በዚህ አስከፊ ዘመን እርስ በርሳችን ደም ስንፋሰስ ሰላም ስትርቀን ወንድሞቻችን ሲሞቱ፣ ሕጻናት
ሳይቀር ሲጨፈጨፉ፣ እናቶች በልጆቻቸው አስከሬን ላይ ቁጭ በሉ እየተባሉ ሲደበደቡ የሚያጽናናን አባት ማጣታችን ልባችንን ሰብሮት
ነበር፡፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ ፓትርያርኩ ከምእመናን በተሰበሰበ ሽራፊ ሳንቲም በሚንቀሳቀሰው የቤተክርስቲያናችን ቴሌቪዥን ላይ
ብቅ እያሉ ማን የጻፈላቸውን እንደሆነ ባናውቅም ከአንድ እረኛ የማይጠበቅ መግለጫ መሰል ንግግራቸውን ሲያነበንቡብን በጣም እጅግ
አዝነን ነበር፡፡ ኤልያስ ስለ ናቡቴ ከንጉሡ አክአብና ንግሥት ኤልዛቤል ጋር የተጋጨው፣ ዮሐንስ መጥምቅ የወንድምህን ሚስት ልታገባት
ህግ አይፈቅድልህም በማለት ከንጉሥ ሔሮድስ ጋር የተጋፈጠው፣ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ አንዲት ደሃ መበለት ከንግሥት አውዶክስያ ጋር
የተከራከረው እና መከራን የተቀበለው፣ አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያ ለፋሽስት ባህል እምነት እንዳትገዛ በማውገዛቸው በጥይት የተገደሉ እረኝነታቸው እውነተኛ ስለነበር ነው፡፡ ዛሬ ግን ፓትርያርኩ የሚሰጡት መግለጫ
እረኝነታቸውን የማያሳይ ምእመናንን ይበልጥ ውስጣቸውን እየጎዳቸው ያለ ነገር ነው፡፡ እረኝነት የሞቱ በጎቹን እየፈታ መቅበር ከዚያም
ነፍሳቸውን ማርልን ብሎ ማስተጋባት ብቻ አይደለም እንዳይሞቱ መጠበቅ ጭምር እንጅ፡፡ Friday, September 30, 2016
“አባታችን ስንለው ልጆቼ የሚለን እረኛ አግኝተናል”
በዚህ አስከፊ ዘመን እርስ በርሳችን ደም ስንፋሰስ ሰላም ስትርቀን ወንድሞቻችን ሲሞቱ፣ ሕጻናት
ሳይቀር ሲጨፈጨፉ፣ እናቶች በልጆቻቸው አስከሬን ላይ ቁጭ በሉ እየተባሉ ሲደበደቡ የሚያጽናናን አባት ማጣታችን ልባችንን ሰብሮት
ነበር፡፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ ፓትርያርኩ ከምእመናን በተሰበሰበ ሽራፊ ሳንቲም በሚንቀሳቀሰው የቤተክርስቲያናችን ቴሌቪዥን ላይ
ብቅ እያሉ ማን የጻፈላቸውን እንደሆነ ባናውቅም ከአንድ እረኛ የማይጠበቅ መግለጫ መሰል ንግግራቸውን ሲያነበንቡብን በጣም እጅግ
አዝነን ነበር፡፡ ኤልያስ ስለ ናቡቴ ከንጉሡ አክአብና ንግሥት ኤልዛቤል ጋር የተጋጨው፣ ዮሐንስ መጥምቅ የወንድምህን ሚስት ልታገባት
ህግ አይፈቅድልህም በማለት ከንጉሥ ሔሮድስ ጋር የተጋፈጠው፣ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ አንዲት ደሃ መበለት ከንግሥት አውዶክስያ ጋር
የተከራከረው እና መከራን የተቀበለው፣ አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያ ለፋሽስት ባህል እምነት እንዳትገዛ በማውገዛቸው በጥይት የተገደሉ እረኝነታቸው እውነተኛ ስለነበር ነው፡፡ ዛሬ ግን ፓትርያርኩ የሚሰጡት መግለጫ
እረኝነታቸውን የማያሳይ ምእመናንን ይበልጥ ውስጣቸውን እየጎዳቸው ያለ ነገር ነው፡፡ እረኝነት የሞቱ በጎቹን እየፈታ መቅበር ከዚያም
ነፍሳቸውን ማርልን ብሎ ማስተጋባት ብቻ አይደለም እንዳይሞቱ መጠበቅ ጭምር እንጅ፡፡ Monday, September 26, 2016
“ደርሰናል!”
© መልካሙ
በየነ
Friday, September 9, 2016
“ዘመን ለዘመናት”
ጳጉሜን 4/ 2008 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=============================================
በመጀመሪያ ይህንን ገጽ ላይክ ያድርጉ facebook.com/beyenemlkm
==============================================
ዓለም ከተፈጠረችበት ዕለት ጀምሮ ያለውን ያለፈና የሚመጣ ዘመን በተለያዩ የቀን አቆጣጠሮች እንቆጥራለን።
ከእነዚህ የዘመንና የቀን አቆጣጠር ስልቶች መካከል አንዱ ያልተበረዘውና ያልተከለሰው የእኛው የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ነው። የእኛ ዘመን አቆጣጠር ዓመትን በ ፲፫ ወር ይከፍላል። ፲፫ ኛዋ ወር
ጳጉሜን ትባላለች። ይህች ወር የወርን ቀመር አታከብርም። ፩ ወር ፴ ቀናትን ይይዛል ይህች ጳጉሜን ግን ስትፈልግ ፭ ሲያሻት ደግሞ
፮ ትሆናለች።
ደስ የሚለው ነገር የቤት ኪራይ አይታሰብባትም በእርግጥ ደመወዝም አንቀበልባትም። ባትሰራ ደመወዝህ
የሚቆረጥባት ብትሰራ ደግሞ ክፍያ የማታገኝባት ወር ...... ጳጉሜን። የውኃ፣ የመብራት፣ የስልክ ወጭ ግን ከምንጊዜውም በላይ
የሚልቅባት ጭማሪ ወይም ትርፍ ወር ናት ……. ጳጉሜን። ይህች ወር መሸጋገሪያ ድልድይ ናት። አሮጌውን ዓመት ሽኝተን አዲሱን ዘመን
የምንቀበልባት መሸጋገሪያ ናት። አሮጌው ዘመን ለሚመጣው አዲስ ዘመን ቦታውን ሲለቅ የመልቀቂያ ውሉ መፈጸሚያና መፈራረሚያ ጳጉሜን ናት።
በባህላችን ዘመን ሲተካ እንኳን አደረሳችሁ እንባባላለን፡፡ እንቁጣጣሽ እየተባባልን መልካም ምኞት
እናቀርባለን። አዲስ ዘመን ላይ ብዙ ተስፋ እንጥላለን አዲስ እቅድ እናቅዳለን፣ አዲስ መሠረት እንመሠርታለን። በመንፈሳዊውም ሆነ
በሥጋዊው መንገድ እቅድ እናቅዳለን። ዘመኑን መኖር ስንጀምር የተወሰነውን እቅድ እንሰራዋለን፤ የተወሰነውን እንረሳዋለን፤ የተወሰነውንም
ለሚቀጥለው ዓመት እናዞረዋለን። ዘመን ወደፊት አሻግሮ ሲያዩት የሚያልቅ አይመስልም፤ ነገር ግን ባላወቅነውና ባላሰብነው ሰዓት ፀሐይ
ይጠልቅብናል ዘመን ያልቅብናል። ዘመን ማለት እንዲህ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ግን ላንተ የተሰጠ ዘመን ለእኔ አልተሰጠኝም ምናልባት
ግን የሆነ ዘመን የጋራችን ሊሆን ይችላል።
እንቁጣጣሽ የሚለውን ቃል እንደመልካም ምኞት መግለጫ የምንጠቀመው ዘመኑን በሚገባ ስለምናውቅና
ስለምንረዳ ነው። እንቁጣጣሽ የሚለው ቃል የሁለት ቃላት ጥምርታ ነው የ "እንቊ" እና የ "ጣጣሽ"
ማለት ነው። የዘመን መለወጫ ወር መስከረም በእኛ አገር ልዩ ወር ነው። ገደሉ፣ ሜዳው፣ ጋራው፤ ሸንተረሩ ሁሉ በተፈጥሮ አበባ የሚያምርበት
የሚያጌጥበት የሚፈካበት ወር ነው። የአበቦች መዓዛ እንኳንስ ንቦችን ዝንቦችንም የሚስብበት ወቅት ነው። ስለዚህ ነው እንግዲህ እንቁ
የሚያስብለው። ውኃው የሚጠራበት ጋራው የሚያሸበርቅበት እንቁ የሚሆንበት ነው። በሌላ ጎን ደግሞ መስከረም ማለት የተዘራው የማይደርስበት፣
የጎተራው የሚያልቅበት ወቅት ነው። በዓሉን ደግሞ ለማክበር በጉን ዶሮውን ማረድ ለምደናል። ጎተራችን አልቆ በግ እና ዶሮው በሌለበት ሁኔታ አዲስ ዘመን ስንቀበል ደግሞ ቅር ያሰኘን ይሆናል። ነገር ግን
ካልቻልን ምን ማድረግ እንችላላን? ምንም። በተለይ በዚህ ወቅት ደግሞ ከባድ ፈተና ነው። በጉን ከጓሮ ጎትተን አናቀርበው ነገር
የለንም። ስለዚህ ምርጫችን መግዛት ብቻ ነው። ያንን ማድረግ ደግሞ አንችልም። ከዚህ በተጨማሪም ልጆች አዲሱን ዘመን ምክንያት አድርገው
ልብስ ጫማ እንዲገዛላቸው ይጠይቃሉ፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱበት ወር በመሆኑ ደብተር እስክብሪቶ እርሳስ ይፈልጋሉ።
አቤት የዘመን መለወጭ ጣጣ! እውነትም ጣጣሽ ብንላት ሲያሳት እንጅ አይበዛባትም። ለዚህ ነው እንግዲህ " እንቁጣጣሽ
" የምንባባለው።
ዘንድሮ ደግሞ ማለቴ አዲሱ ዓመት 2009 ዓ.ም ለሀገራችን የደስታ የዘመን መለወጫ አልሆነልንም
የሀዘን ሆነብን እንጅ፡፡ ወገኖቻችን በግፍ ደማቸው ፈስሷል፣ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን ያለርኅራኄ በጭቃኔ ተገድለዋል፡፡ በዚህም
አንገታችንን ደፍተናል፡፡ እንደእኔ ከሆናችሁ የዘንድሮው የዘመን መለወጫ በዓል ምንም አልመስልህ ብሎኛል፡፡ በዓል በዓልም አልሸተተኝም
ውስጤ በዓሉን ለመቀበል ደስተኛ አይደለም፡፡ ብቻ ግን ዘመናትን የሚያቀዳጅ ፈጣሪ ይህንን ዘመን አሳልፎ መጭውን ዘመን እንድቀበል
በሕይወት ስላኖረኝ አመሰግነዋለሁ፡፡
አዲሱን ዓመት የንስሐ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመልካም ነገር፤ የሰላም፣ የመረጋጋት፣ የመደማመጥ፣
የመተሳሰብ፣ ያድርግልን። ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም ያሸጋግረን።
አሜን፡፡
=============================================
ዓለም ከተፈጠረችበት ዕለት ጀምሮ ያለውን ያለፈና የሚመጣ ዘመን በተለያዩ የቀን አቆጣጠሮች እንቆጥራለን።
ከእነዚህ የዘመንና የቀን አቆጣጠር ስልቶች መካከል አንዱ ያልተበረዘውና ያልተከለሰው የእኛው የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ነው። የእኛ ዘመን አቆጣጠር ዓመትን በ ፲፫ ወር ይከፍላል። ፲፫ ኛዋ ወር
ጳጉሜን ትባላለች። ይህች ወር የወርን ቀመር አታከብርም። ፩ ወር ፴ ቀናትን ይይዛል ይህች ጳጉሜን ግን ስትፈልግ ፭ ሲያሻት ደግሞ
፮ ትሆናለች።Thursday, September 8, 2016
“ሰውነታችንን ካላስቀደምን ሰላምን አናመጣም”
ጳጉሜን 3/ 2008 ዓ.ምደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
========================
በመጀመሪያ ይህንን ገጽ ላይክ ያድርጉ facebook.com/beyenemlkm
========================
ሁላችን አሁን ከደረስንበት ደረጃ ከመብቃታችን በፊት ሰው ነበርን፡፡ ሰው ሳንሆን ቀድሞ ሃይማኖት የለንም፣ ሰው ሳንሆን ቀድሞ ብሔር የለንም፣ ሰው ሳንሆን ቀድሞ ዘር የለንም፣ ሰው ሳንሆን ቀድሞ ጎሳ የለንም፣ ሰው ሳንሆን ቀድሞ ጎጥ የለንም፡፡ ከዚህ ሁሉ ቀድሞ የነበረው ሰውነት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ በስፋት ከሚያስተምሩ የቤተክርስቲያናችን ፈርጦች መካከል አንዱ የሆኑት ብርቅየ ሊቅ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ናቸው፡፡ እርሳቸው ሰው እንሁን እንደ ሰው እናስብ እያሉ ሁልጊዜ ይሰብካሉ ያስተምራሉ ይመክራሉ ነገር ግን ሰሚ ጆሮ ያጡ ይመስላል፡፡ ሰው እንሁን ሰውነታችንን እናስቀድም ማለት ፖለቲካ አልያም ሃይማኖታዊ ስብከት አይደለም፡፡
ሰውነታችንን ስናስቀድም በሃይማኖት አንለያይም ምክንያቱም ሃይማኖት ሰው ከመሆናችን በኋላ የሚመጣ ጉዳይ ነውና፡፡ የኦርቶዶክ ተዋሕዶ፣ የፕሮቴስታንት፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ ወዘተ እምነት ተከታዮች መሆን የጀመርነው ሰው ከመሆናችን በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ በሃይማኖት ልዩነትን ፈጥረን አንዱ ለአንዱ ጠላት የሚሆነው ሰውነታችንን ስለማናስቀድም ብቻ ነው፡፡ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ እንመለከታለን፣ መስጊዶች ሲፈራርሱ እናስተውላለን ይህ ክስተት የሚፈጠረው ሰውነታቸውን ባላስቀደሙ ሰዎች ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ሰው ከመሆናቸው ያስቀደሙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሃይማኖትን እንደልዩነት በመጠቀም ከሰውነት አንድነታችን መውጣት የለብንም፡፡ ምንም እንኳ በሃይማኖት ብንለያይም ሰው በመሆናችን ግን እንተባበራለን፡፡ ትብብራችን ደግሞ ቀድሞ ባገኘነው የሰውነት ጸጋ እንጅ በኋላ ባገኘነው የሃይማኖት ጸጋ መሆን አይገባውም፡፡
ሌላው ሰውነታችንን ስናስቀድም በሃገር፣ በዘር፣ በብሔር፣ በጎሳ፣በጎጥ ወዘተ አንለያይም፡፡ አገሬ፣ ዘሬ፣ ብሔሬ፣ ጎሳየ፣ ጎጤ ወዘተ ከማለታችን በፊት ሰው መሆናችን ይቀድማል፡፡ ሰው ስንሆን ያን ጊዜ አምላክ ባወቀ በሆነ አገር፣ በሆነ ብሔር፣ በሆነ ጎጥ፣ ከሆነ ዘር እንድንወለድ አደረገን፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ጉዳይ ፈልገን የተወለድንበት አገር፣ ብሔር፣ ዘር፣ ጎሳ እንደሌለ ነው፡፡ የአምላክ ፈቃድ ሆኖ ከሆነ አገር፣ ከሆነ ብሔር፣ ከሆነ ጎጥ፣ ከሆነ ዘር ፈጠረን እንጅ እኛ የመረጥነው እንዳልሆነ እናስተውላለን፡፡ ስለዚህ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በዘር ከመከፋፈላችን እና አንድነታችንን ከመበታተናችን በፊት ሰውነታችንን እናስቀድም፡፡ ሰውነታችንን ካስቀደምን በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ በብሔር አንከፋፈልም፡፡ ደግሞም እኮ ሁሉን ያደረገልንን አምላክ ልናመሰግነው ይገባል እንጅ በእነዚህ ነገሮች መለያየትን እንዴት እንቀበላለን፡፡ ዛሬ በብሔር በቋንቋ እና በዘር እንድንከፋፈል ያደረገን ሰውነታችንን ስላላስቀደምን ብቻ ነው፡፡ የትም ተወለድ የት፣ የትም ተፈጠር የት ሰው ነህ፡፡ ሰው በመሆንህ ደግሞ አንድነትን ታጠነክርበታለህ እንጅ ልዩነትን አትፈጥርበትም፡፡ ምክንያቱም ሰው ከሰው በምንም ሊለያይ አይችልምና፡፡
ሰውነታችንን ስናስቀድም ማንም ማንንም አይገድልም፤ ማንም በማንም አይሞትም አይገደልምም፡፡ አንዱ ባለስልጣን ሌላው ሎሌ፣ አንዱ ገዳይ ሌላው ተገዳይ፣ አንዱ ሰጭ ሌላው ተቀባይ፣ አንዱ ጠጋቢ ሌላው ተራቢ፣ አንዱ ረጋጭ ሌላው ተረጋጭ በመሆን መለያየት የመጣው ሰው ከመሆናችን በኋላ ነው፡፡ እንደ ሰው ስታሰብ ሌሎች ባንተ ላይ ሊያደርግብህ የማትፈቅደውን ነገር በሌሎች ላይ አታደርግም፡፡ ስለዚህ አንተን እንዲገድሉህ እንደማትፈቅድ ሁሉ ሌሎችን ለመግደል አትፈቅድም፡፡ አንተን ሲረግጡህ ሲጨቁኑህ እንደማትወድ ሁሉ ሌላውን አትረግጥም አትጨቁንም፡፡ ስለዚህ ነው ሰውነታችንን ማስቀደም አለብን የምንለው፡፡ አንተ ባማረ በተዋበ ባሸበረቀ በዕንቁ ባጌጠ ቪላ ቤት ላይ እየተንፈላሰስክ ሌላው መንገድ ላይ ወድቆ በብርድ ሲሰቃይ መመልከት እንደ ሰውነቱ ለማያስብ እንጅ እንደሰውነቱ ለሚያስብ ሰው እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡
እንደሰውነታችን ስናስብ ሰውን አንገድልም ምክንያቱም እኛን እንዲገድሉን ስለማንፈልግ፡፡ አሁን ግን እያስቀደምነው ያለ ጉዳይ ከሰውነታችን በኋላ የመጡ ጉዳዮችን ሆኗል፡፡ በቅርቡ ያየነው እና ያስተዋልነው የአገራችን ጉዳይ ሰውነታቸውን ካላስቀደሙ ወገኖች በተሰነዘረ ጥቃት የብዙዎች ደም ፈስሷል፡፡ ሁልጊዜ ሳስበው ከኅሊናየ አልወጣልህ ያለኝ ግን ማረሚያ ቤቶች ሲቃጠሉ ለማምለጥ ሞክረዋል ተብለው በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉት ንጹሐን ወገኖቻችን ናቸው፡፡ በእውነት እንደሰውነት ለሚያስብ ሰው ማረሚያ ቤቱ ሲቃጠል ታሳሪዎች ምን ማድረግ ነበረባቸው? በእሳት ላለመቃጠል ከማምለጥ ውጭ ምን ተስፋ አላቸው? ከእሳቱ ከማምለጥ ውጭስ ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ ነበረባቸው? ሳስበው በጣም ይዘገንነኛል፡፡ በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ መወሰን ሰው ከመሆን ውጭ ያለው የሚያስበው ከንቱ ሀሳብ ነው፡፡ እንደ ሰውነታችን ካሰብን በእርግጠኝነት እንዳይቃጠሉ እንተባበራቸው ነበር እንጅ አመለጡ ብለን ተኩሰን አንገድላቸውም ነበር፡፡
ሰውነት አንድ ያደርጋል፡፡ በመወለድ አንድ ሆነናል በመሞትም አንድ እንሆናለን፡፡ በመብላት አንድ ሆነናል በመጠጣትም አንድ እንሆናለን፡፡ ዘርን በመተካት አንድ ሆነናል በማሰብም አንድ እንሆናለን፡፡ ስለዚህ ከሁሉ አስቀድመን ሰው መሆናችንን እናረጋግጥ ከዚያ በኋላ ሃይማኖት፣ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ጎሳ ከዚህ በኋላ የሚመጣ ጉዳይ ነው፡፡ ሰው ስንሆን ለሁሉ እንራራለን፣ ሰው ስንሆን ለሁሉ እናስባለን፣ ሰው ስንሆን ሁሉን እንመግባለን፣ ሰው ስንሆን ሁሉን እንታደጋለን፣ ሰው ስንሆን ሁሉን በፍቅር እንመለከታለን፣ ሰው ስንሆን አድልዎ አንፈጽምም፣ ሰው ስንሆን ለሁሉ እኩል እንጨነቃለን፡፡ ሰው ካልሆንን ግን የዚህ ተቃራኒ እንሆናለን፡፡ እኛ ጮማ እየቆረጥን ጠጅ እያንቆረቆርን ሌላው በረሃብ ሲያልቅ እንስቃለን፡፡ እኛ ባማረ ቤት ሞቆን እየኖርን የሚወጥሩት ሸራ እንኳን አጥተው መንገድ ላይ የሚያድሩትን ወገኖቻችንን አናስባቸውም፡፡ ስለዚህ እንደሰውነታችን እናስብ እንደሰውነታችን ካሰብን ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት ማንም ሊቀማን ማንም ሊነፍገን የማይችላቸው ሃብቶቻችን ይሆናሉ፡፡
Wednesday, September 7, 2016
“የወላጅ ቁንጥጫ ረሃብን አያጠፋም”
ጳጉሜን 2/ 2008 ዓ.ምደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
=======================
በመጀመሪያ ይህንን ገጽ ላይክ ያድርጉ facebook.com/beyenemlkm
አንድ ነገር አሰብኩ፤ ያሰብኩትንም እንዲህ ጻፍኩት፡፡ ልጆች ሲርባቸው፣ ሲበርዳቸው፣ ሲታመሙ ወዘተ ያለቅሳሉ፡፡ የሚያለቅሱበትን ምክንያት በአግባቡ መለየት የወላጆች ድርሻ ነው፡፡ የሕጻንኛን ቋንቋ በሚገባ ያልተረዳ ወላጅ በማይመክርና በማያስተምር እንዲሁም በማይገስጽ መልኩ ልጆቹን ይቀጣል፡፡ ልጆቹም ለጥቂት ጊዜ ከማልቀሳቸው ዝም ይላሉ፡፡ ከማልቀሳቸው ዝም ስላሉለት ብቻ ግን ለልጆቹና ለራሱ ሰላም የፈጠረ የመሰለው ወላጅ ጅል ነው፡፡ ምክንያቱም ልጆቹ ከማልቀሳቸው ዝም ያሉ ችግራቸው ስለተፈታላቸው ወይም ጥያቄያቸው ስለተመለሰላቸው ሳይሆን ስለቆነጠጣቸው እና ስላስፈራራቸው እንደሆነ አልተረዳም ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ወላጅ የወላጅነት ድርሻው ለስሙ አባት ወይም እናት ለመባል ብቻ ነው፡፡
ራበኝ አብላኝ ጠማኝ አጠጣኝ እያለ ረሃብ ጎድቶት የሚያለቅስብንን ህጻን እንደወላጅነታችን ማብላትና ማጠጣት ካልቻልን ያልቻልንበትን ምክንያት ማስረዳት ይጠበቅብናል እንጅ ቆንጥጠን ዝም ማስባል አይገባንም፡፡ ልጆቹ እኮ ያለቀሱብን ስለራባቸው እና ስለጠማቸው ነው፤ ታዲያ የእኛ ቁንጥጫ እና ኩርኩም ረሃብን የሚያስታግስ ይመስል ለምን ቁንጥጫና ኩርኩሙ አስፈለገ? በተገቢው መልኩ ልጆቻችን ያለቀሱበትን መረዳትና ተገቢውን መልስ መስጠት የወላጅነት ድርሻችን ነው፡፡ እንደወላጅነታችን ተገቢውን መልስ መስጠት ከእኛ የሚጠበቅ ነው፡፡ ለምን አለቀሱብን አትበሉ ሲርባቸው ያለቅሳሉ፣ ሲጠማቸው ያለቅሳሉ፣ ሲበርዳቸው ያለቅሳሉ፣ ግፍ ሲበዛባቸው ያለቅሳሉ፡፡ የወላጅ ቁንጥጫ ደግሞ ረሃብን አያስታግስምና ልጆች ለጊዜው ከማልቀሳቸው ቢቆጠቡም ቆይተው ግን ለቅሷቸውን በአዲስ መልኩ ይጀምሩታል፡፡ ስለዚህ ሁነኛው መፍትሔ የወላጅነትን ምግባር ተላብሶ የልጆችን እንባ ማበስ ነው፡፡ ምክንያቱም የልጆች ጥያቄ ረሃብና ጥማት በዛብን የሚል እንጅ ማልቀስ አይደለም፡፡ ወላጆችም እንዳያለቅሱባቸው ከመደብደብ ባለፈ ለምን እንዳለቀሱባቸው መረዳት አይፈልጉም፡፡ ይህ ደግሞ ዘላቂ መፍትሔ የሚሆንበት አንዳች ነገር የለውም፡፡
በርካቶቻችን መፍትሔ የምንሰጠው ለችግሩ ሳይሆን ችግሩ ለወለደው ሌላ ችግር ነው፡፡ ጎርፍ ቤታችን ውስጥ ሲገባ የገባውን ውኃ ወደ ውጭ እየረጨን መጨረስ መፍትሔ እናደርጋለን፡፡ ከዚያም በጎርፉ የተበላሹ ዕቃዎቻችንን ፀሐይ ላይ በማስጣት ማድረቅ እንጀምራለን፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ነገ ጎርፉ ቤታችን ላለመግባቱ ምንም ዋስትና የለንምና፡፡ ስለዚህ ዘላቂ የሚሆነው መፍትሔ የጎርፉን አቅጣጫ ማስቀየር አልያም ቤትን ማስተካከል ብቻ ነው፡፡
በሀገራችን እየሆነ ያለውም እንደዚሁ ያለ ነው፡፡ ሰልፍ እንዳይወጡ በማስፈራራት ወይም የወጡትን በመደብደብ የህግ የበላይነትን አስከብረናል ሰላምንም አስፍነናል ማለት ያስቸግራል፡፡ ህዝቡ ሰልፍ እንዳይወጣ ማድረግ ወይም የተሰለፈውን መበተን በምንም መልኩ ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ ችግሩ እኮ ሰልፍ መውጣታቸው አይደለም ሰልፍ እንዲወጡ ያደረጋቸው ጉዳይ እንጅ፡፡ ሰልፍ እንዲወጡ ያደረጋቸው ምክንያት ሰልፉ ቢበተንም አብሮ አይበተንም፡፡ የተሰለፈውን ሰው ብናስፈራራው እና ብንገድለውም ሰልፉን ሊበትነው የሰውን ቁጥር ሊቀንሰው ይችላል እንጅ ችግሩን ሊፈታው አይችልም፡፡ ስለዚህ መፍትሔ ሊሆን የሚችለውን ነገር እንደተማረ፣ ለሀገር እንደሚያስብ፣ ለወገን እንደሚቆረቆር ሰው ሆነን በጋራ ልንፈታው ያስፈልጋል፡፡ ህጻናት ተርበው ሲያለቅሱ በወላጅ ቁንጥጫ ለጊዜው ዝም ቢሉም ረሃቡ ሲጸናባቸው ቁንጥጫውን ከምንም ሳይቆጥሩ አብልጠው እንደሚያለቅሱ ሁሉ ችግሩ ካልተፈታለት ይህ ህዝብም ሞትን ሳይሰቀቅ ወደፊት ማለቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ የወገኖቻችን ደም ሳይፈስ ዘላቂ መፍትሔ የሚፈለግበትን መንገድ መፈለግ ይገባናል፡፡
Friday, August 26, 2016
“ከጎልያድ ሰይፍ የሚልቅ የዳዊት ጠጠር”
© መልካሙ በየነ
ነሐሴ 20/ 2008 ዓ.ም
አምላክ ይሁን
ካላለ በቀር አንዲት ነገር አትደረግም፡፡ ጎልያድ የእግዚአብሔር ሰው አይደለም፡፡ የህዝበ እስራኤላውያንን ደም ለማፍሰስ የሚፈጥን
እጅ የያዘ ግፈኛ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ የህዝቡን ደም ከእጁ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የጎልያድ ዛቻ፣ የጦር መሣሪያ፣ ማስፈራራት፣
ኃይልና ጉልበት ሁሉ በእስራኤላውያን ዘንድ ቦታ የለውም፡፡ ምክንያቱም እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸውና፡፡ እነርሱ ዘንድ
እምነት አለ፣ እነርሱ ዘንድ እግዚአብሔር አለ፣ እነርሱ ዘንድ ድል መንሳት አለ፣ እነርሱ ዘንድ ማሸነፍ አለ፣ እነርሱ ዘንድ ሞገስ
አለ፡፡ ለጊዜው ጎልያዳውያኑ ደም ሊያፈሱ ይችላሉ፣ ለጊዜው ፍልስጥኤማውያኑ ሊገድሉ ይችላሉ፣ ለጊዜው ጎልያዳውያኑ ያሸነፉ ይመስላቸዋል፣
ለጊዜው ፍልስጤማውያኑ ኃይላቸው ከእነርሱ ጋር ይቆይ ይመስላቸዋል፣ግን አምላክ ከማን ጋር እንዳለ አያውቁም፡፡Tuesday, August 23, 2016
“በአግባቡ ያልተጠገነ ስብራት”
ነሐሴ 17/ 2008 ዓ.ም
Thursday, August 11, 2016
“ወማየ ብሔራሰ እኩይ ውእቱ”
ኤልሳዕ መምህሩ ኤልያስን ሸኝቶ ሲመለስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ኢያሪኮ ደረሰ፡፡ ከዚያም ከከተማው ገባና “ሠናይት
ንብረታ ለዛቲ ሐገር” አለ፡፡ ኤልሳዕ እየተመለከታት ያለችው ሀገር መልካም ናት፡፡ ከውጭ ሲመለከቷት መልካም ናት፣ ያማረች ናት፣
ያጌጠች ናት ለዚህም ነው ኤልሳዕ መልካምነቷን የሚመሠክርላት፡፡ ሆኖም ግን የሀገሪቱን መልካም መሆን አለመሆን የሚያውቁ በውስጧ
የሚኖሩ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎች የሚመለከቱት ህንጻውን ነው፣ ሌሎች የሚመለከቱት መንገዱን ነው፣ ሌሎች የሚመለከቱት የቤተ መንግሥቱን
ልምላሜ ነው፣ ሌሎች የሚመለከቱት 24 ሰዓት ያለአገልግሎት የሚፈሰውን ፋውንቴን ነው እውነቱ ያለው ግን በኗሪዎች እጅ ብቻ ነው፡፡
ለዚህም ነው ኤልሳዕ ሐገሪቱ መልካም ናት እያለ ስለሐገሪቱ መልካምነት ሲናገር ከታይታ መልካምነቷ ያልተጠቀመው ህዝብ “ወማየ ብሔራሰ እኩይ ውእቱ፣ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልሳዕ ሆይ! ውኃው ግን
ወላድ ቢጠጣው ያመክናል፣ መካን ብትጠጣውም አንጀቷን ቆርጦ ሆዷን በጥብጦ ይገድላታል” ማለቱ፡፡Wednesday, August 10, 2016
“ወሥሉጥ ስምኪ በኀበ እግዚአብሔር”
© መልካሙ በየነ
ነሐሴ 04/2008 ዓ.ም
ደብረማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
የአባ ሕርያቆስ ረድኤት በረከት ይደርብንና እመቤታችንን ባመሰገነበት ቅዳሴው እንዲህ አለ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም እንዲህ ብለው ተረጎሙልን፡፡ የቃሉ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን፡፡ወሥሉጥ ስምኪ በኀበ እግዚአብሔር፡፡ ስምሽም በእግዚአብሔር ዘንድ በማማለድ ሥሉጥ ነው፡፡ ይህም በአንድ ሰው ታውቋል፡፡ ታሪክ እጅግ ገንዘቡ የበዛ የተረፈው አንድ ባለጸጋ ነበረ ላዝማሪ ለዘዋሪ እየሰጠ አለቀበት፡፡ አንድም የዚህ ዓለም ገንዘብ ሲሰበሰብ እንጅ ሲጠፋ አይታወቅምና፡፡ ኅልፈቱ ቅድመ አስተርእዮቱ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ ከብሬ በኖርሁበት አገር ተዋርጄ ሰጥቼ በኖርሁበት አገር ለምኜ አልኖርም ብሎ አገር ጥሎ ቁርበት ጠቅሎ ሲሄድ ሰይጣን የጨዋ ልጅ መስሎ ከጎዳና ቆይቶ ወዴት ትሄዳለህ አለው ከብሬ በኖርሁበት አገር ተዋርጄ ሰጥቼ በኖርሁበት አገር ለምኜ አልኖርም ብየ አገር ጥየ ቁርበት ጠቅልየ መሄዴ ነው አለው፡፡ ያዘነ መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ ይህን ብሰጥህ አትመለስምን አለው፡፡ ይህንንማ ካገኘሁ ስንኳን ለእኔ ለልጅ ልጄ አይበቃም አለው ከዚህ በኋላ ሰጠው አንተም ፈቃዴን ፈጽምልኝ አለው፡፡ ምን ላድርግልህ አለው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ካድልኝ መላእክት ጻድቃን ሰማዕታትን አያማልዱም በል አለው፡፡ ካደ አያማልዱም አለ፡፡ ከተለያዩ በኋላ ነገር ረስቼ ቆየኝ አለው፡፡ ምእመናን አፍረው አክብረው ስሟን የሚጠሯት ማርያም የምትባል አለች ወላዲተ አምላክ መሆኗን ካድልኝ አለው፡፡ የለማኝ ምኩዜን ምን ይዞ ይሄዷል ጉዞ እንዲሉ እርሷንስ አይሆንም አለው፡፡ እንኪያስ አምጣ ብሎ ወርቅ አስመስሎ የሰጠውን ደንጊያ ተቀብሎ ልብ ራሱን ብሎ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት ነፍሱን ከሥጋው ለይተው እጅ አድርገዋታል፡፡ መላእክተ ብርሃንም የጌታን ቁርጽ ፍርድ ሳያዩ አይለዩምና ከእመቤታችን ዘንድ ሂደው ምነው ዝም አልሽ ይህች ነፍስ ከሥጋው የተለየች ባንቺ ምክንያ አይደለምን አታማልጅም አሏት፡፡ እርሷም መሐር ሊተ ወልድየ ዛተ ነፍሰ አለችው፡፡ ከልብኑ ይትመሐር አባቴን እኔን የባሕርይ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስን የወዳጆቼ የመላእክትን የጻድቃን የሰማዕታት አማላጅነታቸውን የካደ ይማራልን አላት፡፡ ዘጸውዐ ስምኪ ወዘገብረ ተዝካረኪ እምሕር ለኪ ያልኸው ቃልህ ይታበላልን አለችው፡፡ ያውስ ቢሆን የሕጸጸ ምግባር ነው እንጅ የሕጸጸ ሃይማት ነውንነገር ግን ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቼ ሰው መሆኔ ፈቃድሽን ላልፈጽምልሽ ነውን ምሬልሻለሁ አላት፡፡ እንኪያስ ከማርህልኝ ነፍሱን ከሥጋው አዋሕደህ አስነሣልኝ አለችው፡፡ ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋሕዶ አስነሣላት ለምን ካድህ አለችው፡፡ ባጣ አላት ያጣ ይለምናል እንጅ ይክዳልን አሁንም ከልጄ አማልጄህ እንዲህ ካለ ቦታ ምግብህን አዞልሃልና ሂድ አለችው፡፡ በዚያች ቦታ አንድ ባለጸጋ ነበር፡፡ አንዲት መልከ መልካም ልጅ ነበረችው፡፡ ባለጸጋ መጥቶ ልጅህን ስጠኝ ያለው እንደሆነ ልጄን በመልክ አትተካከላትም ይለዋል፡፡ መልከ መልካም መጥቶ ስጠኝ ያለው እንደሆነ ልጄን በገንዘብ አትተካከላትም ይለዋል፡፡ እንዲህ አድርጎ ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ያኖራት ነበረ፡፡ በዚያች ቀን እመቤታችን ከቤተ ክርስቲያን እንዲሄድ አድርገዋለች፡፡ የባለጸጋ ጸሎት አጭር ነውና የሰጠኸኝን አትንሣኝ ይህችን አንዲት ቅንጣት ልጄን ባርክልኝ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ወዲያው ተደሞ መጣበት፡፡ ያም ሰው ጠፈር ጠፈሩን እያየ ሲዞር ከሱ አጠገብ ደረሶ ቆመ፡፡ ልጅህንም ከብትህንም ለዚህ ሰው ስጠው አለችው፡፡ ቀና ቢል አየው፡፡ ከዚህ በኋላ ወስዶ ልጁንም ከብቱንም ሰጥቶት ወዲያው ዐረፈ፡፡ እርሱም ቆርቦ የእመቤታችንን ስሟን ሲጸራ ዝክሯን ሲዘክር የሚኖር ሁኗል፡፡ ከሞተም በኋላ በዚህ ጊዜ ያልፋልየማይባል መንግሥተ ሰማያትን አውርሰዋለችና እንዲህ አለ፡፡
፩ዱ ነዳይ ዘክሕደ ሃይማኖቶ ኪያኪ ክሕደ ሶበ አበየ በቅድመ ሰይጣን ዘአስሐቶ
አሚነ ዚአኪ ድንግል ለአድኅኖ ነፍሱ በቍዐቶ
እንዘ ይሴባሕ ተአምርኪ ወለጽጌኪ ምሕረቶ
ተንሥአ እምንዋሙ ወአተወ ቤቶ እንዳለ ደራሲ፡፡
(ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጉም ገጽ 30 እና 31)
ይቆየን……
“አትናገር፤ ተናገር ካሉህ ግን እውነቱን ብቻ ተናገር!”
ደብረማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
Monday, August 8, 2016
"ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴ በሠሉስ... አክለለ ምክሕነ"
©መልካሙ በየነነሐሴ 3/2008 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ ኢትዮጵያ
ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ፡፡
ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፡፡ ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም ትለዋለች እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ወድሰኒ ትለዋለች በዕለተ ሰኑይ ክርክር አልቋልና ባርክኒ ይላታል፡፡ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላእሌከ ትለዋለች፡፡ ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡
ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴ በሠሉስ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ ይላል ቃለ ጸሐፊ ነው እርሱ ግን አክሊለ ምክሕነ ብሎ ይጀምራል፡፡
አክሊለ ምክሕነ…. አክሊል የወዲህኛው ምክሕ የወዲያኛው
ወቀዳሚተ መድኃኒትነ…. ቀዳሚት የወዲህኛው መድኃኒት የወዲያኛው
ወመሠረተ ንጽሕነ…. መሠረት የወዲህኛው ንጽሕ የወዲያኛው
ኮነ በማርያም ድንግል… በማርያም ድንግል ሆነልን አለ፡፡ ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም በዚህ ቀን ከነገሥታት ዳዊትን፣ ከመሣፍንት ኢያሱን፣ ከደናግል ኤልያስን አስከትላ መጥታለች፡፡ ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ብትባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለህም፡፡ ኢያሱም መድኃኒት ብትባል የደኅንነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም፡፡ ኤልያስም ንጹሕ ድንግል ብትባል የንጽሕናችን መሠረት መሆን አልተቻለህም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት ድንግል ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም አክሊሎሙ ለሰማዕት እንዲለው አክሊለ ሰማዕት የሚባል ጌታ፤ ጥንተ ሕይወቶሙ እንዲለው ጥንተ ሕይወት የሚባል ጌታ አኃዜ ዓለም በእራኁ ኩሉ እኁዝ ውስተ እዴሁ መሠረተ ዓለም ይጸውር ድደ ወይነብር ጠፈረ እንዲል፡፡ መሠረተ ዓለም የሚባል ጌታ በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡
ትላንት ስሟን አላነሣም ዛሬ ስሟን አነሣ በእንግዳ ልማድ እንግዳን ዕለቱን ስሙን አይጠሩትም ከዋለ ካደረ በኋላ ስሙን ይጠሩታል በዚያ ልማድ ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው፡፡ ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና፡፡ ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና፡፡ አንድም ጸጋ ወሐብት ማለት ነው ለጊዜው ለእናት ለአባቷ ጸጋ ሆና ተሰጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ ጸጋ ሁና ተሰጥታለችና፡፡ አንድም መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው ምእመናንን መርታ ገነት መንግሥተ ሰማያት አግብታለችና፡፡ አንድም ልዕልት ማለት ነው፡፡ ሮም አርያም ማለት ልዑል ማለት እንደሆነ፡፡ እርሷንም መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ይላታልና፡፡ አንድም ማኅበረ መሐይምናን ወሕዝብ ተለአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ተፈሥሒ ቤተ እስራኤል ወተሐሰዪ ቤተ ይሁዳ ማለት ነው፡፡ አንድም ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው ያንንማ ዘዕብራይስጢ እንጅ አይለውም ብሎ ማሪሃም ማለት ቅሉ እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት እንደሆነ፡፡
እንተ ወለደት ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ… መመኪያነቷን በቅጽል አመጣው አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡
ዘኮነ ሰብአ በእንተ መድኃኒትነ… እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ
እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ… ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ሐራ ጥቃ ቃል ሥጋ ሆነ ያለውን ይዘው ወደ ታች ተለወጠ ይላሉና ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው፡፡
ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ… ስለዚህ ነገር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው
መንክር ኃይለ ወሊዶታ ዘኢይትነገር… ድንቅ የሚሆነው የመውለዷ ሥራ የማይመረመር ነው፡፡ የማይመረመር የመውለዷ ሥራ ድንቅ ነው፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት… በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ ሐተታ እንደ ሰኞ ።
Sunday, August 7, 2016
"መንግሥት ማለት ሕዝብ ነው"
የሀገራችን መሪዎች እና በሥሮቻቸው የሚገኙት ባለሥልጣናት "መንግሥት ማለት ሕዝብ ነው" የምትለዋን አባባል ከአፋቸው አይለዩአትም በተለይ ደግሞ የምርጫ ሰሙን!
በነገራችን ላይ መንግሥትን እንደ መንግሥት በአንድ ግዛት ላይ ለመመስረት 5 መሠረታዊ ጉዳዮች መኖር እንደአለባቸው ብዙ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው:-
ሉአላዊነት
ህዝብ
ድንበር/ወሰን
መንግሥት
እውቅና ናቸው።
ከዚህ እንደምንረዳው መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት አይደለም። መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ቢሆን ኖሮማ ISIS የተባለው መንግሥትም ሕዝብ ነው በተባለ ነበር። ነገር ግን እውቅና ስላልተሰጠው የራሱ የግዛት ወሰን ወይም ድንበር ስለሌለው እርሱን መንግሥት ነው ልንለው አንችልም። መንግሥት እንደ መንግሥት ለመቀጠል ሕዝብ ያስፈልገዋል ሕዝብ ብቻ ሳይሆንም መንግሥት የሚሆንበትንም ወሰን ማስከበር አለበት። ሱማሊያ መንግሥት አልባ ሐገር ናት እየተባለች ያለችው እኮ ሕዝብ ስለሌላት አይደለም ሉአላዊነቷን ስላላስከበረች ነው እንጅ።
መንግሥት ማለት ሕዝብ ነው የሚባለው እኮ ሕዝቡ የመሾምና የመሻር ሙሉ ስልጣን የያዘ ሲሆን እና የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ያለምንም ገደብ በነጻነት የተፈቀደለት ሲሆን ነው። የአገራችን መንግሥት ይህንን መብት የሰጠ ቢሆንም ወደዚህ ለመግባት ግን በርካታ ደረጃዎች ተቀምጠዋል። እነዚያን ደረጃዎች ለማለፍ ደግሞ በወቅቱ ከሚገኘው መንግሥት ጋር መስማማት ይኖርብሃል። ተስማምተህ መቃወም ደግሞ በሕዝብ ዘንድ ነቀፌታን ያስከትላል። ይህ የዋህ ሕዝብ ለቅድስናው አብልጦ ይጨነቃል። ለዚህም ነው ውኃ መብራት ኔትወርክ ዘይት ስኳር ወዘተ ሲቋረጥ ሁሉ አሜን ብሎ ሲቀበል የኖረው። ይህን የህዝብ የዋህነት ተመልክቶ እንኳ አጥፍቻለሁ ብሎ መንግሥት ይቅርታ አይጠይቅም ምክንያቱም ሥራው ነውና።
ሕዝብ ማለት ከፖለቲካ አስተሳሰብ በላይ ነው። መንግሥት ደግሞ በፖለቲካ አስተሳሰብ ሥር የተወሽቀ ነው። መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ነው ስንል መንግሥት ከፖለቲካ በላይ ነው እንደማለት ነው። መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ከሆነ ሕዝቡ ውረድልኝ ሲልህ መውረድ ውጣ አስተዳድረኝ ምራኝ ሲልህ ሥልጣን ላይ መውጣት ተግባርህ ይሆን ነበር። ምክንያቱም መንግሥት የሚመሠረተው በሥሩ ላሉ ሰዎችም ሥልጣን የሚሰጣቸው ሕዝቡ ስለፈቀደላቸው ብቻ መሆን አለባቸው። ይህ ሥልጣን እኮ የባሕርያችን አይደለም በጸጋ ያገኘነው ሥልጣን ነው። ጸጋው ደግሞ ከአምላክ ብቻ ሳይሆን ከሕዝቡም የሚሰጠን ነው። ስለዚህ የሕዝብን ቅሬታ አቤቱታ እና ጩኸት መስማት ያስፈልገናል ምክንያቱም መንግሥት ማለት ሕዝብ ነው ብለናላ። የሕዝቡ ጩኸት የመንግሥትም ጩኸት መሆን አለበት።
ስለአገራችን ሰላም ጸልዩ። አባቶቻችን ሆይ በጸሎታችሁ አስቡን የሕዝቡ ደም እየፈሰሰ ነውና። እንደ ባሮክ እና አቤሜሌክ የአገራችንን ጥፋት አታሳየን እያልን ፈጠሪያችንን እንለምነው። የወገናችንን እልቂት አታሳየን እንበለው። ትናንትና በድርቅ በረሃብ ስንገርፈው የነበረውን ሕዝብ ዛሬ ደግሞ በጥይት ልንደበድበው እንዴት እንደፍራለን? መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ከሆነማ በአደባባይ የሚፈሰው የሕዝብ ደምም ደማችን በሆነ ነበር።
እኛ የምንበረታው በወንድሞቻችን ላይ ነው። ትናንትና ድንበራችንን ጥሰው የጋምቤላ ተወላጆችን አርደው ንብረታቸውን እና ልጆቻቸውን ዘርፈው ሲወጡ እኮ አንድ ጥይት አላባከንንም ነበር። ምክንያቱም ጉዳዩ ከሌላ አገር ጋር ከሌላ ሕዝብ ጋር ነበርና። እነዚያ ታጥቀው መጥተው ገደሉን ዝም ተባለ ዛሬ ሳይታጠቁ መልካም አስተዳድርን ናፍቀው አደባባይ ላይ ወጡ ጥይት ዘነበባቸው ደማቸው ፈሰሰ። ታዲያ የወገኖቻችንን ደም እንዲህ ደመ ከልብ የምናደርገው መንግሥት ማለት ሕዝብ ማለት ሰለሆነ ይሆን?
እንዲህ አይነቱን የሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ጆሮን መስጠት ከመንግሥት ይጠበቃል። መስቀላቸውን ይዘው እንደ ሰማእተ ጽድቅ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ቆሞ ደም እንዳይፈስ መገላገል ደግሞ ከአባቶቻችን ይጠበቃል። ሆኖም ግን መንግሥት እሥር ቤቶቹ ስለማይሞሉበት ጥይቱም ተተኩሶ ስለማያልቅበት ማሰርና መግደል ሥራውን ካደረገ ግን አገራችን ወደ ከፋ አደጋ መጓዟ አያጠራጥርም። ሰለዚህ በቅርበት የሕዝቡን ጩኸት ብታዳምጡት እድሜያችሁ ይረዝማል እንጅ አያጥርም ነበር። አንሰማችሁም በባዶ ሜዳ ላይ ጩኹ የምትሉን ከሆነ ግን መንግሥት ማለት ሕዝብ ነው ልትሉን ባልተገባም ነበር።
የትናንቱ ጩኸት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጩኸት ነበር፣ የትናንትናው ጩኸት የመቃወም ጩኸት ነበር፣ የትናንትናው ጩኸት የክልል ጩኸት ነበር፣ የትናንትናው ጩኸት የግለሰብ ጩኸት ነበር፣ የትናንትናው ጩኸት የመለያየት ጩኸት ነበር፤ የዛሬው ጩኸት ግን ከዚያም በላይ ነው። የማንነት ጥያቄ ነው፣ የሰብአዊነት ጥያቄ ነው፣ የሀገር ጥያቄ ነው፣ የአንድነት ጥያቄ ነው፣ የሁሉም ጥያቄ ነው፣ የኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ነው። ሰለዚህ እንደትናንትናው ሁሉ አንሰማችሁም ልንባል አይገባንም። መሰማማት፣ መደማመጥ፣ መረዳዳት፣ መወያየት እና መስማማት ይገባናል እኮ ምክንያቱም በአገራችን ጉዳይ ላይ ሁላችን እኩል እንደሆንን ስለሚሰማን። እኛ ድንበር ሲወረር ድንበራችንን ለማስከበር ብቻ አይደለም ኢትዮጵያዊ የሆነው በውስጧ ካለው ንብረትም ገንዘብም እኩል ለመሳተፍ ጭምር እንጅ። አንዱ እየተራበ ሌላው የሚጠግብባት፣ አንዱ እየተጠማ ሌላው የሚሰክርባት፣ አንዱ ዘይት አጥቶ በቃሪያ እየተቃጠለ ሌላው በቅቤ የሚመገብባት፣ አንዱ በረንዳ ላይ ወድቆ እያደረ ሌላው ከ5ቤት በላይ የሚሠራባት፣ አንዱ ሥራ አጥቶ ሌላው ሳይማር በዝምድና እና በፖለቲካ ከሥራ ሥራን የሚያማርጥባት አገር ሰትሆን ስናይ እኛም ይቆጨናል እኮ። ይህ የማይቆጨው ሰው ካለ ምናልባትም ሰው አይደለም። መንግሥት ደግሞ ሕዝብ ነኝ ይላልና ይበልጥ ቁጭታችን ሊቆጨው ይገባል። ያ ካልሆነ ግን ሕዝቡ ጠያቂ መንግሥት አጥቂ መሆናችን መቆሚያ አይኖረውም።
ይህን የሕዝብ ጩኸት ኔትወርክ በማጥፋት፣ በጥይት በማስፈራራት፣ መብራት በማጥፋት ማፈንና ማዳፈን ይከብዳል። ለጩኸት ማዳፈኛውና ማፈኛው ማደመጥ ብቻ ነው። አዳምጦ ምላሽ መስጠት ከበሳል መሪ የሚጠበቅ ነው። ምክንያቱም በመግደልና በመደፍለቅ ሕዝብን ለመጨረስማ መንግሥት ባላስፈለገንም ነበር። ምሩን አስተዳድሩን ከእኛ ትሻላላችሁ ብሎ በራሱ ላይ ያሰለጠናችሁ እኮ ሕዝብ ነው። ታዲያ እንዴት መንግሥት ሕዝብ ነው እያልን እያወራን ቃላችንን መጠበቅ ተሳነን?
አምላከ ቅዱሳን ለሀገራችን ሰላምን ለህዝቦቿም አንድነትን ፍቅርን መረዳዳትን አድልልን አሜን። እመ ብርሃን ሆይ በዚህ በያዝነው ሱባኤ ምሕረትን ረድኤትን ጸጋ እና በረከትን አድይን አሜን።
Friday, August 5, 2016
“ቃና የለሹ ቃና”
ደብረማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
አንድ የኢትዮጵያ
ብሮድ ካስቲንግ ባለሥልጣን በእነዚህ የግል ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ ተጠይቆ በገሪቱ ቴሌቪዥን ማሰራጫ በኢ.ቢ.ሲ ሲመልስ “የእኛ
ባለሥልጣን ለማንኛውም የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ እውቅና አልሰጠንም፡፡ ሆኖም ግን እስካሁን ድረስ ከተከፈቱት የቴሌቪዥን ጣቢያ ፕሮግራሞች
የአገራችንን ባህል፣ ወግ እና እሴት የሚጻረሩ አይደሉም” ብሏል፡፡ በእውነት የእኛ ባሕል ቀኑን ሙሉ ከቴሌቪዥን ስክሪን ላይ አፍጥጦ
መዋል ነው እንዴ? የእኛ ባሕል እና እሴት እኮ መረዳዳት፣ መከባበር፣ መፈቃቀር፣ እንግዳን መቀበል፣ ፈጣሪን ማመስገን፣ሥራን አብዝቶ
መሥራት፣ ጀግንነት ወዘተ ነው፡፡ ባሕልና እሴት ፖለቲካ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ፖለቲካ ደጋፊም አለው ተቃዋሚም አለው ህላችን ግን
ለሁላችን ነው ለተቀዋሚውም ለደጋፊውም፡፡ በእውነት እነዚህ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሀገራችንን መንግሥት ደካማ ጎኖች የሚገልጹ ቢሆኑ
ኖሮ ይህን ያህል ዕድሜ ይኖራቸው ነበር? የኢሳትን እድል ይገጥማቸው ነበር፡፡ እንደ ዳይኖሰር ከምድረ ገጽ ይጠፋ ነበር፡፡ Thursday, August 4, 2016
“የአንድ ቀን ስህተት እስከሞት”
© መልካሙ በየነ
ሐምሌ 28/2008 ዓ.ም
ደብረማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
ወንድሞቼ እህቶቼ እንደምን ከረማችሁ፡፡ በሥራ ምክንያት የተወሰኑ ሳምንታትን ጠፍቻለሁ ወደፊትም ልጠፋ እችላለሁ በእርግጥ፡፡ አምላክ ፈቀደልኝና ዛሬ ይችን መልእክት እንድጽፍ ቻልኩ፡፡
እውነት አለ ውሸትም አለ፤ ትክክል አለ ስህተትም እንዲሁ፡፡ ምንም ቢታፈኑ እውነትና ጭስ መውጫ አያጡም ይባላል፡፡ በእርግጥ ስህተትም ቢታፈን ስህተትነቱን እንደ እውነት እንደ ትክክል እስካልተቀበልነው ድረስ መውጫ አያጣም፡፡ ስህተትነቱ ይታወቅ ዘንድ ለሁሉ ይገለጣል ሆኖም ግን ታፍኖ እንዲኖር የእኛ ተጽእኖ ከባድ ነው፡፡ ለዚህም ነው አንድ ቀን በተሳሳትነው ስህተት እድሜ ልካችንን ስህተት እንድንሠራ እድልን የምንሰጠው በርን የምንከፍተው፡፡ የትምህርት ማስረጃዎቻችንን ተመልከቷቸው፡፡ በሆነ ሰው ስህተት ወይም በሆነ አጋጣሚ ስማችን ላይ ያልተገባ ፊደል ተጨምሮ ወይም ከሚገባው ፊደል ጎድሎ የትምህርት ማስረጃ ተሠርቶ ይሰጠናል፡፡ ይህ የትምህርት ማስረጃ ስህተት መሆኑን እያወቅን ማስተካከል ባለመቻላችን ብቻ ወደ ቀጣይ ስህተት እንጓዛለን፡፡ በብዛት እነዚህ አጋጣሚዎች የውጭ ዕድል ባገኙ ሰዎች ዘንድ ጎልተው ይወጣሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ <<ABEBE>> የሚባል ሰው <<ABEBA>> ተብሎ የትምህርት ማስረጃ በስህተት ተሠርቶ ይሰጠዋል፡፡ የውጭ ዕድል አግኝቶ መሄዱ ግድ ከሆነ ይህ ሰው ፓስፖርቱ <<ABEBA>> በሚል ስም ነው የሚሠራለት፡፡ ከዚህ በኋላ ይህ ሰው አንድ ቀን በተሳሳተው ስህተት መታወቂያው፣ የመንጃ ፈቃዱ፣ በቀጣይ የሚማራቸው የትምህርት ማስረጃዎች በሙሉ የሚሠሩለት በ <<ABEBA>> ይሆናል፡፡ የአንድ ቀን ስህተት ዕድሜ ልኩን እንዲሳሳት ያደርገዋል ማለት ነው፡፡ ሆኖም ግን ስህተቱን ስለሚለምደው እንደ ትክክል ይቆጥረዋልና <<ABEBA>> በሚለው ስም መጠራትን ይለምደዋል፡፡
ይህ ስህተት በሀገራችን በልዩ ልዩ ተቋማት ላይም እንመለከተዋለን፡፡ አንድ ሰው በሆነ ወቅት በሆነ አጋጣሚ መመሪያ ጥሶ ህግ አፍርሶ የሆነ ነገርን በስህተት መሥራት ይለምዳል፡፡ ከዚያ በኋላ ያ ስህተት አሠራር እንደ ህግ ይሆንና ሁሉም ይሠራበታል፡፡ እርሱ ወርዶ በተራው ሌላ ሰው ቢተካ እንኳ አንዴ ስህተቱ ተሠርቷልና በዚያ ስህተት አሠራር ይቀጥላል፡፡ ይህ የስህተት አሠራር ትክክለኛ አሰራር ሆኖ በህብረተሰቡ ዘንድም እንደ መመሪያ ጸድቋልና ማንም ቅሬታ አያቀርብም፡፡ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ማለት ይህ ነው፡፡ አንድ ጊዜ በስህተት ዝናብ በስብሻለሁና ዳግም ለሚዘንብብኝ የስህተት ዝናብ ዣንጥላ አያስፈልገኝም ምክንያቱም አንዴ በስህተት በስብሻለሁና የሚል አመለካከት ያነገበ ነው፡፡
የህዝብን የጥያቄ ጩኸት በድብደባ ዝም ማስባል ከለመድህ እድሜ ልክህን ያንን ትፈጽመዋለህ፡፡ ምክንያቱም አንተ መደብደብን (ይላላል) ህዝቡም መደብደብን (ይጠብቃል) ልማድ አድርገዋልና እንደ ትክክለኛ አሠራር ይቆጠራል፡፡ የተለያዩ የስህተት ሥራዎቻችን ልማድ ወደ መሆን ይቀየሩና ለስህተታችን ይቅርታ በማለት ፋንታ ስህተታችን ትክክል እንደሆነ ልናስረዳ እንሞክራለን፡፡ መብራት ሲጠፋ፣ ኔት ወርክ ሲቋረጥ፣ ውኃ ስትቀር፣ ስኳር እና ዘይት ሲጠፋ ወዘተ ይቅርታ ብሎ የሚያውቅ ማን አለ? ማንም የለም ምክንያቱም ይህን ማድረጋቸው በራሱ ስህተት እንደሆነ አላወቁማ፡፡ ይቅርታ ለመጠየቅ እኮ በመጀመሪያ ስህተትን ማመን ያስፈልጋል ስህተቱን ያላመነ ሰው ይቅርታን ከወዴት ያውቀዋል፡፡
የወጣቱንም ሱስ እንዲሁ ተመልከቱት አንድ ቀን በሆነ አጋጣሚ በሆነ ሰው ግፊት የጀመራት ሲጋራ ዛሬ ድረስ ጓደኛው አድርጎ ይዟታል፡፡ ጫትና መጠጡ ዝሙትና መዳራቱም እንዲሁ ነው፡፡ በሆነ አጋጣሚ የሆነ ስህተት ስለሠራና ከእነዚህ ሱሶች ጋር ስለተጣበቀ ስህተት ያደረገ አይመስለውም፡፡ ፈጣሪውን የበደለ ራሱንም ያዋረደ አይመስለውም፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ ስህተቱን ትክክል ነው ብሎ ራሱን አሳምኖታልና፡፡
አንድ ቀን የተሰራ ስህተት እድሜ ልክን እንደተሳሳትን የሚያደርግ ልማድ ነው፡፡ ስለዚህ ስህተታችን ማየት መቼም ቢሆን የምንሠራውን ነገር ትክክል ስለመሆኑ መመርመር ያስፈልገናል፡፡
Friday, July 22, 2016
“የንስጥሮስ ክህደት ዛሬ በቅብአት እምነት ውስጥ ሲደገም”
ደብረማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
![]() |
| ወልደ አብ ገጽ 127 |
Friday, July 15, 2016
“ብራና እና ጥንታዊነት”
ደብረማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
Friday, July 8, 2016
የተዋሕዶ መደምደሚያ ቅብአት ነው?
የቅብአትን ኑፋቄ ባለፉት በርካታ ጽሑፎቼ መጽሐፋቸውን መነሻ በማድረግ ሳሳውቅ ቆይቻለሁ። አሁን መጽሐፋቸው አደባባይ ላይ እየተሸጠ እያለ እንኳ "ጎጃምን ትልቁን አገር አታሰድብ ቅብአት የሚባል ነገር የለም" የሚሉ አልታጡም። እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ሀገር እና ክፍለ ሀገርም የማያውቁ መሆናቸው ግልጽ ነው። ምክንያቱም ሀገር ብለን ኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር ብለን ጎጃም እንላለን እንጅ "ትልቅ ሀገር ጎጃም" አንልም። ሲቀጥል የሀገር ትልቅነት በምን ይለካል? ለሚለው ጥያቄም በቂ መልስ ማቅረብ አይችሉም። ጎጃም ትልቅ እንደሆነ እናውቃለን ሆኖም ግን ከትልቁ ዝሆን ላይ ትንኝ እንደማትታጣ መረዳት አያዳግተንም። ስለዚህ "ቅብአት የለም" የሚለው የአንዳንድ ሰዎች አስተያየት (አቡነ ማርቆስን ጨምሮ ማለቴ ነው) ተቀባይነት የለውም። ድሮ አቡነ ዘካርያስ ይህንነ ሲሉን ነበር ያን ጊዜ እውነታቸውን ይሆን? ብለን ነበር። ምክንያቱም ከወሬ ያለፈ ተጨባጭ ማስረጃ ስላልነበረን። ዛሬ ግን ሽህ ሰው "ቅብአት የለም" ቢለኝ ሺህ ውሸታም እላቸዋለሁ እንጅ እንደ ድሮው እውነት ይሆን? ብየ አልጠራጠርም። ምክንያቱም የቅብአት እምነት ሊቅ የሚባለው "ገብረ መድኅን" ወይም "ሄኖክ" የጻፈልን "ወልደ አብ" የተባለ መጽሐፍ ማስረጃችን ነውና። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ጆሮ የለውም። እልፍ ፐርሰንት ያህል እተማመናለሁ ቅብአት አለ ያውም ከቤታችን ከቤተክርስቲያናችን። በዚህ ጉዳይ ይህን ያህል ካልኩ ወደ ዋናው ጉዳየ ልግባ። የቅብአት እምነት ተከታዮች "ለተዋሕዶ መደምደሚያ ቅብአት ነው" ይላሉ። ይህን እስኪ ከራሳቸው መጽሐፍ እንመልከተው።
ወልደ አብ ገጽ 219 ላይ “ይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደአብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ሆነ ልጅነት አገኘ፡፡ ይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ሆነ፡፡ እንዘ ባዕል ውእቱ በኩሉ አንደየ ርእሶ እን ጳውሎስ ፪ኛ ቆሮ ም፰ ቁ፱ ስለዚህ ከእምቅድመ ዓለም ልደቱ ፩ድ ለማድረግ በሰውነቱ የባሕርይ ህይወቱን በመላ ተቀብሎ ከአብ ተወለደ እንጅ የቀደመ ልጅነቱስ አልተነሣውም፡፡ ወልድስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ባይወለድ ወልድ በሰውነቱ እንደ አብ ባልገዛም አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን በመላ በሰፋ ባልሰጠውም ነበር ኢይሁብ ክብርየ ለባዕድ ለተሳትፎ ወስብሐትየ ለግልፎ እን ኢሳ ም፵፪ ቁ፰ መንፈስ ቅዱስን ከአብ ተቀብሎ ቢወለድ ግን እንደአብ ገዛ አዘዘ፡፡ አብም ለወልድ በሰውነቱ አገዛዙን ክብሩን ሰጠው አኮ ዘይሁብ እግዚአብሔር አብ መንፈሶ በመስፈርት አላ አብሰ ያፈቅር ወልዶ ወኲሎ ኲነኔሁ አወፈዮ ለወልዱ ውስተ እዴሁ እን ወን ዮ ም፫ ቁ፴፬፡፡ ወረሰዮ ወራሴ ለኲሉ እን ጳው ዕብ ም፩ ቁ፪” ይላል። ይህን ጉዳይ "የቅብአት ምንፍቅና መደበቂያ ካባዎች ክፍል 8" ላይ በዝርዝር ተመልክተነዋል። እዚህ ላይ መድገም ያስፈለገው ይህ አገላለጽ "ለተዋሕዶ መደምደሚያ ቅብአት ነው" የሚል አንድምታ ስላለው ነው። ምክንያቱም እርስ በርሱ የሚጋጭ የሚመስል ሃሳብ ይዟል ነገር ግን አይጋጭም ይላሉ የቅብአት እምነት ተከታዮች። ስለዚህ የማይጋጭ ሃሳብ ከሆነ ሊስማማ የሚችለው እንደሚከተለው ይሆናል። መጀመሪያ ሁለት የተዋሕዶ ሂደቶች ይከወናሉ። የመጀመሪው"ይህ የጸጋ ልጅነት የሌለው ባእድ ሥጋ እምቅድመ ዓለም የባሕርይ ልጅነት ካለው መለኮት ጋራ ቢዋሐድ የቃልን ገንዘብ ተቀብሎ ወልደአብ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ሆነ ልጅነት አገኘ"የሚለው መለኮት ከሥጋ ጋር ያደረገው ተዋሕዶ ነው። በዚህ ተዋሕዶ ላይ መለኮት ከሥጋ ጋር ተዋሐደ እንጅ ሥጋ ከመለኮት ጋር አልተዋሐደም።በዚህ ተዋሕዶ ሥጋ የቃልን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ በቃል መጠሪያ ተጠራ ቃለ አብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ተባለ ማለት ነው። የሚገርማችሁ እስከዚህ ድረስ መለኮት የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ አላደረገም በሥጋ ስምም አልተጠራም። ስለዚህ ሙሉ ተዋሕዶ ይደረግ ዘንድ ሥጋ ከመለኮት ጋር መዋሐድ አለበት። ይህኛው ቀጣዩ ተዋሕዶ ነው። ሁለት ነጥላ ተዋሕዶዎች ናቸው እንግዲህ አንድ ሙሉ ተዋሕዶን የሚፈጥሩት። በነገራችን ላይ ይህን የምላችሁ እነርሱ ተዋሐደ እያሉ ስለጻፉት እንጅ እንደ እኔ ይኼ ተዋሕዶ አይባልም። የኅድረት ተዋሕዶ ሊሆን እንደሚችል ብቻ ነው የምገምተው። ስለዚህ ኅድረት ያለበት ተዋሕዶ እንደሆነ እረዳለሁ። ቀጣዩ ተዋሕዶ የሥጋ ከመለኮት ጋር መዋሐድ ነው። "ይህ ልጅነት ያለው ቃል ልጅነት ከሌለው ሥጋ ጋራ ቢዋሐድ በሥጋ ርስት ልጅነትን የሚሻ ሆነ" ይላል ሥጋ ከመለኮት ጋር እንደተዋሐደ ለማጠየቅ። ቅድም ልጅነት አገኘ ቃለአብ ቃለ መንፈስ ቅዱስ ሆነ ያሉት ሥጋ አሁን ልጅነትን የሚሻ ሆነ ምክንያቱም መለኮት ቢዋሐደው ልጅነት አገኝ እንጅ ሥጋ ከመለኮት ጋር ስላልተዋሐደ የሚቀረው ልጅነት አለ። ስለዚህ ይህን ሙሉ ልጅነት ያገኝ ዘንድ ሥጋ ከመለኮት ጋር መዋሐድ ያስፈልገዋል ማለት ነው። እንግዲህ እነዚህ የተዋሕዶ ሁለት ሂደቶች ከተጠናቀቂ በኋላ ይፈጠራል። ወልደ አብ ገጽ 131 "ወልድንም በሰውነቱ ፍጡር ብሎ ማመን ይገባል። ለሊሁ ፈጣሪ በእንተ ከመ ውእቱ አምላክ ወእግዚአብሔር ውእቱ ወዓዲመ ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ እምብእሲት እን ቅዱስ ቂርሎስ ሃ አ ስምዓት ክ፪ ቁ፲፱ ሥጋ በመለኮት ርስት ፈጣሪ ነው። መለኮት በሥጋ ርስት ፍጡር ነው። ሥጋ ሲፈጠር መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሕዶ አብሮ ተፈጠረ ካላሉ እንደ ንስጥሮስ ፪ አካል ማድረግ ኃደረበብእሲ ማለት ነውና ክህደት ነው" አሁን መለኮት ከሥጋ ጋር ሥጋም ከመለኮት ጋር ተዋሕዶ ተፈጥሯል። ማን ፈጠረው አትሉኝም መቸም ምክንያቱም አምላክ ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ ተፈጥሯልና። መለኮት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ ተፈጠረ ካላሉ ክህደት ነው ብለዋል እኮ ደግሞ። እንግዲህ ይህ ተዋሕዶ ከተከናወነ በኋላ የተፈጠረው አካል እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ ያዝዝ ይገዛ ዘንድ በቅብአት መክበር ያስፈልገዋል። ይህንንም እንዲህ ያስረዳሉ "ስለዚህ ከእምቅድመ ዓለም ልደቱ ፩ድ ለማድረግ በሰውነቱ የባሕርይ ህይወቱን በመላ ተቀብሎ ከአብ ተወለደ እንጅ የቀደመ ልጅነቱስ አልተነሣውም" ስለዚህ ከተዋሕዶ በኋላ ቅብአት መደምደሚያ ሆኖ እናገኘዋለን። አንድ ያልተረዱት ነገር አለ እግዚአብሔር በመለካት በመፍጠር አንድ ነው። ይህን ካመኑ ደግሞ መለኮት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ ተፈጠረ ማለት ምን ማለት ነው? ወይስ ደግሞ እኛን ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ አጡለት ስለሚሉን ቦታ ለመፈለግ ይሆን? የወልድ መለኮት ከሥጋ ጋር ተዋሐደ አንድ ቦታ ለወልድ ተገኘለት። ቀጣይ መለኮት የተዋሐደውን ሥጋ አብ ፈጠረው ለአብ ሌላ ቦታ ተሰጠው ቀጣይ ይህን ከመለኮት ጋር ተዋሕዶ የተፈጠረውን ሥጋ መንፈስ ቅዱስ አከበረው ለመንፈስ ቅዱስም ቦታ ሰጡት።
አምላከ ቅዱሳብ ይቅር ይበለን!!!
"የቅብአት ምንፍቅና በአደባባይ"
"የቅብአት ምንፍቅና መደበቂያ ካባዎች" በሚል ርእስ መነሻነት እስከ ክፍል 10 ድረስ እንደተማማርን ታስታውሳላችሁ። ዛሬም በዚህ ክፍል ምንፍቅናቸው ምን ላይ እንደሆነ በግልጽ እንመለከታለን። እዚህ ላይ ግን ልብ ማለት የሚገባን የምጽፈው ነገር ከራሴ አንቅቸ እንዳልሆነ ነው። የምጽፍላችሁ ነገር ራሳቸው ካሳተሙት የክህደት መጽሐፍ ሲሆን የሚጠቅሱትንም ጥቅስ ትክክለኛውን እና ሙሉውን በግእዝም በአማርኛም እጽፍላችኋለሁ።
ወልደ አብ ገጽ 131 "ወልድንም በሰውነቱ ፍጡር ብሎ ማመን ይገባል። ለሊሁ ፈጣሪ በእንተ ከመ ውእቱ አምላክ ወእግዚአብሔር ውእቱ ወዓዲመ ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ እምብእሲት እን ቅዱስ ቂርሎስ ሃ አ ስምዓት ክ፪ ቁ፲፱ ሥጋ በመለኮት ርስት ፈጣሪ ነው። መለኮት በሥጋ ርስት ፍጡር ነው። ሥጋ ሲፈጠር መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሕዶ አብሮ ተፈጠረ ካላሉ እንደ ንስጥሮስ ፪ አካል ማድረግ ኃደረበብእሲ ማለት ነውና ክህደት ነው" ይላል።
አሁን ይህን ድፍረትና ክህደት አንድ በአንድ እንመልከተው። "ወልድንም በሰውነቱ ፍጡር ብሎ ማመን ይገባል" ይላሉ ሲጀምሩ። በመጀመሪያ "ወልድ" የሚለው ስም ሥጋን ሲለብስ የጠራንበት ሳይሆን ጥንት ከሌለው ዘመን ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል በጥበበ እግዚአብሔር ከአብ ያለእናት በተወለደ ጊዜ ነው። ሰለዚህ ይህ የመወለድ ግብር ያለው "ወልድ" ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም አያንስምም እኩል ነው እንጅ። ይህ ከሥላሴ አንድነት ለቅጽበት ያህል እንኳ ያልተለየው "ወልድ" ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋንከነፍሳ ነፍስን ነሥቶ በተዋሕዶ የተወለደው ከአምላክነት ክብሩ ዝቅ ለማለት አይደለም። መለኮት ከሥጋ ጋር ሥጋም ከመለኮት ጋር በተዋሐደ ጊዜ ሥጋ አምላክ ሆነ አምላክም ሰው ሆነ። አሁን ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋንና መለኮትን መከፋፈል አንችልም ምክንያቱም "አምላክ ወሰብእ" የሚባል ነውና። ቅብዓቶች እዚህ ላይ የሠሩት ስህተት ከተዋሕዶ በኋላ መለኮትን ከሥጋ ከፍለው "ወልድንም በሰውነቱ ፍጡር ብሎ ማመን ይገባል" ይላሉ። ቅዱስ ቄርሎስ የመሰለውን የጋለ ብረት አስታውሱት ብረቱ ከጋለ በኋላ እሳት ይባላልን? ወይስ ደግሞ ብረት ብቻ ይባላል? አይባልም። ትክክለኛ ስሙ "የጋለ ብረት" የሚለው ነው። ብረት ወይም እሳት ልንለው የሚገባ ከመጋሉ በፊት ነው እንጅ ከጋለ በኋላስ "የጋለ ብረት" እንለዋለን እንጅ "ብረት" ወይም "እሳት" ብቻ ብለን እንደማንጠራው የታወቀ ነው። የመለኮት እና የሥጋም እንዲሁ ነው። ከተዋሕዶ በፊት "ወልድን ፈጣሪ" ብቻ እንለዋለን "ሥጋንም ፍጡር ብቻ" እንለዋለን። ከተዋሕዶ በኋላ ግን የቃልን ገንዘብ ሥጋ የሥጋንም ገንዘብ ቃል ገንዘቡ ስላደረገ የብቻ መጠሪያ አይኖራቸውም። ስለዚህም "ክርስቶስ" እንለዋለን ከሁለት አካላት እንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ያለው "አምላክ ወሰብእ" ነውና። ልብ በሉ "ክርስቶስ" የሚለው ሥም ከተዋሕዶ በኋላ የተጠራበት ነው። ይህም ማለት "ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው" ነው ማለት ነው። ስለዚህ ከዚህ ተዋሕዶ ከፍለን ሥጋን ለብቻው መለኮትንም ለብቻው ልናደርገው እንዴት እንደፍራለን።
"ለሊሁ ፈጣሪ በእንተ ከመ ውእቱ አምላክ ወእግዚአብሔር ውእቱ ወዓዲመ ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ እምብእሲት እን ቅዱስ ቂርሎስ ሃ አ ስምዓት ክ፪ ቁ፲፱ ሥጋ በመለኮት ርስት ፈጣሪ ነው" ይላሉ። ሁልጊዜ የሚገርሙኝ ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱት ነገር ከሚናገሩት ጽንሰ ሃሳብ ጋር በምንም የሚገናኝ አይደለም። በመጀመሪያ ግን የፊደል ግድፈትን እንኳ ማጣራት ይገባቸው እንደ ነበር እረዳለው። "ቄርሎስ" ን "ቂርሎስ" ብለው የጻፉት ምናልባትም ሃይማኖተ አበውን ገልጠን ስንመለከት እንዳናገኘው ፈልገው ይሆናል። ከየት ቆርጠው እንደወሰዱት ልብ ብላችሁ ተመልከቱት የጠቀሱትን የቄርሎስ ስምዓት ሙሉውን ግዕዝም በአማርኛም አንብበት ከዚህ በታች ቀርቦላችኋል።
ቄርሎስ ሃ አ ስምዓት ክ፪ ቁ፲፱ "ወካዕበ ይቤ ተሰምየ ገብረ ወውእቱ እግዘኣ ኩሉ ከመ አምላክ ለሊሁ በግዕ ወለሊሁ ካህን ዓዲ ኅቡረ እስመ ውእቱ ሦዐ ርእሶ ባህቲቱ በከመ ንቤ ቅድመ አዕረገ ሥጋሁ ባህቲቱ በፈቃዱ መሥዋእተ ውኩፈ ወዕጣነ ምዑዘ ለእግዚአብሔር አቡሁ በእንቲአነ ለሊሁ ፍጡር ወለሊሁ ፈጣሪ ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲት ወካዕበ ይቤ ዝንቱ ዓምደ ሃይማኖት በእንቲአሁ ትብልኑ እስመ ዘተፀንሰ ካልእ ውእቱ ዘምስለ ፈጣሪ በከመ በውስተ መለኮት ወትስብእት ወፈጣሪ ወፍጡር ፍልጣን ሐሰ ለነ እምዝንቱ ንባብ ሙሱን ወርኩስ"
አማርኛውንም እነሆ ሳልጨምር ሳልቀንስ:
"ዳግመኛም አገለገለ ተባለ ግን እሱ አምላክ እንደመሆኑ ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ ነው እሱ መሥዋእት ነው። ወዲህም ከመሥዋእቱ የማይለይ ካህን ነው እሱ ብቻ ሥጋውን በፈቃዱ የተወደደ መሥዋእት የተወደደ ዕጣን አድርጎ ስለእኛ ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ ብለን አስቀድመን እንደተናገርን እሱ ራሱን ብቻ ሠውቶአልና እሱ ሰው ነው እሱ አምላክ ነው አምላክ እግዚአብሔር ሰለሆነ ፈጣሪ እንለዋለን ወዲህም ከድንግል በሥጋ ስለተወለደ ሰው እንለዋለን ዳግመኛ ይህ ዓምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ስለ እሱ ስትናገሩ በመለኮትና በትስብእት በፈጣሪና በፍጡር መካከል መከፋፈል እንዳለ አድርጋችሁ የተፀነሰው ከፈጣሪ ጋር ያለ ሌላ ነው ትላላችሁን ሌላ አይደለም እኛ ግን እንዲህ ያለ የተጠላ የተነቀፈ አነጋገር ልንናገር አይገባንም አለ" ብሎ ትምህርታቸውን ያወግዛል። ከተዋሕዶ በኋላ በሥጋና በመለኮት መካከል መከፋፈል እንደሌለ ሰው ሲሆን አምላክ አምላክ ሲሆን ሰው ነው ብሎ ትምህርተ ተዋሕዶን በጎላ በተረዳ ነገር ነገረን እንጅ ቅብአቶች እንደሚሉት "ወልድንም በሰውነቱ ፍጡር ብሎ ማመን ይገባል" አላለንም። ይህ ደግሞ ግልጽና ግልጽ አነጋገር ነው እንዲያውም እንዲህ የሚሉትን አወገዛቸው እኮ። ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋና መለኮትን ይከፍሉና አሁንም "ሥጋ በመለኮት ርስት ፈጣሪ ነው" ብለው ይደመድማሉ። ከዚህ ቀጥለው የሚጽፉት ደግሞ በክርስትናዋ ዓለምን ከምታስደንቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖር ሰው የማይጠበቅ ከባድ ክህደት ነው። ይህም እንዲህ ይላል "መለኮት በሥጋ ርስት ፍጡር ነው። ሥጋ ሲፈጠር መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሕዶ አብሮ ተፈጠረ ካላሉ እንደ ንስጥሮስ ፪ አካል ማድረግ ኃደረበብእሲ ማለት ነውና ክህደት ነው" ብለው ለክህደታቸው ሌላ ክህደትን ይሹለታል። መጀመሪያ "ኃደረበብእሲ" የሚለውን ጸሐፊዋን "ኃደረ በብእሲ" ብላ እንድታስተካክለው አሳስቧት። ይህን ክህደት ሳይ ዛሬስ ምነው ንስጥሮስ ባየ ኖሮ አልኩ ለራሴ። ተመልከቱት የምንፍቅናቸውን ሂደት መጀመሪያ መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሐደ እዚህ ውህደት ላይ ሁለት ትልልቅ ሂደቶች አሉ። እነርሱን በሌላ ጊዜ እናያቸዋለን። ከዚያ ሂደት በኋላ ሙሉ ተዋሕዶ ይደረጋል። ከዚያ ያ ከመለኮት ጋር የተዋሐደውን ሥጋ ይፈጥረዋል። ማን እንደሚፈጥረው ግን እንጃ። ምክንያቱም መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሕዶ ሊፈጠር ነውና ሌላ ፈጣሪን ይሻል ማለት ነው። ከዚያ ማን እንደሚፈጥረው ባይታወቅም መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሕዳ ይፈጠራል አሉ። ከዚህ በኋላ ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ ፍጡር የሆነ መለኮት አገኙ ማለት ነው። ይህ ፍጡር የሆነ መለኮት ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ እኩል እንዲገዛ እኩል እንዲስተካከል ቅብአት አስፈለገው። ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ቅብአት የሚያስፈልገው። አያችሁ የክህደታቸውን ሰንሰለት። ስለ እውነት እንዲህ ያለውን ምንፍቅና ምን ሲሉ ጀመሩት ይሆን ግን። ንስጥሮስ ፪ ግብር ያለ መለኮት ከሥጋ ጋር ሳይዋሐድ ተፈጠረ ስላለ ነው እንዴ? ምነው ንስጥሮስን ሆናችሁ የንስጥሮስ ክህደት ጠፋችሁ። በእርግጥ የእናንተ ደግሞ ከንስጥሮስም ከአርዮስም የተጨመቀ ክህደት ነው ያፈለቃችሁት። በእውነት የትኛው ሊቅ የትኛው መጽሐፍ ነው "መለኮት ከሥጋ ጋራ ተዋሕዶ ተፈጠረ" የሚል? መቸም አሁንም ያላነበባችሁትን መጽሐፍ ትጠቅሱት ይሆናል። የምትጠቅሱትን መጽሐፍ ቢያንስ ማወቅ ያስፈልጋችኋል። ለክህደታችሁ ግን እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን ድንግል ማርያም በምልጃዋ ትጠብቃችሁ።






