Thursday, September 21, 2017

✍✝ ስም የሌለው ሃይማኖት አለን? ✝✍





፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ላይክ ላይክ ላይክ
facebook.com/beyenemelkamuA
  facebook.com/melkamubeyeneB  
ላይክ ላይክ ላይክ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝
#በቅባቶች መካከል ስላለው እንቅስቃሴ አንድ ቪዲዮ በውስጥ መስመር ተልኮልኛል፡፡ ቪዲዮው የተቀረጸው ከርቀት ስለሆነ የድምጹ ጥራት መስተካከል ስላለበት እርሱን በሚገባ አስተካክየ ጨርሻለሁ፡፡ ድምጹ በሚገባ ስለሚሰማ ጠብቁኝ ይለቀቅላችኋል፡፡
#በመጀመሪያ #ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱት፡፡
ኤፌ ፬፥፭ “…አንድ ሃይማኖት…” ይላል ብርሃነዓለም ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ይች ሃይማኖት ግን የትኛዋ ናት? እንግዲህ ይህንን ለመመለስ የግድ ??የሃይማኖቶችን?? የትመጣነት ማጥናት እና መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ባለበት ዘመን የነበረው ሃይማኖት የትኛው ሃይማኖት ነበር ቅዱስ ጳውሎስስ የኖረበት ዘመን ከመቸ እስከመቼ ነው? እያንዳንዳችን እየተከተልነው ያለው ሃይማኖትስ መቼ የተጀመረ በማን የተጀመረ እንደሆነ መርምረን እናውቃለን? አሁን ግን የግድ መመርመር ይኖርብናል፡፡
ዛሬ እየሰማነው ያለው ጉዳይ የሃይማኖት ስም እንደማያስፈልግ ነው፡፡ በዋናነት ይህንን ሃሳብ የሚጠቀሙት #ተሐድሶ #መናፍቃኑ ቢሆኑም #በተዋሕዶ ስም የሚንቀሳቀሱት #አቡነ #ማርቆስም ይህንኑ ተጋርተውታል፡፡ #ተዋሕዶ #ቅባት #ጻጋ #ካራ የሚባል ነገር የለም በእግዚአብሔር ማመን ብቻ ነው ይሉናል፡፡ ይህንን ትምህርት #በጋሻው #ደሳለኝም የገደል ማሚቶ በመሆን አስተጋብቶላቸዋል፡፡ ሃይማኖት ስም ከሌለው #እስልምና #ፕሮቴስታንት #ካቶሊክ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ ወዘተ እየተባለ መከፋፈል የጀመረው እንዴት እና መቼ ነው የሚለውን መመለስ አለባችሁ፡፡ ቀደምቲቱ ርትዕት ሃይማኖት  የእኔ ናት የሚል ሰው ሁሉ የሃይማኖቱን ጀማሪ እና የተጀመረበትን ቀን ግልጹልን፡፡ በዋናነት የሃይማኖት መከፋፈል የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በኋላ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ #መሐመድ #እስልምናን መቼ ጀመረው ለምን ጀመረው? #ማርቲን #ሉተር #ፕሮቴስታንትን መቸ እና ለምን መሠረተው? #ልዮንስ #ሁለት ባሕርይ ማለትን #ካቶሊክን ለምን እና እንዴት መቼስ መሠረተው? እነዚህ ሁሉ የተከፈሉት ከአንዲት የክርስትና ሃይማኖት ነው፡፡ የክርስትና ሃይማኖትን ትቶ  መሐመድ እስልምናን ሲመሠርት ከእስልምና ለመለየት የእኛ እምነት የግድ ክርስትና የሚል ስም ያስፈልገዋል፡፡

#በክርስትና ስም ደግሞ ከክርስትናው ተገንጥለው የራሳቸውን ጎራ ሲፈጥሩ ፕሮቴስታንት ካቶሊክ መባል ሲመጣ እኛስ የራሳችንን ጥንታዊ የሆነች ሃይማኖት ልዩ መጠሪያ አያስፈልጋትምን ያስፈልጋታል፡፡ ስለዚህም ኦርቶዶክስ (ቀጥተኛ) የሚል ስም ተሰጥቷታል፡፡ ሆኖም ግን ሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሚል ክርክር ስለተነሣ ኦርቶዶክስም ከካቶሊካውያን ለመለየት ወልድ ዋሕድ አንድ ባሕርይ አንድ አካል ነው የምትል ርትዕት ሃይማኖት “ተዋሕዶ” ተባለች፡፡ “ቅባት” ፣“ካራ” “ጸጋ” የሚባሉት አገር በቀል የሆኑ በካቶሊካውያን የተዘሩ ሃይማኖቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሃይማኖቶች የራሳቸው አስተምህሮ የራሳቸው የሆነ መሠረተ እምነት ስላላቸው እኛ ከምናምናት ሃይማኖት ከ”ተዋሕዶ” በጣም ይለያሉ፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ የሃይማኖት ድርጅቶች ለመለየት የግድ ስም ያስፈልጋል፡፡ ስም የሌለው ሃይማኖት የለም፡፡ ስም የሌለው ሰው እንኳ የለም እንኳን የዘላለም ሕይወትን የምንወርስበትን ሃይማኖት ስም አልባ ልናደርገው፡፡
የዚህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ዋና ዓላማው በተዋሕዶ ሃይማኖት ስም የራሳቸው የሆነን ድብቅ ሃይማኖት ለማስተላለፍ ስለሚፈልጉ ነው፡፡ ምሥራቅ ጎጃም ላይ በተለይ በከተማ ቦታዎች ላይ “ተዋሕዶ” ተብሎ በድፍረት መድረክ ላይ የማይነገረው ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ ወደድህም ጠላህም ቅባት ሆንህም ጻጋ ካራ ሆንህም ካቶሊክ እኛ ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ወጥተህ  በልብህ ብታምንም ባታምንም “ተዋሕዶ” ብለህ ልትጠራ ግዴታህ ነው፡፡ ሲጀመር መድረኩ ላንተ አይገባም ነበር ነገር ግን ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሠብራል እንዲሉ ጊዜ ሰጥቶሃልና መድረኩን ይዘኸዋል፡፡

ማመን በእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ነው ማለት ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔርን ልጅ ምንድን ነው ብለን እንመነው፡፡ አምላክ ነው ብለን ወይስ እንደፕሮቴስታንቱ አማላጅ ነው ብለን ወይስ እንደ ካቶሊኩ ሁለት ባሕርይ አንድ አካል ብለን ወይስ ምን ብለን እንመን፡፡ ስም የሌለው ሃይማኖት የለንም፡፡ #የበጋሻው #ደሳለኝን እና #የአቡነ #ማርቆስን #አስተምህሮዎች በቪዲዮው ላይ ተመልከቱት እና ልዩነታቸውን አሳዩኝ እስኪ፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በነገራችን ላይ የፌስቡክ ገጼን አድራሻ ከላይ ባስቀመጥሁላችሁ መልኩ ቀይሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ፳፻፲ ይህን ፷፻ የማይበልጠውን የገጹ ላይክ በእጥፍ ማሳደግ አለብን፡፡ ይህን ደግሞ የማደርገው እኔ ሳልሆን እናንተም ጭምር ናችሁ፡፡ አንተ/አንች አንድ ሰው ላይክ እንዲያደርግ ብታደርግ/ጊ እጥፍ ላይክ ተደረገ ማለት አይደል፡፡
ስለዚህ ይህን አዲስ ዓመት ላይኬን በእጥፍ ማሳደግ አለብኝ፡፡ አሁን ከእናንተ የምጠብቀው ሸር በማድረግ #አንድ #ሰው #በመጋበዝ #አንድ #ላይክ #ማምጣት #ብቻ #ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ፮ መቶ በላይ ጓደኝነት የጠየቃችሁኝ ወንድሞች እና እህቶች መቀበል ስለማልችል #ላይክ በማድረግ በዚህ ተከታተሉኝ፡፡

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝

© መልካሙ በየነ
መስከረም ፲፪ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት
#comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

No comments:

Post a Comment