Saturday, September 16, 2017

✍✝ ተሐድሶ መናፍቃን እና ስልታቸው ---ክፍል ፩✝✍




====================================
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
====================================

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
ምንፍቅና ዛሬ ሳይሆን ገና በፍጥረት መጀመሪያው ዕለት በሳጥናኤል አንድ ብሎ የጀመረ መርዝ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ ዲያብሎስ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ  ሰዎችን በምንፍቅና ሲያሰለጥናቸው ቆይቷል፡፡ በየዘመኑ  የሚነሡት  መናፍቃን የሚያነግቧቸው የኑፋቄ ትምህርቶች እጅግ በርካታዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ዘመን የሚገኙ መናፍቃንም ካለፉት በመማር የራሳቸውን የጥፋት ስልት ነድፈው በጨለማ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ በቅርቡ እየሰማንና እያየን ያለው ነገር ከቀድሞው የተለየ የረቀቀ መንገድ መከተላቸውን ነው፡፡ ከምዕመንነት እስከ ጵጵስና ደረጃ ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ብዙ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ስብከቶቻቸውና ዝማሬዎቻቸው ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጣሱና ለመንፈሳዊ ጥንካሬ ምንም  የማይጠቅሙ ዋዛ ፈዛዛ ነገሮች እና ሥጋዊ ፍላጎቶች የሚንጸባረቁባቸው እየሆኑ በመምጣታቸው ሥርዓት የጠበቁት እንዳይደመጡና እንዲጠሉ አድርገዋቸዋል፡፡ በዚህ አገልግሎት ሥር የተሰማሩ የተሐድሶ መናፍቃን መሪዎችም በየግላቸው ዘብ የሚቆምላቸውና እነርሱን የሚደግፍ ትውልድ በመፍጠር በአንዲት  ቤተክርስቲያን ውስጥ የተለያዩ  ሁለት ጎራዎች
እንዲፈጠሩና ብጥብጡ እንዲባባስ አድርገውታል፡፡ የቀደሙት መናፍቃን ከቤተክርስቲያናችን ተገንጥለው የራሳቸውን የፍልስፍና ትምህርት የሚሰጡበት አዳራሽ እየሰሩ በዚያ ምንፍቅናቸውን ያራምዱ ነበር፡፡ የአሁኖቹ መናፍቃን ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው ቅርሶቿን ለባዕድ አሳልፈው በመሸጥ ሥርዓቷን በመናድ ቤተ ክርስቲያንን  ባዶ አዳራሽ በማድረግና ምዕመናንንና ካህናትን ለግላቸው መጠቀሚያ እየደለሉ ከቤተክርስቲያን ለማውጣት ረቂቅ ሥልት ያላቸው ናቸው፡፡ ከገጠር እስከ ከተማ የተዳረሰውን ይህ የተሐድሶ ምንፍቅና ሁላችንም ልንታገለው ይገባል፡፡ ማንን እየተከተልን፣ ለማን እያጨበጨብን እንደሆነም ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ መስቀል የያዘው ሁሉ ቄስ፣ ቆብ የደፋው ሁሉ መነኩሴ፣ መቁጠሪያ የያዘው ሁሉ ባህታዊ፣ በመንበረ ጵጵስና የተቀመጠው ሁሉ ጳጳስ፣ ድምጽ ያለው ሁሉ ዘማሪ፣ መናገር የሚችለው ሁሉ ሰባኪ፣ የሚቀድሰው ሁሉ ዲያቆን፣ የሚያብረቀርቀው ሁሉ ወርቅ አይምሰላችሁ፡፡ ፍሬያቸውን ተመልክተን ከፍሬያቸው ማዎቅ እንችላለን፡፡ ለበለጠ ደግሞ በጸሎት፣ በጾም፣ በትሕትና መትጋት ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ በእነዚህ መናፍቃን የተደናገርን እኔ ክርስቶስ ነኝ እያለ በምትሐት ፀሐይና ጨረቃን በእጁ መዳፍ የያዘ መስሎ ሲመጣ ስንቶቻችን ነን በክርስትናችን ጸንተን የምንገኝ፡፡ እባካችሁ ወገኖቼ ኃይልን ከአርያም እስክንለብስ ድረስ በኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ጸንተን እንቆይ፡፡ ከዚያ በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲሰጠን መናፍቃንን ድል የምንመታ ኃይለኞች እንሆናለን፡፡ ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብርታትና ጽናት ስለሚሆነን ሐዋርያት ባስተማሩት ትምህርት በክርስቶስ መሠረትነት ላይ ታንጸን ለመኖር አይከብደንም፡፡ ቤተክርስቲያናችን በምንም አይነት የረቀቀ መንገድ ለሚመጣ መናፍቅ አጉልቶ  በሚያሳይ ትምህርቷ ትረታቸዋለች፡፡ ስለዚህ የምንከተለው እረኛ እውነተኛ መሆኑን አውቀን የእኛን የበጎቹን ድምፅ መለየት እንደሚችል ተገንዝበን ልንከተል ያስፈልጋል እንጅ ነፋስ በፈለገው አቅጣጫ እንደሚያወዛውዘው ዛፍ ወደዚያ ወደዚህ መወላወል ለክርስትና ሕይወታችን እንቅፋት ነው፡፡
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡


✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

No comments:

Post a Comment