====================================
✍ላይክ ✍ላይክ ✍ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
facebook.com/melkamubeyeneB
✍ላይክ ✍ላይክ ✍ላይክ
====================================
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s
ተሐድሶ ሁሌም
ለቅሶ
ተሐድሶ በዚህ ዘመን ለተነሡ መናፍቃን መጠሪያ ስም ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችንን
ሥርዓት በማፍረስ እና መሠረቷን ለማናጋት የሚንቀሳቀስ ኃይል ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን የገሐነም ደጆች እንኳ የሚርዱላት በክርስቶስ ደም የተመሠረተች በመሆኗ ከውጭ
የሚወረወረው ቀስትና ከውስጥ ለማፍረስ የሚገፏት ምንም ሊያደርጓት አይችሉም፡፡ እነዚህ መናፍቃን በሚያነሧቸው ርዕሰ ጉዳዮች ቤተክርስቲያናችን
ስለምትረታቸው “ተሐድሶ ሁሌም ለቅሶ” ሆኖባቸዋል፡፡
ስላልሰማህ
ይሆናል
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ ከመድረክ ላይ ወጥቶ በመጀመሪያ ስሙን ቀጥሎም
የሚማርበትን ኮሌጅ ከገለጠ በኋላ ስብከት አይሉት ስድብ መናገር ጀመረ፡፡ “ይህች ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከ 10 ዓመታት በፊት
ወንጌል አልተሰበከባትም ነበር ክብር ምስጋና ይግባው የኔ ጌታ ዛሬ ግን እኔን በፊታችሁ አቁሞ ወንጌልን እንድሰብክ በክብር ሾመኝ፡፡
ይኼውላችሁ እኔን አስነሥቶ የተመረጠውን ሕዝብ በእግዚአብሔር ቃል ያረሰርሳል፡፡ ለዚህ እልልታ አይገባም? እልል በሉ እባካችሁ!
አጨብጭቡ!” እያለ ከስብከቱ ይልቅ የእልልታው ጊዜ በዝቶ እልል የሚሉት ጉሮሯቸው ደረቀ፡፡ ይህን ኑፋቄውን እንደጨረሰ ለመርኀ ግብር
መሪው ቦታውን ለቅቆ ከመድረኩ ወርዶ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ መርሐ ግብር መሪው በጣም አስተዋይና የተማረ ነበርና “ወንድማችን ተሐድሶዎች
የሚያስተምሩትን ትምህርት በግልጥና በሚገባ ስለነገረን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀድሞ በነቢያት
ኋላም በሐዋርያት ትምህርት የጸናች ናት፡፡ ወንድማችን ምናልባት ከ
10 ዓመታት በፊት ያለውን ስላልሰማህ ይሆናል እንጅ እነ አትናቴዎስ፣ እነ ዮሐንስ አፈወርቅ በሐገራችንም እነ አቡነ ተክለ ሐይማት፣
እን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ኧረ ስንቱ! ወንጌልን ዞረው አስተምረዋል፡፡ አያችሁ ወገኖቼ የዘመኑ መናፍቃን ወንጌል የተሰበከ እነርሱ
ከተወለዱ በኋላ ስለሚመስላቸው ከ 10 ዓመታት በፊት ወንጌል የተሰበከ አይመስላቸውም፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ አይነቱን ትምህርት
የሚያስተምሩት” በ ማለት የተሐድሶውን ትምህርት ውድቅ አደረገበት፡፡
ቤተ ክርስቲያንስ
ሄዋን ናት
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ“ያረጀችው ቤተ ክርስቲያን አሮጊቷ ሣራ ወለደች፡፡
እኔን ወለደች፣ እገሌን ወለደች፣ እገሊትን ወለደች” እያለ ተሐድሶ የወለደቻቸውን ይዘረዝራል፡፡ቤተክርስቲያን አሮጌ መባሏ ያበሳጨው
የተዋሕዶ ልጅ ወደ “ሰባኪው”ተጠግቶ “መጽሐፍ ማንበብ ይቀርሃል ሣራ በእርጅናዋ ወራት የወለደችው አንድ ልጅ ይስሐቅን ብቻ እንደነበር
አላወቅህም እንዴ? አሮጊቷ ሣራ እኔን፣ እገሌን፣ እገሊትን ወለደች እያልህ የምትቀባጥር፡፡ ቤተ ክርስቲያንስ አሮጊት ሣራ ሳትሆን
ቀድሞ የነበረች መንታ መንታ የምትወልድ የብዙዎች እናት ሄዋን ናት፡፡፡ የግል ክብርህን ፈልገህ ደግ ይስሐቅን ነኝ ለ ማለት ክብርት ቤተክርስቲያንን ዝቅ ዝቅ ያደረግህበት ይህ ደፋር አንደበት በደሙ በመሠረታት
በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት ስትቆም ምን ይናገር ይሆን?” በ ማለት ብዙ ትምህርት አስተማረው፡፡
ሥርዓቷ ሳይሆን
ሕንጻዋ
አንድ መናፍቅ“ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያረጀች ያፈጀች ናትና
በአዲስ ነገር መታደስ ይገባታል፡፡” እያለ በይፋ ይናገራል፡፡ ይህን የሰሙ አንድ የቤተክርስቲያን ሊቅ መናፍቁን አስጠርተው“የምትለው
ሁሉ ልክ ነው፡፡ መታደስ ያለበት ግን ሥርዓቷ ሳይሆን ሕንጻዋ ስለሆነ የማሳደሻ ገንዘብ አሰባስብ” ሲሉት ያ መናፍቅ“መታደስ የሚገባው
ትምህርቷ ሥርዓቷ ነው እንጅ ሕንጻዋ አይደለም”ይላቸዋል፡፡ሊቁም “በል እንግዲያውስ የራስህን አእምሮ በመልካም ትምህርትና ሥርዓት
አድስና ከዚያ በኋላ ብንገናኝ ይሻላል” ብለው አባረሩት፡፡
እንዘምራለን
ስትናፍቀን
ተሐድሶ መናፍቃን እግዚአብሔርን የሚናፍቁበትና የማይናፍቁበት ቀንና ጊዜ
አላቸው፡፡ ምክንያቱም ሲፈልጉ ዘማሪ ክርስቲያን ሲፈልጉም ታዋቂ ዘፋኝ በመሆን በተደበላለቀና በተመሰቃቀለ ሕይወት ውስጥ ስለሚኖሩ
ነው፡፡ በዝማሬዎቻው ውስጥ የምንሰማው
“ዛሬም የአንተ ነው አዲሱ ቀን
እንዘምራለን
ስትናፍቀን”
የሚል ነው፡፡ በእውነት እግዚአብሔር የማይናፈቅበት ወቅት አለን? በዚያስ
ወቅት መዘመር አስፈላጊ አይደለምን? ዝማሬን የናፍቆት መግለጫ ያደረጉት፡፡ ወገኖቼ ሳናውቅ በተኩላ እየተበላን ስለሆነ መንቃት ያስፈልጋል፡፡
መዶሻ ያልያዘ
ሠራዊት
ተሐድሶ መናፍቃን በስብከታቸው እና በመዝሙራቸው ውስጥ “መዶሻ ያልያዘ
ሠራዊት” የሚለው መሪ ቃላቸው ሆኗል፡፡ በእውነትም መዶሻ ያልያዘ ከንቱ ሰራዊት ነው፡፡መዶሻው ቃለ እግዚአብሔር የሚገኘው ቤተክርስቲያን
ውስጥ ስለሆነበየቦታው ሲዞሩ ይህን ማግኘት ባለመቻላቸው ቃለ እግዚአብሔርን ያልያዘ ሠራዊት ነን ሲሉ “መዶሻ ያልያዘ ሠራዊት” ነን
ይላሉ፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን ያልያዘ ሠራዊት ደግሞ የአጋንንት ስለሆነ ከተዋሕዶ ልጆች ጋር ምንም ሕብረት የለውም፡፡
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን
፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች
አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ
#አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች
እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
© መልካሙ በየነ
መስከረም ፰
/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝