© በመልካሙ በየነ
ታህሳስ 1/2008 ዓ.ም
ደብረማርቆስ፣
ኢትዮጵያ

የኤማሑስ መንገደኞች ሉቃስና ኒቆዲሞስ እየተነጋገሩ ይሄዱ የነበረው ስለኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ
ያለበደሉ፣ ያለኃጢአቱ ለሰው ፍቅር ሲል ለመስቀል ሞት ተላልፎ መሰጠት ስለነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አብሮ መጓዝ ጀመረ፡፡
በጉዞው መካከልም ስለምን እንደሚነጋገሩ ጠየቃቸው ፍቅራቸው እጅግ ብዙ ስለነበር ኢየሱስ ክርስቶስ የሚባለውን አምላክ አይሁድ ተመቅኝተው
እንዴት እንደገደሉት ነገሩት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ፣ ደግ፣ ለድሆች የሚራራ፣ ለበሽተኞች መድኃኒት፣ ለተራቡት
እውነተኛ ምግብ ለተጠሙት ደግሞ እውነተኛ መጠጥ እንደሆነ እነርሱ በጣም የሚወዱት አምላክነቱን የማይጠራጠሩ እንደሆኑ አስረዱት፡፡
ከማን ጋር እንደሚነጋገሩ ባወቁ ኖሮ ዝቅ ብለው ወድቀው በሰገዱለት ነበር ነገር ግን ማን እንደሆነ ስላላወቁ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን
እንዲያምን ሊያስተምሩት ነበር የሞከሩ፡፡ ምንም እንኳ በኋላ አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን የሚያውቁ ቢሆኑም ማለት ነው፡፡
እነዚህ የተቀደሱ የኤማሑስ መንገደኞች አይሁዳውያንን ለማማት ያበቃቸው የክርስቶስ ፍቅር ነው (በእርግጥ ይህ ሐሜት አይደለም ምክንያቱም
አይሁድ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሠሩትን እውነተኛ የግፍ ሥራ ስለነበር የሚነጋገሩ) ስለስሙ በሚነጋገሩት ተጓዦች መካከል አምላክ
ተገኝቶ ባረካቸው፡፡ ሰውና ሰው ሲገናኝ የሰውን ጥፋት ያቅዳል፣የሌላውን ውድቀት ይመኛል፣ ሰውን እንዴት ማጥፋት እንደሚቻል ይወያያል፣
ሰውን በሌለበት በተሳለ ምላስ በሐሜት ይበላል እንጅ በእውነት የክርስቶስ ፍቅር፣ የእመብርሃን ፍቅር፣ የመላእክት ክብር፣ የቤተክርስቲያን
ጉዳይ አገብሮት አንዳች ነገር የሚተነፍስ የሚነጋገር ሰው ከቶ የለም፡፡ እኔ በመኪናም ይሁን በእግሬ ስጓዝ አብረውኝ የሚጓዙ ሰዎችን
ንግግር ማዳመጥ ደስ ይለኛል፡፡ ምክንያቱም ስለምማርበትና ሰውም ስለምመክርበት እኔም ስለምመከርበትና ስለምገሰጽበት ነው፡፡ እናም
ስጓዝ የሰማሁትን ላካፍላችሁ ወደድሁ መልካም ንባብ…
ይቀጥላል፡፡
No comments:
Post a Comment