© መልካሙ በየነ
ሰኔ 07/2009
ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
ሰኔ 04/2009 ዓ.ም የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የከተሞችን መድረክ
በደብረ ማርቆስ ከተማ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ የከተሞች መድረክ ላይ ስለመብራት መቆራረጥ ስለ ውኃ እጥረት ስለ ቆሻሻ አወጋገድ
ስለ ስልክ ጥራት ስለመኖሪያ ቤት ችግር ወዘተ ወዘተ ሁሉም እየተነሣ የራሱን ጥያቄ አቀረበ፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር አንዲት ጥብእት
ቆራጥ የተዋሕዶ አርበኛ እህታችን በሀገረ ስብከቱ ስለተፈጠረው ችግር ያነሣችው፡፡ ወ/ሮ ውባለም “አባታችን ከዚህ
ተቆጠቡ ከዚህ ተከልከሉ ብለው አላስተማሩንም ሁልጊዜ መድረክ በወጡ ቁጥር ስድብ ነው የሚያወርዱብን፡፡ ስለዚህ አንፈልጋቸውም ይነሡልን” በማለት ነበር የተሰበሰበውን ህዝብ ያስጨበጨበችው፡፡ ከዚህ ቀጥለውም መጋቤ አእላፍ ጥበቡ የወ/ሮ ውባለምን ንግግር በማጠናከር ነበር የተናገሩት፡፡ ታዲያ ይህ የከተሞች መድረክ በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በአጭር ሞገድ እና በኤፍ. ኤም ጣቢያዎቹ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሰጥቶት ነበር፡፡
ተቆጠቡ ከዚህ ተከልከሉ ብለው አላስተማሩንም ሁልጊዜ መድረክ በወጡ ቁጥር ስድብ ነው የሚያወርዱብን፡፡ ስለዚህ አንፈልጋቸውም ይነሡልን” በማለት ነበር የተሰበሰበውን ህዝብ ያስጨበጨበችው፡፡ ከዚህ ቀጥለውም መጋቤ አእላፍ ጥበቡ የወ/ሮ ውባለምን ንግግር በማጠናከር ነበር የተናገሩት፡፡ ታዲያ ይህ የከተሞች መድረክ በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በአጭር ሞገድ እና በኤፍ. ኤም ጣቢያዎቹ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሰጥቶት ነበር፡፡
አባታችን አቡነ ማርቆስ ወ/ሮ ውባለም የተናገረችውን ሙሉ ንግግር የሬድዮናቸውን
ሞገድ እያስተካከሉ በሚገባ ሰምተዋታል፡፡ መጋቤ አእላፍንም እንዲሁ በንቀት ተከታትለዋቸዋል፡፡ በተለይ መጋቤ አእላፍን የሰሟቸው
ጊዜ “ቆይ እሠራለታለሁ” ያሉ ነው የሚመስለኝ ግን በየት አግኝተዋቸው ከሀገረ ስብከቱ ነው አባረዋቸዋል፡፡ አባ ማርቆስ ይህንን
እንደሰሙ በጣም ተበሳጭተው በእጅ ስልካቸው በ (+251915851397) ወደ ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ እንባቆም ጫኔ የእጅ ስልክ
(+251912056647) ይደውላሉ፡፡ አባ እንባቆም የብጹእነታቸውን የስልክ ጥሪ ያነሡታል፡፡ “አንተን ሥራ አስኪያጅ ብየ የመደብኩህ
እንዲህ በየመድረኩ በጋለሞታ ልታሰድበኝ ነው? አሁንም ባስቸኳይ ይህን ነገር ማስተባበል አለባችሁ፡፡ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አብርሃምስ
ቢሆን የመለሰው መልስ ተገቢ ነው ብለህ ነው የምታስብ? አሁንም የምሥጢር ደቀ መዛሙርቴን ሰብስበህ መላ ፈልግ” ይሏቸዋል፡፡ አባ
እንባቆም ጫኔም የምሥጢር ደቀመዛሙርትን ማለትም፡
1. መልአከ ገነት ቄስ ሙሉ አያሌው የእንድማጣ ኢየሱስ አስተዳዳሪ፡፡ የግቢ
ጉባኤ ተማሪዎች እንዳይማሩ አዳራሽ በመዝጋት የሚታወቁ ናቸው፡፡ የተማሪዎች የዳቦ ብር ሽያጭ ወደ እኛ ኪስ ይግባ በሚልም ከዩኒቨርሲቲው
ፕሬዝዳንት ድረስ በመሄድ አቤቱታ ያቀረቡ ነገር ግን በፕሬዝዳንቱ አፍረው የተመለሱ ናቸው፡፡ በዚህ ሥራቸውም አቡነ ማርቆስ በቅጽል
ስም “በላይ ዘለቀ” ብለው የሚጠሯቸው ናቸው፡፡ የበላይ ዘለቀን ጀግንነት ለእንደዚህ ዓይነት ሰው መስጠት በራሱ ወንጀል ይመስለኛል፡፡
2. መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ፍቅረ ማርያም፡- በዋሻው ቅዱስ ሚካኤል
ጠንካራ የሰበካ ጉባዔ አባላት አቤቱታ የተነሡ እና ጌቴሴማኒ ፈረስ ቤት መድኃኔዓለም አስተዳዳሪ ሆነው እየሠሩ የሚገኙ ናቸው፡፡
3. አባ ኪዳነ ማርያም፡- አባ ፍቅረ ማርያም ወደ ጌቴሴማኒ ፈረስ ቤት መድኃኔዓለም
አስተዳዳሪነት ሲሄዱ ከጌቴሴማኒ ፈረስ ቤት መድኃኔዓለም አስተዳዳሪነት ወደ ገዳመ ሕያዋን ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪነት የተመደቡት
አሁንም በዚሁ የሚገኙ፡፡
4. መሪጌታ ልዑል ብዙዓለም፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳድር ወረዳ ቤተክህነት
ሥራ አስኪያጅ፡፡
እነዚህ አምስት ሰዎች በድንገተኛ አስቸኳይ ጥሪ ተሰባስበው የብጹእነታቸውን
መልእክት ለመፈጸም ወደ ክልል (ባሕር ዳር) ማምራት ነበረባቸው፡፡ በዚህም መሠረት የሐገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የተመደበችውን
ኮድ 35 ዕድ ታርጋ ቁጥር 2825 መኪና በሥራ አስኪጁ ሹፌርነት እያበረሩ ሰኞ ሰኔ 5/2009 ዓ.ም ከሰዓት ወደ ባሕር ዳር ከነፉ፡፡ አምስት ነፍሳትን አሳፍራ ስትከንፍ የነበረችው
ይች መኪና አሮጌው እንጅባራ ዝቅዝቀቱን ጨርሳ መታጠፊያው ላይ ስትደርስ ከአንድ አይሱዙ ጋር የጥል አይሉት የፍቅር ትሳሳማለች፡፡
ትጋጫለች እኮ ነው የምላችሁ! በቃ ተጋጨች፡፡ መኪናዋ ላይ የደረሰው መጠነኛ ጉዳት የሚባል ሲሆን እግዚአብሔር በጥበቡ ትረፉ ያላቸውን
ነፍሳት በዚህ መልኩ ያለምንም አካል መጉደል አትርፏቸዋል፡፡ ተመስገን አምላካችን ዕድሜን ለንስሐ መስጠት ታውቅበታለህ መቸም፡፡
መኪናዋን በዚህ መልኩ የተመለከታት አንድ እረኛ ዋሽንቱን አወጣና እንዲህ
አለ፡
“ከምሥራቅ አለፉ
በምዕራብ ፈሰሱ
አዊ እንጅባራ በአይሱዙ ተገፉ” በማለት ተቀኘላቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነኝ
ነገር አባ ማርቆስ ጉንደወይን ግንቦት 19/2009 ዓ.ም በሄዱ ጊዜ ግርማ እስቲያውቅ በተባለ አእምሮ በሽተኛ በሹፌሩ በኩል የነበረውን
መስታወት አርግፎባቸው ከ250 ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ ማስጠገናቸው ይታወቃል አሁን ደግሞ ይች መኪና በዚህ መልኩ ስትገጭ ስንት
ብር ያስፈልጋት ይሆን? አቡነ ዘካርያስ የመለሱት 1.6 ሚሊዮን ብር በዚህ እንዳያልቅ ብቻ እሰጋለሁ፡፡
እግዚአብሔርን ተመስገን እንበለው ምናልባትም እነዚህ በእግዚአብሔር ጥበብ
የተረፉ ነፍሳት ንስሐ ገብተው ከጀመሩት የጥፋት መንገድ ይመለሱ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡
No comments:
Post a Comment