Monday, June 19, 2017

“የመቅደሱ ቦክሰኛ----ማብራሪያ ለምትሹ”


© መልካሙ በየነ
ሰኔ 12/2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
መረጃዎች ለማግኘት (facebook.com/beyenemlkm እና/ወይም facebook.com/melkamtiwulid ) ላይክ ያድርጉ፡፡
===================================================
**************************************************************************************
የሰማ ላልሰማው ያሰማ ይህ የመጨረሻየ ነው የመጨረሻ ብያለሁ!
“ትግላችን ስለቤተክርስቲያናችን ስለ ሃይማኖታችን ነው”
“በሃይማኖታችን በቤተክርስቲያናችን ለመጣ ጠላት ደግሞ ነፍሳችንንም አንሰስትም”
***************************************************************************************
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በአቡነ ማርቆስ ምክንያት በተፈጠሩ ችግሮች ዙሪያ መረጃዎችን ሳደርስ በውስጥ መስመርም፣ በስልክም፣ አስተያየት ላይ በመጻፍም እየተሯሯጡ የሚገኙ በርካታ “ፍቅረ ማርቆስ” የነደፋቸው ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለምን ስልክ ደወሉ፣ ለምን በውስጥ መስመር ለማስፈራራት ሞከሩ፣ ለምን አስተያየት ሰጡ የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ ነገርግን ሁሉ ነገራቸው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ከዚያም የተረፈው ስድብ እና ሃሜት የተጠናወተው ዓይነት ጽሑፍ ስለሆነ ከዓላማችን ጋር አብረው የማይጓዙ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እነማን እንደሆኑ በውስጥ መስመር በጣም ጎበዝ የተዋሕዶ ልጆች ይህ እኮ እገሌ ነው ይሉኛል፡፡ በዚህም መሠረት ፕሮፋይላቸውን በማጣራት ደረጃ ብቁ እና ተገቢ የሆነ መረጃ አግኝቻለሁ፡፡
==============================================================

ይህ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ልጅ ዲ.ን በረከት ሞላ ይባላል፡፡ ይህ ልጅ በአባ ማርቆስ የዘመድ አዝማድ ዝርዝር ውስጥ ተራ ቁጥር 33 ላይ የተጻፈው ነው፡፡ እንዲያገለግል የቀጠሩት ደግሞ ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ደብረ ማርቆስ ውስጥ) በቀዳሽነት ነው፡፡ ተወልዶ ያደገው ጉንደወይን ሲሆን የአባ ማርቆስ የወንድማቸው ልጅ ነው፡፡ በዚህም “የጳጳስ ዘር መባል እንዴት ያኮራል መሰላችሁ” እያለ የሚመካ ትምክህተኛ ነው፡፡ ከታች የምትመለከቱት ፎቶ በራሱ ካሜራ ተነሥቶ በራሱ እጅ የለጠፈው ፌስቡክ ፕሮፋይሉ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህንን ፎቶ ለማውጣት የተገደድሁት “እባክህ መረጃ አለኝ የምትለውን ላከውና እንመልከተው ልማጸንህ” ባለኝ መሠረት ነው፡፡ እኔ በዚህ ደረጃ እንድወርድ ያደረገኝ ራሱ ልጁ ስለሆነ ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ ፎቶውን እዩት ከጀርባው የእመቤታችን ስዕል አለ እርሱ ግን እርቃኑን ነው፡፡ ምናልባትም ከሚኖርበት ቤት የተነሣው ፎቶ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶች አሁን ባለው የዘመናዊነት እና የተሐድሶአዊነት አስተሳሰብ ውስጥ ሆነው “ይመስለኛል፣ አይመስለኝም” የሚሉ ተወዛጋቢ ግለሰቦች አሉ፡፡ ይህ መዓርግ አስተያየት እንደሰጣችሁት ያለ አይደለም፡፡ በቤቱ የሆነ እንደሆነ እርቃኑን እየተነሣ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ ተፈቅዶለታል እንዴ፡፡ ወገኖቼ አስተውሉ! ይህን ጉዳይ “ቤቴ ውስጥ ደግሞ የፈለግሁትን ባደርግ ምን አገባችሁ” ተብሎ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም፡፡ ቤትህ ውስጥ ስለሆነ የተከለከለ ነገር ተፈቅዶልሃል ያለው ማነው፡፡ አስተያየት ሰጭዎች ያልተረዳችሁት እና ያልተገነዘባችሁት ነገር አለ፡፡ ይህን ፎቶ ስፖርተኛ ከመሆን ጋር ያያዛችሁት አላችሁ፣ ቤቱ ውስጥ የፈለገውን ቢያደርግ ምን አገባህ ያላችሁም አላችሁ፣ የግድ ነጠላ መልበስ አለበት እንዴ ያላችሁም አላችሁ በገሩ ግን ከሁላችሁም የራቀ ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 6 ቁጥር 222 ላይ “ከሰው ወገን ከማናቸውም ፊት ቄሱ ፈጽሞ አይራቆት፡፡ በችግር ጊዜ ካልሆነ በቀር” ይላል፡፡ ለቄሱ የታዘዘው ለዲያቆኑም የታዘዘ ነው፡፡ ችግር ካልገጠመው በቀር ቄስም ሆነ ዲያቆን (ክህነት ያለው ሰው ሁሉ) በሰው ፊት መራቆት የለበትም ይላል፡፡ ይህ ልጅ እንዲህ እርቃኑን የሆነው ችግር ገጥሞት ይመስላችኋል? ችግር ገጥሞት ከሆነ ምንም ማድረግ አይችልም የተፈቀደ ነው፡፡ ግን ችግር የገጠመው አይመስልም ዘና ብሎ ነው የተነሣው፡፡ ሌላው ይህ አንቀጽ የተናገረው “በሰው ፊት አይራቆት ብሎ ነው ታዲያ ልጁ በሰው ፊት መቼ ተራቆተ?” የምትሉም አትታጡም፡፡ ይኼው በእኛ ፊት ተራቆተ እኮ፡፡ ለዓለም እኮ ነው ይህን ፎቶ የላከው፡፡ ይኼውላችሁ ተራቆትሁላችሁ ብሎ እኮ ነው የላከልን፡፡ ታዲያ ፍትሐ ነገሥቱን ፍቃችሁ ታጠፉት፡፡ አብዛኛው አስተያየት ሰጭ አስተያየት የሰጠ ከዘመናዊነት እና ምን ችግር አለው ከሚል የሰነፎች አባባል የተነሣ እንጅ ከሕጉ አንጻር እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡

 
ሌላው ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 9 ቁጥር 324 “ቄስ ጠጥቶ ቢሰክር ቢራቆትም ሰባት ሱባዔ ይለይ፡፡ በዝቅተኛ መዓርግ አንድ ዓመት ይቀመጥ፡፡ እርሱ ይህን ታላቅ መዓርግ አዋርዷልና፡፡ ዲያቆን ቢሆን አምስት ሱባዔ ይለይ፡፡ በንፍቀ ዲያቆኑ አምሳል ለሹማምንቱ እያገለገለ አንድ ወር ይቀመጥ፡፡ አናጉንስጢስ ወይም ዐጻዌ ኆኅት ቢሆን ሦስት ሱባዔ ይለዩ፡፡ በቄሱ ትእዛዝ አንዲት ሳትቀር ዐርባ ጊዜ ይግረፏቸው” ይላል፡፡ አስቡት እንግዲህ እዚህ ላይ ከልብሱ የተራቆተ ዲያቆን የሚገባው ቅጣት ነው የተዘረዘረው፡፡ “ምን ችግር አለው” የምትሉ ወገኖች ችግሩ ይኼው ነው፡፡ ከልብሱ የተራቆተ ዲያቆን አምስት ሱባዔ ይለይ ነው ያለው፡፡ አሁንም ቢሆን “ጠጥቶ ቢሰክር ቢራቆትም ነው እንጅ ያለ ሳይጠጣ ከሆነ ምን ችግር አለው” ብላችሁ የምትሟገቱ አትታጡም፡፡ ሰክሮ ነፍሱን የማያውቅ ሰው እንዲህ ከተቀጣ ሳይሰክር በኅሊናው ያለ ሰው የሰከረ ሰውን ግብር ከፈጸመማ ምንኛ ቅጣቱ ይከፋበት፡፡ ስለዚህ ከልብስ መራቆት ለካህናትና ለዲያቆናት  ያስቀጣል፡፡

ወገኖቼ አስተውሉ! የቆረበ ሰው ከልብሱ ይራቆት ዘንድ የተከለከለ አይደለምን? ይህ ልጅ ዲያቆን ነው ያውም ቀዳሽ ዲያቆን፡፡ በዚህ መልኩ ተራቁቶ የተነሣውም ምናልባትም ቀድሶ ከወጣ በኋላ ይሆናል፡፡ (ይህንን ግን ሊሆን ይችላል በሚል አልናገርም አምላክ እርሱ ይወቀው እንጅ)፡፡ ቤትህ ውስጥ ይህን ፎቶ ተነሣ እሽ ችግር የለውም እንበል ለአደባባይ ግን እዩልኝ ብሎ መልቀቅ ምን ይሉታል? አንዳንድ ጊዜማ ጭፍን የሆነ አስተያየት አትስጡ አመዛዝኑ፡፡ ምእመን ቢሆን ይህን ያህል ባይመለከተንም ነበር ይህ ልጅ እኮ ቀድሶ ደሙን የሚያቀብል ዲያቆን ነው፡፡ ይህን ልጅ ያየ ሰው “የምቅደሱ ቦክሰኛ” ነው በማለት ገልጾታል፡፡ ትክክለኛ አገላለጽ ነው!!! አዎ አቡነ ማርቆስ ከገጠሪቱ የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አምጥተው የወንድማቸው ልጅ ስለሆነ ብቻ ደብረ ማርቆስ ከተማ ያውም ዋሻው ቅዱስ ሚካኤል ቀዳሽ ብለው የቀጠሩት ቦክሰኛ ነው፡፡ ይህ መረጃ ለሁሉ ለእናንተ እንዲደርስ ብየ እንጅ እኔ ከመቅደሱ አገልግሎት ጀምሮ እስከ ማኅሌት ድረስ ከዚያም እስከ ዐውደ ምሕረት ድረስ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ አብሬው ስለማገለግል በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ ለመጻፍ ያነሣሣኝ ቅናት ምቀኝነት ጥል ክርክር ወዘተ አይደለም!!! አቡነ ማርቆስ እንዲህ ያለውን ቦክሰኛ ነው ቀዳሽ ዲያቆን ብለው የቀጠሩብን፡፡ ስንት ዲያቆን ቦታ አጥቶ ተቀምጦ ለምን ቦክሰኛ ሰው ቀጠሩብን ብሎ መጠየቅ ለእኔ ምቀኛ አያስብልም ባይ ነኝ፡፡

ሁለተኛው ፎቶ ግራፍ ደግሞ ጡንቻውን የሚያሳይበት ቦክስ የሰነዘረበት ነው፡፡ ይህን ፎቶ አንሥቶ በራሱ ገጽ ላይ የለጠፈው ራሱ ነው፡፡ እኔ ይህን ልጅ ፎቶ ለማንሣት የደከምኩበት የለፋሁበት ምንም ጊዜ የለም፡፡ ነገር ግን አማረብኝ መስሎት ራሱ አንሥቶ በራሱ ገጽ ላይ ለጥፎታል፡፡
ሦስተኛው ፎቶ ደግሞ ክላሹን ደግኖ የተነሣበት ፎቶ ነው፡፡ እዚህ ላይ የወታደር ሥልጠና እየወሰደ በሚመስለው ፎቶ ውስጥ እንደ አንድ አገልጋይ ዲያቆን ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት ምን እንደሆነ አይታወቅም፡፡

ደግነቱ ባለፈው እርቃኑን የተነሣውን ፎቶውን ለህዝብ ይፋ ካደረግሁት በኋላ በጣም በመደናገጥ ምን ላድርግ ብሎ ጓደኞቹን ሲያማክር በፍጥነት እንዲያነሣው ስለነገሩት በዚያ መሠረት ፎቶዎቹን ከገጹ ላይ አንሥቷቸዋል፡፡ በጣም ደስ የሚል ትልቅ ሥራ ሠርተናል ማለት ነው፡፡ ቢያንስ እርቃኑን ተነሥቶ ፎቶ የሚለጥፍ ዲያቆን እያሉ ሰዎች እንዳይሰድቡት አድርጓል፡፡
=====================================
አንብባችሁ ከጨረሳችሁ አስተያየት #comment ስጡ
#share አድርጉ፡፡

No comments:

Post a Comment