Friday, September 15, 2017

✍✝ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ ማቴ ፳፬፥፳፬✝✍




====================================
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
====================================

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
ወገኖቼ ዛሬ ላይ ዘመኑ ያለቀበት ቀኑ የመሸበት ጊዜ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ “ዘመኑ ቀርቧልና ንስሐ ግቡ” የሚለውን ዐዋጅ ዛሬም በድጋሜ ቢያውጀው እንዴት መልካም ነበር፡፡ ዳሩ ግን ማን ያስተውል ማን ይሰማና፡፡ ሳናውቅ በስህተት አውቀንም በድፍረት ቃለ እግዚአብሔርን እየተላለፍን እንገኛለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረንን የዘመን ፍጻሜ ምልክቶች አላስተዋልናቸውም፡፡ ብልህ ከሌሎች ሞኝ ከራሱ ይማራል ይላሉ አበው፡፡ ብልህ የሌሎችን ጥፋት አይቶ ራሱን ከጥፋት ይሰውራል ሞኝ ግን ራሱ ይጠፋል፡፡ ዛሬ ብዙ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሠተኞች ነቢያት እንደ አሸን የፈሉበት ጊዜ ነው፡፡ ሥራቸውን ደግሞ በሕብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያኝላቸው ብዙ ስልቶችን ቀይሰው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ ባሕታዊ እገሌ፤ ቀሲስ እገሌ፤ ዲያቆን እገሌ ፓስተር እገሌ ዘማሪ እገሌ ወዘተ ወዘተ በሚሉ ማዕርጎች ራሳቸውን የሸፈኑ ተኩላዎች ናቸው፡፡ ለስሙ ቃለ እግዚአብሔርን ይጠራሉ አጋንንትንም አስወጣንላችሁ አባረርንላችሁ ይላሉ ይህንንም በዘመኑ ማኅበራዊ መገናኛዎች ይለጥፉታል፡፡ ብዙው ሰው ዝናቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ነገ ዱባይ ከነገ ወዲያም አሜሪካ ከዚያ ወዲያም ለንደን ወዘተ በመርኃ ግብር የፈውስ አገልግሎት እንሰጣለን እያሉ የማይጠረቃ ኪሳቸውን በገንዘብ ይሞሉታል፡፡ አመናችሁም አላመናችሁም ዋናው ዓላማቸው ገንዘብ መሰብሰብ እንጅ ምእመናንን መሰብሰብ አይደለም፡፡ ዘመኑ አልቋል መጠንቀቅ ይበጀናል፡፡ ማቴ ፯፥፳-፳፫ ስንመለከት “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጅ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም:: በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል የዚያን ጊዜም:- ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ” ይላል የማይታበለው አምላካዊ ቃል፡፡ ስለዚህ መንቃት ይኖርብናል፡፡ ከዚህ ቃል ውጭ በመሆን ክርስቶስ በበረሃ አለ እዚህ ቦታ አለ እያለ የሚጭበረብር ወንበዴ ስትከተል ዕድሜ ዘመንህ እንዳያበቃ ተጠንቀቅ፡፡


ይህ በቪዲዮው ላይ የምትመለከቱት ነቢይ ነኝ በሚል ካራባቱን አስሮ ነው ትንቢት የሚናገረው፡፡ እንዲያውም ትንቢትህ እውነት እንዲሆን ጸልይ ሲሉት ይህማ እውነት ነው ይፈጸማል እያለ በራስ መተማመን ሲናገር ይሰማል፡፡ አንድ ህመምተኛ ስትመጣ ደግሞ “ተፈወሽ” በሚል ቃል እንዳሰናበታት ያሳያል፡፡ ቅዱሳን ሲፈውሱ “በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም…” እያሉ ነበር ይኼ ግን የድፍረቱ መጠን ራሱን እንደ አምላክ እንዲቆጥር አድርጎታል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” እንዳለው መጻጉእ “ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል” እንዳላት መግደላዊት ማርያም እርሱም “ተፈወሽ” ሲል ሰማነው፡፡ ይህ የድፍረት ድፍረት ነው፡፡ አንዱን ደግሞ “ብልትህ አይሠራም ና ወደዚህ ልጸልይልህ” አለውና ልጁ መጣ ነቢይ ተብየውም ጸለየለትና “ሂድ እና መሥራቱን አረጋግጥ” ብሎ የሚገርም የዝሙትን ትምህርት አስተማረው፡፡ ምን ይኼ ብቻ ሰውየው ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል እርሱ ፓርላማ ወንበር ላይ እንደሚቀመጥ የፖሊስ እና የደሕንነት አካላትም እርሱ በሚናገረው ቃል እንደሚበታተኑ ተናገረ ሰውም አሜን አለ፡፡ ግን አንዲትም አልተፈጸመችም፡፡ ትንቢት እኮ አምላክ ሲናገር እንጅ በሰው ፈቃድ የሚሆን አይደለም፡፡ ይህ ሀሰተኛ ነቢይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነግሮኛል እያለ ነው እየተናገረ ያለው፡፡ ክርስቶስ ደግሞ ውሸት አይናገርም፡፡ ሰይጣን ያሳየህን የልብህን መሻት ብቻ ነው እያወራህ ያለህ፡፡ አንዲትን ህጻን ልጅ ደግሞ “አንች ኦርቶዶክስ ነሽ አላት” እርሷ ግን አይደሁም አለች፡፡ ያን ጊዜ አንገቷ ላይ ክር አለ የእግዚአብሔር ሰው በማለት አስተናጋጁ ውርደቱን ተከናነበ፡፡ለማንኛውም ይህን ቪዲዮ ተመልከቱትና ፍረዱት፡፡


ራሳችንን ከሐሰተኞች ነቢያት እንጠብቅ፡፡ ይህ ሰው ሱፍ እና ካራባት ስለለበሰ እና በፕሮቴስታንቶች አዳራሽ ውስጥ ስለተናገረው ምንም ጉዳይ ላንሰጠው እንችላለን፡፡ እኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ የበግ ለምድ ለብሶ ወገቡን በሀብል ጠፍሮ ቢመጣ እውነት ነው ብለን አንቀበልምን እንቀበለዋለን፡፡ ቤተክርስቲያናችን እገሌ እንዲህ ነው ብላ ስታወግዘው እኮ በግል ጠብ ነው ወዘተ እያልን ራሳችንን የምናታልል ሰዎች ነን፡፡


በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም ፮ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

No comments:

Post a Comment