Friday, September 1, 2017

“የሰኔ ጎልጎታ ልብ ወለድ ነው”-------ብጹእነታቸው



© መልካሙ በየነ
ነሐሴ 26/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

ሰኔ ጎልጎታን የሚያውቅ ያውቃታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ መቃብር ላይ ሰኔ 21 የተናገረችው እና ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስም የገባላትን ቃል ኪዳን የምትዘክር መጽሐፍ ናት የሰኔ ጎልጎታ፡፡ በየቀኑ አንብቡኝ አንብቡኝ የምትል ልዩ የጸሎት መጽሐፍ ናት፡፡ ቤተክርስቲያናችንም እያሳተመች ለምእማናን እያደረሰች እንደሆነ ግልጥ ነው፡፡ የሰይጣንን ክፉ ፈተና ለማራቅ፣ ከልዩ ልዩ በሽታዎችም ለመላቀቅ ፍቱን መድኃኒት ናት ሰኔ ጎልጎታ፡፡ እንኳን ለእኛ ለልጆቿ ለላም እና ለበሬው ለሁሉም እንስሳት ሁሉ በሰኔ ጎልጎታ ማየ ጸሎት ይድናሉ፡፡ ልዩ ልዩ በሽታ ሁሉ አይደርስባቸውም፡፡ ምክንያቱም ልጇ ወዳጇ አማንየ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላታልና፡፡

አባታችን አቡነ ማርቆስ ግን ይህችን የእመቤታችንን የቃል ኪዳን መጽሐፍ ልብ ወለድ ፍልስፍና ነው በማለት ነበር እንዳንጸልያት ያስተማሩን፡፡ ይህ በእውነቱ ለእመቤታችን ያላቸውን ክፉ ጥላቻ የገለጡበት እንጅ መጽሐፏን የነቀፉበት መስሎ አልታየኝም፡፡ ይችን መጽሐፍ አምኖ በአንገቱ ያነገታት ከብዙ መከራዎች እንደሚድን የታወቀ ነው፡፡ ሰይጣንም አይፈታተነውም ሊቀርበውም አይችልም፡፡ ይችን መጽሐፍ እንድንጥላት የሚመክረን ብቸኛው ጠላት ቢኖር ያው ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ብቻ ነው፡፡ ይችንም መጽሐፍ ልብ ወለድ ፍልስፍና ናት ብሎ ደፍሮ የሚናገር አፍ እርሱ ዲዳ አፍ ነው፡፡ በዲያብሎስም ቀንበር ውስጥ የተጠመደ ነው፡፡ መጽሐፏን የምታውቁ ታውቋታላችሁ የማታውቋትም ካላችሁ የሰኔ ጎልጎታ ብላችሁ ከ10 ብር በማይበልጥ ዋጋ ገዝታችሁ አንብቧት፡፡ ከዚያ ልብ ወለድ ስለመሆን አለመሆኗ ራሳችሁ አረጋግጡ፡፡ የአባታችንን ንግግር የተያያዘውን አጭር ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

ጎጉል እንኳ ያመነውን ጉዳይ አባታችን እንዴት እንደካዱት አላውቅም፡፡ ጎጉል ላይ ከታች ባለው ሊንክ መሠረት እንዲህ ተርጉሞታል፡፡
“ጎልጎታ የሚባል መጽሐፍ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታ መቃብር የጸለየችው ነው ተብሎ መነኵሴ የሚደግመው ጎልጎታ መጽሐፍ ይባላል” ይላል ታዲያ አባታችንን ምን ነካቸው ልበል፡፡

የቻላችሁ መጽሐፉን ገዝታችሁ ለሀልጊዜ ተጠቀሙበት ያልቻላችሁ ደግሞ ከዚህ በታች መጽሐፉን ጽፈነዋልና አንብባችሁ ልብ ወለድ የሚያሰኘው ምኑ እንደሆነ መርምሩ፡፡
==========================================================
*************************************************************************************
==========================================================
የሰኔ ጎልጎታ

አንድ፡ አምላክ፡ በሚሆኑ፡ በአብ፡ በወልድ፡ በመንፈስ ቅዱስ፡ ስም፡ በእውነት፡ እናምናለን፡፡ ልመናዋ፡ ክብሯ የልጅዋም፡ ቸርነት፡ ከወዳጆችዋ ፡-

ከሁላችን፡ ጋር፡ ይኑር ለዘለዓለሙ፡ አሜን፡፡

አምላክን፡ የወለደች፡ በውስጥ፡ በአፍአ ንጽሕት: የምትሆን፡ የብርሃን፡ እናቱ፡ እመቤታችን እግዝእትነ፡ ማርያም፡ በሰኔ፡ ሃያ፡ አንድ፡ ቀን በጎልጎታ፡ ይኸውም፡ የጌታችን፡ የመድኃኒታችን፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ መካነ፡ መቃብር፡ በሚሆን እንዲህ፡ ስትል፡ የጸለየችው፡ጸሎት፡ ይህ፡ ነው፡፡

ልጄ፡ ወጃዴ፡ ጌታዬ፡ አምላኬና፡ ንጉሤ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ሰውን፤ ለማዳን፡ ስትል፡ በፈቃድህ፡ ከእኔ፡ ተወልደህ፡ ጡቶቼንም፡ጠብተህ፡ በግዕዘ፡ ህጻናት ብታድግ፡ ሰማይና፡ ምድር ፡ አይችሉህም እኮን፡፡ የዓለም፡ ዳርቻዎች፡ አይወስኑህም፡ ምድርም፡ ልትሸከምህ፡ አትችልም፡ ቀላያትና፡ አብርሕትም ከጥልቀታቸው፡ የተነሳ፡ የክረምት፡ ማዕበል፡ በእፍኝህ አይመሉም፡ ኃይላት፡ መላእክትም፤ ቢሆኑ፡ ወደ፡ አንተ ሊቀርቡ፡ አይችሉም በማህፀኔ፡ ዘጠኝ፡ ወር፡ ከአምስት፡ ቀን ተሸክሜሃለሁና፡ ጡቶቼንም፡ አራት፡ ዓመት፡ እየጠባህ አድገሀልና፡ እለምንሃለሁ፡ እማልድሀለሁ፡ ሄሮድስ በምቀኝነት፡ ሊገድልህ፡ በፈለገ፡ ጊዜ፡ አንተን፡ በጀርባዬ አዝዬ፡ አራት፡ ዓመት፡ ከአንዱ፡ ሀገር፡ ወደ፡ አንዱ ሀገር፡ ተሰድጃለሁና፡ አቤቱ፡ ጌታዬና ፡ አምላኬ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ጸሎቴንና፡ ልመናዬን፡ ስማኝ፡፡ አቤቱ ማህፀኔን ፡ ዓለም፡ አድርገህ፡ ዘጠኝ፡ ወር፡ ከአምስት ቀን ተሸክሜአለሁና፡ እለምንሃለሁ፡ አማልድሀለሁ፡፡ አቤቱ በቁርና፡ በብርድ፡ ወራት፡ ከቤተልሔም፡ ከኔ መወለድህን አስብ፡፡ አቤቱ፡ ከአንተ ፡ ጋር፡ ከሀገር፡ ወደ፡ ሀገር፡ መሰደዴን፡ ስለአንተም፡ የደረሰብኝን፡ ጭንቅና፡ መከራ ረሀብና፡ ጥም፡ አስብ፡ የምለምንህም፡ ለደጋጎች ለጻድቃን፡ ብቻ፡ አይደለም፡ በዚህ፡ ዓለም ሳሉ ስሜን፡ ለሚጠሩ፡ መታሰቢያዬን፡ ለሚያደርጉ በአማላጅነቴ፡ ለሚተማመኑ፡ ኃጥአንም፡ ነው፡ እንጂ፡፡ አቤቱ፡ ጸሎቴንና ፡ ልመናየዬን፡ አስተውል ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ የምሻውን፡ የቃሌን፡ ልመና፡ ትሰማኝ ዘንድ፡ የልቦናዬን፡ ሀሳብ፡ ትፈጽምልኝ ዘንድ፡ በዚህች፡ ዕለትና ፡በዚህች፡ ሰዓት፡ አስራ ሁለት የብርሃን፡ መላእክት፡ ሁለት፡ የይቅርታ መላእክት ሃያ፡ አራት፡ የምሕረት፡ መላእክት ከእኔ ፡ ጋር፡ በመቆም፡ የልመናዬን፡ ቃል ይፈጹሙልኝ፡ ዘንድ፡ ላክልኝ፡፡ ካንተ ፡ ዘንድ፡ የምሻውን፡ ቸርነትህን አታርቅብኝ፡፡ ልጄ፡
ወዳጄ፡ ሆይ፡ ይህ፡ ዓለም፡ ሳይፈጠር፡ አስቀድሞ ከአንተ ፡ ጋር፡ በነበረ፡ በእግዚአብሔር፡ አብ፡ ባህርይ አባትህ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ ፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ፡ ሰማይና፡ ምድር፡ ተራሮችና ኮረብታዎች፡ ሰውና፡መላእክት፡ ፀሐይና፡ ጨረቃ ከዋክብት፡ ሳይፈጠሩ፡ ቀንና ሌሊት፡ ሳይለዩ፡ በነበረ በእግዚአብሔር፡ ስምህ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! የአብ፡ የባሕርይ፡ ሕይወቱ፡ የሆነ፡ ከአብ፡ የተገኘ፡ የአንተም፡የባሕርይ፡ ሕይወትህ፡ በሆነ፡ ከአንተ፡ ጋር፡ የተካከለ፡ በጰራቅሊጦስ፡ መንፈስ ቅዱስ፡ ከኮከብ፡ መውጣት፡ በፊት፡ ከአንተ፡ ጋር፡ በነበረ፡ ፡አሁንም፡ ያለ፡ለዘለዓለምም፡ በሚኖር፡ በአብና፡ በመንፈስ ቅዱስ፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! እለ፡ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ፡ በተባሉ፡ ፀወርተ፡ መንበርህን፡ በረዓድ፡ እየተንቀጠቀጡ መንበርህን፡ የሚሸከሙ፣ አንተን፡ ባዘለችህ፡ ጀርባዬ፡ ቃል፡ ኪዳን ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወጃጄ፡
ሆይ! አንተን ፡ ይገድሉሃል፡ እያልኩ ሳስብ፡ ከዓይኖቼ፡ እንደ ፡ ጠል፡ ውሃ፡ እየፈሰሱ በክብርት ሥጋህ፡ ላይ፡ በወረዱት ፡ ዕንባዎቼ፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡

ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ምን፡ ምን፡ ሊቀርብህ፡ የማይችል፡ አንተን፡ በሳሙ፡ ከንፈሮቼ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ከአንተ፡ ጋር፡ ቃል፡ ለቃል በተነጋገረ፡ አንደበቴ፡ ሱራፌል ፡ ኪሩቤል፡ድምፅህን ሰምተው፡ ፀንተው፡ ለመቆም፡ የማይቻላቸው፡ ጥዑማት ቃላትህን፡ በሰሙ፡ ጆሮዎቼ፡ ሰላሳ፡ ሶስት፡ ዓመት ከአውራጃ፡ ወደ አውራጃ፡ ከአንተ፡ ጋር፡ በተመላለሱ እግሮቼ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ወዳጄ፡ ሆይ! ልብሱ፡ እሳት፡ ክዳኑ፡ እሳት እየተባልክ፡ የምትመሰገን፡ አንተ፡ እሳተ፡ መለኮት ስትሆን፡ በጨርቅ፡ ተጠቅልለህ፡ በተጣልክበት፡ ዋሻ (በረት)፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! መልአከ፡ምክርህ፡ በሆነ፡ በቅዱስ፡ ሚካኤል፡ አንተን፡ በክብር፡ እወልድ፡ ዘንድ፡ የመወለድህንም፡ ዜና፡ (ምስራች)፡ በነገረኝ፡ በቅዱስ ገብርኤል፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! በምጥ፡ የተያዙትን፡ ሴቶች ማህፀን፡ ይፈታ፡ ዘንድ፡ ሥልጣን፡ በሰጠኸው በቅዱስ፡ ሩፋኤል፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ ሆይ! የሰላምና ፡ የደኅንነት፡ መልአክ በሆነ፡ በቅዱስ፡ ዑራኤል፡ መልአክ፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ዙፋንህን፡ በሚሸከሙ፡ አርባዕቱ፡ እንስሳ፡ ኪሩቤል፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ እግዚአብሔር፡ እያሉ፡ አኗኗርህን፡ በማመስገን መንበርህን፡ በሚያጥኑ፡ ሃያ፡ አራቱ ፡ ካህናተ፡ ሰማይ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ተልእኮታቸውን፡ ለማፋጠን በሚፋጠኑ፡ ዘጠና፡ ዘጠኙ፡ ነገደ፡ መላእክት፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! እልፍ፡ ሆነው፡ በፊትህ በሚቆሙ፡ እልፍ፡ ሆነው፡ በኋላህ፡ በሚቆሙ፡ እልፍ ሆነው ፡ በቀኝህ፡ በሚቆሙ፡ እልፍ፡ ሆነው፡ በግራህ፡ በሚቆሙ፡ መላእክት፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ተራሮችና፡ ኮረብቶች ከመፈጠራቸው፡ አስቀድሞ፡ በፀሐይና፡ በጨረቃ ውስጥ፡ በሚመላለሱ፡ ብርሃናውያን፡ መላእክት፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ ፡ ወዳጄ፡ ሆይ!
በሰማይ፡ ተድላ፡ መንበርህ በእግርህ፡ መረገጫ፡ በሆነ፡ በምድር፡ ቃል፡ ኪዳን ትገባልኝ ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! በኢየሩሳሌም፡ ሰማያዊት ሀገርህ፡ ብርሃነ፡ መለኮትህ፡ በተገለጠበት፡ በደብረታቦር ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! በደብረዘይት፡ በበአተ መንግስህ፡ በደብረ፡ ጽዮንም፡ ቃል፡ ኪዳን ትገባልኝ ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ሥርዓተ፡ ጥምቀትን ለመመሥረት፡ በትሕትና፡ በቆምክበት፡ በማዕከለ ዮርዳኖስ፡ በቅዱስ፡ መንፈስህና፡ ከአንተም፡ ዘንድ ፡ በወጣው፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ፡ በተቸነከሩት፡ እጆችህ፡ እና እግሮችህ፡ በቅዱስ፡ ሥጋህና፡ በክቡር፡ ደምህም፡ ቃል ፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ለሰው፡ ልጅ፡ ስትል በተቀበልከው፡ መከራና፡ ሞትህ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ቃል፡ ኪዳን ትገባልኝ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ሦስት፡ ሌሊትና፡ ሦስት መዓልት፡ በከርሠ፡ መቃብር፡ ባደርክበት፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! አዳምን፡ ከነልጆቹ፡ ለማውጣት በአካለ፡ ነፍስ፡ ወደ፡ ሲኦል፡ በመውረድህ፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ሙስና፡ መቃብርን፡ አጥፍተህ በሦስተኛው፡ ቀን፡ ከሙታን፡ ተለይተህ፡ በመነሳትህ በታላቅ፡ ምስጋና፡ ወደ፡ ሰማይ፡ በማረግህ፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! በማይሻረው፡
መንግሥትህ በማያልፈው፡ ዘመንህ፡ ጉድለት፡ በሌለበት፡ የደስታ ወንዝ፡ ዝቅ፡ ከፍ፡ ዓፅንኖ በሌሉበት፡ መንበርህ፡ ቃል፡ ኪዳን ትገባልኝ ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ጼቃና ፡ ሴቃ፡ በተባሉ፡ ስሞችህ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ጠላትን፡ በሚያሸንፍ፡ በኢያኤል በጠላት፡ በማይጠቃ፡ በታዳኤል፡ ስምህ፡ ቃል፡ ኪዳን ትገባልኝ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ለመናገር፡ በማይቻል፡ በኅቡእ ስምህ፡ ለመተርጎም፡ በማይቻል፡ በክሱት፡ ስምህ ቃል፡ ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ሳዶር፡ አላዶር፡ ዳናት፡ አዴራ ሮዳስ፡ በተባሉ፡ በአምስቱ፡ ቅንዋተ፡ መስቀልህ፡ ቃል ኪዳን፡ ትገባልኝ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡

ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ከኔ፡ ጋር፡ ቆመህ፡ የልቦናየን ሃሳብ ትፈጽምልኝ፡ ዘንድ የተዘጉ፡ በሮችም፡ ተከፍተው፡ የሞት፡ ስልጣን፡ ይወገድ ዘንድ፡ የርኩሳን፡ መናፍስት፡ ሥልጣን፡ ተሽሮ የጨለማ፡ ኃይል፡ ከሁሉ፡ ቦታ ፡ እንደ፡ ሰም፡ ቀልጦ፡ እንደ፡ ውሃ፡ ፈሶ፡ ይቀር፡ ዘንድ፡ ጣኦታትም ተደምስሰው፡ የጣኦታትም፡ ቦታና፡ አዳራሽ ተመዝብረውና፡ ተቀጥቅተው፡ ይጠፋ፡ ዘንድ እማልድሃለሁ፡፡ ዳግመኛ፡ በዚህ፡ ጸሎት የሚተማመኑትን፡ ከኃጢአት፡ ማሠሪያ፡ ሰማያዊ በሆነ በአባትህ፡ ሥልጣን፡ ማሕየዊ፡ በሚሆን በአንተም ስልጣን፡ የኃጢአት፡ ሥር፡ ተቆራርጦ የሚጥል፡፡ ነፍስን ከሥጋ፡ የሚለይ፡ ስሑል፡ ነበልባላዊ በሆነ፡ በመንፈስ ቅዱስ፡ ስም፡ ቃል የተፈቱ፡ እና ነፃ፡ የወጡ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ፡ እማልድሃለሁ፡፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ! ጸሎቴንና፡ ልመናዬን፡ ሰምተህ ወደ፡ እኔ፡ ትመጣ፡ ዘንድ፡ አለምንሃለሁ እማልድሃለሁ፡፡

ከመዓርና፡ ከወተት፡ ይልቅ፡ ስሟ፡ ጣፋጭ፡ የሆነው፡ አምላክን፡ የወለደች፡ የብርሃን፡ እናቱ እመቤታችን፡ ማርያም፡ እንዲህ፡ ብላ፡ በጸለየች፡ ጊዜ ምድር፡ ተነዋወጠች፡ ድንጋዮች፡ (አለቶች)፡ ተሰነጣጠቁ መቃብራትና፡ የተዘጉ፡ በሮችም፡ ተከፈቱ፡፡ በዚህ፡ ጊዜ ዘጠና፡ ዘጠኙ፡ ነገደ፡ መላእክት፡ ከአለቆቻቸው፡ ጋር ከሰማይ፡ ወርደው፡በግራ፡ እና በቀኝ፡ ቆሙ፡ ጌታ ኢየሱስ፡ ክርስቶስም፡ ከፀሐይና፡ ከጨረቃ፡ ሰባት፡ እጅ፡ የሚያበሩ፡ አራቱ፡ ብርሃናት፡ ከፊት፡ እና ከኋላው፡ እያበሩ፡ እልፍ፡ አእላፋት፡ ወትእልፊት አእላፋት፡ መላእክት በግራ፡ በቀኝ ተሰልፈው፡ ወረደ፡፡ እመቤታችን፡ ማርያም፡ ይኸን፡ ባየች፡ ጊዜ፡ ልጅዋን፡ ወዳጅዋን፡ በታላቅ፡ ግርማ፡ አየችው ፈጽሞም፡ አደነቀች፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም፡ እናቱ፡ ማርያምን፡ ይህ ያስደንቅሻልን? ዘጠኝ፡ ወር፡ ከአምስት፡ ቀን፡ በማኀፀንሽ የተሸከምሺኝ፡ አይደለምን? አላት፡ ቡርክት ማርያምም፡ እንዲህ፡ ስትል፡ መለሰችለት ቀድሞ፡ በዚህ፡ አኳኋን፡ አላየሁህም፡ የሰውን፡ ሥጋ፡ ለብሰህ በማህፀኔ፡ ተሸከምኩህ፡ እንጂ፡ ዛሬ ግን እጅግ በሚያስደነግጥና፡ በሚያስፈራ፡ በመለኮት፡ ግርማ አየሁህ፡፡ ጌታችንም፡ መለሰ፡ እንዲህም፡ አላት፡ እናቴ ፡ ሆይ፡ ዘጠኝ፡ ወር ከአምስት ፡ ቀን፡ በማህፀንሽ የተሸከምሽኝ፡ በጀርባሽም፡ ያዘልሽኝ ከመዓር ከስኳር፡ ይልቅ፡ የሚጣፍጥ፡ ከበረድ፡ የነፃ፡ ከገነት ፈሳሽም፡ ይልቅ፡ የሚጣፍጥ፡ ከበረድ፡ የነፃ፡ ከገነት ፈሳሽም፡ ውሃም፡ ንጹህ፡ የሆነ፡ ጡትሽን፡ ያጠባሽኝ እናቴ፡ ማርያም፡ ሆይ! ምን፡ ላደርግልሽ፡ ትፈቅጃለሽ እነሆ፡ የለመንሽውን ፡ ሁሉ፡ የምትሽውንም እፈጽምልሻለሁና፡፡

ቡርክት፡ መርገመ፡ ሥጋ፡ መርገመ ነፍስ፡ የሌለባት፡ ማርያምም፡ ለልጅዋ፡ ለወዳጅዋ፡ እንዲህ፡ ስትል፡ መለሰች፡ ልጄ፡ ወዳጄ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ተስፋዬ፡ አምባየ፡ መጠጊያዬ አንተ፡ ነህ፡ እምነቴም፡ በአንተ፡ ላይ፡ ነው፡ ገና፡ በእናቴ፡ ማህፀን፡ ሳለሁ፡ አንተ፡ ጠበቅኸኝ፡ አፀናኸኝም፡ ለሁል፡ ጊዜም፡ መታሰቢያዬ፡ እና አለኝታዬ አንተ፡ ነህ፡ በኋለኛውም፡ ዘመን፡ ትንቢቱ ሲፈጸም፡ ሰዓቱ፡ ሲደርስ፡ በአንተ፡ ፈቃድ፡ በአባትህም ፈቃድ፡ ማኀየዊ፡ በሚሆን፡ በመንፈስ፡ ቅዱስም፡ ፈቃድ፡ ከእኔ፡ ተወልደሃልና፡ ዛሬ፡ የአንደበቴንም፡ ቃል፡ ጸሎቴን፡ እና ልመናዬን፡ ስማኝ፡ እኔ፡ ወላጅ፡ እናትህ፡ ማርያም፡ የምነግርህን፡ሁሉ፡አድምጥ፡ መታሰቢያዬን፡ ለሚያደርጉ፡ በስሜ ቤተክርስትያን ስለሚሰሩ፡ አንተ፡ የብርሃን፡ ማህደር፡ አዘጋጅህላቸው፡፡ አቤቱ ፡ ስለእኔ፡ የታረዘውን፡ ያለበሰ፡ በሰው፡ እጅ ያልተሰራውን፡ ዕፁብ፡ ድንቅ፡ የሆነውን የማይጠፋውን፡ የማያረጅውን፡ ዕውነተኛውን፡ ልብስ አልብሰው፡፡ አቤቱ፡ በእኔ፡ ስም፡ በሽተኞችን፡ የጎበኘ፡ (የጠየቀ) በቸርነትህ፡ እና ፡ በይቅርታህ፡ ጎብኘው፡ አቤቱ ስለስሜም፡ ብሎ፡ ለተራበ፡ ያበላውን፡ የሕይወት እንጀራ፡ አብላው፤ ሰማያዊ፡ በሆነ፡ ማዕድህም አስቀምጠው፣ ለተጠማ፡ ያጠጣውንም፡ በዔዶም፡ ገነት ከሚፈሰው፡ የሕይወት፡ ውሃ፡ አጠጣው፡፡ አቤቱ፡ ስለኔ ፡ስም፡ ያዘነውን፡ ያረጋጋ፡ ነፍሱ ከሥጋው፡ በምትለይበት፡ ጊዜ፡ አጽናናው፡ ያዘነውንና የተከዘውንም፡ ያስደስተ፡ እና ፡ ያጽናናው፡ ስለስሜ፡ ብለህ አስደስተው፡ እድል፡ ፈንታውንም ፡ በዚህ ፡ ዓለም፡ ሳሉ፡ አንተን፡ በምግባር፡ በሃይማኖት፡ ደስ፡ ካሰኙህ ከቅዱሳን ፡ ጋር፡ አድርገው፡፡ አቤቱ፡ ምስጋናዬን፡ የሚናገሩትን፡ መጻሕፍት፡ የጻፈ ያጻፈ፡ በእኔ ፡ ስምም፡ የጸለየ፡ ሰማያዊ በሆነ፡ ዓምደ ብርሃን ፡ ስሙን፡ ጻፈው፡ በጸሎቱ፡ ተማምኖ፡ ይህን መጽሐፍ፡ በአንገቱ፡ ያነገተ፡ በሰው፡ ልብ ያልታሰበውን፡ ዓይን፡ ያላየውን፡ ጆሮ፡ ያልሰማውን መልካሙን፡ ዋጋ፡ ክፈለው፡፡ አቤቱ፡ በስሜ፡ የሚያምኑ፡ ሁሉ፡ ከሲዖል፡ ሞት ነፃ፡ የወጡ፡ ይሆኑ፡ ዘንድ፡ አለምንሃለሁ እማልድሃለሁ፡፡ አስቦ፡ መታሰቢያዬን፡ ያደረገ፡ (ዝክሬን የዘከረ)፡ በበዓሌም ፡ ቀን፡ በምመሰገንበት፡ ምስጋና የሚያመሰግኑ፡ እና፡ የሚዘምሩትን፡ አቤቱ ዝማሬ፡ መላእክትን፡ አሰማቸው፡፡

ጌታችንም፡ ይሁን፡ እንደወደድሽ፡ ይደረግልሽ፡ አላት፡፡ በአንቺ፡ ስም፡ ቤተክርስትያን፡ ያሳነፀ የብርሃን ቦታ፤ አዘጋጅለታለሁ፤ በመንግስተ ሰማያትም፡ ንፁህ ማደሪያ፡ እሰጠዋለሁ፡፡ ከባሕርይ፡ አባቴ፡ ከአብ ከባሕርይ፡ ሕይወቴ፡ ከመንፈስ፡ ቅዱስ ፡ ፊት አቀርበዋለሁ፡፡ የታመመን፡ በስምሽ፡ የጎበኘ፡ ታሞ በአልጋ፡ ላይ፡ በተኛ፡ ጊዜ፡ አጎበኘዋለሁ፡፡ ከዚህ ከሚያልፈው፡ ዓለም፡ ወደማያልፈው፡ ዓለም፡ በሞት፡ በተለየ፡ ጊዜም፡ መሪር፡ የሆነ፡ የሞት፡ ጽዋዓን አላጠጣውም፡፡ ወደ፡ መንግሥተ፡ ሰማያት፡ እስኪገባ ድረስ፡ አልለየውም፡ ርኩሳን፡ መናፍስትም በተከራከሩት፡ ጊዜ ፡ እኔ ጠበቃ፡ እሆነዋለሁ፡፡ በችግሩ ጊዜም፡ እደርስለታለሁ፡፡ ዳግመኛም፡ በስምሽ ለታረዘ (ለተራቆተ)፡ ያለበሰ፡ በሰው፡ እጅ፡ ያልተፈተለ እና ያልተሰራ፡ ኀብሩ፡ ዕጹብ፡ ድንቅ፡ የሆነ፡ የሕይወት ልብስ፤ አለብሰዋለሁ፡፡ የማይጠፋ፡ የማይጠወልግ የሕይወት ፡ አክሊልም፡ አቀዳጀዋለሁ፡ ስለ፡ አንቺም ብሎ፡ ከዕለት፡ ጉርሱ፡ ለተራበ፡ ያበላ ምድራዊ፡ ያይደለ፡ ሰማያዊ፡ የሆነ፡ የሕይወት፡ እንጀራ፡ አበላዋለሁ፡ ለተጠማ፡ ያጠጣ፡ ከመዓር ከስኳር፡ የሚጣፍጥ፡ ወተት፡ እጅግ፡ ነጭ፡ የሆነ ከዔዶም፡ ገነት፡ ከሚፈሰው፡ የሕይወት፡ ውሃ አጠጣዋለሁ፡፡ በስምሽ፡ ያዘነውን፡ የተከዘውን፡ ያስደሰተ፡ ስለ፡ ስምሽ፡ ብዬ በሰማያዊ፡ አባቴ፡ ፊት፡ ደስ፡ አሰኘዋለሁ፡፡ የምስጋና መጽሐፍሽን፡ የጻፈ፡ ያጻፈ፡ እኔ በሕይወት፡ መፅሐፍ ስሙን፡ እጽፈዋለሁ፡ ስለ ፡ አንቺ፡ መብራት፡ ዘይት፡ ዕጣንም፡ ለቤተክርስቲያን፡ መብዓ፡ የሰጠ፡ እኔ ከፀሐይ፡ ከጨረቃ፡ ይልቅ፡ ሰባት፡ እጅ፡ የሚያበራ መብራት፡ በመንግሥተ፡ ሰማያት፡ አበራለታለሁ፡፡ ንፁህ መዓዛ፡ ዕጣንም፡ የሰጠ፡ መዓዛ፡ ሽታውን፡ እንደ መላእክት፡ መዓዛ፡ አደርገዋለሁ፡፡ ሴት ፡ ወይንም፡ ወንድ፡ ልጁን፡ በአንቺ ስም፡ የሰየመውን፡ በምድራውያን፡ ሰዎች፡ እና በሰማያውያን፡ መላእክት፡ ዘንድ ፡ ከፍ፡ ያለ፡ ግርማ ሞገስ፡ ያገኛል፡፡ ይህ፡ መጽሐፍ፡ ባለበት፡ ቦታ፡ሁሉ፡ እስከ፡ ዘለዓለም ድረስ፡ ምሕረት፡
ቸርነት፡ ተድላ፡ ደስታ፡ ጥጋብ በረከት፡ ይሁን፡፡ ስምሽ፡ በተጠራበት፡ ስእልሽም፡ ባለበት፡ መታሰቢያሽም፡ በተደረገበት፡ በስምሽም በሚጸለይበት፡ ቦታ፡ ሁሉ፡ እኩያን፡ አጋንንት አይቀርቡም፡ በረቂቅ፡ ሰውን፡ የሚያሰቃዩ፡ ጸሊማን ዛር፡ ውላጆችም፡ ይርቃሉ፡፡ ይህን መጽሐፍ በክብር ይዞ ፡ ለሚጸልይ፡ የጨለማ ፡ ኃይል፡ አይጋርደውም ርኩሳን፡ መናፍስትም፡ የቀትር፡ አጋንንትም፡ ሊቀርቡት፡ አይችሉም፡፡ በሌሊት፡ በህልም የሚያስደነግጡ፡ በመዓልት፡ በእሾህ፡ መውጋት፡ ቢሆን በእንቅፋት፡ የሚመሰሉ፡ በምግብ ማሳነቅ፡ ወይም ፡ በውሃ ትንታ፡ የሚመሰሉ፡ በስካር እና ፡ በቁጣ፡ የሚመሰሉ፡ ልብን፡ በመፋቅ፡ በቃር የሚመሰሉ፡ በጥርስ፡ በሽታ፡ አፍን፡ በማምረር፡ በራስ ምታት፡ እና፡ በዓይን፡ ህመም፡ ወይም፡ በሆድ ቁርጠት፡ የሚመሰሉ፡ በንዳድ፡ (በወባ)፡ በማንቀጥቀጥም የሚመሰሉ፡ በባህር፡ እና ፡ በየብስ፡ በእንጨት፡ በድንጋይ፡ የሚመሰሉ፡ በእሳት፡ እና ፡ በዲን የሚመሰሉ፡ በፍቅር፡ እና ፡ በሰላም ወይም፡ በጠብ የሚመሰሉ፡ በአራዊት፡ እና፡በአዕዋፋትም፡ የሚመሰሉ በፀሀይ፡ ሐሩር፡ ወይም፡ በቁርና፡ በአመዳይ፡ በውርጭ በነፋስ፡ ንውጽውጽታ፡ ኃይል፡ ወይም ፡ በውሻ፡ መንከስም የሚመስሉ፡ በእፍኝት፡ መንደፍም፡ ቢሆን፡ በእሳት ማቃጠል፡ የሚመሰሉ በሌሊት፡ ጨለማ ፡ በቀን ብርሃንም፡ የሚመሰሉ፡ እነዚህ፡ ሁሉ፡ አይቀርቡም ይህን፡ መፅሐፍ፡ በንጹህ፡ ህሊና፡ በቅን፡ ልቡና፡ የያዘ የቡዳ፡ ዓይን፡ አያስፈራውም፡ ይህች፡ መጽሐፍ በምትደገምበት፡ ቦታ፡ ሁሉ፡ ሰላቢዎች፡ ሟርተኞች መድኃኒተኞች፣ የሌሊትና፡ የቀን፡ የዱር ፡ አራዊቶች የሚታየውም፡ የማይታየውም፡ በረድ፡ ከብኩባ አንበጣም፡ ቢሆን፡ ሊቀርቡ፡ አይችሉም፡፡ ከብቶችም ቢታመሙ፡ ይህን፡ ጸሎት፡ ቢደግሙላቸው፡ ክፉ በሽታ፡ አይነካቸውም፡፡ ይህን፡ መጽሐፍ፡ በንጽህና የሚይዝ፡ ሁሉ፡
ከደዌው፡ አድነዋለሁ፡፡ ከሚያስጨንቅ ችግርም፡ እሠውረዋለሁ፡ ኃጥአትም፡ ቢኖርበትም ይሠረይታል፡ ደዌው፡ ለሞት፡ የሚያዘዝ፡ ቢሆን እኔ አስቀድሜ፡ መላእክተ፡ ብርሃን፡ እልክለታለሁ ነፍሱንም፡ በክብር፡ ተቀብለው፡ ወደ፡ እኔ ያመጧታል፡፡ ከሦስተኛው ፡ ሰማይም፡ በደረሰ፡ ጊዜ፡ መናፍስተ ርኩሳን፡ አይቃወሙትም፡ ጸዋጋን፡ አጋንንት፡ ከእርሱ ጋር፡ አይቆሙም፡ ሊቀርቡትም፡ አይችሉም፡፡

ዳግመኛም ፡ እኔ፡ በዚያን፡ አስፈሪ፡ በሆነ፡ ሰዓት፡ ረዳት፡ እሆነዋለሁ፡ እኔ፡ እና፡ የባሕይ፡ አባቴ፡ አብ፡ የባሕርይ፡ ሕይወቴ፡ የእውነት፡ መንፈስ፡ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ፡ ወደ፡ እርሱ፡ እንመጣለን፡፡ አስራ፡ ሁለቱም፡ ሊቃነ፡ መላእክትም፡ ከዝርግፍ፡ ወርቅ፡ ጋር የወርቅ፡ ጥናቸውን፡ ይዘው፡ ይመጣሉ፡፡ ቀስተ፡ ደመና በመሰለ፡ በናርዱ፡ ሽቱ፡ መብረቅም ፡ በመሰለ፡ የእሳት ሰረገላ ፡ ሆነን፡ ይህን፡ መጽሐፈ፡ ጸሎት፡ የያዘን፡ ሰው እንቀበለው፡ ዘንድ፡ እስከ፡ አምስተኛው፡ ሰማይ፡ ድረስ እንወርዳለን፡ በደረቴ፡ አቅፌ፡ ባህረ፡ እሳትን አሻግረዋለሁ፡፡ ወደ፡ መንበረ፡ መንግሥቴም፡ አቀርበዋለሁ፡፡ መንፈሳውያን፡ የመላዕክት፡ አለቆችም፡ በአዩት፡ ጊዜ ደስ፡ ይላቸዋል፡፡ ይህን ፡ ጸሎት፡ በንጽህና፡ እየፀለየ የያዘን፡ ሰው፡ እያሸበሸቡ፡ ይቀበሉታል፡፡ በቅዱስ ወንጌል፡ የተነገረውን፡ አልሰማሽምን፡ መቶ፡ በጎች ያሉት፡ ሰው፡ ከመቶው፡ አንዷ፡ ብትጠፋበት፡ ዘጠና ዘጠኙን፡ በዱር፡ ትቶ፡ የጣፋችውን፡ በግ፡ ሊፈልግ እንደሄደ፡ በአገኛትም፡ ጊዜ፡ በትከሻው፡ ተሸክሞ ካልጠፉት፡ ከዘጠና፡ ዘጠኙ፡ በጎች፡ ይልቅ፡ ጠፍታ በተገኘችው፡ በግ፡ ደስ፡ እንደሚለው፡ ባልንጀሮቹን እና ጎረቤቶቹን፡ ጠርቶ፡ የጠፋችው፡ በጌ፡ ተገኝታለች እና፡ ደስ፡ ይበላችሁ፡ ይላቸዋል፡፡ እውነት፡ እውነት፡ እላችኋለሁ፡ ንስሐ፡ ከማይገቡ ፃድቃን፡ ይልቅ፡ ንሰሐ፡ በሚገባ፡ አንድ፡ ኃጥአ፡ ሰው በሰማይ፡ ታላቅ፡ ደስታ፡ እንደሚደረግ፡፡

ሁለተኛም ይኸን፡ መጽሐፍ፡ የሚደግም፡ እና ፡ በሚይዝ፡ ሰው ሰማያውያን፡ መላእክት፡ ደስ፡ ይሰኛሉ፡፡ ከዚህ ከሚያልፈው፡ ዓለም፡ ወደ፡ ማያልፈው፡ ዓለም፡ ነፍሱ ከሥጋው፡ ተለይታ፡ በምትወጣበት፡ ሰዓት፡ ደብረ መቅደሴን፡ አወርሰዋለሁ፡፡ ከባሕርይ፡ አባቴ፡ ከአብ ከባሕርይ ፡ ሕይወቴ፡ ከመንፈስ፡ ቅዱስም፡ ዘንድ አቀርበዋለሁ፡፡ ይህ፡ መጽሐፍ፡ ካለበት፡ ቦታ፡ ይቅርታ ቸርነት፡ ምህረት፡ ጥጋብ፡ ተድላ፡ ደስታ፡ እስከ ዘለዓለም፡ ድረስ፡ ይሆናል፡፡ በእውነት፡ ይህ፡ ጸሎት በተደገመበት፡ እና፡ በተነበበበት፡ ቦታ፡ ንዳድ እንቅጥቅጥ፡ በያይነቱ፡ በሽታ፡ ሁሉ፡ አይቀርቡም፡፡ ይህን፡ የጸሎት፡ መጽሐፍ፡ በንጹህ፡ የያዘ፡ እርሱን ልጆቹን፡ ገንዘቡን፡ ሀብቱን፡ እባርካለሁ፡፡ በዚህ መጽሐፍ፡ አምኖ፡ በንጹህ፡ ልቡና፡ በቀና፡ ሃይማኖት ያለጥርጥር፡ በማየ፡ ጸሎቱ፡ የተጠመቀ፡ የጠጣ፡ በቤቱ (በስራው፡ ቦታ) ፡ የረጨ፡ እኔ፡ ጸሎቱን፡ እሰማዋለሁ እንደ፡ ልቡም፡ ፈቃድ፡ እፈጽምለታለሁ፡፡ ሚካኤልና ገብርኤልም፡ ፈቃዱን፡ ይፈጽሙለት፡ ዘንድ፡ ዘወትር፡ ወደ ፡ እርሱ፡ ይመጣሉ፡፡ ይህን፡ መጽሐፍ በንጽህና የያዘ፡ ሁሉ፡ የሰራዊተ፡ መላእክት፡ አለቆች፡ ዘወትር እየመጡ፡ ይጎበኙታል፡፡ እናቴ ማርያም፡ ሆይ፡ በሰማይና ፡ በምድር፡ ይህን፡ሁሉ፡ ቃል፡ ኪዳን (አስራት) ሰጠሁሽ፡፡
ቡርክት፡ መርገመ፡ ሥጋ፡ መርገመ፡ ነፍስ የሌለባት፡ እመቤታችንም ፡ ልጄ፡ ወዳጄ፡ ሆይ ይህ፡ የምትለኝ፡ ሁሉ፡ እውነት፡ ነውን፡ አለችው፡፡ ጌታም፡ መለሰ፡ እንዲህም፡ አላት፡ እናቴ፡ ማርያም፡ ሆይ በእግዚአብሔር፡ አባቴ፡ በክርስቶስ፡ ስሜ፡ በዕውነት መንፈስ፡ በጸራቅሊጦስ፡ እውነት እንደሆነ፡ ቃል ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡ አላት፡፡ መልአከ ምክሬ፡ በሆነው በሚካኤል፣ የመወለዴን፡ ዜና በአበሰረሽ፡ በገብርኤል ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡ አላት ክንፋቸው፡ ስድስት በሆኑ፡ ምሉዓነ፡ አዕይንት፡ በሆኑ መንበሬን በሚሸከሙ፡ ዐራቱ፡ እንስሳት፡ (ኪሩቤል) ቃል፡ ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ አኗኗሬን፡ በአንድነት፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ ቅዱስ፡ እያሉ፡ እያመሰገኑ፡ መንበሬን፡ በሚያጥኑ፡ በሃያ ዐራቱ፡ ካህናተ፡ ሰማይ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡ እልፍ፡ ሆነው ፡ በቀኝ ፡ እልፍ፡ ሆነው፡ በግራ፡ እልፍ ሆነው ፡ በኋላ፡ እልፍ፡ ሆነው በፊቴ፡ በሚቆሙ፡ መላእክት፡ ቃል፡ ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ በእልፍ፡ አእላፋት፡ ብዙ፡ የብዙ፡ ብዙ፡ በሚሆኑ ትጉሃን፡ መላእክት፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ የፍጥረት ተቀዳሚ፡ በሆነ፡ በአዳምና፡ በልጆቹም፡ በአቤልና፡ በሴት፡ በቃይናን በመላልኤል፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ በኄኖክና፡ በኄኖስ፡ በያሬድ፡ እና፡ በማቱሳላም፡ ቃል ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ዳግመኛም፡ ምድርን፡ በንፍር፡ ውሃ፡ እንዳላጠፋት ኪዳነ፡ ሰማይ፡ ወምድር፡ በሰጠሁት በባሪያዬ፡ በኖህ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ የትዕዛዜ፡ ጠባቂ፡ በኩር፡ በሆነ፡ በሴም፡ ምሳሌየ፡ በሆነ፡ በመልከ፡ ጼዴቅ ካህን፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ስለ፡ ወዳጄ፡ ስለ አብርሃም ስለ፡ ባለሟሌ፡ ስለ፡ ይስሐቅ፡ ዘሩን፡ በአስራ፡ ሁለቱ ነገድ፡ ከፍዬ ፡ ስለ አከበርኩት፡ ስለ፡ ያዕቆብ፡ ቃል፡ ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ንጹሃን ፡ ቅዱሳን ፡ በሆኑ፡ በቀደሙ፡ አባቶች በይሁዳ፡ እና፡ በፋሬስ፡ በዮሴፍ፡ እና፡ ብንያም፡ በሌዊ እና፡ በይሳኮር፡ በአስራ፡ ሁለቱ፡ ነገደ፡ እስራኤል፡ ቁጥር፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ጸሐፍተ፡ ትዕዛዝ፡በሆኑ፡ በሄኖክ፡ እና፡ በኤልያስ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ዘጠኝ፡ ወር ከአምስት፡ ቀን በተቀመጥኩባት ፡ ንጽህት፡ በሆነች ማኀፀንሽ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡  ጣፋጭቱ፡ ከመዓር፡ ከስኳር፡ የሚጥመው፡ ንጹሕነቱ፡፡ ከኤዶም ምንጭ፡ ውሃ፡ ንጣቱ፡ ከበረዶ፡ እና፡ ከወተት የበለጠውን፡ ወተት፡ መግበው፡ ባሳደጉኝ፡ ጡቶችሽ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ትእዛዜን፡ እና፡ ሕጌን ባስተማሩ፡ አስራ፡ አምስቱ፡ ነብያት ሄሮድስ ባስገደላቸው፡ አስራ፡ አራት፡ እልፍ፡ የቤተልሔም ሕፃናት፡ ቃል ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ የወንጌልን፡ መንግስት፡ ለዓለም፡ በሰበኩ፡ ሐዋርያት ስለ፡ እኔ፡ ነፍሳቸውን፡ ለሞት፡ አሳልፈው፡ ስለ፡ ሰጡ ሰባ፡ ሁለቱ፡ አርድእት፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ዙፋኔ፡ በተዘጋጀባት፡ ሉዓላዊት፡ ሰማይ፡ የእግሬ መረገጫ ፡ በሆነች፡ ታህታዊት፡ ምድር፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ነደ፡ እሳት፡ በሆነ፡ የእሳት፡ ነጋረጃዬ ፍጹም፡ ማደሪያዬ ፡ በሆነ በአርያም ፡ ሰማይ፡ ቃል ፡ ቃል ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ በተሰቀልኩበት፡ ዕፀ፡ መስቀል እጅና እግሬ፡ በተቸነከረበት ቅኖት፡ (ችንካር)፡ በጦር በተወጋው፡ ጎኔ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ በዕለተ ዓርብ፡ በፈሰሰው፡ ደሜ፡ በሕመሜ፡ እና፡ ሞቴ፡ ሦስት፡ መዓልትና፡ ሦስት፡ ሌሊትም፡ በከርሰ፡ መቃብር፡ ባደርኩበት፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ከመቃብር፡ ወጥቼ፡ አዳምን፡ ከነ፡ ልጆቹ፡ ከሲኦል ለማውጣት፡ ወደ፡ ሲኦል፡ በመውረዴ፡ በሦስተኛው፡ ቀን፡ ከሙታን፡ ተለይቼ፡ ሙስናን፡ መቃብርን፡ አጥፍቼ በመነሳቴ፡ በዐርባኛው፡ ቀን፡ ወደ፡ ሰማይ፡ በማረጌ ዳግመኛው፡ ዓለምን፡ ለማሳለፍ፡ በታላቅ ፡ ምስጋና በምመጣበት፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ ክቡር ፡ በሆነ ደሜ፡ ቅዱስ፡ በሆነ፡ ስጋዬም፡ ቃል፡ ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ ሰማያዊት ፡ በሆነች፡ በኢየሩሳሌም፡ ሀገሬ በክቡር፡ በምስጋና፡ በተጌጠች፡ በጽዮን፡ ቃል፡ ኪዳን ገባሁልሽ፡፡ የሙሽራ፡ አምሳል፡ በሆነች፡ በቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስትያን፡ ከዕለታት፡ መርጬ፡ የተወለድኩባት የተጠመቅኩባት፡ ለሰው፡ ልጅ፡ ድኀንነትን፡ የምታስገኝ ትንሳኤዬንም፡ በገለጥኩባት ሰንበተ፡ ክርስትያን፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ በደብረ ዘይት፡ በተቀደሰውም፡ በጽዮን፡ በደብረ፡ መንግስቴ በመቃብሬ፡ በጎልጎታ ንጹህ፡ ብሩሕ፡ በሆነ፡ ደም፡ ግባትሽ፡ ንጹሐት፡ ክቡራት፡ በሆኑ፡ ልብሾችሽ፡ በዚህ ሁሉ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ገባሁልሽ፡፡ አናቴ፡ ድንግል ማርያም፡ ሆይ፡ የሰጠሁሽን፡ ቃል፡ ኪዳን፡ እንዳልነሳሽ እማንዬ፡ ብዬ፡ በራሴ፡ ማልሁልሽ፡፡ በአንቺ፡ ስምም የሚቀደስበትን፡ ቦታ፡ እኔ፡ እባርካለሁ፡፡ እንደ፡ አቤልም መሥዋዕት፡ እቀበለዋለሁ፡፡

መርገመ፡ ሥጋ፡ መርገመ ነፍስ፡ የሌለባት እመቤታችንም፡ መለሰች፡ እንዲህም አለች፡ እንተ ብሩክ ፡ ነህ፡ ሰማያዊ፡ አባትህም፡ ብሩክ ፡ ነው፣ የባሕርይ፡ ሕይወትህ፡ መንፈስ፡ ቅዱስም የተባረከ፡ ነው፡፡ ይህን፡ ሁሉ፡ በቸርነትህ፡ ስለሰጠኸኝ፡ አቤቱ፡ ለአንተ፡ ምስጋና ፡ ይገባል፣ ለቸር አባትህም፡ ምስጋና፡ ይገባል፡ ማኀየዊ፡ ለሚሆን፡ ለመንፈስ፡ ቅዱስም፡ ምስጋና፡ ይገባል፡ ዛሬም፡ ዘወትርም፡ ለዘለዓለሙ፡ አሜን፡፡ ጌታችን፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ለእናቱ፡ ይህን፡ ነግሯት፡ ከፈጸመ፡ በኋላ ሰላምታ፡ ሰጥቷት፡ በታላቅ፡ ምስጋና፡ ወደ፡ ሠማይ፡ ዐረገ፡ እርሷም፡ እግዚአብሔርን፡ እያመሠገነች፡ ወደ ቤቷ፡ ተመለሠች፡ እንዲህ፡ እያለች፡ አቤቱ፡ አንተ የተመሠገንህ፡ ነህ፡ ስምህም፡ የተመሠገነ፡ ነው፣ መንግሥትህም፡ ስም፡ ይባረክ፡ ከመንፈስ፡ ቅዱስ ጋር፡ ክብር፡ ጽንዕ፡ ለአንተ፡ ይገባል፡ ዛሬም፡ ዘወትርም፡ ለዘለዓለሙ፡ አሜን፡፡ እመቤቴ፡ ማርያም ሆይ፡ በዚህ፡ ቃል፡ ኪዳንሽ፡ ከተንኮለኞች፡ ሠዎች፡ ከጸዋጋን፡ አጋንንት፣ መከራና፡ከመከራ፡ ሥጋ፡ ከመከራ፡
ነፍስ፡ ከዕለት፡ ዕኪት፡ ዘመን፡ መንሱት፡ እኔን፡ ደካማ አገልጋይሽን አድኚኝ፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

=====================================
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡

No comments:

Post a Comment