኒ እስብክ።
በዚያም አስተምር ዘንድ፤
እስመ እንበይነ ግብር መጻእኩ።
ስለዚህ ነገር ሰው ሁኛለሁና።
፴፱፡ ወሖረ ወሰበከ በምኵራባቲሆሙ ውስተ ኵሉ ገሊላ።
፴፱፡ ሂዶ በገሊላ ሁሉ በምኵራብ አስተማረ።
ወያወጽእ አጋንንተ።
ጋኔን ያወጣ ነበር።
፵፡ ወመጽአ ኀቤሁ ዘለምጽ። ማቴ ፰፥፪። ሉቃ ፫፥፲፪።
፵፡ ለምጽ የያዘው ሰው መጣ፤
ሰገደ ሎቱ አስተብረከ ወአስተብቁዖ።
ሰገደ ማለደው
ወይቤሎ እግዚኦ እመሰ ፈቀድከ ትክል አንጽሖትየ።
አቤቱ ከወደድህስ እኔን ማዳን ይቻልሃል አለው
፵፩፡ ወምህሮ እግዚእ ኢየሱስ
፵፩፡ ጌታም ራራላት
ወሰፍሐ እዴሁ ወገሠሦ
እጁን ዘርግቶ ዳሰሰው
ወይቤሎ ፈቀድኩ ንጻሕ
እወዳለሁ ዳን አለው
፵፪፡ ወዘንተ ብሂሎ ሐይወ ለምጹ ሶቤሃ
፵፪፡ ይህን በተናገረ ጊዜ ለምጹ ፈጥኖ ዳነ
፵፫፡ ወገሠፆ ወፈነዎ ወይቤሎ ዑቅ ኢትንግር ወኢለመኑሂ
፵፫፡ ለማንም ለማን እንዳትነግር አስተውል ብሎ ገሥፆ ሰደደው
፵፬፡ ወሑር ወአፍትን ርእሰከ ለካህን። ሌዋ ፲፬፥፬።
፵፬፡ ነገር ግን ሂደህ ራስህን ለካህን አስመርምር።
ወአብእ መባአከ በእንተ ዘነጻሕከ።
ስለ ነጻሕም መባሕን ስጥ።
በከመ አዘዘ ሙሴ
ከመ ይኩን ስምዓ ላእሌሆሙ
ሙሴ እንዳዘዘ መፈራረጃ ይሆንባቸው ዘንድ። ማቴዎስ ዘለምጽን ያስቀድማል ሐማተ ጴጥሮስን ወደኋላ ያደርጋል ማርቆስ ሐማተ ጴጥሮስን አስቀድሞ ዘለምጽን አስከተለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም። ለወንጌልና ለድጓ ተራ የለውም።
፵፭፡ ወወጺኦ አኀዘ ይስብክ ወይንግር ብዙኃ እስከ ያነክሩ ኵሉ ሀገር።
፵፭፡ በወጣም ጊዜ ሰው ሁሉ እስኪያደንቅ ብዙ ተናገረ ያወራም ጀመረ።
ወስዕነ በዊአ ሀገር ክሡተ።
ተገልጦ ወደሀገር መግባት ተሣነው።
(ሐተታ) በሰው ጥላ ነዋሪ ነበርና አምስት ገበያ ሰው ይከተለው ነበርና።
አላ አፍአ ገዳመ ይነብር።
ብቻውንስ በገዳም ይገኝ ነበር እንጂ።
ወይመጽኡ ኀቤሁ ሰብእ እምኵለሄ።
ከየቦታውም ሰዎች ሁሉ ወደእሱ ይመጡ ነበር።
አንድም ወስዕነ እያልክ መልስ። ከሥጋዌ አስቀድሞ መወሰን ተሳነው ከመወሰን በአፍአ ነበር እንጂ።
አንድም ከሥጋዌ አስቀድሞ ታይቶ ተአምራት ማድረግ ተሳነው ታይቶ ተአአምራት ከማድረግ በአፍአ ነበር እንጂ።
አንድም ከሥጋዌ አስቀድሞ በሰው ልቡና ማደር ተሳነው በሰው ልቡና ከማደር በአፍአ ነበር እንጂ።
አንድም በመዓልት በደብረ ዘይት መዋል ተሳነው በመዓልት በምኵራብ ሲያስተምር ይውል ነበር እንጂ።
አንድም በሌሊት በምኵራብ ማደር ተሳነው ሌሊት በደብረ ዘይት ሲጸልይ ያድር ነበር እንጂ።

No comments:

Post a Comment