Tuesday, August 20, 2019

የማርቆስ ወንጌል--------ምዕራፍ ፮።


ዘከመ ሰበከ ኢየሱስ በናዝሬት።

፩፡ ወወጺኦ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ቦአ ሀገሮ። ማቴ ፲፫፥፶፬። ሉቃ ፬፥፲፮።
፩፡ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሀገሩ ገባ
ወተለውዎ አርዳኢሁ።
ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።
፪፡ ወበሰንበት መሐሮሙ በምኵራብ።
፪፡ ቅዳሜ በምኵራብ አስተማራቸው።
ወብዙኃን ያጸምዕዎ ወያነክሩ እንዘ ይብሉ እምአይቴ ሎቱ ዝንቱ ኵሉ ትምሕርት።
ብዙ ሰዎች ሰምተው ይህ ሁሉ ከወዴት ተገኘለት ብለው አደነቁ።
ወምንትኑ ዛቲ ጥበብ እንተ ተውህበት ሎቱ
ይህችስ የተሰጠችው ጥበብ ምንድናት።
ወዝኒ ኃይል ዘይትገበር በእደዊሁ።
ይህስ በእጁ የሚደረግ ኃይል ምንድን ነው።
፫፡ አኮኑ ዝንቱ ውእቱ ወልዱ ለፀራቢ። ዮሐ ፮፥፵፪።
፫፡ የፀራቢ ልጅ አይደለምን።
ወወልደ ማርያም
የማርያምስ ልጅ አይደለምን።
ወአኀዊሁኒ ያዕቆብ ወዮሳ ወይሁዳ ወስምዖን።
ወንድሞቹስ ዮሳና ያዕቆብ ይሁዳም ስምዖንም አይደሉምን።
ወአኮኑ አኃቲሁኒ ሀለዋ ዝየ ኀቤነ።
እኅቶቹስ ከእኛ ዘንድ ያሉ አይደለምን ብለው።
ወተአቅፉ።
በእሱ ምክንያት ተጠራጠሩ።
፬፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ኢኮነ ምኑነ ነቢይ ዘእንበለ በሀገሩ ወበቤቱ ወበኀበ አዝማዲሁ። ማቴ ፲፫፥፶፯። ሉቃ ፬፥፳፬። ዮሐ ፬፥፵፬።
፬፡ ጌታም ነቢይ በሀገሩና በወገኑ በቤቱም በቀር አይናቅም አላቸው።
፭፡ ወኢገብረ ኃይለ በህየ ዘእንበለ ኅዳጣን ድውያን ዘአንበረ እዴሁ ዲቤሆሙ ወአሕየዎሙ።
፭፡ እጁን ጭኖ ከአዳናቸው ከጥቂት በሽተኞች በቀር በዚያ ኃይል ተአምራት አላደረገም።
፮፡ ወአንከረ ኢአሚኖቶሙ።
፮፡ አለማመናቸውን አደነቀ።
ወአንሶሰወ እግዚእ ኢየሱስ ውስተ ኵሉ አህጉረ አድያም እንዘ ይሜህር።
እያስተማረ በአውራጃው ሀገር ሁሉ ተመላለሰ።

ዘከመ ፈነዎሙ ለሐዋርያት ይስብኩ።

፯፡ ወጸውዖሙ ለ፲ቱ ወ፪ቱ ሐዋርያት። ማቴ ፲፥፩። ማር ፫፥፲፬። ሉቃ ፱፥፩።
አስራ ሁለቱን ሐዋርያት መረጣቸው።
ወፈነዎሙ በበ፪ቱ።
ሁለት ሁለቱን ላካቸው።
(ሐተታ) አንዱ ቢደክም አንዱ ያጸናዋልና። ለእመ ወድቀ ፩ዱ ያነሥኦ ካልዑ ፈትል ሥሉስ ኢይትበተክ እኍኒ ዘይትራዳዕ እኅዋሁ ከመ ሀገር እንተ ባቲ ጥቅም እንዲል።
ወአብሖሙ ላዕለ አጋንንት እኵያን።
በክፉ አጋንንት ላይ ስልጣን ሰጣቸው።
፰፡ ወአዘዞሙ ከመ አልቦ ዘይሰንቁ ለፍኖት።
፰፡ ለመንገድም ስንቅ እንዳይዙ አዘዛቸው።
ወኢይንሥኡ ዘእንበለ በትር ባሕቲታ።
ከበትር ብቻ በቀር እንዳይዙ፤
(ሐተታ) ማቴዎስ ኢበትረ ይላል ከዚህ ማርቆስ ዘእንበለ በትር አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም። አምልኮቱን እስኪያውቁ ድረስ አትያዙ ይላል። አምልኮቱን ከአወቁ በኋላ ግን ቢይዙም ባይዙም አይጎዳምና ዘእንበለ በትር አለ።
አንድም ማቴዎስ ጌጸኛውን አትያዙ ሲል ኢበትረ አለ። ማርቆስ ተራውን ሲል ነው።
አንድም በትር ሳይቀር አትያዙ ሲል ነው።
ወኢኅብስተ።
እንጀራ ስንኳ።
ወኢጽፍነተ።
ከረጢትም።
ኢወርቀ ወኢብሩረ።
ወርቅ ብር አትያዙ።
ወኢጸሪቀ ውስተ ቅናቶሙ።
በመታጠቂያቸውም ናስ።
፱፡ ዘእንበለ አሣዕን ዘውስተ እገሪሆሙ። ግብ ፲፪፥፰።
፱፡ በእግራቸው ካለ ጫማ በቀር።
(ሐተታ) ማቴዎስ ኢአሣዕነ ይላል ከዚህ ማርቆስ ዘእንበለ አሣዕን አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አደጣላም አምልኮቱን እስኪያውቁ ድረስ አታድርጉ ይላል። አምልኮቱን ካወቁ በኋላ ግን ቢያደርጉትም ባያደርጉትም አይጎዳምና ዘእንበለ አሣዕን አለ።
አንድም ማቴዎስ ጌጸኛውን ሲል ነው።
አንድም ጫማ ሳይቀር አታድርጉ ሲል ነው አግብኡ ሊተ ንዋይየ ዘእንበለ ብእሲትየ አንዲል።
ወኢይልበሱ ፪ኤ ክዳናተ።
ሁለት ልብስም እንዳይለብሱ።
፲፡ ወይቤሎሙ ቤተ ኀበ ቦእክሙ ህየ ንበሩ እስከ አመ ትወጽኦ እምህየ።
፲፡ ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በገባችሁበት ቤት ኑሩ።
፲፩፡ ወብሔረ ኀበ ኢተወክፉክሙ ወኢሰምዑክሙ ወጺአክሙ እምህየ ንግፉ ፀበለ አገሪክሙ። ማቴ ፲፥፲፬። ሉቃ ፱፥፭። ግብ ፲፫፥፶፩።
፲፩፡ የማይሰሟችሁና የማይቀበላችሁ ሰዎች ካሉበት ሀገር ወጥታችሁ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።
ከመ ይኩን ስምዓ ላዕሌሆሙ
ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ
አማን እብለክሙ ከመ ይረክባ ሳሕተ ሰዶም ወገሞራ አመ ዕለተ ደይን እምይእቲ ሀገር።
ከዚያች አገር ይልቅ ሰዶም ገሞራ በፍርድ ቀን ዕረፍትን እንዲያገኙ በእውነት እነግራችኋለሁ።
፲፪፡ ወወጺኦሙ ሰበኩ ኵለሄ ከመ ኵሉ ይነሥሑ።
፲፪፡ በወጡም ጊዜ ሁሉ ንስሐ ይገቡ ዘንድ አስተማሩ።
፲፫፡ ወብዙኃነ አጋንንተ ያወጽኡ።
፲፫፡ ብዙ አጋንንትም ያወጡ ነበር።
ወይቀብዕዎሙ ቅብዓ ለብዙኃን ድውያን። ያዕ ፭፥፲፬።
ብዙ በሽተኞችንም ዘይት ይቀቧቸው ነበር
ወየሐይዉ።
ይድኑም ነበር።
(ሐተታ) መጽሐፈ ቀንዲል የሚባል አለ ያን በዘይት እየደገሙ ይቀቧቸው ነበርና።
አንድም ጸሎቱን ቅብዕ አለው ሌላውን የሚቀባው ሰው እጁን ሳይነካው እንዳይቀር ጸሎትም የሚጸልይ ሰው ራሱን ሳይጠቀም ሌላውን አይጠቅምምና።
ዘከመ ስምዓ ኮነ ዮሐንስ መጥምቅ።
፲፬፡ ወሰሚዖ ሄሮድስ ንጉሥ እስመ ክሡተ ኮነ ስሙ ወይቤ ዮሐንስ መጥምቅ ተንሥአ እምነ ምውታን። ማር ፲፬፥፪። ሉቃ ፱፥፰።
፲፬፡ ሄሮድስ ንጉሥ ስሙ እንደተገለጠ ሰምቶ ዮሐንስ መጥምቅ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል።
ወበእንተዝ ይትገበር ሎቱ ኃይል
ስለዚህ ኃይል ይደረግለታል ይረዳዋል አለ።
፲፭፡ ወቦ እለ ይቤሉ ኤልያስ ውእቱ
፲፭፡ ኤልያስ ነው ያሉም አሉ።
ወቦ እለ ይቤሉ ነቢይ ውእቱ።
ነቢይ ነው ያሉም አሉ።
ወእመ አኮ ከመ ፩ዱ እምነቢያት።
ወይም ከነቢያት አንዱ ነው አሉ።
፲፮፡ ወሰሚዖ ሄሮድስ ይቤ ዮሐንስ ውእቱ ዘአነ መተርኩ ርእሶ።
፲፮፡ ሄሮድስ ግን በሰማ ጊዜ እኔ እራሱን የቈረጥኩት ዮሐንስ ነው አለ።
ውእቱ ተንሥአ እሙታን።
እሱ ከሙታን ተነሥቷል።
፲፯፡ እስመ ውእቱ ሄሮድስ ፈነወ አግብርቲሁ ወአኃዞ ለዮሐንስ ወሞቅሖ። ሉቃ ፫፥፲፱።
፲፯፡ እሱ ሄሮድስ ብላቴኖቹን ልኮ ዮሐንስንም ይዞ በግዞት አኑሮት ነበረና።
በእንተ ሄሮድያዳ ብእሲተ ፊልጶስ እኍሁ።
በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት።
፲፰፡ እስመ ኪያሃ አውሰበ እስመ ይቤሎ ዮሐንስ ኢይደልወከ ታውስብ ብእሲተ እኍከ። ዘሌ ፲፥፰-፲፮።
፲፰፡ እሷን ስላገባ ዮሐንስ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።
፲፱፡ ወተቀየመቶ ሄሮድያዳ
፲፱፡ ሄሮድያዳም ቂም ይዛበት ነበርና።
ወፈቀደት ታቅትሎ።
ልታስገድለውም ትወድ ነበር።
ወስዕነት።
አልተቻላትም ማለት ነውር አጣችበት።
፳፡ እስመ ኮነ ይፈርሆ ሄሮድስ ለዮሐንስ።
፳፡ ሄሮድስ ዮሐንስን ይፈራው ነበርና።
እስመ የአምር ከመ ብእሲ ጻድቅ ወቅዱስ ውእቱ።
ደግ ሰው ቅዱስም እንደሆነ ስላወቀ።
ወይትዓቀቦ።
ይጠባበቀው ነበር።
ወብዙኃ ሰምዓ በኀቤሁ።
በእሱ ዘንድ ብዙ ነገር ሰምቶ።
ወይፈቅድ ይርአይ ተአምረ ዘይገብር።
የሚያደርገውን ተአምራት ሊያይ ይወድ ነበር።
ወያስተሐውዝ።
ምን ያምር ይል ነበር።
ወይፈቅድ ይስምዖ።
ሊሰማውም ይወድ ነበር።
፳፩፡ ወኮነት ዕለተ አመ ይገብር ሄሮድስ በዓለ በዕለተ ተወልደ።
፳፩፡ ሄሮድስ የተወለደበትን በዓል አድርጎ በነበረ ጊዜ።
አምስሐ መኳንንቲሁ።
መኳንንቱ ቀኛዝማች ግራዝማች።
ወመላእክቲሁ።
አለቆቹን።
ወመሳፍንቲሁ።
ደጃዝማቾቹን።
ወመገብቶ።
ሹማምንቱን።
ወአበይተ ሀገረ ገሊላ።
የገሊላን ታላላቆችን ማለት ወይዛዝሩን ምሳ አበላ።
፳፪፡ ወቦአት ወለተ ሄሮድያዳ ወዘፈነት።
፳፪፡ ወለተ ሄሮድያዳ ገብታ ዘፈነች።
ወአሥመረቶ ለሄሮድስ።
ሄሮድስን ደስ አሰኘችው።
ወእለ ይረፍቁ ምስሌሁ።
ከእሱ ጋራ የተቀመጡትን ደስ አሰኘች።
ወይቤላ ንጉሥ ለይእቲ ወለት ሰአልኒ ዘትፈቅዲ ወእሁበኪ።
ንጉሥም ያችን ብላቴና የምትወጂውን ለምኝኝ እሰጥሽአለሁ አላት።
፳፫፡ ወመሐለ ላቲ ከመ የሀባ ዘሰአለቶ እስከ መንፈቀ መንግሥቱ።
፳፫፡ እስከ መንግሥቱ እኵሌታ ስኳን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ ማለላት።
፳፬፡ ወወጽአት ወትቤላ ለእማ ምንተ እስአሎ።
፳፬፡ ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት።
ወትቤላ ርእሶ ለዮሐንስ መጥምቅ።
የዮሐንስ መጥምቅን ራስ አለቻት።
፳፭፡ ወቦአት ሶቤሃ ኀበ ንጉሥ እንዘ ትጔጕዕ ወሰአለቶ።
፳፭፡ ያን ጊዜውንም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ ለመነችው
ወትቤሎ እፈቅድ ይእዜ ተሀበኒ ርእሶ ለዮሐንስ መጥምቅ።
የዮሐንስ መጥምቅንም ራስ በገበታ አሁን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለችው።
፳፮፡ ወተከዘ ንጉሥ በእንተ መሐላሁ።
፳፮፡ ንጉሥ ስለ ማላው አዘነ።
ወበእንተሂ እለ ይረፍቁ ምስሌሁ።
ከእሱ ጋራ ስለ ተዋመጡት።
ወኢፈቀደ ይዕበያ።
ሊነሳት ግን አልወደደም።
፳፯፡ ወፈነወ ንጉሥ ሶቤሃ መስተራትአተ ሐራ።
፳፯፡ የዚያን ጊዜም ንጉሥ ጭፍራውን የሚያቅናኑትን ላከ።
ወአዘዘ ያምጽኡ ርእሶ።
ራሱን ያመጡ ዘንድ አዘዘ።
፳፰፡ ወሖሩ ወመተሩ ርእሶ ለዮሐንስ መጥምቅ በቤተቅሕ።
፳፰፡ ሂደው በግዞት ቤት ራሱን ቆረጡ።
ወአምጽኡ ርእሶ በፃሕል ወወሀብዋ ለይእቲ ወለት።
ራሱንም በገበታ አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጧት።
ወይእቲኒ ወለት ወሀበት ለእማ
ያችም ብላቴና ለእናቷ ሰጠች።
፳፱፡ ወሰሚዖሙ አርዳኢሁ ሖሩ ወነሥኡ በድኖ ወቀበርዎ።
፳፱፡ ደቀ መዛሙርቱ በሰሙ ጊዜ ሄደው በድኑን አንስተው ቀበሩት።

ዘከመ ተመይጡ ሐዋርያት።

፴፡ ወተጋብኡ ሐዋርያት ኀበ እግዚእ ኢየሱስ ወነገርዎ ኵሎ ዘገብሩ።
፴፡ ሐዋርያት ወደ ጌታ ተሰብስበው ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት
ወዘከመ መሐሩ።
እንዳስተማሩም ነገሩት
፴፩፡ ወይቤሎሙ ንኡ ንፃዕ ገዳመ ባሕቲተነ ወታዕርፉ ሕቀ። ማቴ ፲፬፥፲፫። ሉቃ ፱፥፲። ዮሐ ፮፥፩።
፴፩፡ ጥቂትም ታርፉ ዘንድ ለብቻችን ወደ ምድረ በዳ እንሂድ አላቸው።
፴፪፡ እስመ ብዙኃን እለ የሐውሩ ወይገብኡ።
፴፪፡ የሚወጡ የሚገቡ ብዙ ነበሩና።
ወኢያበውሕዎሙ ይብልዑ እክለ።
እህል ይበሉ ዘንድ አያሰናብቷቸውም ነበርና።
እስመ ኢያስተርክቡ።
ጊዜም አላገኙምና።
፴፫፡ ወሖሩ ሐቅለ በሐመር ባሕቲቶሙ።
፴፫፡ ብቻቸውንም በመርከብ ወደ ምድረ በዳ ሄዱ።
 ወርእይዎሙ እንዘ የሀውሩ ወአእመርዎሙ ብዙኃን።
ብዙ ሰዎችም ሲሄዱ አይተዋቸው አወቋቸው።
ወሖሩ እንተ እግር ኀቤሁ እምኵሉ አኅጕር።
ከየሀገሩ ወጥተው በእግር ወደእሱ ሄዱ።
ወተቃደምዎሙ ወመጽኡ ኀቤሁ።
ቀድመዋቸውም ወደእሱ መጡ።

ዘከመ አብዝኃ በቀዳሚ ኀምሰ ኅብስተ።

፴፬፡ ወወጺኦ እግዚእ ኢየሱስ ርእየ ብዙኃ ሰብአ። ማቴ ፱፥፴፮። ፲፬፥፴።
፴፬፡ ጌታም በወጣ ጊዜ ብዙ ሰው አየ።
ወመሐሮሙ።
አስተማራቸውም።
እስመ ከመ አባግዕ ዘአልቦ ኖላዊ እሙንቱ።
ጠባቂንደሌላቸው አባግዕ ናቸውና።
ወአኃዘ ይምሐሮሙ ብዙኃ።
ብዙ ያስተምራቸው ጀመር።
፴፭፡ ወእምድኅረ ብዙኅ ሰዓት መጽኡ አርዳኢሁ ወይቤልዎ ሐቅል ውእቱ ብሔር።
፴፭፡ ከጥቂት ሰዓት በኋላም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ይህ ቦታ ምድረ በዳ ነው።
ወሰዓቱኒ ወድዓ መስየ።
ጊዜው ፈጽሞ መሽቷል
፴፮፡ ሠዓር ሰብአ ይሑሩ ውስተ አዕፃዳት ወይሣየጡ ሎሙ ሲሳየ። ሉቃ ፱፥፲፪።
፴፮፡ ወደ መንደር ሄደው ምግባቸውን ይገዙ ዘንድ ሕዝቡን አሰናብታቸው አሉ።
(ሐተታ) ወምሴተ ከዊኖ እንደ ማቴዎስ ወእምድኅረ ብዙኅ ሰዓት እንደ ማርቆስ። ወተቈልቈለ ፀሐይ እንደ ሉቃስ፤ መገናኛ ዮሐንስ በተገናኝ ሲመሸ ማለት ነው ፍትሖሙ ማቴዎስ። ሠዓር ሰብአ ማርቆስፈንዎሙ ሉቃስ መገናኛ ዮሐንስ በተገናኝ አሰናብት አሉት።
፴፯፡ እስመ አልቦሙ ዘይበልዑ።
፴፯፡ የሚበሉት የላቸውምና።
ወአውሥአ ወይቤሎሙ ሀብዎሙ አንትሙ ዘይበልዑ።
እናንተም የሚበሉትን ስጧቸው አላቸው።
ወይቤልዎ አርዳኢሁ ንሑርኑ ወንሣየጥ በ፪፻ ዲናር ኅብስተ
በሁለት ድሪም እንጀራ እንገዛ ዘንድ እንሂድን አሉት፤
፴፰፡ ወይቤሎሙ ሑሩ ወርእዩ ሚመጠን ኃባውዝ ብክሙ።
፴፰፡ ምን ያህል እንጀራ እንዳለ ሄዳችሁ እዩ አላቸው።
ወርእዮሙ ይቤልዎ ኃምስ ኅብስት ወ፪ቲ ዓሣት።
አይተው አምስት እንጀራ ሁለት ዓሣም አለ አሉት።
፴፱፡ ወአዘዞሙ ለኵሎሙ ያርፍቅዎሙ በበምርፋቃቲሆሙ ዲበ ሐመልማለ ሣዕር። ዮሐ ፮፥፲።
፴፱፡ በለመለመ ሣር ላይ በየመቀመጫቸው ሁሉንም ያስቀምጧቸው ዘንድ አዘዛቸው።
፵፡ ወረፈቁ በበምርፋቃቲሆሙ።
፵፡ ተከፍለው ተከፍለው ተቀመጡ
በበ፻ት።
መቶ መቶው
ወበበ፶።
አምሳ አምሳው።
አንድም መቶ መቶውን በአምሳ ሰደቃ፤ አምሳ አምሳውን በመቶ ሰደቃ።
፵፩፡ ወነሥኦን ለ፭ ኅብስት ወለክልኤቲ ዓሣት ወነጸረ ሰማየ።
፵፩፡ አምስቱን እንጀራ ሁለቱንም ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አየ።
ወባረከ።
ባረከም።
ወፈተተ ኅብስተ ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ ያቅርቡ ሎሙ።
ኅብስቱን ቈርሶ ያቀርቡላቸው ዘንድ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤
ወከፈሎሙ ለኵሎሙ እም፪ቲ ዓሣትኒ።
ሁለቱንም ዓሣ ለሁሉ ከፈለ።
፵፪፡ ወበልዑ ኵሎሙ ወጸግቡ።
፵፪፡ ሁሉም በልተው ጸገቡ።
፵፫፡ ወአግኃሡ ዘተርፈ ፍተታተ ፲ ወ፪ተ መሳይምተ፣
፵፫፡ የተረፈውንም ቁራሽ አሥራ ሁለት መሶብ አነሱ።
ወእምዓሣሁኒ
ዓሣውም።
፵፬፡ ወእለሰ በልዕዎ ለውእቱ ኅብስት ዕደው ፶፻ት።
፵፬፡ ያን እንጀራ የበሉት ሰዎች ግን ወንዶቹ አምስት ሽህ ናቸው።

ዘከመ ሖረ ዲበ ማይ፤

፵፭፡ ወአገበሮሙ ሶቤሃ ለአርዳኢሁ ይዕርጉ ሐመረ ወይቅድምዎ ማዕዶተ ቤተ ሳይዳ
፵፭፡ ወደ መርከብ ገብተው ወደ ቤተ ሳይዳ ወደ ማዶ ይቀድሙት ዘንድ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ግድ አላቸው።
እስከ ሶበ ይሥዕሮሙ ለሕዝብ።
ሕዝቡን እስኪያሰናብት ድረስ
ወእምድኅረ ፈነዎሙ ሖረ ወኃለፈ እምህየ።
አሰናብቷቸው ከዚያ ወጣ።
ወዓርገ ደብረ ከመ ይጸሊ።
ሊጸልይም ወደ ተራራ ወጣ።
፵፮፡ ወመስዮ ብሔር ሀለወት ሐመር ማእከለ ባሕር።
፵፮፡ በመሸም ጊዜ መርከቢቱ ከባሕር መካከል ነበረች፤
ወውእቱሰ ባሕቲቱ ሀሎ ውስተ ምድር።
እሱ ግን ብቻውን በምድር ነበር፤
፵፯፡ ወርእዮሙ እንዘ የሐውሩ ወጥቀ ይትመነደቡ።
፵፯፡ እጅግም እየተጨነቁ ሲሄዱ አያቸው።
ወየሐምሞሙ ነፋስ፤
ነፋስም ያስጨንቃቸው ነበር።
እስመ እምገጾሙ ውእቱ።
ከወደፊታቸው ነውና።
፵፰፡ ወበራብዕት ሰዓተ ሌሊት መጽአ ኀቤሆሙ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ የሐውር ዲበ ባሕር። ማቴ ፲፬፥፳
፵፰፡ በአራተኛው ሰዓተ ሌሊት ጌታ በባሕር ላይ እየሄደ መጣ።
ወፈቀደ ይትዓደዎሙ
ሊያልፋቸውም ወደደ፤
፵፱፡ ወሶበ ርእይዎ የሐውር ዲበ ባሕር መሰሎሙ ምትሐተ።
፵፱፡ በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሐት መሰላቸው።
፶፡ ወኵሎሙ ርእይዎ ወደንገፁ።
፶፡ ሁሉም አይተው ደነገጡ።
ወአውየው።
ጮሁም።
ወነበቦሙ ሶቤሃ።
ያን ጊዜም ተናገራቸው።
ወይቤሎሙ ተአመኑ ከመ አነ ውእቱ።
እኔ እንደሆንኩ እመኑ ኣላቸው፤
ወኢትፍርሁ፤
አትፍሩ።
፶፩፡ ወዓርገ ኀቤሆሙ ውስተ ሐመር።
፶፩፡ ወደ መርከብ ወደሳቸው ወጣ።
ወሀደገ ነፋሰ።
ነፋስም ጸጥ አለ።
ወፈድፋደ ተደሙ፣
ፈጽመው ተደነቁ።
ወአንከርዎ፣
አደነቁት
፶፪፡ ወአመሂ ኅብስት ኢለበውዎ።
፶፪፡ በእንጀራው ጊዜ አላስተዋሉም ነበር።
ስመ ጽሉል ልቦሙ።
ልቡናቸው ተሸፍኑዋልና።

ዘከመ ገብረ መንክራተ በጌንሴሬጥ በገሚሠ ጽንፈ ልብስ።

፶፫፡ ወሶበ አደዉ ወበጽሑ ምድረ ጌንሴሬጥ። ሜቴ ፴፥፴፬።
፶፫፡ ተሻግረውም ከጌንሴሬጥ ምድር በደረሱ ጊዜ።
አርሰዩ ህየ
ከዚያ መርከባቸውን አስጠጉ።
፶፬፡ ወወጺኦሙ እምሐመር አእመርዎ ሶቤሃ ሰብአ ይእቲ ሀገ
፶፬፡ ከመርከቡም በወጡ ጊዜ ያንጊዜ የዚያ አገርዎች አወቁት።
፶፭፡ ወሮፁ ውስተ ኵሉ በሐውርት ወአምጽኡ ድውያነ በአራታት
፶፭፡ ወደየሀገሩ ሮጡ ድውያንንም በአልጋ አመጡ።
ወይወስዱ ኀበ ሰምዑ ከመ ሀሎ ውእቱ ህየ።
እሱ ያለበትን ወደሰሙበት ይወስዷቸዋል።
፶፮፡ ወውስተ አኅጕር ወአዕፃዳት ኀበ ቦአ ውስተ ምሥያጣት ያነብርዎሙ ለድውያን።
፶፮፡ ከገባበት ቦታና አገር ድውያንን ከአደባባዩ ያኖሯቸው ነበር
ወአስተብቊዕዎ ከመ ይግሥሡ ጽንፈ ልብሱ።
የልብሱንም ጫፍ ይይዙ ዘንድ ማለዱት።
ወኵሎሙ እለ ገሠሥዎ የሐይዉ
የያዙትም ሁሉ ይድኑ ነበር፤

No comments:

Post a Comment