፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍ላይክ ✍ላይክ ✍ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
facebook.com/melkamubeyeneB
✍ላይክ ✍ላይክ ✍ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
፠ #በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ አንድ ቪዲዮ በውስጥ መስመር ተልኮልኛል፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት
ስለሆነ የድምጹ ጥራት መስተካከል ስላለበት እርሱን በሚገባ አስተካክየ ጨርሻለሁ፡፡ ድምጹ በሚገባ ስለሚሰማ ጠብቁኝ ይለቀቅላችኋል፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s
ይህ ክፍል የማጠቃለያ ክፍል ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ተሐድሶ መናፍቃን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን
ውስጥ እያደረሱ ያሉትን ጥቃት ተመልክተናል፡፡ በዐውደ ምሕረት ላይ ያደርጉት የነበረው የድፍረት እንቅስቃሴ አሁን በአብዛኛው ዕገዳ
ተደርጎበታል፡፡ ሆኖም ግን ይህንን መርዛቸውን በልዩ ልዩ መንገዶች ለክርስቲያኖች በማድረስ እያወናበዱ ይገኛሉ፡፡ አሁን ላይ ምእመናንን
የሚያገኙባቸው ስልቶችም፡-
፩ኛ. የማኅበራዊ መገናኛዎች፡- ተሐድሶ መናፍቃን ከዐውደ ምሕረታችን መባረራቸውን ሲያውቁ ወደ ማኅበራዊ
መገናኛዎች በብዛት ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣በብሎግ፣ በድረገጽ፣ በቴሌቪዥን ወዘተ በብዛት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ
ያህልም፡ የዲያቆን አሸናፊ መኮነን ድረገጽ፣ የዲን አቤንኤዜር ተክሉ ድረገጽ፣ አባ ሰላማ ድረገጽ፣ ደጀ ብርሃን ድረገጽ፤ ዐውደ
ምሕረት ድረገጽ ወዘተ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህ ድረገጾች የቤተክርስቲያናችንን ሕልውና የሚፈታተኑ የመናፍቃን ድረገጾች ስለሆኑ
ማንኛውም ግለሰብ እነዚህን ከመጠቀም መቆጠብ ይኖርበታል፡፡
፪ኛ. በመጽሐፍ፣ በመጽሔት እና በጋዜጣ መልክ ሕብረተሰቡን ለማግኘት እየጣሩ ናቸው፡፡ ማንኛውም ግለሰብ
አንድን መጽሐፍ መጽሔት እና ጋዜጣ የቤተክርስቲያናችን ነው ብሎ ከማንበቡ በፊት ይህንን ጽሑፍ ለሊቃውንቱ ማሳየት እና እውነተኛነቱን
ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ቤተክርስቲያናችንን የሚሳደቡ መጻሕፍት መጽሔቶችና ጋዜጦች በብዛት ተሰራጭተዋልና ከመጠቀም እንታቀብ፡፡
“የዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ የዲግሪ ደቀመዝሙር” በሚሉ ግለሰቦች መጽሔት ሊባሉ እንኳ የማይችሉ ትንንሽ መጻሕፍትን በማሳተም እና በማሰራጨት
ላይ ስለሆኑ ይህንን በትኩረት እንጓዝበት፡፡
፫ኛ. በቴሌቪዥን ሥርጭት፡፡ ገንዘባችንን አውጥተን በገዛነው ቴሌቪዥን የመናፍቃኑን የድንቁርና ንግግር ልንመለከትበት አይገባንም፡፡
እስካሁን ድረስ እንኳ የእኛ አለመሆኑን ያልተረዱ የቤተክርስቲያናችን ልጆች #ቃለ #ዓዋዲን ይመለከታሉ፡፡ መመልከቱ ችግር ባልሆነም
ነበር ነገር ግን አትጹሙ አትጸልዩ አትመጽውቱ እያለ ከሃይማኖታችን መንገድ ሊወጣን የሚጣጣር የምንፍቅና ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡
አሁን ወደ ፊትም በቅርቡ ይከፈታሉ የተባሉ የዚሁ አጋዥ ጣቢያዎች እንደሚኖሩ እየተነገረ ነው፡፡ ስለዚህ አንድን የቴሌቪዥን ጣቢያ ከመከታተላችን በፊት የማን እንደሆነ በሚገባ ማዎቅ አለብን፡፡
ስለዚህ የማጠቃለያ መፍትሔ ሃሳቦቻችን ምን ሊሆኑ ይገባል ብለን ስንመለከት፡-
፩. እስካሁን ድረስ ሳናውቅ ከእነዚህ ግለሰቦች የገዛናቸውን የመዝሙር እና የስብከት ካሴቶችን በሙሉ አውጥተን
ማቃጠል፡፡
፪. ሳናውቅ ገዝተን ያስቀመጥናቸውን መጻሕፍት ማቃጠል፡፡
፫. የእነዚህን ግለሰቦች ድረገጾች አለመከታተል፡፡ በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ፣ በብሎግ ወዘተ አለመከተል፡፡
፬. ከእነዚህ ግለሰቦች ጋራ በስልክም፣ በዋትሳፕ በቫይበር፣ በኢሞ በሚሴንጀር ወዘተ አለመገናኘት፡፡
፭. የቴሌቪዥን ስርጭታቸውን አለመከታተል፡፡
፮. የእነዚህን ግለሰቦች ስብከቶች መዝሙራት ከሞባይላችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት፡፡
ይህንን አድርጉ ስንል ግን አማራጮችን በመስጠት እንጅ ዝም ብለን አይደለም፡፡ ተሐድሶዎቹ አማራጭ እንኳ
አይሰጧችሁም በማለት ወሬያቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡
ለሕይወታችን ለሃይማኖታችን ጠቃሚ የሆኑ የቤተክርስቲያናችን ድረገጾች፡፡
በፌስቡክም
በዩቲዩብም በሌሎች መገናኛ ዘዴዎችም የእነዚህን ድረገጾች መከታተል የተሻለ ነው፡፡ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ከእነዚህ ድረገጾች እኩል
ባላሰፍረውም እንደአማራጭ የእኔን ድረገጽም መከታተል ትችላላችሁ፡፡ አንተ ማን ነህና እንዳትሉኝ እንጅ፡፡
በቴሌቪዥንም
በኩል ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን
Aleph Television Nilesat (E8WB)
Frequency: 11595
Polarization: Vertical
Symbol Rate: 27500
FEC: 3/4
የኢኦተቤ
ቴሌቪዥን
EOTC Television Nilesat (7WA)
Frequency: 11353 (5)
Polarization: Vertical
Symbol Rate: 27500
FEC: 5/6
እነዚህን በመከታተል ራሳችንን ከተሐድሶ መናፍቃ እንጠብቅ፡፡
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን
፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች
አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ
#አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች
እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
© መልካሙ በየነ
መስከረም ፲፩
/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
No comments:
Post a Comment