Friday, August 16, 2019

የማርቆስ ወንጌል-------ምዕራፍ ፬።


በእንተ ምሳሌ ዘራኢ

፩፡ ወአኀዘ ካዕበ ይምሐሮሙ ለአሕዛብ እንተ መንገለ ባሕር። ማቴ ፲፫፥፩። ሉቃ ፰፥፬።
፩፡ ዳግመኛ በባሕር አጠገብ ያስተምራቸው ጀመር።
ወተጋብኡ ኀቤሁ ብዙኃን ሰብእ እስከ ሶበ የዓርግ ውስተ ሐመር ወይነብር።
ከመርከብ ወጥቶ እስኪቀመጥ ብዙ ሰዎች ወደሱ ተሰበሰቡ።
ወኵሉ ሰብእ ውስተ ሐይቅ ይቀውሙ።
ሕዝቡ ሁሉ ከወደቡ ተቀምጠው ነበር።
፪፡ ወመሐሮሙ ወመሰለ ሎሙ ብዙኃ።
፪፡ ብዙ መስሎ አስተማራቸው።
፫፡ ወይቤሎሙ እንዘ ይሜህሮሙ ስምዑ።
፫፡ ሲያስተምራቸውም ስሙ አላቸው።
ወፈረ ይዝራእ ዘይዘርእ
የሚዘራ ሊዘራ ወጣ።
፬፡ ወእንዘ ይዘርእ ቦ ዘወድቀ ውስተ ፍኖት።
፬፡ ሲዘራ ከመንገድ የወደቀ ዘር አለ፤
ወመጽኡ አዕዋፍ ወበልዕዎ
አዕዋፍም መጥተው የበሉት።
፭፡ ወቦ ዘወድቀ ዲበ ኰኵሕ ኀበ አልቦ መሬት ብዙኅ።
፭፡ ብዙ መሬት ከሌለበት ጭንጫ የወደቀ።
ወፍጡነ በቈለ።
ፈጥኖም የበቀለ ዘር አለ፣
እስመ አልቦ ዕመቅ ለመሬቱ
ለመሬቱ ጥልቅነት የለውምና
፮፡ ወሠሪቆ ፀሐይ እውዓዮ።
፮፡ ፀሐይ በወጣም ጊዜ ደረቀ።
እስመ ኢኮነ ዕሙቀ መሬቱ
መሬቱ ጥልቅ አይደለምና።
ወአልቦ ሥርው።
ሥር የለውምና።
የብሰ።
ደረቀ።
፯፡ ወቦ ዘወድቀ ውስተ ሦክ ወሐነቆ ሦክ ኢፈረየ
፯፡ ከእሾህ ውሥጥ ወድቆ እሾህ አንቆት ያላፈራም ዘር አለ።
፰፡ ወቦ ዘወድቀ ውስተ ምድር ሠናይት።
፰፡ ከመልካም ምድር የወደቀ።
ወበቈለ።
የበቀለ።
ወልሕቀ።
ያደገ።
ወፈረየ።
ያፈራ።
ወወሀበ ፍሬ።
ፍሬውን ያቀረጠ ዘር አለ።
ቦ ዘ፴።
ሠላሳ ያፈራ አለ፤
ወቦ ዘ፷።
ስሳም ያፈራ አለ።
ወቦ ዘ፻።
መቶም ያፈራ አለ።
፱፡ ወይቤሎሙ ዘቦ ዕዝን ሰሚዓ ለይስማዕ።
፱፡ ጆሮ ያለው ይስማ አላቸው።
፲፡ ወሶበ ተባሕተወ ተስእልዎ እለ ኮኑ ምስሌሁ ምስለ ፲ወ፪ አርዳኢሁ ምሳሌሁ ለዝንቱ ነገር
፲፡ ብቻውንም በሆነ ጊዜ ከእሱም ጋራ የነበሩት ከአሥራ ሁለቱ ጋራ ምሳሌውን ጠየቁት።
፲፩፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለክሙ ተውህበ ታእምሩ ምሥጢራ ለመንግሥተ እግዚአብሔር።
፲፩፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ለእናንተ ተሰጥቷችኋልና።
ወለእለ አፍአሰ በምሳሌ ይከውኖሙ ኵሉ።
በውጭ ላሉ ግን ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።
፲፪፡ ወርእየ ይርአዩ ወኢርእዩ። ኢሳ ፮፥፱። ማቴ ፲፫፥፲፬። ዮሐ ፲፪፥፵። ግብ ፳፰፥፳፮። ሮሜ ፲፬፥፰።
፲፪፡ ማየትን አይተው እንዳይመለከቱ።
ወለሰሚዓ ይሰምዑ ወኢይሌብዉ።
መስማትም ሰምተው እንዳያስተውሉ።
ከመ ኢይነስሑ።
እንዳይመለሱ።
ወኢይሣሃሎሙ
ይቅር እንዳይላቸው።
ወኢይትኃደግ ሎሙ ኃጢአቶሙ።
ኃጢአታቸውም እንዳይሠረይላቸው።
፲፫፡ ወይቤሎሙ ኢተአምሩኑ ዛተ ምሳሌ።
፲፫፡ ይህን ምሳሌ አታውቁምን።
እፎ እንከ ተአምሩ ኵሎ አምሳለ።
ምሳሌውን ሁሉ እንደምን ታውቃላችሁ ማለት ይህን ያታውቁ ሌላውን እንደምን ታውቃላችሁ ይህን ያታውቁ ሌላውን ታውቁን አላቸው።
፲፬፡ ዘይዘርእሰ ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ።
፲፬፡ ዘሪው ቃለ እግዚአብሔር ነው።
፲፭፡ ወእሉ እሙንቱ እለ ውስተ ፍኖት ኀበ ተዘርአ ቃል እም ከመ ሰምዑ ቃለ ይመጽእ ሰይጣን ሶቤሃ ወይነሥእ እምልቦሙ ቃለ ተዘርዓ።
፲፭፡ በመንገድም የተመሰሉ ቃል የሚዘራበት የተባሉ ከሰሙ በኋላ ሰይጣን ፈጥኖ መጥቶ የተዘራውን ቃል ከልባቸው የሚወስድባቸው ናቸው።
፲፮፡ ወእሉ ካዕበ እሙንቱ ዘውስተ ኰኵሕ ተዘርኡ እለ ይሰምዑ ቃለ ወይትዌከፍዎ ሶቤሃ በፍሥሐ።
፲፮፡ ዳግመኛም በጭንጫ የተዘሩትን ቃል ሰምተው ለጊዜው ደስ ብሏቸው የሚቀበሉት ናቸው።
፲፯፡ ወአልቦ ሥርው።
፲፯፡ ሥር ግን የላቸውም።
ወጊዜሃ ዳዕሙ እሙንቱ።
ለጊዜው ናቸው እንጂ።
ወእምከመሰ ኮነ ምንዳቤ ወስደት በእንተዝ ቃል የዓልዉ ሶቤሃ።
ስለዚህ ነገር ስደትና መከራ የሆነ እንደሆነ ግን ፈጥነው ይክዳሉ።
፲፰፡ ወእሉ እሙንቱ እለ ውስተ ሦክ ተዘርኡ እለ ይሰምዕዎ ለቃል።
፲፱፡ ወሕሊና ዝንቱ ዓለም ወፍትወተ ብዕል ወባዕዳንኒ ኵሉ ፍትወት ይበውዕዎ ወየሐንቅዎ ለቃል። ፩፡ጢሞ ፮፥፲፯።
፲፰፡ በሾህ የተዘሩ ቃልን ሰምተው ብልጥግና መውደድና።
፲፱፡ የዚህ ዓለም አሳብ ሌላውም መመኘት ሁሉ መጽቶ ነገሩን የሚያንቀው ነው።
ወኢይፈሪ።
አያፈራም።
፳፡ ወእሉ እሙንቱ እለ ውስተ ምድር ሠናይት ተዘርኡ እለ ይሰምዑ ቃለ ወይትዌከፍዎ
፳፡ በመልካም ምድር የዘሩት ግን ቃልን ሰምተው የሚቀበሉት
ወይፈርዩ
የሚያፈሩ
፩ዱ ፴።
አንዱ ሠላሳ
ወ፩ዱ ፷።
አንዱ ስሳ።
ወ፩ዱ ፻።
አንዱ መቶ።
፳፩፡ ወይቤሎሙ ቦኑ ዘየሐቱ ማኅቶተ ወያነብራ ታሕተ ከፈር። ማቴ ፭፥፲፭። ሉቃ ፰፥፲፮።
፳፩፡ እንቅብ ቅርጫት ሊደፉባት ፋና የሚያበራ የለም። እንደዚህም ሁሉ ላይተረጕም የሚመስል የለም።
አላ ያነብርዋ ዲበ ተቅዋማ።
ከመቅረዝ ላይ ሊያኖሩት ነው እንጂ ሊተረጕም ነው እንጂ።
፳፪፡ ወአልቦ ኅቡዕ ዘኢይትከበት። ማቴ ፮፥፪። ሉቃ ፮፥፴፰።
፳፪፡ የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፤
ወአልቦ ክዱን ዘኢይትከሠት።
የማይገለጥ የተሸፈነ የለምና
፳፫፡ ወዘቦ ዕዝን ሰሚዓ ለይስማዕ
፳፫፡ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።
፳፬፡ ወይቤሎሙ ለብዉ ዘትሰምዑ። ማቴ ፯፥፪። ሉቃ ፮፥፴፰።
፳፬፡ የምትሰሙ እናንተ አስተውሉ።
በውእቱ መሥፈርት ዘሰፈርክሙ ይሰፍሩ ለክሙ።
በሰፈራችሁበት መሥፈሪያ ይሰፍሩላችኋል።
ወይዌስኩክሙ።
ይጨምሩላችኋልም እንደ አእምሯችሁ ሕፀፅ መጠን እንዲመስሉባችሁ ዕወቁ አላቸው።
፳፭፡ እስመ ለዘቦ ይሁብዎ።
፳፭፡ ላለው ይሰጡታል።
ወይዌስክዎ። ማቴ ፲፫፥፲፪። ሉቃ ፰፥፲፰። ፲፱፥፳፮።
ይጨምሩለታልና።
ወለዘሰ አልቦ እለሂ ቦ የሐይድዎ።
የሌለውን ግን ያለውን ቅሉ ይወስዱበታል።

በእንተ ዘርዕ ወማዕረር

፳፮፡ አኮኑ ከመዝ ርትዕት ይእቲ መንግሥተ ሰማያት ከመ ብእሲ ዘይዘርእ ሠናየ ዘርአ ውስተ
፳፯፡ ገራህቱ ወነዊሞ ይትነሣእ መዓልተ ወሌሊተ ወይዋሕዮ
፳፮፡ ነዊሞ ሌሊተ ይትነሣእ መዓልተ ብለህ ግጠም መንግሥተ ሰማይ ሕገ ወንጌል፤ ሕገ ወንጌል ተስፋ፤ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ።
፳፯፡ በእርሻው መልካም ዘር ዘርቶ ሌሊት ተኝቶ ቀን ተነሥቶ እርሻውን የሚጐበኝ ገበሬን ትመስላለች እኮን፤ ትመስል የለምን
(ሐተታ) ጌታ ኑሮ ኑሮ ለበውክሙኑ ማለቱን መናገር ነው።
ወዘርዑ የዓቢ ወይልሕቅ።
ዘሩም በቅሎ ያድጋል።
፳፰፡ ወውእቱሰ የአምር ከመ ባሕቲታ ምድር ትሁብ ፍሬሃ፤
፳፰፡ እሱም ምድር የዘሩባት እንደሆነ ፍሬ እንድታቀርጥ አውቆ ይዘራባታል እኔም የተማራችሁ እንደሆነ ከፍጹምነት እንድትደርሱ አውቄ አስተምራችኋለሁ።
አንድም ውእቱሰ የአምር ከመ ኢትሁብ ምድር ፍሬ፤ ምድር ካልዘሩባት ፍሬ እንዳታቀርጥ አውቆ ይዘራል፤ እኔም ካልተማራችሁ ከፍጹምነት እንዳትደርሱ አውቄ አስተምራችኋለሁ።
አንድም ውእቱሰ ኢየአምር ከመ ትሁብ ወከመ ኢትሁብ ፍሬ ይላል፣ እሱ ታቀርጥም እንደሆነ አታቀርጥም አንደሆነ ሳያውቅ ይዘራል። እኔ ግን የተማራችሁ ያወቃችሁ እንደሆነ ፍጹማን እንድትሆኑ ከፍጹምነት እንድትደርሱ አውቄ አስተምራችኋለሁ።
ቀዳማዊ ሣዕረ፤
መጀመሪያ ሣዕርን ማለት ቡቃያ
ወእምዝ ሰብለ፤
ቀጥሎ ዝርዝር
ወእምሰብል ይመልዕ ፍጹመ ሥርናየ።
በዛላው ስንዴን ይመላል ማለት ጐምር ይሆናል።
፳፱፡ ወሶበ ፈጸመ ፈርየ ይፌኑ ማዕፀደ።
ፈጽሞ ባፈራ ጊዜ ማለት መከር በደረሰ ጊዜ አጫጅ ይልካል።
አንድም ቡቃያ ጥንተ ስብከት፤ ዝርዝር ቂሣርያ፤ ጎምር ደብረ ታቦር፤ ይፌኑ ማዕፀደ ዕለተ ዓርብ።
አንድም ቡቃያ ቂሣርያ፤ ዝርዝር ደብረታቦር፤ ጎምር ዕለተ ዓርብ፤ ይፌኑ ማዕፀደ ትንሣኤ ዕርገት ዕለተ ምጽአት።
አንድም ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ሞት ሠናይት ነው።
እስመ በጽሐ ማዕረር።
መከር ይርሷልና።

በእንተ ኅጠተ ሰናፔ።

፴፡ ወይቤ በምንት አስተማስላ ለመንግሥተ እግዚአብሔር።
፴፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እመስላታለሁ።
ወምንተ ትመስል።
ማንንስ ትመስላለች።
፴፩፡ ትመስል ኅጠተ ሰናፔ እንተ ተዘርዓት ውስተ ምድር። ማቴ ፲፫፥፴፩። ሉቃ ፲፫፥፲፰።
፴፩፡ በምድር የተዘራች የሰናፍጭ ቅንጣትን ትመስላለች።
፴፪፡ ወእምከመ ተዘርዓት ትበቊል፤
፴፪፡ በተዘራችም ጊዜ ትበቅላለች።
ወተዓቢ እምኵሎን አህማላት፤
ከለምለም ሁሉም ትበልጣለች
ወትገብር አዕፁቀ ዓበይተ።
ታላላቅ ጫፎችም ታወጣለች።
እስከ ይክሉ አዕዋፈ ሰማይ አጽልሎ ታሕተ አዕፁቂሃ።
የሰማይ ወፎች ከጽላዋ በታች ማረፍ እስኪቻላቸው።
፴፫፡ ወበዘከመዝ አምሳል ተናገሮሙ ቃሎ በአምጣነ ይክሉ ሰሚዓ።
፴፫፡ መስማት በሚቻላቸው መጠን እንዲህ ባለ ምሳሌ ቃሉን ነገራቸው።
፴፬፡ ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናገሮሙ።
፴፬፡ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም።
ወበባሕቲቶሙ ለአርዳኢሁ ይፌክር ኵሎ።
ለደቀ መዛሙርቱ ግን ለብቻቸው ሁሉን ይተረጕምላቸው ነበር።
፴፭፡ ወይእተ ዕለተ ሶበ መስየ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ንዕዱ ማዕዶተ።
፴፭፡ በዚያም ቀን በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ማዶ እንሂድ አላቸው።
፴፮፡ ወኃደጎሙ ለሕዝብ ወነሥእዎ በሐመር ምስሌሆሙ። ማቴ ፰፥፳፫። ሉቃ ፰፥፳፪-፴፮።
፴፮፡ ሕዝቡን አሰናብቶ በመርከብ ይዘውት ሄዱ።
ወቦ ካልዓትኒ አሕማር ምስሌሆሙ።
ሌሎችም መርከቦች ከእሳቸው ጋራ ነበሩ።
፴፯፡ ወመጽአ ዓውሎ ዓቢይ ነፋስ።
፴፯፡ ታላቅ ዓውሎ ነፋስ መጣ።
ወይሰውጥ ማየ እሞገድ ውስተ ሐመር እስከ ይመልዕ ማየ ውስተ ሐመር።
ውኃው መርከቡን እስኪመላው ድረስ ውኃውን እያፈሰ ከመርከቡ ይጨምረው ነበር።
፴፰፡ ወውእቱሰ መንገለ ከዋላ ሐመር ተተርኢሶ ኖመ።
፴፰፡ እሱ ግን በከበሮ ቤት በኩል ክንዱን ተንተርሶ ተኝቶ ነበር
ወአንቅሕዎ።
ቀሰቀሱት።
ወይቤልዎ ሊቅ ኢየኃዝነከኑ እንዘ ንመውት
መምሕር ሆይ ስንሞት አናሳዝንህም አሉት።
፴፱፡ ወተንሥአ ወገሠፆሙ ለነፋሳት
፴፱፡ ተነሥቶ ነፋሳትን ገሠፃቸው
ወይቤላ ለባሕር ተፈጸሚ ወአርምሚ።
ባሕርን ጸጥ በይ ዝም በይ አላት።
ወጎደገ ነፋስ።
ነፋስ መንፈሱን ተወ።
ወኮነ ዓቢይ ዛኅን።
ታላቅ ጸጥታም ተደረገ።
፵፡ ወይቤሎሙ ምንትኑ ያፈርኃክሙ ኦ ድኩማን።
፵፡ እናንት ደካሞች ምን ያስፈራችኋል
ከመዝኑ አልብክሙ ሃይማኖት
እንዲህ ሃይማኖት የላችሁምን አላቸው
፵፩፡ ወፈርኁ ዓቢየ ፍርኃተ
፵፩፡ ፈጽመው ፈሩ።
ወተበሃሉ በበይናቲሆሙ መኑ እንጋ ውእቱ ዝንቱ ዘይትኤዘዙ ሎቱ ባሕርኒ ወነፋሳትኒ።
ባሕርም ነፋሳትም የሚታዘዙለት ይህ ማነው እንጃ አሉ።

No comments:

Post a Comment