Tuesday, October 9, 2018

«Recycle Bin»



በኮምፒዩተር ትምህርት ቋንቋ መሠረት «Recycle Bin» ትርጉሙ ከፍተኛ ነው። አንድን ነገር እንሠራለን ከሠራንም በኋላ ቦታ እንዳይዝብን በማሰብ እናጠፋዋለን «Delete» እናደርገዋለን። «Delete» ማድረግ በራሱ ችግር አይደለም ምክንያቱም አንደኛ ቦታ ስለሚይዝብን ኹለተኛም ካጠፋነው የተሻለ ለመሥራት በማሰብ ነውና። በዚያውስ ላይ የጠፉ ፋይሎች የሚታገቱበት «Recycle Bin» የተባለ የጠፉት መገኛ እያለ ምን ችግር ሊመጣብን ነው። ችግር የሚኾነው «Undo» ብለን ወይም «Restore» አድርገን መመለስ በማንችልበት መልኩ ፋይሎችን ካጠፋናቸው ነው። ለዚኽም እኮ ነው የ «IT» ተማሪዎች «Undo» ባትኖር ኖሮ እኮ አንመረቅም ነበር ይላሉ የሚባለው። በስህተት እናጠፋለን በስህተት ያጠፋነውንም ነገር በ«Undo» እና በ«Restore» እንመልሳቸዋለን።
ነገር ግን በ«Undo» እና በ«Restore» እንዳይመለስ አድርገን «Permanently Delete» ካደረግነው በራሳችን ስናዝን ከመኖር ውጭ የጠፉትን ኹሉ መመለስ አንችልም። አውቀንም ኾነ በስህተት «CTRL+DEL»ን ከተጫንነው ፋይላችንን «Recycle Bin» ከተባለው የጠፉት መሰባሰቢያ ካምፕ ላይ አናገኘውም። በዚኽም የተነሣ ለአንድ ቀንም ቢኾን እንኳ ያ ያጠፋነው ፋይል አስፈላጊ ኾኖ ብናገኘው ጸጉራችንን ከመንጨት ከንፈራችንን ከመምጠጥ ውጭ ነበረን እኮ ከማለት ውጭ «Undo» እና «Restore» እንኳ ተባብረው ሊመልሱት አይችሉም።
አሁን ስለ ኮምፒዩተር እያስተማርኩ እንዳይመስላችሁ ስለራሳችን ስለሥራችን ስለተግባራችን እንጅ። አንድ ሰው ወንጀል ሊሠራም ላይሠራም ይችላል፣ በኾነ ምክንያት ብቻ «Permanently Delete» እንዲደረግ ይፈረድበታል። ማን እንደሚፈርድበት እንኳ አይታወቅም ብቻ የኾነ አካል «Permanently Delete» አድርጎት ዳግም ላናገኘው እንሰናበተዋለን። በዚህ መልኩ በርካታ ለሀገር ለወገን የሚጠቅሙ በርካታ ሰዎችን አጥተናል። እነ በላይ ዘለቀ፣ እነመንግሥቱ እና ግርማሜ ንዋይ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አቡነ ሚካኤል፣ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ፣  እነቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ እነበዓሉ ግርማ፣ እነ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ፣ እነ ሳሙኤል አወቀ ወዘተ ወዘተ። በነገራችን ላይ ዘርዝሬ መጨረስ እንደማልችል አውቃለሁ ግን የተወሰኑትን በየዘመናቱ «Permanently Delete» የተደረጉ ሰዎችን ነው የጠቀስሁላችሁ። እነዚህ ሰዎች በማን «Permanently Delete» እንደተደረጉ እንዴት እንዲጠፉ እንደተደረጉ የሚታወቅ ነገር የለም። በርግጥ በስቅላት እና በጥይት ተደብድበው በሰው ፊት በአደባባይ «Permanently Delete» የተደረጉትን ማን እንዳጠፋቸው እናውቃለን። ታሪክም መዝግቧቸው ስለሚገኝ በዚያ እናውቃለን። አብዛኞቹ ግን በማን እንዴት እንደጠፉ በራሱ አይታወቅም።
እኛ ሰዎች ነን። ዘመናችን ከዚህ እስከ እዚህ ተብሎ የተገደበ፣ ቋሚ ኾኖ ለዘለዓለም የሚኖር ዘላለማዊ ሰው እንደሌለም እናውቃለን። ታዲያ አንዱ አንዱን ያጠፋው ዘንድ ምን ዓይነት ሰይጣን ነው የመከረው? ይችን አጭር ዘመን መታገስ እንዴት ያቅተናል? አንተ አጠፋኸውም አላጠፋኸውም አንተም እርሱም በኾነ ዘመን ላይ ሳትወዱ በግድ መጥፋታችሁ አይቀርም እኮ። ታዲያ የኾነ ጊዜ ላይ ያ ያጠፋነው ሰው ለሰው ለወገን ቢያስፈልግ «Undo» እና «Restore» አድርገን ልንመልሰው እንዴት እንችላለን?
ሰዎች ነንና እናጠፋለን፣ እንሳሳታለን፣ ሕግ ልንጥስ ሥርዓት ልናፈርስ እንችላለን። ነገር ግን ይህ ጥፋት ኾኖ ቢገኝ እንኳ ማሰር እንጅ መግደል መፍትሔ ይኾናል ብየ አላስብም። የታሰሩ ሰዎች «Recycle Bin» ውስጥ እንደሚገኙ የጠፉ ፍይሎች ይቆጠራሉ። እነዚኽ በእስር ቤት የሚገኙ ሰዎች ለሀገር ለወገን አስፈላጊ ኾነው ቢገኙ ባስፈለጉ ሰዓት ከእስር «Undo» እና «Restore» በማድረግ ፈትቶ ማሠራት ይቻላል። እነ በላይ ዘለቀ፣ እነመንግሥቱ እና ግርማሜ ንዋይ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ፣ እነ አቡነ ሚካኤል፣ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ፣  እነቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ እነበዓሉ ግርማ፣ እነ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ፣ እነ ሳሙኤል አወቀ ወዘተ ወዘተ «Recycle Bin» በተባለ እስር ቤት ቢኾኑ ኖሮ ዛሬ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሀገሪቱ መንግሥት በወሰነበት ጊዜ በቀላሉ ከእስር ፈትቶ ለሀገር ለወገን በጠቀሙ ነበር። ነገር ግን ዳግም «Undo» እና «Restore» አድርገን እንዳናገኛቸው ኾነው  «Permanently Delete» ተደርገዋልና ከንፈር ከመምጠጥ ጸጉር ከመንጨት ያለፈ ነገር ልናደርግ አንችልም። ዛሬ አያስፈልገንም ብለን ያጠፋነው ፋይል ነገ እንደሚያስፈልገን ስለምናውቅ «Recycle Bin» ውስጥ እንደምናጠራቅመው ኹሉ ዛሬ አጥፍተዋል ወንጀለኞች ናቸው የምንላቸውን ሰዎችም ነገ አስፈላጊ ስለሚኾኑ እስር ቤት ውስጥ ብናጠራቅማቸው ይሻላል። ከእስር ቤት ውጡ በሚል ቃል ብቻ ማስወጣት ይቻላልና «Permanently Delete» የተደረጉ ፋይሎችን ዳግም መመለስ እንደማንችል ኹሉ ማን እንደኾነ እንዴት እንደኾነ ሳይታወቅ ሰውንም በሞት ማስወገድ ለነገ ቁጭትን የሚፈጥር ስለኾነ እንደ ሰው አስበን ብንኖር መልካም ነው።
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
መልካሙ በየነ
ግንቦት ፫/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍

የርክበ ካህናት ሲኖዶስ እና ተስፈኛው ተጓዥ

በሕገ ቤተክርስቲያናችን መሠረት የቤተክርስቲያናችን ወሳኝ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ኹለት ጊዜ ለቤተክርስቲያናችን ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ለመወሰን ጉባዔ ያደርጋል። በዚኽ መሠረት ነው በርክበ ካህናት የሚጀመረው የዘንድሮው ዓመት ኹለተኛው ሲኖዶስ ስብሰባ ነገ የሚጀመረው። ነገ ረቡዕ ሚያዝያ ፳፬/፳፻፲ ዓ.ም በሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የቤተክርስቲያናችን ዐበይት ጉዳዮች እንደሚዳሰሱበት እናምናለን። የቅዱስ ሲኖዶስን ስብሰባ ተከትሎ የአባትነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማሳሰብ በርካታ ተስፈኛ ተጓዦች በጸሎቱ መርኃ ግብር እየተገኙ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በተለይ የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ከተስፈኛ ተጓዦች መካከል ወደር ያልተገኘላቸው መኾናቸው የታወቀ ነው። አቡነ ማርቆስ ምሥራቅ ጎጃምን ከተቆጣጠሩበት ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚሰበሰብባቸው ጉባዔያት ኹሉ አቤቱታውን ሳያሰማ ቀረበት ቀን ያለ አይመስለኝም። የሚያሳዝነው ጉዳይ ግን ጆሮ የሚሰጥ አካል አለመገኘቱ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሰበሰብ ለማሳሰብ ብቻ ሳይኾን ከስብሰባ በፊትም የምእመናን ተወካዮች ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት እየሄዱ ስለአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን አቤት ማለታቸው የአደባባይ ሐቅ ነው። ስለቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነት ሲሉ ስለምእመናንም ድኅነት ሲሉ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አንድ እልባት መስጠት ቢችሉ ምንኛ በተደሰትን ነበር። ግን አልኾነም።
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ላይም በመደገፍ እና በመቃወም ላይ በኹለት ሐሳብ ተከፍለው የሚታዩ ናቸው። ፓትርያርኩ፣ አቡነ ማርቆስ፣ አቡነ ቶማስ፣ አቡነ አረጋዊ በአንድ መስመር ለጥፋት ሌሎችም እንደ እነ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ አቡነ ቀውስጦስ፣ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ አብርሃም፣ አቡነ ኤልሳዕ ወዘተ የመሳሰሉት ደግሞ በሌላ መስመር ለምእመናን ድኅነት ተሰልፈዋል። በእርግጥ ወደየትኛው ማዘንበል እንዳለባቸው ግራ ተጋብተው መሐል ላይ ያሉም አይታጡም። ያም ኾነ ይህ ግን መንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ለጥፋት የሚሮጡትን አፋቸውን እየከፈተ ፊታቸውንም እየጸፋ ለምእመናን ድኅነት ወደሚተጋው እውነተኛ መንገድ መምጣታቸው አይቀርም የጊዜ ጉዳይ እንጂ።
አቡነ ማርቆስ ከምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ጋር ሳይግባቡ ይኼው ፮ ዓመታት ተቆጠሩ። ይህን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይፈታው ዘንድ ምእመናን በራሳቸው ወጭ ብዙ ጊዜ ተመላልሰዋል። የዛሬው ጉዞ ፲፩ኛ መኾኑ ነው እንግዲህ። መናፍቃን በቤተክርስቲያናችን ካደረሱት ፈተና ይልቅ አቡነ ማርቆስ ያደረሱባት በደል የከፋ ነው። ይህን የተረዳው ቅዱስ ሲኖዶስ በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ይህ ኹሉ ችግር እንዲፈታ አጣሪ ኮሚቴ ወደቦታው እንዲሄድ መወሰኑ አይዘነጋም። ሆኖም ግን ለብር እንጅ ለቤተክርስቲያናችን ክብር የማይጨነቅ አባል የኮሚቴው አባል ኾኖ መምጣቱ ጉዳዩን የከፋ ማድረጉ አይዘነጋም። ምእመናንን ሳያወያይ ከቤተክርስቲያን ሳይኾን ከአቡነ ማርቆስ ደጋፊዎች ጋር ብቻ ተወያይቶ ያንን ወስዶ ለጠቅላይ ቤተክህነት በዘገባ መልኩ ማቅረቡ ይታወሳል። የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ብጹእ አቡነ ዲዮስቆሮስ ግን አጣሪ ኮሚቴው ባሳየው ኢክርስቲያናዊ ተግባር ማዘናቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም። ወደቦታው ሌላ አጣሪ ኮሚቴ እንደሚላክም አሳስበው ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነበር የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በሚቀያየሩበት የመጨረሻው ቀን ላይ አቡነ ማርቆስ የእኔ ጉዳይ ከዚህ በኋላ እንዳይታይ አጀንዳየ እንዲዘጋልኝ እጠይቃለሁ በማለት እርሳቸው አባል በነበሩበት የመጀመሪያው ቋሚ ሲኖዶስ አቤቱታ ያቀረቡት። ሆኖም ግን ይህ ጉዳይ በምልዓተ ጉባዔው እንጅ በቋሚ ሲኖዶሱ መታየት አይገባውም በሚለው የአቡነ ሳዊሮስ (የሲኖዶስ ጸሐፊ) ሰፊ ክርክር ተደርጎበት ስብሰባው ያለስምምነት ተበትኖ እንደቀረ የታወቀ ነው። እንዲያውም ቃለጉባዔውን ይጽፍ የነበረው ሰው የእርሳቸው ጉዳይ እንደተዘጋ አድርጎ ቃለጉባዔውን ጽፎ ሳያነቡ እንዲፈርሙ አድርገው ነበር። ነገር ግን ስለቤተክርስቲያናችን ተግተው እየሠሩ የሚገኙት ብጹእ አቡነ ሳዊሮስ ቃለ ጉባዔውን አስነብበው በውይይታቸው ያልተካተተ ሐሳብ ተካቶ ስላገኙት ቃለጉባዔውን ሳይፈርሙ እንደወጡ የታወቀ ነው።
ተስፈኛው ተጓዥ የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ዛሬም እልህ አስጨራሹን ረዥም መንገድ እየተጓዙት ነው። ፲፩ኛውን ጉዞ ዛሬ በምእመናን ተወካዮች ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እያደረገ ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም ይህን ስለአንዲት ቤተክርስቲያን ለ፲፩ኛ ጊዜ እየደከመ ያለውን ምእመን መልካም አቀባበል ያደርጉለታል ተብሎ ይጠበቃል። አባቶቻችን ሆይ በደሙ ስለገዛን ስለክርስቶስ ኢየሱስ ብላችሁ የቤተክርስቲያናችንን ጉዳይ በትኩረት ተመልከቱት። ምሥራቅ ጎጃም የቀደመ ክብሩን የቀደመ ማንነቱን ሃይማኖታዊ ተግባሩን በሚገባ እንዲፈጽም እንቅፋት የኾኑትን ኹሉ እንድታስወግዱልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። እንቅፋቶቹ ብዙዎች ናቸው በጣም ብዙዎች እንደእኛ ግን አቡነ ማርቆስ ትልቁ እንቅፋታችን ኾነዋል። ይህንን ለ፲፩ኛ ጊዜ የሄደውን የምእመናንን ተወካዮች ጉዞ ተከትሎ የአቡነ ማርቆስ ደጋፊዎች (በግድ እንድትመጡልኝ የተባሉት) ነገ መሄዳቸው አይቀርም። እነርሱ በቤተክርስቲያን በጀት ቤተክርስቲያኒቱን ለማጥፋት ይተጋሉ የምእመናን ተወካዮች ደግሞ ከኪሳቸው በሚያወጡት ገንዘብ ቤተክርስቲያንን ይታደጋል። እግዚአብሔር ያሸንፋል አንጠራጠርም። የተስፈኛው ተጓዥ አሁንም እየተጓዘ ነው። አበው ሊቃነ ጳጳሳትም መልካም አቀባበል ያደርጉለታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። እግዚአብሔር አምላክ ስለቤተክርስቲያናችን ሲል መልካሙን ኹሉ እንዲያሳስባቸው እንለምናለን።


✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
መልካሙ በየነ
ሚያዝያ ፳፫/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍

Friday, April 27, 2018

የቁጥሮች ምክር ቤት


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በአንድ ወቅት የቁጥር መስመር የተባለው የቁጥሮች አለቃ ቁጥሮችን ለስብሰባ ጠራቸው። የስብሰባው ዓላማ የዜሮን የማንነት ጥያቄ ተቀብሎ በዚያ ላይ በሰፊው ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ ነበር። ቁጥሮች በሙሉ ተሰብስበዋል። ጎደሎ ቁጥሮችም (ኢ ተጋማሽ)፣ ሙሉ ቁጥሮችም (ተጋማሽ) አዎንታ ቁጥሮችም አሉታ ቁጥሮችም ክፍልፋዮችም ዐሥርዮሾችም ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ታዳሚዎች ኾነዋል።
ሰብሳቢው ወደተዘጋጀለት ወንበር እያመራ ነው። ቁጥሮች ኹሉ ተነሥተው አጨበጨቡለት ላንቃቸው እስኪላቀቅ ድረስ አፏጩለት። እርሱም እጁን ከፍ አድርጎ እንደሚባርክ ሊቀ ጳጳሳ እጁን አንሥቶ ፉጨታቸውን እና ጭብጨባቸውን መቀበሉን አረጋገጠ። ኹለት እጁን ሲያነሣ ለተመለከተው ግን ደህና ሁኑ ብሎ አውሮፕላን ውስጥ የሚገባ ባለሥልጣን ይመስል ነበር።
ሰብሳቢው ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ ኹሉም ጭብጨባ እና ፉጨታቸውን አቁመው አዳራሹን በጸጥታ አስወረሩት። ሰብሳቢው የድምጽ ማጉያውን ተረከበና ስብሰባውን እንዲኽ ሲል ጀመረ።
«የተከበሩ የአዎንታ ቁጥሮች ተወካይ፣
የተከበሩ የአሉታ ቁጥሮች ተወካይ፣
የተከበሩ የክፍልፋይ ቁጥሮች ተወካይ፣
የተከበሩ የዐሥርዮሽ ቁጥሮች ተወካይ፣
የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፣
ክቡራን እና ክቡራት ከኹሉ አስቀድሜ ምንም ስለኾነችው ቁጥር የማንነት ጉዳይ ላይ ለመወያየት ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁ በእኔና በቁጥሮች ማኅበር ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን ሳቀርብ በታላቅ ደስታ ነው»
አዳራሹ በጭብጨባ በፉጨት ተናጠ።  በተለይ ዜሮ ብሎ በስሟ በመጥራት ፈንታ «ምንም ስለኾነችው ቁጥር» ብሎ ነገር ባስረዘመበት የሰብሳቢው ንግግር ተደስተዋል። ነገሩ የረዘመ ቢኾንም እንዲኽ ባለ ሰፊ የውይይት መድረክ ላይ «ምንም» መባሏ በሰብሳቢው በኩል እንኳ ሳይቀር የቁጥር ማንነቷ እንዳልተረጋገጠ ወደፊትም እንደማይረጋገጥ ማሳያ ኾኗልና ነው።
ሰብሳቢው ቀጠለ «ዛሬ ለዚኽ ውይይት መጠራት ዋና ምክንያት የኾነው የዜሮ የቁጥር ማንነት ነው። በቁጥሮች የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉዳዩ ታይቶ እልባት እንዲሰጣት ጠይቃለች። በዚኽም መሠረት ዜሮ ቁጥር የመኾን እና ያለመኾን ከማኅበራችን ጋር የመቀላቀል እና ያለመቀላቀል ውሳኔ በማሳረፍ ከዚኽ በኋላ የማያዳግም ምላሽ መስጠት ይጠበቅብናል» አለ።
ታዳሚው ቅድም የተደሰተውን ደስታ ከመቅጽበት ተነጠቀ። ኹሉም ፊታቸውን ኮሶ አስመሰሉት። ዜሮ ምን ከዕቁብ ብትገባ ነው በዚኽ ኹሉ የቁጥሮች ማኅበር ላይ ስሟ የሚጠራ ተባባሉ ጎን ለጎን እየተያዩ።
ሰብሳቢው ቀጠለ «ጉዳዩ የኹላችን ነው። ጥቅምና ጉዳቱን አመዛዝናችሁ የዜሮን የማንነት ጥያቄ እልባት እንድትሰጡበት መድረኩን ለናንተ ዘርግቻለሁ። ሰፊ ውይይት አድርገን መልካም ውሳኔ እንደምናሳርፍ እተማመናለሁ። በሉ ከዚኽ በኋላ መድረኩ የእናንተ ነው» በማለት ለተሳታፊዎች መድረኩን ለቀቀ።
የአዎንታ ቁጥሮች ተወካይ ተነሣና ጎርነን ባለ የተንደላቀቀ ንግግር «እኛ የአዎንታ ቁጥር አባላት በዚኽ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይትና ምክክር አድርገናል። ዜሮ ማለት ምንም ባዶ ማለት ናት። ምንም የኾነች ባዶ ነገር ደግሞ ከእኛ ጋር አንድነት ሊኖራት አይችልም። እኛ አንድ ኹለት ተብለን እንቆጠራለን ዜሮ ግን ምንም ተብላ አትቆጠርም። እስኪ በኪሱ ብር ያልያዘ ሰው ይጠየቅ። ስንት ብር ይዘሃል ብለን ብንጠይቀው ምንድን ነው የሚመልሰው? ምንም አልያዝሁም ነው የሚለን። ሃምሳ ብር በኪሱ የያዘን ሰው ብንጠይቅ ግን ሃምሳ ብር ብሎ በስማችን ይጠራናል። ስለዚኽ ዜሮን የቁጥሮች አባል ማድረግ ምንም ረብ የለውም» አለ። ክፍሉ በፉጨትና በጭብጨባ ተናወጠ። የኹላችን ሃሳብ ነው ማለታቸው ነው።
ሰብሳቢው «ተጨማሪ ካለ» አለ።
የአሉታ ቁጥሮች ተወካይ ተነሣ «እኛ የአሉታ ቁጥሮች እንደ አዎንታ ወንድሞቻችን ኹሉ የዜሮ ማንነት ላይ ተመሳሳይ አቋም አለን። የተበደረ ሰው በእኛ ይገለጣል፣ ኪሣራ በእኛ ይገለጣል፣ ዝቅታ በእኛ ይገለጣል፣ ወደ ታች መውረድ በእኛ ይገለጣል እስኪ በዜሮ የሚገለጥ ነገር አሳዩን? ምንም የሚታይ የሚጨበጥ የሚዳሰስ ነገር የለም እኮ። ታዲያ በምን መስፈርት ነው ዜሮ የእኛ ማኅበር አባል ልትሆን የምትችለው? ስለዚህ በዜሮ ላይ ያለን አቋም ይኼው ነው» ብሎ ተቀመጠ።
የስብሰባ አዳራሹ አሁንም በፉጨት እና በጭብጨባ ተናወጠ።
ሰብሳቢው «ሌላ ተጨማሪ ሐሳብ ያለው» አለ።
የሙሉ ቁጥሮች (ተጋማሽ) ተወካይ ተነሣ «ዜሮ ምንም ናት ባዶ ናት። ይህንንም የምለው ዝም ብየ አይደለም በማስረጃ ነው። ዜሮ ከእኛ ጋር ተደምራ ፈቀቅ አታደርገንም ከእኛ ላይ ተቀንሳም ምናችንንም አትቀንሰውም። እንዲያውም ከእኛ ጋር ከተባዛችማ እኛን ጨምራ ነው ማንነት አልባ የምታደርገን። በጣም የሚገርማችሁ ግን በዜሮ ማካፈል ነውር መሆኑ ነው። ይህ እኮ ከጥንት ከመሠረቱ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የነበረ እውነታ ነው። ታዲያ ከእኛ ጋር ተባዝታ እኛን ጨምራ ማንነት አልባ እንድታደርገን የሚፈልግ ቁጥር አለ? ታዲያ ማንነት አልባ የምታደርገንን ዜሮ እንዴት ማንነቷን እናረጋግጥላት ይባላል?» አለ በቁጭት።
በፊት ከነበረው ጭብጨባ እና ፉጨት ይልቅ ተሳታፊው አሁን ይበልጥ አዳራሹን አናወጠው።
ዜሮ በማንነቷ ኩራቷ እየጨመረ መጣ። በማንነቷ ይበልጥ ኮራች። አዎንታም አሉታም ዜሮን ያናደዱ መስሏቸው ስሟን ላለመጥራት ሲጠየፉ ስትመለከት ዜሮ በማንነቷ ይበልጥ ኮራች። ራሷን የምታውቅ ኩሩ። እርሷ ምንም ተብላ ሌሎችን ምንም ከመባል የምትታደግ። እርሷ ተሰድባ ሌሎችን ከስድብ የምታወጣ። እርሷ ጥቅም አልባ ተብላ ሌሎችን ተጠቃሚ የምታደርግ። እርሷ እርባና ቢስ ተብላ ሌሎችን እንዲኽ ከመባል የምትሰውር ልዩ ቁጥር ዜሮ። ኹላቸው ስለነርሱ ግዝፈት እንጅ ውስጣቸው ስለተሠራበት ጥሬ ዕቃ ምንም አልተጨነቁም ምንም አላሰቡም ማሰብም አይሹም። ዜሮ ግን ከራሷ አልፋ ተርፋ የሌሎችንም ማንነት የገነባች ኩሩ ቁጥር ናት።
ሰብሳቢው ነገሩን በአጭሩ ለመቅጨት ስላሰበ ሌላ ተጨማሪ ዕድል መስጠት አላስፈለገውም ነበር። «ስብሰባችንን በዚሁ ብንጨርስና የዜሮን የቁጥር ማንነት በአጀንዳ ዘግተን በአዋጅ ብናጸድቀው ሳይሻል አይቀርም» አላቸው።
ሁሉም የሰብሳቢውን ሐሳብ እንደደገፉ ለማረጋገጥ በጭብጨባ እና በፉጨት አዳራሹን አናወጡት።
«ከዚያ በፊት ማንነት ጠያቂዋ ዜሮ ያላትን ሐሳብ ብታቀርብ» አለ ሰብሳቢው።
«በፍጹም በፍጹም በፍጹም» አለ ተሰብሳቢው በአንድ ድምፅ።
ስቅሎ ስቅሎ ስቅሎ ያሉትን የአይሁድ ካህናት አለቃ አስታወሱኝ። ጌታችን ያለበደሉ በፍርድ አደባባይ በቆመ ጊዜ የአይሁድ ካህናት ጌታችን ተሰቅሎ መሞት  እንደሚገባው ላንቃቸው እስኪላቀቅ ድረስ ስቀለው ስቀለው ስቀለው ብለው ነበር። ዛሬ ዜሮ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍም እንደዚያ ይመስል ነበር። ዜሮ ራሷን ማንነቷን አሳውቃ የሚቀበል ቢቀበላት የማይቀበል ባይቀበላት ምን ነበረበት? ዝም ብሎ መጮኽ፣ ዝም ብሎ መነፍረቅ፣ ሌሎች ሲያላዝኑ አብሮ ማላዘን ብቻ።
ዜሮን ከኋላቸው አስከትለው እነርሱ ከፊት በመቆማቸው ብቻ ቁጥር ሆነው የቆሙ የመሰላቸው ማንነታቸውን የማያውቁ ኅሊና ቢሶች በዝተዋል። 1፣10፣100፣1000፣10000 ወዘተ እነዚኽ ቁጥሮች ማንነታቸው ቢፈተሽ ከዜሮ ማንነታቸው ይልቅ በ1 ማንነታቸው ነው የሚኮሩ ግን ለምን? ከ 1 እና ከ 0 ለእነዚህ ቁጥሮች ትልቁ ማንነታቸው ማን ሆኖ ነው? ዜሮ በማንነታቸው ውስጥ ሰፊውን ድርሻ መያዟን በመዘንጋት «ምንም» «ባዶ» የሚለውን ስድብ ለማረፍ ብቻ በ 1 ማንነታቸው ይንጠራራሉ። እስኪ 0 ን ከእነዚህ ቁጥሮች ማንነት ውስጥ እናውጣት ሁሉም 1 ሆነው ይቀራሉ። 1 ወደ 10 ከፍ ልበል ካለች ከዜሮ ጋር መኖር የዜሮንም ማንነት መቀበል የግድ ይላታል። 1 ወደ 100 ከዚህም ወደ በለጠ ቁጥር ከፍ ለማለት የዜሮን ማንነት የግድ መቀበል ይገባል። ነገር ግን ይህን የራሳቸውን ማንነት ካለማወቅ የተነሣ የሌሎችን ማንነት ሲጨፈልቁ በአዳራሽ መካከል ሲያጨበጭቡ ሲያፏጩ ተመለከትናቸው። 99 ሲያጨበጭብ 100 ም ያጨበጭባል። 999 ሲያፏጭ 1000ም አብሮ ያፏጫል። ጎረቤትህን ሳይሆን ራስህን መስለህ መገኘት ካልቻልህ ከባድ ነው። አንተ እኮ 1000 ተብለህ ከ999 ገዝፈህ የታየኸው 0ን ከኋላህ ስላስከተልህ በዜሮ ማንነት ላይ ራስህን ስለገነባህ ብቻ ነው። ግን አላስተዋልኸውምና ዜሮ ምንም ናት ባዶ ናት ጥቅም የላትም ማንነትም የላትም ትላለህ።
ሰብሳቢው የአጀንዳውን ቃል አነበበ። «ዜሮ የተባለች የቁጥር ማንነት ፈላጊ ባመለከትችው ማመልከቻ መሠረት ዛሬ የተሰበሰበው የቁጥሮች ምክር ቤት በዜሮ የቁጥር ማንነት ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተለውን የማያዳግም የመጨረሻ ውሳኔ ወስኗል» አለ። የምክር ቤቱ አባላት የተወሰነውን ውሳኔ በጭብጨባ እና በፉጨት ለመደገፍ ተዘጋጅተዋል።
«ዜሮ ምንም ናት፣ ባዶ ናት፣ ጥቅም አልባ ናት በሚል ምክር ቤቱ የዜሮን የቁጥር ማንነት አልተቀበለውም። በዚህም መሠረት ዜሮ ቁጥር እንዳልሆነች ማንነቷም ተቀባይነት እንደሌለው በአዋጅ እንደነግጋለን። የዛሬውን የስብሰባ ውሎ በዚህ እንፈጽማለን» አለ።
የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ፣ እጃቸው እስኪያብጥ አጨበጨቡ ላንቃቸው እስኪላቀቅ ድረስ አፏጩ። ዜሮ ግን በብዙኃኑ ድምጽ በመረገጧ ሳታዝን በማንነቷ ኮርታ ከአዳራሹ ወጣች።
ያለዜሮ ማንነት የሚደምቅ ቁጥር ማነው? ዜሮ ጥቅም አልባ ናት የሚለው አረ ማነው? ዜሮ ባዶ ናት ምንም ናት የሚለውስ የቱ ነው? ቁጥሮች ዜሮን ያናደዱ መስሏቸው የማንነት ጥያቄዋን ውድቅ ቢያደርጉትም ለራቸው ህልውና ግን የዜሮ ማንነት ወሳኝ ቦታ አለው። ይህ ስብሰባ ላይ ብቻ አጀንዳ ለማርቀቅ አዋጅ ለማጽደቅ እንጅ መሬት ላይ ያለው እውነታ ይኼ አይደለም።
ከስብሰባው ወጥቶ ኹሉም የራሱን ኑሮ መኖር ጀመረ። ግን ከዜሮ ማንነት ጋር በተያያዘ እክል የገጠማቸው ነበሩ። እነዚኽ ቁጥሮችም በዜሮ ላይ የተገነቡ ዜሮን ከኋላቸው አስከትለው እነርሱ ከፊት የሚታዩ ቁጥሮች ነበሩ። 10፣20፣30፣40፣50፣60፣70፣80፣90፣100፣200፣300፣400፣500፣600፣700፣800፣900፣1000፣2000፣3000፣4000፣…፣100000000000000000000000000000000000000000 እና ሌሎችም ለንባብ እንኳ የሚያዳግቱ በዜሮ ማንነት ላይ የተገነቡ ቁጥሮች ያለዜሮ ምንም እንዳልሆኑ ገባቸው። 10 አንተ ማነህ ሲሉት ዐሥር ነኝ ይላል ዐሥርማ ማንነት ከሌላት ዜሮ ጋራ የተወዳጀ አይደለምን? እያሉ ይሳለቁበት ጀመር። በአዳራሽ አጨብጭበው ጥቅም አልባ ናት ማንነት የላትም ያሏት ዜሮ የራሳቸው ማንነት ሆና ተገኘች። 100ን ማነህ ሲሉ መቶ ነኝ ይላል። አንተማ ከኹለት 0ዎች ጋር የተቆራኘህ ማንነት አልባ ከሆነችው ጋር የተዛመድህ አይደለህምን? እያሉ ያሸማቅቁት ጀመር። በራሱ ፊርማ በራሱ ድምፅ በራሱ ፉጨት በራሱ ጭብጨባ የዜሮን ማንነት የነፈገው 100 ዛሬ የራሱም ማንነት 0 ሆና ስትገኝ ምን ይበል? ማስተዋል የጎደለው ግራ ቀኙን አይቶ የማይወስን የቁጥሮች ምክር ቤት ሁሉም የሚስቅበት ሁሉም የሚቀልድበት ሁሉም የሚሳለቅበት ሆነ።
0ን የያዙ ሁሉ ከትንሹ 10 ጀምረው መጨረሻው እስከማይታወቀው ቁጥር ድረስ የቁጥር መስመርን የዜሮ ማንነት ይረጋገጥልን ብለው ጠየቁ። በሰላማዊ ሰልፍ የዜሮ ማንነት ይረጋገጥ ብለው ጮኹ። ሰብሳቢው ግን አፋጣኝ ምላሽ አልሰጣቸውም ነበር። አሁንም መጡ በደብዳቤም ጠየቁ ምክር ቤቱ እንዲሰበሰብና የዜሮ ማንነት እንዲረጋገጥ ጠየቁ። ጩኸቱ የበዛበት ሰብሳቢ «የማያዳግም የመጨረሻ ውሳኔ ወስኗል» በማለት በአዋጅ ደንግጎ ከመውጣቱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንዲህ ያለ ቀውስ ሲመጣበት ጊዜ የምክር ቤቱን አባላት ሰበሰባቸውና በዜሮ ማንነት ላይ ድጋሜ ለመወያየት ተቀመጠ። ሁሉም ቁጥሮች በቦታቸው ተቀምጠዋል ሰብሳቢውም ተቀምጧል። ዛሬ ስብሰባው የሚደረገው 0 ስለጠየቀች አይደለም ሌሎች ስለጠየቁ ነው። ዜሮ ማንነቷ ስለተጨፈለቀ ቁጥርም አይደለሽም ተብላ ስለነበር በስብሰባው አልተገኘችም ነበር። «የዛሬው ስብሰባ የ0ን ማንነት ማጽደቅ ነው» አለ ሰብሳቢው። ውይይት ድርድር ክርክር የሌለው በቃ ማጽደቅ ብቻ። ሁሉም ወደ 0 መቀመጫ ተመለከቱ 0 ግን በቦታው የለችም።
«0 እኮ በቦታው የለችም ያለጥያቄዋ ለምን» አለ አንዱ አባል።
«0ማ ድሮ ጠይቃን ነበር እኛም ምላሽ ሰጥተናት ነበር። አሁን ግን ከእኛ መካከል በዜሮ ማንነት ማጣት የተነሣ የተጎዱ ቁጥሮች በመኖራቸው እነርሱ በጠየቁት መሠረት ነው የምናጸድቀው» አለ።  
«ማን ነው?» አለ አንዱ ተወካይ።
«ለምሳሌ10፣1000፣1000000፣1000000000000…» ወዘተ አለ ሰብሳቢው።
«እንዴ በ0 የተነሣ እነ 1000000000000ም ማንነታቸው ላይ ጥያቄ ፈጠረ? ይህ ከሆነማ 0ን እንቀበልና የቁጥር ማንነቷን እናረጋግጥላት» አሉ።
በሕጉ በአግባቡ የማንነት ጥያቄ የጠየቀችውን 0 አንሰማም ብሎ ማንነቷን የጨፈለቀው ምክር ቤት ዛሬ ግን በሌሎች ጥያቄ ማንነቷ ይጽደቅ ተባለ።
«የ0ን ማንነት የሚቃወም ካለ» ብሎ ሰብሳቢው ዕድሉን ለተሳታፊው ሰጠ። አንድ የሚቃወም ጠፋ።
ይገርማል ይሰቀል ሲሉ ይሰቀል ይሙት ሲሉ ይሙት በቃ ያለማመዛዘን የራስን ውሳኔ የማይወሰንበት የምክር ቤት ስብሰባ። ሁሉን ነገር በሙሉ ድምፅ ማጽደቅ ሁሉን ነገር ይፈጸም ማለት። ለድጋፍ ብቻ እጅ ማስቆጠር። አቤት ስብሰባ አቤት ውሳኔ።
ሁሉም የ0ን ማንነት በሌለችበት አጸደቁት። 0ን ማን እንደሆች የተረዱ በራሷ ጥያቄ ሳይሆን በሌሎች ጥያቄ ነው። በቃ ከእኛ ጋር ተባዝታ እኛን እንደርሷ ታድርገን፣ ከእኛ ጋር ትደመር ከእኛ ላይ ትቀነስ በቃ ችግር የለውም ተባለላት። 0ንም ያከበሩ ስለመሰላቸው ማንነቷን የተቀበሉበትን አጀንዳ በወርቅ ቀለም ጻፉት።
በሕይወታችን ራሳችንን ችለን ግራ ቀኙን አመዛዝነን ውሳኔ መስጠት ካልቻልን ራሳችንን እንጎዳለን። ማንነትህ የራስህ ነውና ሰው ባይቀበልልህም አትዘን ይልቁንም ተደሰት እንጅ። 0 ማንነቷን ሲጨፈልቁባት ምንም አልተበሳጨችም በደስታ ከስብሰባው ወጣች እንጅ ምክንያቱም ማንነቷን ራሷ ታውቃለችና አሁን ግን በግድ ተለምና ማንነቷን በወርቅ መዝገብ ላይ አስጻፈች። በዚህ ትዕግስቷም ማንም ማንነቱ ቀድሞ የተረጋገጠለት ቁጥር ባልተጻፈበት ወርቅ ቀለም ለመጻፍ በቃች።
መልእክቱ ምንድን ነው? ለሚል ሁሉ መልእክቱ አሁን አንብበህ ስትጨርስ የተረዳኸው ነገር ነው።
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
መልካሙ በየነ
ሚያዝያ ፲፱/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍

Friday, March 23, 2018

ተአኪያሁ!

  ======= ======= ======= ======= =======

ታኦጎሎስ የተባለው ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ብሎ የካደውን ንስጥሮስን ከቊስጥንጥንያ ቤተክርስቲያን ያሳደደበት ድርሳኑ ነው ተአኪያሁ! ትርጓሜውም “የወላዲተ እግዚአብሔር ማርያም ድርሳን” ማለት ነው። በዚህ ድርሳኑም ታላቁ ሊቅ እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ ያመሰግናታል፦

Thursday, February 8, 2018

ቅብዓት ባሕለ ትምህርት ወይም ምሥጢር ነውን?



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

አውቀናል በቅተናል የሚሉ የቅብዓት አስተማሪዎች ቅብዓት ምስጢር ነው ባህለ ትምህርት ነው እንጅ ሃይማኖት አይደለም ይላሉ፡፡ ካሳሁን ምናሉ የተባለው የመሠረተ ሐይማኖት መጽሐፍ ጸሐፊ ግን እውነቱን እንዲህ ሲል ተናግሮታል፡፡ “የናንተ የሆነ አሐዳዊ መጽሐፍ የላችሁ ጳጳስ የላችሁ እዚህ በሃይማኖት በኩል አናሳ የምንባለው ግፍና መከራ ዛሬ እንሆ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ይኸው መሠረተ ሐይማኖት መጽሐፍ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ” ይላል፡፡ ስለዚህ ቅብዓት የእምነት ስም እንጅ ባህለ ትምህርት ወይም ምሥጢር አይደለም፡፡ ምስጢር ነው እንዳንል በቤተክርስቲያናችን የምናውቃቸው ምሥጢራት አምስቱ አእማደ ምሥጢራት እና ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡
እነዚህም

Wednesday, January 31, 2018

ገዳም እና ሰንበት ትምህርት ቤት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በዚህ ርእስ ላይ የምንመለከተው ሰንበት ትምህርት ቤት እና ገዳማትን በተመለከተ ስላላቸው ዝምድና ይሆናል፡፡ ለጽሑፌም ማስረጃ የማደርገው የቤተክርስቲያናችንን መተዳደሪያ ደንብ ቃለ ዓዋዲ ይሆናል፡፡ የምጠቀመው ቃለ ዓዋዲም አዲሱን ባለፈው ዓመት በ፳፻፱ ዓ.ም ለዐራተኛ ጊዜ የተሻሻለውን ይሆናል፡፡

ቃለዓዋዲው ሰንበት ትምህርት ቤት እንዴት ለምን የት በማን ለማን ሊቋቋም እንደሚገባው የሚናገረውን ያህል ስለገዳማትም እንደዚሁ በማብራራት ይናገራል፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ስለገዳማት ቃለ ዓዋዲው የሚለውን እንመልከትና በመቀጠልም ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት እንመለከታለን፡፡

Sunday, January 28, 2018

ጾመ ነነዌ እና የድንግል ማርያም በዓለ እረፍት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ጾመ ነነዌ እና የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም በዓለ እረፍት አንድ ላይ ተገጣጥመዋል፡፡ ነነዌ ከጥፋት የዳኑበት ዕለት የአዳም ተስፋ ከሆነችው ከድንግል ማርያም እረፍት ጋር አንድ ላይ ተገናኝተዋል፡፡ ጾመ ነነዌ ከዐቢይ ጾም ፪ ሳምንታት ቀደም ብሎ ለሦስት ቀናት /ከሰኞ እስከ ረቡዕ/ ድረስ የሚጾም ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ከመጣባቸው የእግዚአብሔር ቁጣ የዳኑበት በመሆኑ እኛም ከሚመጣብን ፈተና ሁሉ እንድን ዘንድ፣ ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ እንድንና እናመልጥ ዘንድ አምነን እንጾመዋለን፡፡ ሙሉ ታሪኩን /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ተመልከት/ ይህ ጾም የዐዋጅ ጾም መሆኑን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭ ቁጥር ፭፻፷፯ ላይ “…የነነዌ ሰዎች ጾም ፫ ቀን…” ብሎ ይናገራል፡፡ ይህ ጾምም እንደ ዐቢይ ጾም በመጠንቀቅ እንዲጾም ያዝዘናል፡፡


Monday, January 22, 2018

ወልዲያን ሳስብ ደብረ ማርቆስ መጣብኝ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በዓለ ጥምቀት በዓለ ቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩን የለወጠ ክስተት ነው የተፈጸመው፡፡ ወልዲያ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት ራሳቸውን ስተው ወድቀዋል ምእመናን ከታቦቱ ፊት ነፍሳቸውን ሰጥተዋል፡፡ የዚህን ክስተት ሙሉ ኃላፊነት ቤተክርስቲያናችን መውሰድ ይገባታል፡፡ ምክንያቱም የበዓላት ሥነሥርዓት አስከባሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሰበካ ጉባዔ እያለ ከሰበካ ጉባዔው ቁጥጥር በላይ የሆነ አንዳች ችግር ሳይፈጠር የመንግሥትን ጸጥታ አስከባሪዎች ወደቦታው መጥራት አስፈላጊ ስላልነበር ነው፡፡ ሕገመንግሥቱ ሃይማኖት እና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው ሃይማኖት በፖለቲካ ፖለቲካም በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ብሎ በደነገገበት ሁኔታ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ከታቦቱ ፊት እንዲገኙ ማድረጋቸው የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች ያስተቻል፡፡

Tuesday, January 16, 2018

ውግዘት በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ሰስብከት በበርካታ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል የተሞላ ሀገረ ስብከት ነው፡፡ ታዲያ ይህን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል ተመልክቶ ዝም ማለት ለተዋሕዶ ልጆች አላስቻላቸውም ነበርና የሚጠበቅባቸውን የልጅነት ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ በርካታዎች ታስረዋል ተደብድበዋል ተንገላተዋል ተጉላልተዋል ተርበዋል ተጠምተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን አያሳስባቸውም ምክንያቱም ትግላቸው ዘላለማዊ ርስትን ስለሚወርሱባት ሃይማኖታቸው ሲሉ ነውና፡፡ ህጋዊውን መንገድ ተከትለው ተስፋ ባለመቁረጥ በልበ ሰፊነት ከሰባት ጊዜ በላይ በግል ወጫቸው አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤት ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን አጥጋቢ መልስ ማግኘት አልተቻለም፡፡

አጣሪ ኮሚቴ ተብሎ በብጹእ ሥራ አስኪያጁ ተልከው የነበሩት ሦስቱ ልዑካንም የእግዚአብሔርን ነገር ትተው ራሳቸውን በይሁዳ መስመር አገኙት፡፡ ይሁዳ እግዚአብሔርን ለአይሁዳውያን ጠቁሞ ስሞ አሳልፎ ይሰጠው እንደሆነ እንጅ ሐዋርያትን መስሎ ከጎኑ አይቆምም፡፡ የእነዚህ የልዑካኑ ጉዳይም እንዲሁ ሆኖ ነው የተገኘው፡፡

Wednesday, January 3, 2018

ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብጹእ አቡነ ዘካርያስን እረፍት ነስቷቸዋል



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ብጹእ አቡነ ዘካርያስን የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ወቅታዊ ሁኔታ ከማንም በላይ አሳስቧቸወል፡፡ ብጹእነታቸው አንድ ሊቀ ጳጳስ በሌላው ሀገረ ስብከት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህግ ሳያውቁ እንዳልሆነ ለቅዱስ ፓትርያርኩ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ገልጠዋል፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ጉዳይ እጅጉን ያሳሰባቸው በጎጃም ተወልደው ያደጉ በዚያው የተማሩ ያስተማሩ በሊቀ ጳጳስነትም ደረጃ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው ብዙ ዲያቆናትን እና ካህናትን ክህነት የሰጡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ሃይማኖትን ደግሞ አድማስ እንደማይገድበው በመግለጽ ጭምር ነው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ የጻፉ፡፡






Sunday, December 31, 2017

ደብረ ምሕረት የረቦ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የረቦ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደጀን ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ከደጀን ከተማ በምሥራቅ አቅጣጫ ሃያ ሰባት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወደቦታው ለመሄድ ለሚፈልጉ ሰዎች ከደጀን ከተማ ተነሥተው ጉባያ በሚለው መኪና ገብተው ቦታውን ያለምንም ችግር ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንደአሁኑ መኪና ሳይኖር ግን ከሦስት ሰዓት እልህ አስጨራሽ የእግር ጉዞ በኋላ ነበር ቦታው የሚገኘው፡፡ ቦታው ጥንታዊ ቦታ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን መዛግብትን ማገላበጥ አባቶችንም መጠየቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ ስለሆነ የተመሰረተበትን ቀን እንዴት እንደተመሠረተ ሙሉ ታሪኩን መናገር አልችልም፡፡ እኔም በቦታው ተወልጀ ያደግሁ መሆኑን እንጅ ጥንታዊነቱን ጠይቄም ሆነ መዛግብትን አገላብጨ አላውቅም፡፡ ሆኖም ግን መዛግብትን ማገላበጥ አባቶችን መጠየቅ እንደሚኖርብኝ አውቃለሁ፡፡ ከቤተክርስቲያኑ በታች የሚገኘው ዋሻ ጥንታዊ የቤተክርስቲያኑ መገኛ እንደነበር ይነገራል ሆኖም ግን በመዛግብት እና በአባቶች ማረጋገጫነት መታገዝ ስለሚኖርበት ወደፊት እገልጥላችኋለሁ፡፡

“ቅባት መጠመቅ አለበት” ሊቀ ሊቃውንት ሰሎሞን ዳዊት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በመጀመሪያ እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም በፍቅር በአንድነት አደረሳችሁ እያልሁ ከዛሬ ሁለት  ዓመታት በፊት የጻፍኋትን ግጥም እነሆ እላለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ያነበበው ሰው ይህንን አልፎ ወደዋናው ርእሰ ጉዳይ መሄድ ይችላል፡፡ መብቱ በሕግ የተፈቀደ ነው ብያለሁ!
                         *********************************
በዱራ ሜዳ ላይ ናቡከደነፆር አምላኩን አቆመው፣
በስድሳ ክንድ ቁመት በስድት ክንድ ወርድ ከወርቅ አቅልጦ ሠራው፡፡
አምላኩን ሊያስመርቅ ያልተመረቀ አምላክ መርቁልኝ ብሎ፣
መኳንንት፣ ሹማምንት፣ አዛዥ፣ አዛውንቱን፣ መጋቢውን ሁሉ ጠራቸው በቶሎ፡፡
የንጉሥ ትዕዛዝ ነው ከታች ባትን ከላይም አንገትን ሊያስቆርጥ የሚችል፣
ታዲያ ማን ይቀራል? ማንስ ይንቀዋል? ማን ያቃልለዋል? READ MORE!
         ****************************************

“ለካስ ጊዜው ኖሯል”



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ድጋሜ እንድለጥፈው ጊዜው አስገደደኝ! ይህንን ጽሑፍ ከዚህ በፊት በራሴ ገጽ ላይ ለጥፌው ነበር፡፡ የዚህን ልጥፍም እዚህ ላይ ጠቅ በማድረግ ማግኘት ይቻላል፡፡ http://melkamubeyene.blogspot.com/2015/05/blog-post_98.html ዛሬም መጠነኛ ማሻሻል በማድረግ እነሆ ብያለሁ!
                                 ******************
አንድ ስሙን ለጊዜው የማላስታውሰው ሰው እንዲህ የሚል አባባል አለው “ALL COLOURS WILL AGREE IN THE DARK” ይህን አባባሉን ሳነበው ትልቅ መልእክት እንዳለው ልቤ ተረዳ፡፡ የተረዳው ልቤም መላ አካላቴን አነቃቃው እና አጆቼን ወደ መጻፊያ ሰሌዳው ወሰዳቸው፡፡ በዚያም የሚንኳኳውን የመጻፊያ ሰሌዳ በእኛው በአገራችን በለመድነው ቋንቋ እንዲጽፍ የመጻፊያ ስልቱን ቃኘሁት (ቀየርሁት)፡፡ ከዚያም ይህንን ቁም ነገር በኢትዮጵያዊ ለዛው ተናዘዝሁ፡፡ እነሆ ኑዛዜየን!
                                *********************

Sunday, December 10, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፮--ተፈጸመ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፵፯ ጀምረን  እስከ መጨረሻ ገጽ ድረስ ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ይህ የመጨረሻየ ክፍል ስለሆነ እስከ ረቡዕ ድረስ ቀስ ብላችሁ ተረጋግታችሁ እንድታነቡት ሰፋ አድርጌ ነው የጻፍሁላችሁ፡፡ ረዘመ እንዳትሉኝ ከወዲሁ እጠይቃለሁ፡፡
********************************

Friday, December 8, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፭



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፵፪ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ካሳሁን ምናሉ በዚህ ገጽ ላይ ምእራፍ ዘጠኝን ይጀምራል፡፡ ምእራፉም ስለጌታችን የልደት በዓል ነው የሚናገረው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት ጥቂት ነገሮችን የተመለከትን ቢሆንም እዚህ ክፍል ላይም በጥልቀት እንመለከታለን፡፡
****************************
ሊቃውንቱ በዚህ ጉዳይ በጥሩ ሁኔታ ያብራሩበት የቪዲዮ ትምህርት አለ ይህንን ሊንክ ጠቅ አድርጉና ተከታተሉት፡፡ ሙሉውን ተከታተሉት እንዳያመልጣችሁ ለሚጠይቋችሁ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ ተብለናል ይህ ደግሞ አንዱ ዝግጅታችን ነው፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=sbriV-ou5NU&feature=youtu.be
***************************

Thursday, December 7, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፬




   ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

የቅባቶቹ መጽሐፍ መሠረተ ሐይማኖት
ዛሬ ከገጽ ፴፪ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
#ረዝሟል_አሳጥረው_እንዳትሉኝ_አደራ_አልቻልሁም፡፡ ምስጢር ከምሥጢር ጋር ሲያያዝ ነውና የሚያምረው ቆራርጨ ማቅረብ አልቻልሁም፡፡ ከዚህ በፊት ቆራርጨ ለወልደ አብ መጽሐፍ ክህደቶች መልስ ስጽፍ አቅርቤው ነበር ሆኖም ግን ምሥጢሩ ከምሥጢሩ ጋር አልተያያዘልንም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሁሉንም በአንድ ማቅረብ ችያለሁ፡፡ “የበረታ ቆሞ የደከመ ተቀምጦ” ብላለች ተአምረ ማርያም እና የበረታ ያንብብ የደከመ #SHARE ያድርግና ጊዜ ሲኖረው ያንብበው፡፡ አንድ ጊዜ ማንበብ ሊደክም ይችላልና፡፡

Monday, December 4, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፫



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፰ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም መድሎተ አሚን ላይ በቅባተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ብለዋል የሚለውን ውሸት መድሎተ አሚንን በፎቶ አስቀምጫለሁ፡፡ ፍትሐ ነገሥቱንም እንዲሁ ለማጣቀሻነት እንድትመለከቱት በፎቶ አያይዠላችኋለሁ፡፡

Friday, December 1, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፪



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፯ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ቅዳሜ እና እሁድን ቀስ ብላችሁ አንብቡት በዛ ብላችሁ እንዳትሰለቹ!
ካሳሁን ምናሉ ገጽ ፳፯ ላይ ምዕራፍ ሰባት ብሎ በሚጀምረው የገጹ መጨረሻ ላይ እንዲህ ይላል “መንፈስ ቅዱስን ትቶ ወልድን ብቻ በተዋሕዶ ከበረ ማት እንደንስጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ህፀፅ እንደማለት ይቆጠራል ምክንያቱም የባሕርይ አባቱን አብን የባሕርይ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስን ትቶ ወልድን በተዋሕዶ ከበረ ማለት ስተት ነው፡፡ ወልድ በማኅጸነ ማርያም ሲፀነስ በመንፈስ ቅዱስ ሲወለድም በመንፈስ ቅዱስ ቀስ በቀስ ሲያድግም በመንፈስ ቅዱስ ነውና ወልደ አብ ወልደ ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለት ይገባል” ይላል፡፡ እስካሁን ድረስ ካሳሁን ምናሉ ከመምህራን እግር ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ሰው ይመስለኝ ነበር ለካ የኔቢጤ ነው በተባራሪ የሰማውን ብቻ ነው የጻፈው፡፡ በፊደል ግድፈቱም ስንወቅሰው የነበረ በስህተት ነው ለካ፡፡ ምን ይፈረድበታል ነገሩን አላወቀውማ አያያዙ አልገባውማ፡፡