፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የረቦ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደጀን ወረዳ ቤተክህነት
ሥር የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ከደጀን ከተማ በምሥራቅ አቅጣጫ ሃያ ሰባት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወደቦታው
ለመሄድ ለሚፈልጉ ሰዎች ከደጀን ከተማ ተነሥተው ጉባያ በሚለው መኪና ገብተው ቦታውን ያለምንም ችግር ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንደአሁኑ
መኪና ሳይኖር ግን ከሦስት ሰዓት እልህ አስጨራሽ የእግር ጉዞ በኋላ ነበር ቦታው የሚገኘው፡፡ ቦታው ጥንታዊ ቦታ መሆኑ የታወቀ
ነው፡፡ ሆኖም ግን መዛግብትን ማገላበጥ አባቶችንም መጠየቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ ስለሆነ የተመሰረተበትን ቀን እንዴት እንደተመሠረተ
ሙሉ ታሪኩን መናገር አልችልም፡፡ እኔም በቦታው ተወልጀ ያደግሁ መሆኑን እንጅ ጥንታዊነቱን ጠይቄም ሆነ መዛግብትን አገላብጨ አላውቅም፡፡
ሆኖም ግን መዛግብትን ማገላበጥ አባቶችን መጠየቅ እንደሚኖርብኝ አውቃለሁ፡፡ ከቤተክርስቲያኑ በታች የሚገኘው ዋሻ ጥንታዊ የቤተክርስቲያኑ
መገኛ እንደነበር ይነገራል ሆኖም ግን በመዛግብት እና በአባቶች ማረጋገጫነት መታገዝ ስለሚኖርበት ወደፊት እገልጥላችኋለሁ፡፡