Wednesday, September 20, 2017

✍✝ ተሐድሶ መናፍቃን እና ስልታቸው ---ክፍል ፫✝✍


====================================
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
====================================

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በምን ዓይነት መንገድ እንደተጀመረ እና ወደፊት በቤተክርስቲያናችን ላይ ማድረስ የሚፈልጉት ጥቃት ምን እንደሆነ ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡ ዛሬም በጋሻው ዘርፌ አሰግድ ምናምን ተሐድሶ ናቸው ምናምን የሚል ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ካለ እርሱ ችግር አለበት፡፡

በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እያደረሱት ያለው ጥፋት ምን ደረጃ ላይ ነው ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=HCvVSwc5uZI&t=2391s
https://www.youtube.com/watch?v=XX-TzKhHnnw&t=3s
https://www.youtube.com/watch?v=qWU7yp46fjY&t=53s
ቤተ ክርስቲያንስ ሄዋን ናት
አንድ የተሐድሶ ሰባኪ“ያረጀችው ቤተ ክርስቲያን አሮጊቷ ሣራ ወለደች፡፡ እኔን ወለደች፣ እገሌን ወለደች፣ እገሊትን ወለደች” እያለ ተሐድሶ የወለደቻቸውን ይዘረዝራል፡፡ቤተክርስቲያን አሮጌ መባሏ ያበሳጨው የተዋሕዶ ልጅ ወደ “ሰባኪው”ተጠግቶ “መጽሐፍ ማንበብ ይቀርሃል ሣራ በእርጅናዋ ወራት የወለደችው አንድ ልጅ ይስሐቅን ብቻ እንደነበር አላወቅህም እንዴ? አሮጊቷ ሣራ እኔን፣ እገሌን፣ እገሊትን ወለደች እያልህ የምትቀባጥር፡፡ ቤተ ክርስቲያንስ አሮጊት ሣራ ሳትሆን ቀድሞ የነበረች መንታ መንታ የምትወልድ የብዙዎች እናት ሄዋን ናት፡፡፡ የግል ክብርህን ፈልገህ ደግ ይስሐቅን ነኝ ለ ማለት  ክብርት ቤተክርስቲያንን ዝቅ ዝቅ ያደረግህበት ይህ ደፋር አንደበት በደሙ በመሠረታት በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት ስትቆም ምን ይናገር ይሆን?” በ ማለት  ብዙ ትምህርት አስተማረው፡፡

ስብከት ጋዜጠኛነት አይደለም
“እገሌ ሲናገር ሲሰብክ ልዩ ተሰጥዎና ግርማ ሞገስ አለው፡፡ ስለዚህም ተሐድሶ መናፍቅ ሊባል አይገባውም” የሚሉ ደጋፊዎች በዝተዋል፡፡እነዚህ ደጋፊዎች ያልገባቸው ነገር የድምፅ ማማር ወይም የንግግር ግርማ ሞገስ መኖር የሰባኪ መመልመያ መስፈርት ማድረጋቸው ነው፡፡ ስብከት የድምፅ ግርማ ሞገስን ብቻ መሠረት ያደረገ የጋዜጠኛነት ሙያ አይደለም፡፡ ስለዚህ የንግግር ግርማ ሞገስ ያላቸው የተሐድሶ መናፍቃን ጋዜጠኛነት መወዳደር ይችላሉ እንጅ በድምጻቸው ማማር ብቻ ተዋሕዶን ሊሰብኩ አይችሉም፡፡ ስብከት በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጅ እንደጋዜጠኛ መናገር ብቻ አይደለምና፡፡
በጣም ይመቸኛል
“እገሌ እና እገሊት ሲዘምሩ ድምጻቸው በጣም ይመቸኛል” የሚሉ በርካታ ደጋፊዎች በዝተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በመዝሙሩ ውስጥ ምን መልእክት እንደተላለፈ አልተረዱም፡፡ እነርሱ የተማረኩት በዘማሪዎች የድምጽ ማማር ብቻ ነው፡፡ የድምጽ ማማርን የሚደግፉ ሰዎች ደግሞ ዘፋኞችንም የሚደግፉ በመሆናቸው መዝሙርና ዘፈን የተቀላቀለባቸው በመሆናቸው“ድምጻቸው ይመቸኛል” ከ ማለት  የዘለለ ሌላ የሚደግፉበት ቃል የላቸውም፡፡ ስለዚህ መዝሙርን በዘማሪዎች ድምጽ ማማር ብቻ ሳይሆን በውስጡ ባለው መልእክትና በዜማው የቤተክርስቲያናችን መሆን አለመሆኑን ልንገነዘበው ያስፈልጋል፡፡
ሌባ ለአመሉ…
“እገሌ ባዘጋጀው ልዩ የስብከት መርኀ ግብር ይህን ያህል ሺህ ብር ለቤተክርስቲያን ገቢ አደረገ፡፡ ስለዚህ እገሌ ተሐድሶ ሊባል እንዴት ይችላል በእኔ በኩል ግን ተሐድሶ መናፍቅ መባሉን አልደግፍም” የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች “ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል” የሚለውን ሥነ ቃል የዘነጉ ናቸው፡፡ እነርሱ እንደሚሉት ለቤተክርስቲያን የሰጠው ገንዘብ እንጅ ጥሩ ምእመን አይደለም እኮ ፡፡ ቤተክርስቲያን የምትፈልገው ደግሞ በሺህ የሚቆጠር ጥሩ ምእመንን ነው፡፡ ስለዚህ ገንዘብ መስጠት ብቻውን የተዋሕዶ ልጅ የሚያሰኝ ባለመሆኑ ትምህርቱን፣ ሥርዓት አጠባበቁን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ 
የሚያስለቅስህ ፈልግ
ተሐድሶ መናፍቃን ስብከቶቻቸው በቀልድ በሳቅ የታጀቡ በመሆናቸው ለመሳቅ የሚከተላቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ አንድ ወጣት“እገሌ ሲሰብክ እየቀለደና እያሳቀ በጣም እያዝናና ስለሆነ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ብውል ባድር እንዴት ደስ ይለኝ ነበር” እያለ ለአባቱ ይነግራቸዋል፡፡ አባቱም “ልጄ ከዛሬ ጀምረህ ኃጢአትህን እየነገረ ስለኃጢአትህ በንስሓ የሚያስለቅስህ ሰባኪ ፈልግ” አሉት፡፡ ስለዚህ የሚያስፈልገው ኃጢአታችንን እያሰብን ወደ ንስሓ የሚመራን ስብከት እንጅ የሚያስቅ የሚያዝናና አይደለም፡፡ ሳቅ ጨዋታማ በዓለምስ ሞልቶ ተርፎ የለም እንዴ? ቤተክርስቲያን መሄድ ያስፈለገው ለንስሓ ነው እንጅ፡፡
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም ፱ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

No comments:

Post a Comment