© መልካሙ በየነ
ሰኔ 29/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
መነሻ እና መድረሻውን የሮም ካቶሊክ ትምህርት ያደረገው በአንዳንድ የምሥራቅ ጎጃም ወረዳዎች የሚገኘው የቅብአት እምነት ሁለተኛውን ልብ ወለድ የፈጠራ ድርሰቱን ከወራት በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ በመጀመሪያ ይህን የክህደት መጽሐፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥም ሲታተም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ዝምታ ጉዳዩን እንደሚደግፉት ያሳብቅባቸዋል፡፡ ከወልደ አብ በተለየ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገርሙ ምን ታመጣላችሁ ዓይነት መልእክቶች በጉልህ ይታያሉ፡፡ የመጀመሪያው መጽሐፋቸው “ወልደ አብ” የት እንደታተመ አይታወቅም ነበረ በዚህ መጽሐፍ ላይ ግን በግልጽ ሀፍረታቸውን ገልጠው “አሐዱ ማተሚያ ታተም ስልክ ቁጥር 0923249433” በማለት በድፍረት ለማውጣት ችለዋል፡፡ አሳታሚዋ የእኛው ቤተክርስቲያን “ምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም” በወልደ አብ ውስጥም የተገለጠች ብትሆንም እንዲህ በአደባባይ ሳይሆን በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ ላይ ብቻ ነበረ የተጻፈችው አሁን ግን ይኼው ሽፋኑ ላይም ብቅ ብላለች፡፡ ከዚህ እንደምንረዳው “በቤተክርስቲያናችሁ ስም የፈለግነውን ነገር ማድረግ እንችላለን ምንም አታመጡም” የሚል መልእክት መያዙን ነው፡፡ ደግሞ እኮ ሁለት ስልኮችን ለቆጋ ገዳም አድራሻ አድርገው አስቀምጠዋል፡፡ 0927620794 እና 0911581038 የሚሉ የቆጋ ገዳም አድራሻዎች ሆነው ተገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ስልኮች መካከል አንደኛው ማለትም 0911581038 አባ ገብረ ኢየሱስ ሙጨ የሚባሉ እንደሆኑ የመረጃ ምንጨ ጠቁሞኛል፡፡ ይህ መጽሐፍ በማን እንደታተመ አይታወቅም ወልደ አብ በ “መምህር” ገብረ መድኅን እንዳለው የሚል እንደነበረበት እናስታውሳለን እዚህ ላይ ግን ማን እንዳሳተመው የሚጠቁም የግለሰብ ሥም አላየሁም፡፡

ሌላው የዚህ መጽሐፍ የጀርባ ሽፋኑን ስትመለከቱት “የአስትሮኖሚ-የሥነ ፈለክ” መጽሐፍ እንጅ የቤተክርስቲያናችን
መጽሐፍ አይመስልም (በእርግጥ የቤተክርስቲያናችን አይደለም ስሟን ብቻ ነው የተጠቀሙባት)፡፡ በዚህ የሽፋን ገጽ ስእል ላይ የተገለጠው
መልእክት እኔ እስከገባኝ ድረስ በሥነ ፈለክ ምርምር የተደረሰ መጽሐፍ እንጅ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተዘጋጀ አለመሆኑን ነው፡፡
ሌላው በጣም የሚደንቀው ነገር የይድረስ የይድረስ አዩኝ አላዩኝ እያሉ እየተሳቀቁ ያሳተሙት እንደሆነ የሚያሳብቁ ነገሮች መኖራቸው
ነው፡፡ ለምሳሌ የመጀመሪያውን ገጽ ተመልከቱት “ሚሥጢረ ሃይማኖት” ይላል በጉልሕ በነጭ ቀለም የተጻፈው ዋናው የመጽሐፉ ርእስ መሆኑ
ነው፡፡ በየትኛውም የመጽሐፋችን ከፍል ውስጥ “ሚሥጢረ” የሚል ቃል አናገኝም ታዲያ ይህ ቃል ከየት መጣ? እያንዳንዷ ፊደላችን የራሷ
ትርጉም እና ቦታ አላት፡፡ ታዲያ “ሚሥጢረ” ማለት ምን ማለት ነው ብላችሁ ብትጠይቁ ትርጉም የለሽ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡ በእርግጥ
ይህን ሲጽፉ “ኢዲት” የሚያደርግ ሰው እንደሌላቸው የሚያስረዳ ነው፡፡ ይህን የምላችሁ ቢያንስ የሽፋኑ ገጽ ስህተቶች እንዴት አይታረሙም
በሚል እንጅ ውስጡ ላይ ስትገቡ በጣም የተበላሸ “ኢዲት” ያልተደረገ ቃል የሞላበት ስልቻ ነው፡፡ እንዲህ ለማለት ፈልገው ይሆናል
እያልን የምናነበው ብቸኛው የአዩኝ አላዩኝ መጽሐፍ ነው “ሚሥጢረ ሃይማኖት”፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ምን ይላል “ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ”
እዚህ ላይ የግእዝ ምሁራን እርዱኝ አገባቡ እንዴት ነው ትክክል ነው ትላላችሁ? “ወትንቢተ” ካለ “ዘዝክሪ ወጳውሊ” ማለት ያለበት
አይመስለኝም፡፡ “ወትንቢት ዘዝክሪ ወጳውሊ” ይላል ወይም “ወትንቢተ ዝክሪ ወጳውሊ” ይላል እንጅ “ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ” ሲባል
አላውቅም፡፡ ስለዚህ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያክራል ይሏችኋል ይኼ ነው፡፡
ስለመጽሐፉ አጠቃላይ ነገር ስንመለከት ታሪክን እንደመሰለው ከየትኛውም የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት
ጋራ የማይመሳሰል የክህደት ትምህርት ታሪክን የሚያጥፋፋ ከንቱ እና መና የሆነ ምናምንቴ ድርሰት ነው፡፡
ይህንን ምንፍቅና ለምን ለሕዝብ ትገልጣለህ ብላችሁ ደግሞ ዛሬም የአባቶቻችን ጠላት ሊቃውንቱን
የምታሳድድ አባቶችን የምትከስ ወዘተ ትሉኝ ይሆናል፡፡ እኔ ግን በእውነት ስለእውነት በሐሰት ማንንም አልከስም ማንንም አልወነጅልም
ማንንም አላሳድድም ማን አሳዳጅ አደረገኝና ነው፡፡ እና ሚዛናዊ ሆነን እንነጋገር መፍትሔ ወደመሻት እንምጣ ይህ ውይይት የሚደረግበት
እንጅ የምንሰዳደብበት መሆን የለበትም፡፡ ግን በመሳደቡ ክህደቱን ለመደበቅ የሚሞክር የቅባት እምነት ተከታይ ካለ ያው በብሎክ እንሰነባበታለን፡፡
በእውነት ምንም ርኅራኄ የለኝም ማንም እየመጣ ሊደሰኩርብን መብት የለውም፡፡
ለዛሬ አበቃሁ በቀጣይ ተከታታይ ቀናት ደግሞ ስለመጽሐፉ የውስጥ ይዘት አንድ በአንድ እንመለስበታለን፡፡
ለዛሬ አበቃሁ በቀጣይ ተከታታይ ቀናት ደግሞ ስለመጽሐፉ የውስጥ ይዘት አንድ በአንድ እንመለስበታለን፡፡
No comments:
Post a Comment