Thursday, September 28, 2017

✍✝ ወልደ አብ የተሰኘው የቅባት መጽሐፍ ተወገዘ✝✍





፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የተወገዘው የቅባቶች መጽሐፍ፡፡
አቡነ ዘካርያስ ወልደ አብን ያወገዙበት መጽሐፍ፡፡
በመጀመሪያ ለዚህ መጽሐፍ መወገዝ ፊርማ የሰጣችሁ የሰበሰባችሁ እህቶች ወንድሞች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ምንም እንኳ ለዛሬው የዚህ መጽሐፍ መወገዝ እንኳ የእኛ ፊርማ ምንም ድርሻ ባይኖረውም ለጥቅምት ሲኖዶስ ግን ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ የሚያደርግ ሥራ ተሠርቷል፡፡
ብጹእ አቡነ ዘካርያስ ወልደ አብን አወገዙ፡፡







ብጹእነታችው አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ለብዙ ዓመታት ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡ ባሳለፍነው ፳፻፱ ዓ.ም ብጹእነታቸው ምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከትን ያገለግሉ በነበረበት ጊዜ ጠፍቶብኛል ያሉትን አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር አሁን እያገለገሉ ካሉበት ከሰሜን አሜሪካ ከምእመናን አሰባስበው መመለሳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የት እንደደደረሰ ምን እንደተሠራበት በማን አካውንት እንደገባ ወዘተ የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ባያውቁትም ማለቴ ነው፡፡
አቡነ ዘካርያስ


ፊርማ የተሰበሰበበት ደብዳቤ፡፡
“ወልደ አብ” የተባለው የቅባቶች የምንፍቅና መጽሐፍ እንዲወገዝልን እኛ የምሥራቅ ጎጃም የተዋሕዶ ልጆች የምእመናንን ፊርማ በማሰባሰብ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ ደረጃውን ጠብቀን አቤቱታችንን እንዳቀረብን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ አቤቱታችሁን ወደ ሊቃውንት ጉባዔ እመራዋለሁ ከማለታቸው በስተቀር አሁን ስለደረሰበት ደረጃ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ወደ ሊቃውንት ጉባዔ ተመርቶ ቢሆን ኖሮ የሊቃውንት ጉባዔው ሰብሳቢ ብጹእ አቡነ እንድርያስ ነገሩን በቸልታ ባላለፉትም ነበር፡፡ ታላቁ ሊቅ አቡነ እንድርያስ ይህን መጽሐፍ ከማውገዝም አልፈው ተገቢውን ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ መልስ ይሰጡ እንደነበርም እተማመናለሁ፡፡ ነገር ግን እስካሁን ድረስ ለሊቃውንቱ ጉባዔ እንዳልደረሰ ይሰማኛል፡፡
ፊርማ የተሰበሰበበት ደብዳቤ፡፡
ፊርማ የተሰበሰበበት ደብዳቤ፡፡
ሆኖም ግን ጉዳዩን በጥልቀት መመርመር የሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዝምታውን የተመለከቱት ብጹእ አቡነ ዘካርያስ ባሉበት ሰሜን አሜሪካ ሆነው ይህን መጽሐፍ አውግዘዋል፡፡ ለምን እና እንዴት አወገዙት የሚለው ጉዳይ ሌላ ምሥጢር ስለመኖር አለመኖሩም ለማረጋገጥ ሞክሬ ነበር፡፡ አቡነ ዘካርያስ ምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከትን በሊቀጳጳስነት ለብዙ ዓመታት መምራታቸውን አስቀድሜ ተናግሬያለሁ፡፡ ከእርሳቸው በኋላ በረከታቸው ይደርብን እና አቡነ ጴጥሮስ ከዚያም አሁን አቡነ ማርቆስ ሐገረ ስብከቱን በሊቀጳጳስነት አገልግለዋል፡፡ ይህ ክህደት መጽሐፍ ደግሞ በብዛት እና በስፋት በይፋ ታትሞ መሸጥ የጀመረው አቡነ ማርቆስ ሐገረ ስብከቱን ከተረከቡት በኋላ ነው፡፡ “ወልደ አብ” የተሰኘው ይክ የክህደት መጽሐፍ መቼ እና የት እንደታተመ መጽሐፉ ውስጥ አልተገለጠም፡፡ አሳታሚውን ብቻ ነው የገለጡት፡፡ ይሁን እንጅ ይህ መጽሐፍ ጉንደወይን እና ደብረ ማርቆስ ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ገዳማት ውስጥ በብዛት እየተሰራጨ እንደሆነ መረጃው አለን፡፡ ይህን መጽሐፍ በይፋ ማሰራጨት የተጀመረው በ፳፻፰ ዓ.ም ነው፡፡ ስለሆነም መጽሐፉ የታተመው በ፳፻፰ ዓ.ም ነው ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ስርጭት ጎን ለጎን “ሚሥጢረ ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ” የሚል ሌላ የክህደት መጽሐፍ በ፳፻፱ ዓ.ም አሳትመዋል፡፡ ይህንን በቤተክርስቲያናችን ላይ እየተቃጣ ያለውን ሴራ ለማክሸፍ በማሰብ ነበር መጻሕፍቱ እንዲወገዙልን ፊርማ አሰባስበን ለቅዱስ ሲኖዶሱ አቤት ያልነው፡፡ ሆኖም ግን እስካሁን ድረስ መልስ አልተገኘም፡፡
ፊርማ የተሰበሰበበት ደብዳቤ፡፡
ፊርማ የተሰበሰበበት ደብዳቤ፡፡

ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና አቡነ ዘካርያስ ይህንን መጽሐፍ ለማውገዛቸው በምክንያትነት የሚጠቀሰው አቡነ ማርቆስ ይህ መጽሐፍ የታተመው እኔ ከመጣሁ በኋላ ሳይሆን ቀድሞ አቡነ ዘካርያስ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ ነው በማለታቸው ነው፡፡ አቡነ ዘካርያስም እኔ በነበርሁበት ጊዜ ሳይሆን ቀድሞ ሱስንዮስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን ነው ብለው ጉዳዩን ለመግፋት ነው፡፡ ለቀጥተኛዋ እምነታችን አስበው ለምእመናንም ድኅነት ተጨንቀው ቢሆን ኖሮ በቅባቶች የታተመው መጽሐፍ ወልደ አብ ብቻ አይደለም ሚሥጢረ ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊም አለ ታዲያ ይህንንስ ለምን አላወገዙትም ብጹእ አባታችን፡፡ ምናልባት መረጃው አልደርስዎ ብሎ ከሆነ ትክክል ነዎት ነገርግን መረጃው ደርስዎት ከሆነ ግን ለምእመናን ድኅነት ተጨንቀው እንዳላደረጉት እረዳለሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን እርስዎን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ ትርጉም ሊሰጠው የሚችል ጉዳይ ነውና ያነሡት፡፡ እርስዎ በግልባጭ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ለፓትርያርኩ  ጽ/ቤትም እንዲሁም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ማሳዎቅዎ ጉዳዩን የግድ እንዲመለከቱት ያደርጋቸዋል ብየ እገምታለሁ፡፡ ቤተክርስቲያናችን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነውና ይህንን ጉዳይ እርስዎም በቅርበት እንዲከታተሉት እንጠይቃለን፡፡ ደብዳቤውን ከመጻፍ ባለፈም ይህን ጉዳይ ሊከታተሉት ይገባል፡፡ ነገር ግን ይህ ጉዳይ እኔን አይመለከትም እኔ በነበርሁበት ዘመን ይህ መጽሐፍ አልታተመም ለማለት ብቻ የጻፉት ደብዳቤ ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ከባድ ፍርድ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም፡፡

ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥቅምት ስብሰባው በጥልቀት አይቶ እንደሚያወግዘው እና ተገቢ ምላሽ እንደሚሰጥበት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ጉዳይ ከምንም ባለመቁጠር ቤተክርስቲያናችንን ለማስደፈር እና ምእመናንን ወደ ምንፍቅና ለሚመሩ ወዮላቸው እዳ አለባቸው፡፡
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
© መልካሙ በየነ
መስከረም ፲፰ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

No comments:

Post a Comment