Saturday, September 23, 2017

✍✝ ሁለተኛ ጥምቀት አለን ? የቅባቶች ሰፈር ሲመረመር✝✍



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠


ቪዲዮውን ላመየት ይህንን ሊንክ  ተጫኑ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=5fRZKnwkGrc&feature=youtu.be
 

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
#በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ የደረሰኝ ቪዲዮ ይኼ ነው፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት ስለሆነ የድምጹ ጥራት ላይ የተወሰነ ችግር ሊኖርበት ይችላል ለዚያ ችግር ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
#በመጀመሪያ #ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡
#በዋናነት በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚነገረው ነገር #ፊርማ ለማሰባሰብ ብቻ ሲባል #ሙሉ #በሙሉ ውሸት እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡
#በሰላምታ የሚጀምረው ይህ የውሸት አባት በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር መሥራቱ ያሳዝናል፡፡ #የማስተምረው ነገር የለኝም ይላል የመርኃ ግብሩ አስፈጻሚ፡፡ የኦሪት መስዋእት ይሰዋባቸው የነበሩ አምስት አብያተ ክርስቲያናትን ዘርዝሮ ተናገረ፡፡ 

#ዲማ ጊዮርጊስ ሚያዝያ ሃያ ሦስት ጉባዔ ስለነበር ስለማይመቻቸው ሚያዝያ ሃያ ዐራት ዐሥራ ዘጠኝ ሰዎች ከሞጣ ሄደው ተጠምቀዋል ለዚህም በቪዲዮ የተቀረጸ ማስረጃ አለን ይላል ይህ ሰው፡፡ #ዳግም ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው? ራስን መለየት መልካም ነው፡፡ ምንም በል ምን #ቤተክርስቲያናችን ዳግም ጥምቀትን አታጠምቅም፡፡ ዝም ብለህ በድፍን በፊቷ ቆመን ሰይጣንን እክድሃለሁ በምንልባት ቤተክርስቲያናችን ላይ ውሸት መለፍለፍ መልካም አይደለም፡፡
ይህ ሰው #የቅባት #እምነት አራማጅ ነው፡፡ ሠለስቱ ምዕት “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት” ብለዋል ኤፌ ፬፥፭ “…አንዲት ጥምቀት…” ብሏል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ በመጽሐፈ ኩፋሌም ወንድ በዐርባ ሴት በሰማንያ ቀን እንዲጠመቁ ያዝዛል፡፡ በማለት ለማብራራት እና ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ ይህ ትክክል አነጋገር ነው፡፡ ነገር ግን አረዳድ እና አተረጓጎም ላይ ችግር አለ በጣም ትልቅ ችግር፡፡ ሠለስቱ ምዕት “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት” ሲሉ እኮ እነርሱ ስላጠመቁት ሰው እንጅ አርዮስ ስላጠመቀው ሰው አይደለም፡፡ እነርሱ “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት” ቢሉም እንኳ አርዮሳውያንን አስተምረው ሲመለሱ አርዮስ አጥምቋቸዋልና አናጠምቃችሁም አላሉም ምክንያቱም አርዮስ ከሀዲ ነውና፡፡ “ወልድ ፍጡር” የምትሉ ወልድ እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ የገዛ ያዘዘ መንፈስ ቅዱስን በማኅጸን ተቀብሎ ከአብ ዳግም ሲወለድ ነው የምትሉ #ቅባቶችም ወልደ አብ ወልደ ማርያም #በተዋሕዶ #ከበረ ወደምትል የሠለስቱ ምዕት እምነት ስትመጡ #በፍትሐ #ነገሥቱ #ሥርዓት መሠረት ይጠመቃል ዐራት ነጥብ (እልፍ ጊዜ)፡፡ በፍትሐ ነገሥቷ ላይ አንቀጽ ፫ ቁጥር ፳፬ ላይ “ከመናፍቃን ጥምቀትን የተቀበለ ሰው ቢኖር አማኒ አይደለም” ይላል፡፡ መጀመሪያ የቅባት ሃይማኖት ምንፍቅና እንደሆነ ማመን ግዴታህ እኮ ነው፡፡ ቅባት ምንፍቅና ነው ብለህ ካመንህ ራሱን ቅባት ነኝ ብሎ ለይቶ ከሚንቀሳቀስ ካህን የተጠመቀ ሰው አማኒ አይደለም እኔ አላልኩም ይኸው ፍትሐ ነገሥቱ ነው፡፡ ታዲያ አማኒ ለመሆን ምን ያስፈልጋል በሉኝ፡፡ ጥሩ ጥያቄ ነው አማኒ ለመሆን የምትሻ ከሆነ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ወደ እኛ እምነት ለሚመለሱ ሰዎች የምታደርገውን ሥርዓት ትቀበላለህ እርሱ ግዴታህ ነው፡፡ ታዲያ አንድ መናፍቅ ሲመለስ ተዋሕዶ ነኝ ስላለ ብቻ ሳይጠመቅ አማኒ ሊሆን ይችላል እንዴ አይችልም፡፡ ግን ትንሽ ያበዛችሁት አልመሰላችሁም ከጀርባህ ያለችው ቤተክርስቲያን እኮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናት ታዲያ ይህን ምንፍቅናህን እንዴት ፊት ለፊቷ ቆመህ ትናገራለህ አረ ፈጣሪህንም ፍራ፡፡
ይባስ ብሎ ይኼ ደፋር ሰው “እያጠመቀ ያለ ማኅበረ ቅዱሳን ነው” ይልልሃል፡፡ #ማኅበረ #ቅዱሳን የራሱ ቤተክርስቲያን የራሱ ካህን የራሱ ጳጳስ የራሱ ፓትርያርክ ያለው አንድ ቤተክርስቲያን አድርገኸው አረፍክ እኮ፡፡ ቅድም #ዲማ ተጠመቁ እያልህ አልነበረም እንዴ አሁን ደግሞ #ማኅበረ #ቅዱሳን ነው ስትል ምን ማለትህ ነው፡፡ ጥምቀትን ማን ያከናውናል የሚለውን እንኳ አታውቅም ለማኅበረ ቅዱሳን ጥላቻ እንዳለህ ብቻ ነው የሚያሳየው፡፡
#ማኅበረ ቅዱሳን #በሲኖዶስ #ተወግዟል ብለህ እርፍ አልህ ደፋር፡፡ በሲኖዶስ የተወገዘው መናፍቁ #አሰግድ #ሳህሉ ነው እንጅ #ማኅበሩ መሰለህ እንዴ ደፋር፡፡ ማኅበሩ #መተዳደሪያ ደንቡ የጸደቀለት #በሲኖዶስ ነው ሲባል የሰማኸውን #ተወገዘ ብለህ አፍህን ሞልተህ ስትባገር አታፍርም፡፡
#ሁለተኛ የሚያጠምቁትን #አባታችን #አቡነ #ማርቆስ እና #ፓትርያርኩ #አቡነ #ማትያስ በጥብቅ እየተከታተሉት ነው አልህ እኛስ ቢሆን ያጠምቃል ያልኸው #ዲማስ ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳንስ ቢሆን ጥምቀት ትደገማለች ያሉ ይመስልሃልን አትሸወድ፡፡ ዋና ዓላማህ ፊርማ አሰባስበህ ቅባትን እንዲያንሰራራ ለማድረግ እንጅ ለቤተክርስቲያኒቱ አስበህ አይደለም፡፡ #ዲማን ግን እንዲህ አድርጋችሁ የምትፈሩት ምን አደረጋችሁ አረ! ነገሩ ግልፅ ነው ያው ለቅባት የተዋሕዶ ፀሐይ ዲማ አያስፈልገውምና ነው ምክንያቱም ይቀልጣላ፡፡
#ከዚህ በፊት #የሞጣ #የጎንቻ #የደብረወርቅ ፊርማ ተሰባስቦ ቅዱስ #ሲኖዶስ ተልኳል አሁን የእኛ ብቻ ነው የቀረው እያልህ በክፉ ምላስህ ትሸነግላለህ፡፡ የሚፈርም ሰው ይፈርም የማይፈርም ሰው እንደፈለገው እኛ #አንድ ሰው ይበቃናል ትላለህ፡፡ አድበስብሰህ ፊርማ ስትለቃቅም ትንሽ አታፍርም ግን፡፡ እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር አለ ያገሬ ሰው፡፡ #ቅባት ይኼ ነው #ተዋሕዶ ይኼ ነው ብለህ ለይተህ አስተምር እና ውሳኔውን ለራሱ ለሚማረው አካል ተውለት እውቀቱ ካለህ ማለቴ ነው፡፡ ታስተምራለህ ምን ላድርግ የሚልህን ሰው #ጥሩ #አባት ታገናኘዋለህ ከዚያ በኋላ በሥርዓቱ መፈጸም አለመፈጸም የእነዚያ አባት ኃላፊነት ይሆናል፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅ ሁለተኛ የተጠመቀ አረመኔ ነው ጌታውን ሁለቴ ሰቅሏልና ብሏል ብለህ ትናገራለህ እስኪ በድርሳን ስንት በምእራፍ ስንት በቁጥር ስንት እስኪ ግለጠው፡፡   ዮሐንስ አፈወርቅ እና የእርሱ መሰሎች እውነተኛ አባቶች ያጠመቁት ሰው ዳግም ልጠምቅ ቢል እርሱ አረመኔ ነው ትክክል፡፡ ቅባቶች እኮ የሚጠመቁት እኔን ያጠመቀኝ ካህን ስልጣኑ ማዕርጉ ዝቅ ያለ ነውና ማዕርጉ ሥልጣኑ ከፍ ባለ አባት ልጠመቅ ብለው አይደለም ካህኑ የሃይማኖት ህጸጽ አለበት ብለው እንጅ፡፡ እውነቱን እየለየን እንነጋገር፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
© መልካሙ በየነ
መስከረም ፲፫ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

No comments:

Post a Comment