Thursday, August 15, 2019

የማርቆስ ወንጌል --------ምዕራፍ ፪።


ዘከመ ሐይወ መጻጕዕ።

፩፡ ወቦአ ካዕበ ሀገረ ቅፍርናሆም። ማቴ ፱፥፩።
፩፡ ሁለተኛ ወደ ቅፍርናሆም ገባ።
ወእምድኅረ ጕንዱይ መዋዕል ሶበ ሰምዑ ሰብእ ዜናሁ ከመ ሀሎ ውስተ ቤት።
ከቤት እንዳለ ከጥቂት ቀን በኋላ ሰዎች ነገሩን በሰሙ ጊዜ።
፪፡ ተጋብኡ ኀቤሁ ብዙኃን ሕዝብ እስከ ኢያገምሮሙ መካን።
፪፡ ቦታ እስኪጠባቸው ብዙ ሰዎች ወደሱ ተሰበሰቡ።
ወኢኀበ ኆኅት።
በደጅም ቢሆን።
ወኮነ ይነግሮሙ ቃሎ ለእለ መጽኡ ኀቤሁ።
ወደሱ ለመጡ ነገርን ይነግራቸው ነበር ማለት ወንጌልን ያስተምራቸው ነበር።
አንድም ቃሉ ይላል አካላዊ ቃል ያስተምራቸው ነበር።
፫፡ ወአምጽኡ ኀቤሁ ድውየ መጻጕዓ እንዘ ይፀውርዎ በዓራት አርባዕቱ እደው። ሉቃ ፭፥፲፰።
፫፡ አራት ሰዎች ባልጋ ተሸክመው ደዌ የጸናበት ሰው አመጡለት።
፬፡ ወሶበ ስዕኑ አብዖቶ ኀቤሁ እስመ ጽፉቅ ሰብእ ኀበ ሀሎ እግዚእ ኢየሱስ።
፬፡ ጌታ ካለበት ቦታ ብዙ ሰው ነበርና ወደ ጌታ ማቅረብ በተሳናቸው ጊዜ ወጽፉቅ በዋዔ ቤታ እንዲል።
ዓርጉ ናህሰ ወነሠቱ ጠፈረ ቤት ወአውረድዎ ምስለ አራቱ ዘዲቤሁ ይሰክብ ውእቱ መፃጕዕ።
ከሰገነቱ ወጥተው ማገሩን አፍርሰው አስፋፍተው ድውዩን ከነአልጋው አገቡት።
አንድም ቤተ ምሕጋይ ቤተ ምክራም አላቸው። በበጋ የሚያነሱት በክረምት የሚደፉት አለ ያን አንስተው አወረዱት።
፭፡ ወርእዮ እግዚእ ኢየሱስ ሃይማኖቶሙ ይቤሎ ለውእቱ መፃጕዕ ወልድየ ተኃድገ ለከ ኃጢአትከ።
፭፡ ጌታ ሃይማኖታቸውን አይቶ ያን ድውይ ኃጢአትህ ተሠርዮልሐል አለው።
፮፡ ወሀለዉ ህየ ጸሐፍት ይነብሩ። ኢዮ ፲፬፥፫። ኢሳ ፵፫፥፴፭።
፮፡ ጸሐፍት ከዚያ ተቀምጠው ነበር።
፯፡ ወሀለዩ በልቦሙ ወይቤሉ ምንትኑ ዝ ዘከመዝ ጽርፈተ ይነብብ፤
፯፡ በልባቸው አስበው ይህ እንዲህ ያለ ስድብ ለምን ይናገራል፤
መኑ ይክል ኃዲገ ኃጢአት ዘእንበለ ፩ እግዚአብሔር፣
ያለአንድ እግዚአብሔርስ ኃጢአት ማስተሥረይ የሚቻለው ማነው አሉ
፰፡ ወአእመሮሙ እግዚእ ኢየሱስ በመንፈሱ ከመ ከመዝ ይሔልዩ ወይቤሎሙ ለምንት ከመዝ ትሔልዩ እኵየ በልብክሙ፤
፰፡ ጌታም እንዲህ እንዲያስቡ በመንፈሱ አውቆ ለምን እንዲህ ክፉን ታስባላችሁ።
፱፡ ምንት ይቀልል እምብሂሎቱ ለዝ መፃጕዕ ተኃድገ ለከ ኃጢአትከ ወእምብሂለ ተንሥእ ወንሣእ አራተከ ወሑር በእገሪከ
፱፡ ይህን ድውይ ኃጢአትህ ተሠረየልህ ከማለትና ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል አላቸው።
፲፡ ከመ ታእምሩ ከመ ብውህ ሎቱ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር።
፲፡ በምድር ላይ ኃጢአት ያስተሠርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው ልታውቁ።
፲፩፡ ወካዕበ ይቤሎ ለውእቱ ድውይ ለከ እብለከ ተንሥእ ወንሣእ አራተከ ውእቱ ቤተከ።
፲፩፡ ዳግመኛ ያን ድውይ ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ እልሃለሁ አለው።
፲፪፡ ወተንሥአ ሶቤሃ ወነሥአ አራቶ ወወፅአ በቅድመ ኵሎሙ ሰብእ።
፲፪፡ ያን ጊዜውንም ተነሥቶ አልጋውን ተሸክሞ በሰው ሁሉ ፊት ወጣ።
ወአንክሩ ኵሎሙ ሕዝብ ወአእኰትዎ ለእግዚአብሔር።
ሰዎች ሁሉ አድንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
ወይቤሉ ኢርኢነ ግሙራ ዘከመዝ።
ከቶ እንዲህ ያለ አላየንም አሉ

ዘከመ ተጸውአ ሌዊ።

፲፫፡ ወእምዝ ሖረ እግዚእ ኢየሱስ ካዕበ መንገለ ጽንፈ ባሕር።
፲፫፡ ከዚህ በኋላ ጌታ ወደ ባሕር ዳር ወጣ።
ወሖሩ ኀቤሁ ኵሉ ሕዝብ።
ሕዝቡ ሁሉ ወደሱ ሄዱ።
ወመሐሮሙ።
አስተማራቸው።
፲፬፡ ወኃሊፎ እምህየ ርእዮ ለሌዊ መጸብሐዊ ወልደ እልፍዮስ እንዘ ይነብር ኀበ ምጽባሕ። ማቴ ፱፥፱። ሉቃ ፭፥፳፯።
፲፬፡ ከዚያም አልፎ ሲሄድ የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን ከሚያስገብርበት ቦታ ተቀምጦ አየው።
(ሐተታ) ማቴዎስን ወልደ ዲቊ ይለዋል ከዚህ ወልደ እልፍዮስ አለው እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ለአንድ ሰው ሁለት ስም አለውና።
አንድም አንዱ የአባቱ አንዱ የአያቱ።
ወይቤሎ ነዓ ትልወኒ።
ተከተለኝ አለው፤
ወተንሢኦ ተለዎ
ተነሥቶ ተከተለው።
፲፭፡ ወእንዘ ይመስሕ ውስተ ቤቱ እግዚእ ኢየሱስ።
፲፭፡ ከዚህ በኋላ ጌታ በቤቱ ተቀምጦ ሲበላ።
ሀለዉ ምስሌሁ ብዙኃን ኃጥአን ወመጸብሐን ዘረፈቁ ምስለ እግዚእ ወአርዳኢሁኒ።
ብዙ ቀራጮችና ኃጥአን ከጌታና ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተቀምጠው የበሉ ነበሩ።
ወብዙኃን እሙንቱ እለ ይተልውዎ
የተከተሉትም ብዙ ነበሩ።
ወኮኑ ይተልውዎ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን።
ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ተከትለውት ነበር
፲፮፡ ወርእዮሙ ከመ ይበልዕ ምስለ ኃጥአን ወመጸብሐን።
፲፮፡ ከኃጥአንና ከመጸብሐን ጋራ ሲበላ ባዩት ጊዜ፤
ይቤልዎሙ ለአርዳኢሁ ለምንት ይበልዕ ወይሰቲ ሊቀክሙ ምስለ ኃጥአን ወመጸብሐን፤
ደቀ መዛሙርቱን መምሕራችሁ ከመጸብሐን ጋራ ለምን ይበላል አሏቸው። ማቴዎስ አርድእተ ዮሐንስ ጠየቁት ይላል ከዚህ ማርቆስ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጠየቁት አለ እንደምን ነው አይጣላም ቢሉ አይጣላም ነገር እንደ ማቴዎስ ነው። ፈሪሳውያን አርድእተ ዮሐንስን ጠይቁልን ብለዋቸው ጠይቀውታል። ማርቆስ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጠየቁት ማለቱ ኋላ ተከትለው ሂደው ጠይቀውታል አማላጅ የሰደደ ሰው አብሮ ተከትሎ ሂዶ እንዲናገር።
አንድም ነገር እንደ ማርቆስ ነው ፈሪሳውያን ሂደው ጠይቀውታል ባይመልስላቸው ለእኛስ አልመለሰልንም እናንተ ሂዳችሁ ጠይቁት ብለዋቸው አርድእተ ዮሐንስ ሂደው ጠይቀውታል እንደ ማቴዎስ ይህን ተካፍለው ጽፈዋል።
፲፯፡ ወሰሚዖ እግዚእ ኢየሱስ ይቤሎሙ ሕሙማን ይፈቅድዎ ለዓቃቤ ሥራይ ወአኮ ጥዑያን። ፩፡ጢሞ ፩፥፲፭።
፲፯፡ ጌታም ይህን ሰምቶ ባለመድኃኒትን ድውያን ይሹታል እንጂ ጤነኞች አይሹትም።
ወኃጥአነ እጸውዕ መጻእኩ ወአኮ ጻድቃነ።
ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ልጠራ መጥቻለሁ አላቸው።
በእንተ ጾም ዘክርስቲያን።
፲፰፡ አርዳኢሁሰ ለዮሐንስ ወእለሂ ፈሪሳውያን ኮኑ ይጸውሙ።
፲፰፡ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና የፈሪሳውያን ወገኖች ይጦሙ ነበርና።
ወመጽኡ ወይቤልዎ በእፎ አርዳኢሁ ለዮሐንስ ወአርዳኢሆሙ ለፈሪሳውያን ይጸውሙ።
የፈሪሳውያንና የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለምን ይጦማሉ።
ወአርዳኢከ ኢይጸውሙ።
ደቀ መዛሙርትህ ግን አይጦሙም አሉት።
፲፱፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ይክሉኑ ደቂቁ ለመርዓዊ ጸዊመ አምጣነ ሀሎ መርዓዊ ምስሌሆሙ።
፲፱፡ ጌታም የሰርግ ልጆች ከሙሽራ ጋራ ሳሉ መጾም ይቻላቸዋልን አላቸው።
፳፡ ወባሕቱ ይመጽእ መዋዕል አመ ይነሥእዎ ለመርዓዊ እምኔሆሙ። ማቴ ፱፥፲፭። ሉቃ ፭፥፴፭።
፳፡ ነገር ግን ሙሽራው ከእሳቸው የሚለይበት ዘመን ይመጣል።
ወአሜሃ ይጸውሙ።
ያን ጊዜ ይጦማሉ።
፳፩፡ ወአልቦ ዘይጠቅብ ግምደ ደርግሃ ውስተ ስጠተ ልብስ ብሉይ።
፳፩፡ ባረጀ ልብስ ቀዳዳ አዲስ እራፊ የሚሰፋ የለም።
ወእመ አኮሰ ያነቅዖ ጥቅበቱ ሐዲስ ለብሉይ።
ያለዚያ ግን ማለት ቢሰፉት ግን አዲሱ እራፊ አሮጌውን ይቀደዋል።
ወየዓብዮ ለስጠቱ።
ቀዳዳውን ያሰፋዋል።
፳፪፡ ወአልቦ ዘይወዲ ወይነ ሐዲሰ ውስተ ዝቅ ብሉይ።
፳፪፡ ጉሽ ጠጅ ባረጀ ራዋት የሚያኖር የለም።
እስመ ያነቅዖ ወይን ሐዲስ ለዝቅ ብሉይ።
ጉሽ ጠጅ ያረጀውን ረዋት ይቀደዋልና።
ወወይኑሂ ይትከዓው።
ጠጁም ይፈሳልና።
ወዝቁሂ ይትኃጐል
ረዋቱም ይጠፋልና።
ወባሕቱ ለወይንሰ ሐዲስ ውስተ ዝቅ ሐዲስ ይወድይዎ
አዲሱን ጠጅ ግን በአዲስ ረዋት ይሾሙታል። ማቴ ፲፪፥፩። ሉቃ ፲፯።
ወይትዓቀቡ በበይናቲሆሙ።
እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ።
በእንተ ሰዊተ ሥርናይ ወሰንበት።
፳፫፡ ወእምዝ ወፈረ እግዚእ ኢየሱስ በሰንበት ማዕከለ ገራውህ።
፳፫፡ ከዚህ በኋላ ጌታ ቅዳሜ በእርሻ መካከል ሄደ።
ወአርዳኢሁኒ ምስሌሁ።
ደቀ መዛሙርቱም ከእሱ ጋራ ነበሩ
ወአኀዙ ይምሐዉ ሰዊተ ወይበልዑ
እሸት እያሹ ይበሉ ጀመር።
ወይጺሑ ሎቱ ፍኖተ።
የተቃወሰውንም ያቃኑለት ጀመረ።
ይገብሩ አርዳኢከ ዘኢይከውን ገቢረ በሰንበት።
፳፬፡ ወይቤልዎ ፈሪሳውያን ርኢ ዘይገብሩ አርዳኢከ ዘኢይከውን ገቢረ በሰንበት።
፳፬፡ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትህ ቅዳሜ ሊሠሩት የማይገባ ሥራ ሲሠሩ አስተውል አሉት።
፳፭፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ግሙራኢ ያንበብክሙኑ ዘገብረ ዳዊት አመ ርኅበ። ፩፡ነገ ፳፥፪።
፳፭፡ ዳዊት በተራበ ጊዜ ያደረገውን ከቶ አልተመለከታችሁም።
ወውእቱኒ።
እሱም።
ወእለ ምስሌሁ።
ከሱም ጋራ ያሉ
፳፮፡ ዘከመ ቦአ ቤተ እግዚአብሔር እንዘ አብያታር ሊቀ ካህናት ወበልዐ ኅብስተ መሥዋዕት ዘኢይደልዎ ለበሊዕ ዘእንበለ ለካህናት ለባሕቲቶሙ ወወሀቦሙ ለእለ ምስሌሁ ወበልዑ። ዘሌ ፳፥፲።
፳፮፡ አብያታር ሊቀ ካህናት ሁኖ ሳለ ከቤተ እግዚአብሔር ገብቶ ለካህናት ብቻ ይገባቸዋል እንጂ ሊበላው የማይገባውን መሥዋዕቱን በልቶ ከሱም ጋራ ላሉ ሰጥቷቸው እንደበሉ ዳዊት ያደረገውን ከቶ አልተመለከታችሁምን።
(ሐተታ) ሊቀ ካህናቱ አቤሜሌክ አይደለም ቢሉ ምሉና ዱግ ሁነው ተሹመው ነበር፤
፳፯፡ ወይቤሎሙ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት ወአኮ ሰብእ በእንተ ሰንበት።
፳፯፡ ሰንበት ለሰው ተፈጥራለች እንጂ ሰው ስለሰንበት አልተፈጠረም አላቸው።
፳፰፡ ወወልደ እጓለ እመሕያው ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት።
፳፰፡ የሰንበት ጌታዋ የሰው ልጅ ነው።

No comments:

Post a Comment